Quarit Meme /የቋሪት ልጆች መዝናኛ ፔጅ/

Quarit Meme  /የቋሪት ልጆች መዝናኛ ፔጅ/ ነፃነት ይቅደም✅

23/12/2024

በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ

| በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ቤተሰቦቻቸው እስረኞቹ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ገልጸዋል።

ሁለቱ ፖለቲከኞች "በተደጋጋሚ አቤቱታ" ከሁለት ሳምንት በፊት ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሁለቱ ግለሰቦቹ በሆስፒታል ይቆዩ ቢባልም "ያንን እምቢ ብለው በሰዓታት ልዩነት በማይመች መኪና ጭነው ወደ ማረሚያ ቤት መልሰዋቸዋል" ሲሉ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

አንድ የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው። ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር" ብለዋል።

ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን ገልጸዋል።

ሕክምናውን ተከትሎ ለሚከሰተው የደም መፍሰስ ማስታገሻ እንደተሰጣቸው ያስታወሱት የቤተሰብ አባላቱ "የተሰጣቸው የማስታገሻ መድኃኒትም አልቆባቸዋል። ሕመሙን ለማስታገስ ቶሎ ቶሎ እየወሰዱት ስለነበር" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአቶ ዮሐንስ ቤተሰብ አባል፤ "ትላንት ማስታገሻ ይዘን ስንሄድ መግባት አትችሉም ተባልን፤ ለምንድን ነው ስንል? ሊቀየሩ ነው አሉን። እስከ ትናንት ግን እነሱ አይሄዱም ብለውን ነበር። ትናንት በድንገት ተነስተው ሊወጡ ስለሆነ ምንም ምግብ ማስገባት አትችሉም መድኃኒትም አይገባም ብለው ከለከሉን" ብልዋል።

የአቶ ክርስቲያንም የቤተሰብ አባል በተመሳሳይ "ትላንትና ምግብም ማስታገሻም ይዘን ስንሄድ የሚያስገባን ስለሌለ ተመለስን" ሲሉ ተናግረዋል።

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ሰኞ ታህሳስ 7/ 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ "ታራሚዎችን ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ ወደሚጠራው ማረሚያ ቤት እንደሚያዘዋውር አስታውቆ ነበር።

ይህን ተከትሎም "በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ" መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ በዚሁ መግለጫው ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የተቋረጠው አገልግሎት ከዛሬ ታህሳስ 14 እንደገና እንደሚጀምር በመግለጫው ገልጾ ነበር።

ነገር ግን የአቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቤተሰቦች ዛሬም ምግብ ማስገባት እና እስረኞቹን መጠየቅ እንዳልቻሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ቢቢሲ ጉዳዩን በተመለከተ የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ገረመው አያሌው ጋር ያደረገው ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ምላሽ ባለማግኘቱ አስተያየታቸውን ማካተት አልቻለም።

ዐቃቤ ህግ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ ላይ ክስ የመሰረተው ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ነበር። ከሁለት የምክር ቤት አባላት በተጨማሪ ሌሎች 50 ግለሰቦች እና ፖለቲከኞችም በአቶ ዮሐንስ ቧያሌው ስም በሚጠራው የክስ መዝገብ ተካትተዋል።

ግለሰቦቹ በ2015 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ በአማራ ክልል ከተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ክስ ሳይመሠረትባቸው ለስድስት ወር ቆይተው ነበር።

ዐቃቤ ህግ ክሱን የመሰረተው የወንጀል ሕጉን እና የፀረ ሽብር አዋጅን ጠቅሶ ነው።

የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በ12 ገጾች የተዘጋጀ የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል።

አዲስ አበባ በ1930 ዓ/ም‼️
16/09/2022

አዲስ አበባ በ1930 ዓ/ም‼️

መልካም ዓዲስ ዓመት‼️🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
10/09/2022

መልካም ዓዲስ ዓመት‼️
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

29/04/2022

ቋሪት ሀይስኩል ውስጥ በላይ ዘለቀ በር ተብሎ የሚጠራውን ቦታ ያወቀ ፎቶ አንስቶ በinbox ለላከልኝ ሰው 25 ብር ካርድ ይሸለማል‼️

በግራ በኩል ያለው ማነው?
27/04/2022

በግራ በኩል ያለው ማነው?

ቀድመው ለመለሱ 3 ሰወች የ25 ብር ካርድ እንሸልማለን‼️ ይህ ፎቶ የተነሳው የት ነው?
24/04/2022

ቀድመው ለመለሱ 3 ሰወች የ25 ብር ካርድ እንሸልማለን‼️
ይህ ፎቶ የተነሳው የት ነው?

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ‼️
23/04/2022

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ‼️

ቋሪቶች አላችሁ?ፎቶው ከየት አቅጣጫ የተነሳ ነው?
22/04/2022

ቋሪቶች አላችሁ?
ፎቶው ከየት አቅጣጫ የተነሳ ነው?

ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች  እንኳን ለጌታችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ‼️እኛን ለማዳን ተሰቀለ‼️
22/04/2022

ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ‼️

እኛን ለማዳን ተሰቀለ‼️

👉ይህ ውጤት ቋሪትን አይገልጽም‼️በክልሉ እንዲሁም በሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ከሚመዘገብባቸው የምትመደበው ቋሪት በዚህ መልኩ ዝቅተኛ ውጤት ይመዘገብባታል ለማለት ይከብዳል።
18/03/2022

👉ይህ ውጤት ቋሪትን አይገልጽም‼️
በክልሉ እንዲሁም በሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ከሚመዘገብባቸው የምትመደበው ቋሪት በዚህ መልኩ ዝቅተኛ ውጤት ይመዘገብባታል ለማለት ይከብዳል።

 #አድዋ‼️
03/03/2022

#አድዋ‼️

😂😂😂‼️
27/07/2021

😂😂😂‼️

Address

Bahir Dar

Telephone

+251918649310

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Quarit Meme /የቋሪት ልጆች መዝናኛ ፔጅ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category