Arbegona Amanuel Light & Life Preparatory school Technical Drawing

Arbegona Amanuel Light & Life Preparatory school Technical Drawing

Share

Education

18/06/2022

and

21/05/2022

እራሳችሁን ጠብቁ
የሩኒ ነገር
Rooney 36 CR7 37
ወዮ ጋሽ ሮኒ ግን ምን ነካቸው ጃል
ገና አርባ ሳይገቡ በ36 አመታቸው የስልሳ አመት ጎልማሳ መስለዋል በተቃራኒው በአንድ አመት የሚበልጣቸው ኦቦ ክሪስቲያኖ ልጃቸው መስሎ ቁጭ ብሎዋል😀
የሩኒ መሸምገል የኳስ አፍቃሪው መነጋገሪያ ሆኖዋል

ብዙ ሰወች ያለ እድሜያቸው ያረጃሉ ለምን ሲባል ብዙ ምክንያቶች አሉ። ብስጭት ፣ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ እራስን አለመጠበቅ፣ በራስ አካላዊ ለውጦች ላይ ጥንቃቄ አለመውሰድ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ እና አልኮል መጠቀም ወዘተ

መቸም የክሪስቲያኖን አመጋገብ ለመከተል እጅግ በጣም ይከብዳል በአለም ላይ በአመጋገባቸው ጥንቁቅነት ከሚታወቁት አንዱ ነው። አልኮል ከነጭራሹ አይጠቀምም። የሩኒ እርጅና ያለጊዜው የመጣ ነው ይሄ ቀምቀሚ
ከጠርሙስ ማዶ ማየት አልችል ብሎዋል😆።ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እንደሚባለው የሆነ የልጅነት ትዝታ ትዝ አለኝ
አንድ ከእኛ ሰፈር ትንሽ ወረድ ብሎ ቶሎሳ ሰፈር አባ ታከለ የሚባሉ ከባድ ጠጅ ቀምቃሚ ነበሩ። አባ ታከለ ምሽት አራት ሰአት ላይ የአካባቢውን ሙድ በመቀየር ይታወቃሉ ሲያሻቸው ምክር ሲያሸቸው ስድብ ይነጠርቁታል። በተለይ ስለሚስታቸው ወይዘሮ ካሰች የሚገጥሙት ግጥም ከአንድ የጠጅ ቤት ሰካራም የሚወጣ አይመስልም ያኔ የኤለመንተሪ ተማሪ ሆኘ ለእረፍት ሰፈር ስመለስ ኦቦ ታከለን መስማት ያዝናናኝ ነበር በተለይ ሚስታቸውን የሚያባብሉባት መንገድ

"የኔማ ካሰች የወርቆች ወርቅ
መጣሁልሽ ቶሎ በምሽት ሳልወድቅ
አልጋው ሞቆ ይቆይ እንደ ትናንትናው
የጠጣሁትን ጠጅ በሽታሽ በትኝው"
ወይኔ ቸሬ ግጥማቸው ግን እየተረሳኝ ነው 😂 ብቻ ብዙ ከገጠሙ በሁዋላ
እትትትትትትት.....ይሉና ትንሽ ቆይተው

አንቺ የሴት ገብረ ሀይጥ ልጆቸ በዚህ ወር አይምጡና ዘንድሮ አለ ነገር ይላሉ ከትንሽ ቆይታ በሁዋላ ወደቤታቸው አጥር ሲደርሱ ወይዘሮ ካሰች ነጠላ ጣል አርገው በር ላይ ይወጡና
" እርሶ ሰውየ ግን መች ነው የሚሰበሰቡት ይሄ ቅንቡላ በአፍጢመወ ሳይደፋወ አይቀርም ገንዘቡንማ አንዴ ጨርሰውታል ቤቱ ነው የቀሮት እሱንም እላያችን ላይ ይሽጡትና ይለይሎት " 😀 ሲሉ አቀባብለው ይተኩሳሉ። ኦቦ ታከለ የድሮ አራዳ ስለሆነ ጠጋ ይሉና የኔ ወርቅ ምንም ባመሽ አንቺን ጥየ አንድም ቀን ውጭ አድሬ አላውቅም አንቺን ጥየማ አልተኛም ልጆቸን ይንሳኝ አመል ሆኖብኝ ነው የኔ ውድ የልጆቸ እናት ነይ ነይማ ይሉና እቅፍ አድርገው ይስሟታል ያኔ የወይዘሮ ካሰች ንዴት በሮ እልም በሽምግልና ፍቅር እፍፍፍፍ ብለው ገብተው ለሽ።
እንደዛ በኦቦ ታከለ ጠጭነት ቢበሳጩም ወይዘሮ ካሰች ለባላቸው ትልቅ ፍቅር ነበራቸው ከስካር ማግስት ያላቸው ፍቅር ሮሚዮ እና ጁሌት በሉት😂። ታዲያ የኦቦ ታከለ የመጠጥ ጎጅነትን ፉርሽ ያደረጉ በሚል በሰፈሩ ይታሙ ነበር ምክንያቱም በዛ እድሜያቸው ያን ሁሉ ቅንቡላ እየለጉ እሳቸው ላይ ከእግራቸው መወላገድ ባቀር የአፍ ወልምታ እንኳን የለም። እድሜንም እንደ ማቱሳላ በበቃኝ በ105 አመታቻው እንዳረፉ ሰማሁ። ግን ለሳቸው ያን ሁሉ እየጠጡ ምንም አለመሆን የውድ ባለቤታቸው ከልብ የመነጨ ፍቅር እና እንክብካቤ ዋና ምክንያት ነው ባይ ነኝ። ገና ለመጠጥ ሲወጡ ምግብ በልተዋል ወይ ብለው ይጠይቃሉ አንዳንዴ በዛ እድሜያቸው ባላቸው ሳይበሉ ከቤት ወተው መንገድ ገና እንደጀመሩ ተከትለው ጎትተው ምግብ ያበሏቸው ነበር። ወይዘሮ ካሰች ለባላቸው ያላቸውን ፍቅር ከመናገር አይቆጠቡም ረጅም የትዳር ዘመን የልጅ ልጅ ያዩ የተባረኩም ናቸው በኦቦ ታከለ ቀምቃሚነት ምክንያት አንድም ቀን ፍቅራቸው ቀንሶ አያውቅም። በጣም የሚደንቀው ኦቦ ታከለም ሰከሩም አልሰከሩም ለባለቤታቸው ያላቸው ፍቅር ሁሌም ፅኑ ነበር። ብዙ የምንማርባቸው ታሪኮች አሏቸው ወደፊት አጫውታችሁዋላሁ

02/06/2020

For all A/A/L & L school Grade 11 students
Draw a multi-view of a given 3d object by first angle projection system.
* The front side is at the front of full circle.

Photos from Arbegona Amanuel Light & Life Preparatory school Technical Drawing's post 13/12/2019
Photos from Arbegona Amanuel Light & Life Preparatory school Technical Drawing's post 13/12/2019

የአ/ብ/ሕ/ት/ቤት 11ኛ ክፍል ተማሪዎች ቴክኒካል ድሮዊንግ ላብ ውስጥ በልምምድ ላይ

10/12/2019

Visualization

10/12/2019

visualization

Photos from Arbegona Amanuel Light & Life Preparatory school Technical Drawing's post 29/11/2019

የአርቤጎና ኤማኑኤል ብርሃን እና ሕይወት ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቼ ጋር....ደስ የሚል ቀን።

Photos from Arbegona Amanuel Light & Life Preparatory school Technical Drawing's post 29/11/2019

የአርቤጎና አማኑኤል ብርሐንና ሕይወት ት/ቤት
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቼ ጋር...ደስ የሚል ቀን

01/11/2019

Pictorial

21/10/2019
Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Gebrel
Awassa