26/06/2021
Science & Technology University Student AsossetionSpetial AASTU& ASTU
inorder to give full information about science&technology
26/06/2021
አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ከሁለተኛ ዲግሪ በላይ ያሉትን ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተገለፀ‼️
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ መጀመራቸው ተጠቆመ፡፡ የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ደግሞ ከየትምህርት ተቋሞቻቸው የሚላኩላቸውን የትምህርት ሰነዶች እያነበቡ እንደሚቆዩ ተገልጿል፡፡
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኤባ ሚጀና በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት በዚህ ወቅት ይካሄድ ስለነበረው የከፍተኛ ተማሪዎች የምረቃ መርሃ ግብር ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት፣ በኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በሽታ ምክንያት የሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ትምህርት በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርቱን እንዲከታተሉና ከአማካሪዎቻቸው ጋርም የሚገናኙበት ምቹ ሁኔታ በመኖሩ ትምህርታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ባይኖርም አንዳንድ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ትምህርት ማስጨረስ እንደ ጀመሩ አመልክተው፣ በዚህም ጅማና ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ይጠቀሳሉ ብለዋል፡፡ ትምህርታቸውን ያልጨረሱ ተማሪዎችም እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ለመጨረስ የቻሉት በተመቻቸው የቴክኖሎጂ የማስተማሪያ ዘዴ በአግባቡ መጠቀም በመቻላቸው፣ እንዲሁም በተማሪውና በአማካሪዎቻቸው ጥንካሬ እንደሆነ የጠቆሙት ዶክተር ኤባ፣ የትምህርት ተቋማቱም በየጊዜው አስፈላጊውን ክትትልና ግምገማ በማድረግ ውጤታማ መሆኑ መቻላቸውን አመልክተዋል፡፡
የመጨረሻ ዓመት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በተመለከተም ዶክተር ኤባ እንዳብራሩት፣ በወረርሽኙ ምክንያት ባለመማራቸው፣ አንዳንዶችም የመጀመሪያ መንፈቅ (ሴሚስተር) ፈተና ለመውሰድ ዝግጅት ላይ እያሉ ወረርሽኙ በመከሰቱ ምክንያት ባለመፈተናቸው በዚህ ክረምት ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ ተማሪዎች አይኖሩም፡፡
እነርሱን በተመለከተ መደረግ ስላበት ነገር በየሳምንቱ ከየትምህርት ተቋማቱ የትምህርት አመራሮች ጋር ግምገማ እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተው፣ ወረርሽኙ ቢገታ ወይም ቢቆም መደረግ ስላለበት ሁኔታ ከወዲሁ ዝርዝር ዕቅድ ያዘጋጁ የትምህርት ተቋማት መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡
ዝርዝር ዕቅዱ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ምን ላይ እንዳቆሙ እና ካቆሙበት በመቀጠል ደግሞ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ በመሸፈን ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል።
በቴክኖሎጂ በመታገዘ የከፍተኛ ትምህርትን ለማስቀጠል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ውይይት ተካሄደ።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተማሪዎች ባሉበት ሆነው ትምህርት ማስቀጠል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ መክረዋል።
በውይይታቸው መማር ማስተማሩ ከገፅ ለገፅ ውጪ ባለው ሁኔታ በቅድመ ምረቃ፣ ድህረ ምረቃ እና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ዘንድ እንዴት ይቀጥል በሚለው ላይ ነው የተወያዩት።
በዚህም የድህረ ምረቃና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካሉበት ሆነው በኦንላይን እንዲከታተሉ ዩኒቨርስቲዎቹ እንዲያመቻቹና መምህራንም በኦንላይን የሚሰጡ ትምህርቶችን በማመቻቸትና በተለያዩ መንገዶች ተደራሽ በማድረግ እንዲያስቀጥሉ ተብሏል።
ተማሪዎች ካሉበት ሆነው ከንባብ ሳይርቁ ወደፊት በሚገለፁ ዌብሳይቶች በመግባት የተለያዩ የትምህርት ሞጁሎች፣ ፓወርፖይንቶችን፣ ማጣቀሻ መፃህፍት አግኝተው እንዲያነቡ የሚያስችሉ ዝግጅቶች በቅርቡ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ተደራሽ ማድረግ እንዳለባቸው መመሪያ ተሰጥቷል።
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመነጋገር ለተማሪዎችና ለመምህራን ለተመረጡ የትምህርትና ምርምር ዌብሳይቶችና መተግበሪያወች ኢንተርኔትን ከክፍያ ነጻ እንዲሆኑ እንዲደረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
በየትምህርት ፕሮግራም የተዘጋጁ የኮርስ መሳሪያወችንና አጋዥ የትምህርት መጽሃፍቶች በመለየት ዝግጁ መደረጉ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዚህም ከ80 ሺህ በላይ መፃህፍት፣ የአንደኛ ዓመት ትምህርት የኮርስ ሞጁሎችና የተለያዩ የመመረቂያ ጥናቶች ዝግጁ መደረጋቸውንና እነዚህም ተደራሽ የሚሆኑባቸው ቴክኖሎጂዎች መመቻቸቱ ተገልጿል።
በውይይቱ ትምህርቶችን በኦንላይን ማስቀጠል ሲባል ምንም እንኳን የአቅርቦትና ፍትሃዊነት ጉዳይ ጥያቄ ሊሆን ቢችልም፤ የተወሰኑትን እንኳን ተደራሽ ለማድረግ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ለሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች ይዘቶችን ተደራሽ የሚያደርግ የዲጂታል ቤተመፃፍህት http://ndl.ethernet.edu.et/ መሆኑንና እንዲሁም http://library.techin.et/ ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል።Yirgalem Aabbo WonshoYirgalem Aabbo WonshoYirgalem Aabbo Wonsho
NADLE Home The National Academic Digital Library of Ethiopia (NADLE) is a project under Ministry of Science and Higher Education, Ethiopia. The objective is to collect and collate metadata and provide full text index from several national and international digital libraries, as well as other relevant sources.....
08/03/2020
የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የምክክር መድረክ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ያወጣው ወቅታዊ የአቋም መግለጫ
እኛ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ፕሬዜዳንቶች እና ምክትል ፕሬዜዳንቶች በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ኢፍትሃዊ የሆነ ውሳኔ ለመወሰንና ለማስወሰን እንዳንድ ሀገራት የተዛባ ውሳኔ እንዲሰጥ ጫና ለመፍጠር እየጣሩ ይገኛሉ፡፡
በአንድ ወቅት ተመሳሳይ የተዛባ ውሳኔ በ League of Nations ሲተላለፍ በ1949 የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበሩት የሚከተለውን ብለው ነበር፡-
‹‹ሀገሬ ኢትዮጵያ በአለም ሸንጎ ላይ ፍርድ ተነፍጓት ስታዝን የመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፡፡ ለነፃነቷና ለመብቷ ከኮሎኒያልስት ጣሊያን ጋር በየጊዜው ስትዋጋ ያሸነፈችውም ብቻዋን ነው፡፡ የተጠቃችውም ብቻዋን ስለሆነ ሀገሬ መቼውንም በሚደርስባት አደጋ ከማንም እርዳታ አገኛለሁ ብላ አትጠብቅም፡፡ ዛሬም ሆነ ነገ ነፃነቷን ለመጠበቅ ታሪኳን ለማስከበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ ያለባት እሷ እራሷ ብቻ ናት!›› እንዳሉት ሁሉ አሁንም ያለን ትውልዶች የተዛባውን ሚዛን ማስተካከል ያለብን እኛው ነን፡፡
እናም የአድዋውን ድል በተባበረው የአያቶቻችን ክንድ እዳሸነፍነው ሁሉ የህዳሴውንም ግድብ በተባበረው አንድነታችን፣ ክንዳችን እና ሀብታችን ሰርተን የምንጨርሰው መሆናችን እያረጋገጥን አቋማችንን በጋራ ስንገልፅ መነሻ ያደረግነው፡-
1. የግድቡ መገንባት በአገሪቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ላይ ልዩነት እንደሌለው፣
2. ኮሎኒያሊስቶች አፍረካን እና ሀብቷን ለመቀራመት አውጥተውት የነበረና አሁን የሚያፍሩበት የ1029 እና የ1929 ዓ/ም ኢትዮጵያ ባልተወከለችበት የሕግ ተገዥ የምትሆንበት ሕጋዊም ሆነ አመክኒያዊ ነገር የሌለ መሆኑን፣
3. የሀገራችን ምሁራን በሰሯቸው ጥናቶች ግድቡ የሚገነባው ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ ባልሆነ ቦታ ከመሆኑ በተጨማሪ ውኃው ግብፅ ወይም ሱዳን ላይ ቢከማች ኖሮ በትንነት የሚባክነውን ውኃ ስለሚያስቀር ተመራጭ የሚያደርገው መሆኑን ነው፡፡
ከዚህ በላይ በቀረበው መነሻነትም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ባለ ስድስት ነጠብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1ኛ/ የጀመርነው እውን ለማድረግ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደምናደርግ እናረጋግጣለን፡፡
2ኛ/ የህዳሴው ግድብ የአንድነታችን ተምሣሌት በመሆኑ በዘር፣ በኃይማኖትና በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይኖር የመንግስትን አቋም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲደግፍ እንጠይቃለን፡፡
3ኛ/ እኛ ጠግበን በብርሃን እየኖርን እናንተ በረሃብና በጨለማ ኑሮ ከሚል እና እራስ ወዳድ አስተሳሰብን በፅኑ እናወግዛለን፡፡
4ኛ/ እኛ የኢትዮጵያ የመንግስ ዩኒቨርስቲ አመራሮች በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን የየድርሻቸውን እንዲወጡና ዲፕሎማሲያዊ ጫና እንደያሳድሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
5ኛ/ የአረብ ሊግ በኢትዮጵያ ህዳሴ ላይ ሰሞኑን የወሰደውን ኢ-ፍትሐዊ ውሣኔ እየተቃወምን የአፍሪካ ህብረት እንዲህ ዓይነት ጣልቃ ገብነትን እንዲቃወምና መርህን እና ሕግን መሠረት በማድረግ ከኢትዮጵያ ጐን እንዲቆም እንጠይቃለን፡፡
6ኛ/ የአሜሪካ መንግስት በታዛቢነት ገብቶ ሀብት እና የዲፕሎማሲያዊ ኃይሉን በመጠቀም ወደ አደራዳሪነት እራሱን ከማሸጋገር በላይ የወሣኝነት ሚና ያለው የሚመስል መግለጫ ማውጣቱን አጥብቀን እንቃወማለን፡፡
ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2012 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
::::::::::::::
በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የተደራጁትን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማዕከላት በማድረግ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈሩ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም በ2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2011 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱና ከታች የተጠቀሱትን ዝርዝር መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡
መመዝገብ የምትፈልጉ የትምህርት መስኮቹን በመምረጥ የመመዝገቢያ መስፈርቶችን የምታሟሉ ከሆነ በተገለፁት የምዝገባ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የምዝገባ ጊዜ፡-
• ከጳጉሜ 2 / 2011 ዓ.ም እስከ መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም
ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡-
• መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡
• የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ www.aastu.edu.et
www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡-
• መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ( ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 11፡00 ድረስ ይሆናል)
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-
• በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
1) የሀገር አቀፍ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት በ እራት(4) የትምህርት አይነት ብቻ እንዲሆን በመወሰኑ ምክንያት ከዚህ በፊት የተካሄደው ምዝገባ ሙሉ በሙሉ የተሰረዘ በመሆኑ ማንኛውም ተማሪ አዲስ በወጣው የመቁረጫ ነጥብ ብቻ ዳግም እንዲመዘገብ እናሳስባለን፡፡
2) የፈተና ጣቢያዎቹ ያላቸው የመፈተኛ ቦታ ውስን በመሆኑ ይህንኑ አውቃችሁ ቅድሚያ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
3) በቂ አመላካቾች የሌሉባቻው የፈተና ጣቢያዎች በቅርበት ወደሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች ሊታጠፉ እንደሚችሉ እናሳውቃለን፡፡
4) ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣
5) ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው እና የፈተና ጣቢያዎች በሚከተሉት ድረ-ገፆች፡-
www.aastu.edu.et , www.astu.edu.et እንደአመቺነቱም በስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚገለፅ ይሆናል፡፡
6) አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም የመሰናዶ (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል፡፡
7) ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል፡፡
8) አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2011 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይ
Home Page ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2012 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የ...
09/12/2018
ye AASTU amest
06/08/2018
The flag of
04/08/2018
AASTU
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Awassa