Werabe University

Werabe University

Share

Werabe University is a public higher education institution in Ethiopia under the Ministry of Education.

It offers undergraduate and postgraduate programs, conducts research, and provides community services. Vision
Werabe University /WRU/ aspires to be one of the best comprehensive universities in the country by the year 2022. Mission
Werabe \university is committed to providing quality education and training to produce well trained human power intellectually, morally, socially, and equip them with

16/05/2026

ማስታወቂያ

የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡

በመሆኑም የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት ከግንቦት 08-12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡

Ministry of Education Ministry of Education | National G*T

15/05/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል።

-------------------------- // -------------------------

(ግንቦት 07/2018 ዓ.ም) ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

በዚህም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ፈተናውን ለመለማመድም በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉም ገልጿል።

ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን በየጊዜው ተማሪዎች የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ መሆኑንም አገልግሎቱ አብራርቷል።
በመሆኑም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

Photos from Werabe University's post 13/05/2026

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2018 3ኛ ሩብ ዓመት ስኬታማ ተግባራትን ማከናወኑን የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ በቀለ መንገሻ ገለጹ

ግንቦት 5፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) ቦርዱ የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

የ3ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙ በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚው አቶ ተማም አርጋው ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ በቀለ መንገሻ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎትና አስተዳደር ዘርፎች በብዙ ቁልፍ የውጤት አመልካቾች (KPIs) ላይ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

ይህንኑ አፈጻጸም በተሻለ ሁኔታ ማስቀጠል እንደሚገባ ያነሱት ክቡር አቶ በቀለ በተለይ በአለም አቀፍ አጋርነትና ትብብር እየተሰራ ያለው ውጤታማ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕ/ር አርጋው አምበሉ በበኩላቸው የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ከሀገራዊ ስታንዳርድ ጋር ለማጣጣምና የመማር ማስተማር፣ የምርምርና የአገልግሎት አሰጣጡን
በቴክኖሎጂ በመደገፍ ረገድ የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል
በሩብ ዓመቱ በዓለም አቀፍ ጆርናሎች በርካታ የምርምር ስራዎች Publish መደረጋቸውንና በአራት የፈጠራ ስራዎች የአእምራዊ ንብረት ባለቤትነት ማስመዝገብ መቻሉን አስገንዝበዋል።

በሁሉም ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ የዳሳሰ ጥናቶችን በመስራትና በተገኘው ውጤትም የአገልግሎት አሰጣጡን ጥራት ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።

በተለይ ተማሪዎች በትምህርት፣ በምግብና በመኝታ አገልግሎቶች ጥራቱ የተጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን እንደ አብነት ጠቅሰዋል።

የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩ የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ተቀምጠው ተጠናቋል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

Photos from Werabe University's post 12/05/2026

የመጀሪያው ዙር አለምአቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ስኬታማ ሆኖ ተጠናቋል- ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል

ግንቦት 4፣ 2018 (ወራ/ ዩ /ህ /አ /አ /ግ) ወራቤ ዩኒቨርሲቲ "Innovation for SDGs and Global Resilience" በሚል ጭብጥ ያዘጋጀው የመጀመሪያው ዙር አለምአቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ስኬታማ ሆኖ መጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢንጂነር ተውፊቅ ጀማል ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ12 አገራት የተውጣጡ ምሁራን የተሳተፉበትን የመጀመሪያው ዙር ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ 43 የምርምር ስራዎች እንደቀረቡበት ተናግረዋል።

ኮንፈረንሱ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ከአገር ውስጥ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማገናኘት፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የፈጠራ ስራዎችን ለማስተዋወቅ ትልቅ መድረክ ሆኖ ማገልገሉን ገልጸዋል።

ኮንፈረንሱ የታለመለትን ግብ መምታቱን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ አሁን ያገኘነውን ውጤት ወደ ማህበረሰቡ በማውረድ ወደ ተግባር እንቀይራለን ብለዋል።

በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የምርምር ስራቸውን ላቀረቡ ምሁራን የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የኮንፍረንስ ተሳታፊዎች ወራቤ ዩኒቨርሲቲ እያከናወናቸው ያሉ የተለያዩ ስራዎችን ጎብኝተው የመጀመሪያው ዙር አለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ፍጻሜውን አግኝቷል።

ፕሬዚዳንቱ ለኮንፍረንሱ መሳካት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ለውጤት ላበቁት ለሁሉም አካላት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ዕውቀት ለልህቀት
ወራቤ ዩኒቨርሲቲ

መረጃዎቻችንን በሚከተሉት የሚዲያ አማራጮቻችን ይከታተሉ!

• Website: https://www.wru.edu.et/

• Telegram:https://t.me/werabeuniversitywru

• YouTube: https://www.youtube.com/

12/05/2026
Photos from Werabe University's post 11/05/2026

Werabe University Holds 1st International Research Conference on Innovation for SDGs and Global Resilience

Werabe University⁠ has officially launched its 1st International Research Conference under the theme “Innovation for the SDGs and Global Resilience,” marking a historic milestone in the university’s academic and research journey.

The international conference brought together scholars, researchers, policymakers, international partners, university leaders, students, and community representatives from Ethiopia and abroad to discuss innovative solutions for sustainable development and global resilience.

The conference was officially opened by H.E. Kora Tushune, State Minister of Education (MoE) and Guest of Honor. In his keynote opening speech, he emphasized that universities must engage with society in a holistic manner and ensure that knowledge is actively applied to solve societal problems.

“Research must not remain confined within institutions,” the State Minister stated, adding that research should contribute to improving irrigation systems, strengthening public administration, supporting local enterprises, informing educational reform, and enhancing human well-being.

The State Minister also highlighted that innovation is not only about advanced technology, but also about mindset, courage, creativity, and the willingness to transform challenges into opportunities. He encouraged students and young researchers to embrace curiosity, imagination, and responsibility as foundations for leadership and innovation.

President of Werabe University, Dr. Ing. Towfik Jemal, described the conference as a defining moment for the university as it expands from national annual research conferences to an international research platform.

Speaking under the message “Global Participation for Local Actions,” the president stated that the university is committed to becoming one of Ethiopia’s leading comprehensive universities with meaningful global impact through excellence in teaching, research, innovation, technology transfer, and community engagement.

He announced that the conference received more than 200 research paper submissions from across the world.

Following a rigorous peer-review process, 43 high-quality research papers from 12 countries were selected for presentation.

The conference showcased growing research interest in Artificial Intelligence and its applications in higher education, digital transformation, innovation systems, and service delivery.

Vice President for Academic, Research, Technology Transfer and Community Engagement, Anwar Ahmed, welcomed participants and highlighted the university’s recent achievements in research, innovation, and community engagement.

He stated that Werabe University has developed innovative technologies such as the Graduate Document Verification System (GDVS), e-Learning Management System, Clinical Management System, and several agricultural technologies.

According to the Vice President, the university is collaborating with international institutions including Yeungnam University, Ovidius University of Romania, Bradford International Business School of India, the University of Rwanda, and many more.

During the event, Prof. LEE Sang H. from Yeungnam University delivered an online message of appreciation regarding the successful organization of the conference.

Keynote speaker Prof. Delenesaw Yewhalaw also presented his keynote address and appreciated the leadership of Werabe University for organizing a successful international conference that promotes research collaboration and knowledge exchange.

Participants from universities, research institutions, government offices, and international organizations attended the conference both physically and virtually.

Organizers stated that the conference will continue tomorrow with additional parallel research presentations and scholarly discussions.

11/05/2026
Photos from Werabe University's post 11/05/2026

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያውን አለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ማካሄድ ጀመረ

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ12 ሀገራት የተውጣጡ ተመራማሪዎች የምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት የምርምር ኮንፈረንስ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል።

አለምአቀፍ የምርምር ኮንፈረንሱ "Innovation for SDGs and Global Resilience በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው መርሀግብር በጤና፣ በት/ት በቴክኖሎጂ እና ግብርና መስኮች 43 የምርምር ውጤቶች ይቀርቡበታል።

Want your school to be the top-listed School/college?

Telephone

Website

https://t.me/werabeuniversitywru, https://www.neaea.com/werabe-university/, https://moe.gov.et/