ACE, Yirga Alem

ACE, Yirga Alem

Share

ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።

የማቴዎስ ወንጌል 12 : 33

11/10/2024

አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ታመልኩታላችሁ፥ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ።
ኦሪት ዘጸአት 23 : 25

17/08/2021

“ሰላም፣ ጥሞናና እረፍትን አለመቀበል የውድቀት መሰረት ነው”፦ ዶ/ር አብርሃም በላይ
*******************

ሰላም፣ ጥሞናና እረፍትን አለመቀበል የውድቀት መሰረት ነው ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡

“እኛ ለተዋለድናቸውና ለጎረቤቶቻችን ጠላትና ቂመኛ አድርጎ ከሁሉም ጋር ያቃቃረንና ደም ያቃባን ትእግስትና የሰላም ጥሪ ፍራቻ የመሰለው ካለፈው ታሪክ የማይማር የሸብር ቡድን አቅፈን ለህዝባችን ሰላም፣ እርካታና እረፍት ልናገኝ እንደማንችል ግልፅ የሆነ ሃቅ ነው” ብለዋል፡፡

ሰላምና መረጋጋትን የምናሰፍነው እኛ ራሳችን በተደራጀ መንገድ የጥፋት ቡድን ጭቆና ዘወር በል ፣ ጦርነትና ባርነት ይበቃል ስንል ብቻ ነው ያሉት ዶ/ር አብርሃም ለህዝባችን ህልውና ደህንነትና ነፃነት በአንድ ላይ የምንቆምበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል፡፡

እነዚህ የከሰሩና ልባቸው የጠፋ የህወሓት የሽብር ቡድን አመራሮችን በጎንህ ሸጉጠህ ህዘባችን ሰላም ያገኛል ብሎ ማሰብ እና ተስፋ ማድረግ ከዝንብ ማር መጠበቅ ይቀላል ነው ያሉት አቶ አብርሃም፡፡

ይህ ሃይል እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው እሱና ተከታዮቹ አይጎዱ እንጂ ለህልውናው ሲል ዘለው ያልጠገቡ የትግራይ ህፃናትንና ወጣቶችን የትግራይ ህዝብና ባህል በማይገልፀው ሁኔታ እንዲሁም የሃገራችንና የአለም አቀፍ ሀግ በሚቃረን መልኩ በእፀ ፋሪስ (በሃሺሽ) አደንዝዞና አስገድዶ ወደ እሳት እየማገዳቸው እና እንደ ቅጠል እንዲረግፉ አያደረገ የሚገኝ የለየለት ፀረ ህዝብ መሆኑን በግልፅ ደጋግሞ አረጋግጧል ነው ያሉት፡፡

አሁንም በግላዊ ጥቅሞቻቸው የተፈጠረው ጥፋትና ክህደት ምክንያት የጠፋው ሕይወት እና የወደመው ንብረት እንዳይበቃን፣ በመልካም ተግባርና ሰላምን በመፈለግ አንድ እርምጃ ወደፊት ለመጓዝ የሚያስችለው የነበረ፣ ለትግራይ ህዝብ ታላቅ ተስፋ ሰጥቶ የነበረውን የተኩስ አቁም ወደ ጎን በመተው ሳይውሉ ሳያድሩ የህዝባችንን የሰላም ተስፋ በማጨለም በድጋሚ ወደ ጦርነት እንድንገባ እያስገደዱን ነው ብለዋል፡፡

የበለፀገች ትግራይና የወላጆቻችሁ ተስፋ የሆናችሁ ወጣቶች ለጥቂቶች የስልጣን ወንበር ሲባል በስሜትና በመሰረተ ቢስ ፕሮፖጋንዳ እያታለለ ክቡር ሕይወታችሁን በከንቱ ለማጥፋት የሚማግዳችሁ የጥፋት ሃይል ቡድን መሆኑን አንድታውቁ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ይህን እየመሩ ያሉ አካላት ደግሞ ስቃይ፣ መከራ የከፋፍለህ ግዛ ሴራ በስተቀር የሰላም፣ የአንድነት፣ የእርጋታ እና የልማት አጀንዳን የማይፈልጉ የአርዮሳውያን ስብስብ ናቸው በማለት ነው ዶክተር አብርሃም የተናገሩት፡፡

እኛ ጥያቄዎች ካሉን ህዝባችንን መሰረት በማድረግ በህግ፣ በስርዓት እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መንቀሳቀስ እንጂ በጦርነትና በጉልበት የሚመለስ ጥያቄ የህዝባችንን ዘላቂ ሰላም ሊያረጋግጥ እንደማይችል አውቀን፣ በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ ብቻ መልስ እንዲገኝ ውይይትን እናስቀድም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ይህ የጥፋት ሃይል ከዚህ በላይ ህዝባችንን ይዞ እንዳይጠፋ ከፌዴራል መንግስት፣ የመከላከያ ሃይል ጎን በመቆም ሁሉን አይነት ድጋፋችንን መስጠት ይገባናል ነው ያሉት፡፡

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
የመዝናኛ ቻናላችን የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ የመዝናኛ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCp9pS23Vw1n8WpcpZBDJNmA
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena

Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Awassa