ሮሜ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
¹³ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
¹⁴ የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ።
መልካም ዕለተ ሰንበት (ቅዳሜ)
Zerhun Getu Muraso
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zerhun Getu Muraso, College & University, Piazza, Awassa.
አብረን እንዘምር
27/08/2025
#ጥምቀት #ሥርዓት ብቻ ሳይሆን #ድነትም ጭምር ነው፡፡
አንዳንድ አስተማሪዎች ጥምቀት ሥርዓት ብቻ እንደሆነ ሰው አምኖ ብቻ ድነት እንደሚያገኝ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ሰው በእምነት (በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን) የእግዚአብሔር ልጅ መሆን ይችላል፡፡ «በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚዘብሔር ልጆች ናችሁና፡፡» ገላ 3፡-26፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች የመባል ስልጣን በክርስቶስ ኢየሱስ በማመናችን ካገኘን ከክርስቶስ ጋር አንድ የመሆንና ሞቱን እና ትንሳኤውን የመተባበር እንዲሁም አዳማዊ ሥጋችንን ገፍፈን ክርስቶስን ለመልበስ መጠመቅ ያስፈልገናል፡፡ ቆላ 2፡-11-15፤ ሮሜ 6፡-3-8፤ ገላ 3፡-27፡፡ ስለዚህ በእምነት በኩል በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን በጥምቀት ደግሞ ከእርሱ ጋር አንድ እንዲንሆንና በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የዳኑበትን የመርከብ ምሳሌ በጥምቀት እንደምንድን ገልጾልናል፡፡ 1ኛ ጴጥ 3፡-20-21 « ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍስ በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግስት በኖኅ ዘመን በቆዬ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም፡፡ 21 ይህም ወኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፤ የሰውነት እድፍ ማስወገድ አይደለም ለእግዚአብሔር የበጎ ሕሊና ልመና ነው እንጂ ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ነው፡፡» በዚህ ክፍል ሐዋሪያው ጴጥሮስ ጥምቀትን ድነት ነው ያድነናል ነው ያለው እንጂ ወግና ሥርዓት ነው አላለም፡፡ ጥምቀት ከላይ ለተገለጸው ሀሳቦች ምሳሌ ነው እንጂ እንዴት ነው ተራ ሥርዓት ሊሆን የሚችለው? መዳን ያገኘንበትን በክርስቶስ አዳማዊ ሥጋችንን የገፈፍንበት ዳግም ልደታችን እንዴት ሆኖ ነው ተራ ሥርዓት የሚሆነው? ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ ቀበር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም፡፡ ዮሐ ወ. 3፡-3፡፡ ይህንን ዳግመኛ መወለድን ጥምቀት አይደለም ብለው የሚሰብኩ ደፋር ሰዎችም አሉ፡፡ ይህን ዳግመኛ ውልደት ትምቀት መሆኑን የሚንረዳው ገላ 3፡-27 እና 1ኛ ጴጥ 1፡-23 በማየት ነው፡፡ 1ኛ ቆሮ 15፡-44 «ፍጥረታዊ አካል ይዘራል መንፈሳዊ አካል ይነሳ፡፡ ፍጥረታዊ አካል ካለ መንፈሳዊ አካል ደግሞ አለ፡፡45እንዲሁ ደግሞ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ፡፡» ይህንን ክፍል ሙሉ አንብቡ፡፡ ጥምቀት ይህ ፊተኛውን ሰው ከመሬት መሬታውን ሽሮ የኋለኛውን አዳም ያስለብሳል፡፡ የፊተኛው አዳም በጥምቀት እንደ ዘር ተቀብሮ ሌላኛው ሥጋ ሆኖ እንደሚበቅል ያስረዳናል፡፡ አዎ ሰው በእምነት መዳን ያገኛል ግን የለበሰውን አዳማዊ ሥጋውን በጥምቀት ሳይቀብር የክርስቶስ ሥጋ መልበስ አይችልም፡፡ ይህ አሁን የለበስነው ዘር በጥምቀት ተቀብሮ ሌላኛው ዘር መተካት አለበት፡፡ ሰው በእምነትበ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በጥምቀት ደግሞ ክርስቶስን መልበስ አለበት፡፡ ለዚህ ነው አምኖ ያልተጠመቀ መዳን አይችልም፡፡ አምኖ ያልተጠመቀ ሰው አይድንም፡፡
ወንድም ዘሪሁን ከሀዋሳ
25/08/2025
አጥማቂው በሌላ ስም ተጠማቂው በሌላ ስም የምል ፍልስፍና
አንዳንድ የኃይማኖት መሪዎች ነን የሚሉ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እውነታውን ሲክዱና ለእነርሱ እራሳቸው ያልገባቸውን ነገር ለተከታዮቻቸው ሲያስተምሩ ሲመለከት ያስገርመኛል፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ያልገባቸውን ነገር ለሌሎች የሚስተምሩ ከሆነ ተከታዮች በአዕምሮአቸው እውነት ያልሆነውን ነገር ይይዙና የያዙትን የስህተት ትምህርት ለሌሎችም ለማስተማር ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህም ተጠያቂዎች እራሳቸው አስተማሪዎች ናቸው፡፡ በሐዋ.ሥራ 20፡-28 «በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉ እና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡» ይላል፡፡
ወደ ዋና ሀሳቤ ሲመለስ አንዳንድ መሪዎች ጥምቀትን እንደ ሥርዓት አድርገው ቢጠመቁም ባይጠመቁም ችግር እንደለሌ እና ዋናው እምነት ስለሆነ እስካመንን ድረስ ምንም እንኳን ባንጠመቅም እንድናለን ይላሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ጥምቀት የኢየሱስ ታላቁ ተልዕኮ ነው ይሉና ማቴ 28፡-19-20 «እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡» የምለውና የኢየሱስ ክርስቶስን ትዕዛዝ ይጠቅሳሉ፡፡
ሦስተኞቹ እና በጣም የሚየስቁኝ የቅርብ ተፈላሳፊች አጥማቂው ሌላ ቃል ይላል ተጠማቂው ሌላ ቃል ይላል የሚሉ ናቸው፡፡ ተልዕኮው ልክ ነው፡፡ ነገር ግን ችግር ያለበት ኢየሱስ በማን ስም እንዲያጠምቁ አዘዛቸው እና የታዘዙ ሐዋሪያቶቹ በማን ስም አጠመቁ የምለው ላይ ነው፡፡ ኢየሱስ አሕዛብን አጥምቋቸው ያለው በአብ፤ በውልድና በመንፈስ ቅዱስ (ስም) ነው እንጂ በአብ ስም በወልድ ስም እና በመንፈስ ቅዱስ ስም (ስም+ስም+ስም) አይደለም፡፡ ይህንን በመንፈስ ቅዱስ የተረዱ ሐዋሪያቶች በበዓለ ኀምሳ ቀን ሰዎችን በኢየሱስ ስም ብሎ አጠመቁ የሐዋ.ሥራ 2፡-38፡፡ ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍልን የሚፈላሰፉ ሰዎች፡-
1. በኢየሱስ ስም መጠመቅ ያለባቸው አሕዛቦች ሳይሆኑ ኢየሱስን የገደሉት የአይሁድ ወገኖች ብቻ ናቸው እንጂ የአሕዛብ ወገን ግን በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም መጠመቅ አለባቸው ይላሉ፡፡
2. አንዳንዶቹ ከአህዛብ ወገን ሆኖ መጀመሪያ ያመነ ሰው ከሆነ መጠመቅ ያለበት በኢየሱስ ስም ነው ይሉና ጥምቀት ጋር ሲመጡ በአብ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ በአንዱ አምላክ ስም ብለው ያጠምቃሉ፡፡
3. ሌሎች ደግሞ ሐዋሪያው ጴጥሮስ ያለው በኢየሱስ ስም ተጠመቁ ነው እንጂ በኢየሱስ ስም ልያጥምቃችሁ አላለም፤ ስለዚህ እሱ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ይላል ተጠማቂዎቹ ደግሞ በኢየሱስ ስም እያሉ መጠመቅ አለባቸው ይላሉ፡፡
እስክ እውነታውን አንሽሽ እና ኢየሱስ ምን አለ ሐዋሪያቶች በማን ስም አጠመቁ እኛስ አሁን በማን ስም ነው የምንጠመቀው እንዲሁም የሚናጠምቀው ብለን እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ሐዋሪያቶቹ በአብ በወለድና በመንፈስ ቅዱስ ስም (በኢየሱስ ስም) አጠመቁ፡፡ በዚህ የኢየሱስ ስም ጥምቀት አሕዛብንም አይሁድንም ነው ያጠመቁት፡፡ የሐዋ.ሥራ 2፡38፤8፡-16፤10፡-48፤19፡-5 ጥምቀት የሚያስፈልገው ላመነ ሰው ብቻ ነው፡፡ በማር ወንጌል 16፡-16 «ያመነ የተጠመቀም ይድናል፤ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡» ይላል፡፡ ከዚህ ክፍል የሚንረዳው ሰው ከመጠመቁ በፊት በኢየሱስ አዳኝነት ማመን እንዳለበት ነው፡፡ ታዲያ በኢየሱስ ያመነ ሰው ሞቱንና ትንሳኤውን እንዲተባበር መጠመቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት አንድ አሕዛብ የሆነ ሰው በኢየሱስ አዳኝነት ካመነ በስሙ ይጠመቃል እንደ ማለት ነው፡፡ ከአሕዛብ ወገን የሆነው ቆርኔለዎስም በኢየሰስ ስም የተጠመቀው በኢየሱስ አዳኝነት በማመን ነው፡፡ እዚህ ሐዋሪያቶቹ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲያጠምቁ ኢየሱስ በመንፈስ ከእነርሱ ጋር እንደሆነም አንዘንጋ፡፡ ማቴ 28፡-20 «… እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡» ይላል፡፡ ስለዚህ እያንዳንዷን ሐዋሪያቶች የሚያደርጉትን እሱም አብሮአቸው ሆኖ ያያል ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኛስ ዛሬ በኢየሱስ ያመንን ሰዎች የስሙን ጥምቀት የሚንሸሸው ለምንድ ነው? ሌሎቻችን ደግሞ እውነታውን ላለመቀበል ብቻ ብለን አጥማቂው በሌላ ስም ሲያጠምቅ ተጠማቂው ደግሞ ሌላ ስም ይጠመቃል እያልን በእግዚአብሔር ቃል ላይ የሚንፈላሰፈውስ እከ መቼ ነው?
ጥምቀት ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ድነትም ጭምር እንደሆነና ሰው በኢየሱስ በማመን ካልተጠመቀ እንደማይድን በቀጣይ ክፍል ይዠላችሁ እቀርባለው፡፡
መልካም ቀን!
ወንድም ዘሪሁን ጌቱ ከሀዋሳ
23/08/2025
መጀመሪያም የሐዋሪያዊት ቤተ እምነት እስተምህሮ ያልገባቸው ሰዎች የእውነት ወንጌልን ከማመን ይልቅ እውነትን ላለመቀበል ምክንየት ሲፈልጉ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ምንም ለእነዚህ የእግዚአብሔርን ወንጌል በተራ ዓለማዊ ነገር ለሚሸጡት መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው ብዬ ባላምንም አንዳንድ በህይወቴ ለምወዳቸ ሰዎቹ ሲል አንዳንድ እውነታዎችን መግለፅ አስፈላጊ ሆኖ ታይቶኛል፡፡
1. የሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን እምነት የተመሠረተው በህልም ሳይሆን በመጽሐፍ ቅዱስ የማቴዎስ ወንጌል 16፡-18 « … በዚህችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፡ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም፡፡» በተባለው ላይ በጴጥሮስ ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ሲትሆን ለዚህም ማሳያ የሚሆነው ሐዋሪያ ጴጥሮስ የመጀመሪያውን ሥራ በሐዋ. ሥራ 2፡-38 ላይ በኢየሱስ ስም ሰዎችን አጥምቆ ሥራ የጀመረበት ነው፡፡
2. የሐዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያን በሰዎች ፍልስፍና የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን ሳትሆን በቃሉ መሠረት ኤፌ 2፡-20 «በሐዋሪያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል ፤- የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡» በምለው በቃሉ መሠት ነው እንጂ Mono, Bi and Tri ከምልና ሰባሪዮስ ከምለው ቅዠት ላይ የተመሠረተች ቤተ ክርስቲያን አይደለችም፡፡
3. ከሰማይ ሥጋ ሳይሆን ቃል ነው የወረደው፡፡ በት. ኢሳይያስ 59፡-16 « ሰውም እንደሌለ አየ፣ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፣ ጽድቁም አገዘው፡፡» ይላል፡፡ ለዚህም አግዚአብሔር የራሱን ሥጋ አዘጋጅቶ ሰዎችን ከራሱ ጋር አስታርቋል፡፡ 2ኛ ቆሮ 5፡-19 « እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበረ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ፡፡» ይላል፡፡ ቃል ሥጋ ሆነ እንጂ ሥጋ ከሰማይ አልወረደም፡፡ የሐዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያንም ቃል ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተሞልቶ በእኛ አደረ የዮሐ. ወንጌል 1፡-14፤ 3፡-31፡፡ ነው ብላ የሚታስተምረው
4. «ኢየሱስ» የአብ፤ ወልድና የመንፈስ ቅዱስ የመድኃን ስም ነው እንጂ ኢየሱስ የወልድ ስም ብቻ አይደለም፡፡ ለዚህ ማሳያ ት.ኢሳይያስ 9፡-6 «ሕፃን ተወልዶናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡» የተባለው የዘላለም አባት በማቴዎስ ወንጌል 1፡-21 ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፡፡ ስለዚህ ይህ የተለደው ልጅም የዘላለም አባትም ነው፡፡ የየሐ ወንጌል 14፡-8-10፤ 10፡-30
5. በመክሊት ስም ሕዝብን አይበዘብዙም፡፡ አንድ ቤተ ክርስቲያን ለወንጌል አገልግሎት የሚሆን ገንዘብ ከራሷ ምዕመናን ወይንም ከውጭ ካሉት ከቤተ ክርስቲያኗ ከመንፈሳዊ አጋር ቤተ ክርስቲያን ታገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያን የውጭ ሀገር ቤተ ክርስቲያንን እርዳታ የምትፈልግ ቤተ ክርስቲያን ስላልሆነች ከራሷ ምዕመና ገቢዋን ታሳድጋለች፡፡ ይህ ማለት ህዝብን መበዝበዝ ሳይሆን ሰው ባለው መክሊት (Talent) ቅዱሳንን እንዲያገለግል ማመቻቸት ነው፡፡ ይህም በበጎ ጎን የሚታይ እንጂ ለትችት የሚያደርጋት የሚያስወቅሳት ነው ብዬ አላምንም፡፡ ለምሳሌ ያኽል አሁን የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በውጭ ሀገር ቤተ ክርስቲያናት ጋር በነበራት ጥምረት እየተፈጸመባት ያለው ችግር ለዚህ በቂ ማሳያ ነው፡፡
6. ሙታን እንደሚነሱ ከሚያምኑ ቤተ እምነቶች በይበልጥ የሚታምን ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ለዚህ ነው ሰው በማመን እንዲጠመቅ እና በጥምቀት የክርስቶስ ኢየሱስ ሞት እንዲተባበር የሚታደርገው፡፡ ሮሜ 6፡-3-5
7. ኢየሱስ ከዳዊት ስርና ዘር የተወለደ ቢሆንም ከዳዊት ዘር ሥጋ የተካፈለ አይደለም፡፡ ነገር ግን “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።”
— ዕብራውያን 2፥14-15
አንድ ሰው የአንድ ዘር አባል ለመሆን ከወንድ ዘር እና ከሴት ዘር ማግኘት አለበት፡፡ ኢየሱስ ግን ይህንን ዘር አላገኘም፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች ግን ኢየሱስን የዳዊት ልጅ፤ የዮሴፍ ልጅ ይሉታል፡፡ ማቴዎሰ 1፡-1፤20፣ 9፡-27፤ 15፡-22፤ 22፡-41-42 ማርቆስ 10፡-48፤ 11፡-10፤ ሉቃስ 18፡-38፡፡
8. ኢየሱስ የአብ ወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም ሲሆን የሰው ሁሉ የመድኃን ሰም ነው፡፡ ሐዋ ሥራ 4፡-12፣ ማቴ 1፡-21፡፡ አንድ ምክያታዊ ጥቅስ ልንገራችሁ፡፡ «በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግስተ ሰማያት የሚገባ አይደለም፡፡ ማቴ 7፡-21» ይልና አሁንም በሐዋ. ሥራ 2፡-21 «የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፡፡» ይላል፡፡ ከእነዚህ ሁለት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የሚንረዳው ሰው ጌታ ሆይ ብሎ ሳይሆን ኢየሱስ ብሎ የጌታን ስም ጠረቶ እንደሚድን ነው፡፡ የመዳን ሰም ኢየሱስ ስለሆነ፡፡
9. ሰው የሚድነው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በስሙ በመጠመቅ እንጂ ሳያምን በጥልቅ ውሃ በመጠመቅ አይደለም፡፡ እሱማ ከሆነ ያላመኑ ሰዎችም በውሃ ይታጠባሉና፡፡ ነገር ግን ሰው ስላመነ ብቻ በኢየሱስ ስም ሳይጠመቅ የኢየሱስን ሞትና ትንሳኤን መተባበር አይችልም እንዲሁም ኃጢአቱ አይስተሰርይም፡፡ ማር 16፡-16፤ ዮሐ 3፡-3፤ የሐ. ሥራ 2፡-38፤ ሮሜ 6፡-3-5፡፡
10. አሥረኛውን እራሱም ሳይገልጽ ወደ አስራ አንደኛው አልፎታል
11. በልሳን መናገር ከፀጋ ሥጦታዎች አንዱ እንጂ የመዳን መስፈርት ወይም ምልከት ነው ብላ አታምንም፡፡ 1ኛ ቆሮ 12፡-4-11
12. ምናልባት አንዳንድ በህብረት ውስጥ እንደ ይሁዳና እንደ ሐናኒያ ያሉ ሰዎች ስለማይጠፉ ሊሆን ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሐዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ታንቆ ይሞታሉ፤ እራሳቸውን ያጠፋሉ፤ በስለት ይወጋሉ የሚለው ነገር ከእውነት የራቄ ነው፡፡ ይልቅ አንዳንድ ከሐዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ ያልሆኑ ሰዎች እራሳቸው ልጆቻቸውን የሚመክሩት እንደ ሐዋሪያዊት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ነእንዲሆኑላቸው ከመምከርም ጭምር ነው፡፡
13. ይህም 5ኛ ቁጥር ያነሳውም ደግሞታል
14. በነፃ ስጡ የተባለው በነፃ የተቀበላችሁትን የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ ሰው ለቤተ ክርስቲያን ገቢ ይሁን ብሎ ያሳተመውን ትራክት፤ ካሴት፤ አንዲሁም መጽሔት አይደለም፡፡ ይህም የሚደረገው ለግለሰብ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያኒቷ ገቢ ነው፡፡ ባይሆን እንደ እነ እንትና የተፀለየ ዘይት ነው፣ የተለየ መጽሔት ነው፡፡ ብላ አትሸጥም፡፡
በመጨረሻም ይህ ግለሰብ መጽሐፍ ቅዱስ እንደምለው 1ኛ ዮሐ 2፡-18-19 ልጆች ሆይ መጨረሻ ሰዓት ነው፣ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳን ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነስተዋል ስለዚህም መጨረሻ ሰዓት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ከእኛ ዘንድ ወጡ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆነ ይገለጥ ዘንድ ወጡ፡፡ የሚለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ግድ ስለሆነ ነው፡፡
25/04/2025
“ይህም ያልፋል!”
አንድ ንጉስ አማካሪዎቹን ሰበሰበና፣ እንዲህ ስል አዘዛቸው፡- ሲከበርም ሆነ ሲዋረድ፣ ሲያገኝም ሆነ ሲያጣ፣ ሲደሰትም ሆነ ሲከፋ፣ ድል ሲያደርግም ሆነ ሲሸነፍ በዚህ ሁሉ ውስጥ ልያስታውሰው የሚችል፣ መንገድን ሁሉ የሚመራኝ፣ ከልክም አልፌ እንዳልሄድ ከልክም ወርጄ ዝቅም እንዳልል በማስተዋልና በጥበብ የሚያስፈልገኝን አንድ አረፍተ ነገር ፈልጉልኝ፣ ነገር ግን የተወሳሰበና ፍልስፍና አልፈልግም፤ ቀላልና ግልጽ የሆነ አረፍተ ነገር እፈልጋለሁ አላቸው፡፡ አማካሪዎቹም ከቤተ-መንግስት ወጡ፤ ለአራት ወር ሙሉ መከሩ፡፡ አወጡ አወረዱ፤ አንዱን ጣሉ አንዱን አነሱ፤ ብዙ ከለፉ በኋላ አንድ ድምዳሜ ላይ ደረሱ፡፡ የደረሱበትን ሀሳብ በብራና ላይ ጽፈው ወደ ንጉሱ ዘንድ መጡ፡፡ የተጠቀለለውን ብራና ሰጡት፡፡ ንጉሱም ገለጠውና አነበበው፤ ጽሁፉም እንዲህ ይል ነበር “ይህም ያልፋል!” “ለምን?” አላቸው ንጉሱ፡፡ እነሱም፡- “በየትኛውም ዝና ላይ ብትሆን እና ስልጣን ሰገነት ላይ ብትወጣም፣ ብትደላደል ይህም ያልፋል ብለህ ካሰብክ ግፍን አትሰራም፣ ፍትህን አታዛባም፣ ድሀን አትበድልም፣ ከልክም አታልፍም፡፡ ነገር ግን ራስህን ዘላለማዊ ነኝ ብለህ ከሰብክ፣ ጊዜ የማይሽርህ፣ ዓለም ፊቷን የ ማታዞርብክ ብመስልህም ነገሮች በቅጽት ይቀየሩና ራስህ በፈጠርከው ወሂን ትወረወራለህ፣ ባወጣኸው ህግ ትቀጣለህ፣ በቆረጥኸው ዱላ ትመታለህ፣ ባሳደግኸው ውሻ ትነከሳለህ፡፡ ስለዚህ አሁን የተቀመጥክበት ዙፋን የሚታንቀጠቀጥበት ስልጣን “ይህም ያልፋል!” ብለህ አስበው ተቀናቃኞችህን እንዳሸነፍክ፣ ዓለምን ሁሉ ጠቅልለህ እንደያዝክ፣ ሁሉ በእጅህ ሁሉ በደጅህ እንደሆነ፣ በለስ እንደቀናልህ፣ አንደኛ እንደወጣህ፣ እንደተጨበጨበልህ፣ እንደታፈርክና እንደተከበርክ በፍፁም አትቀርም፡፡ ይህ በጊዜው ያልፋል፡፡ እነዚህ በዙሪያህ ያሉ አሽቃባጮች ሁሉ፡- ሳታስነጥስ ይማርህ! ሳትወድቅ እኔን! ሳትጠራቸው አቤት! ሳትልካቸው ወዴት! የሚሉህ፣ በገዛ ሀገርህ የሚያጅቡህ ከዙሪያህ ያሉ ሁሉ በቅጽበት ይክዱሃል፡፡ ከአንተ በፊት ሌሎች እንደነበሩ ሁላ ከአንተ በኋላ ሌሎች ይመጣሉ፣ ከፊትክ ሌላ ባይኖር ኖር ከኋላ ሌላ ባልመጣ ነበረ፡፡ በጊዜ ውስጥ ትላንት፣ ዛሬና ነገ አሉ፡፡ ዛሬ ትላንትን ነገ ደግሞ ዛሬን እየሆኑ ያልፋሉ፡፡ አንተ ሌሎችን እንደተካህ ሁሉ ነገ አንተን የሚተካህ ይመጣል፡፡ አንተ ሌሎችን እንዳሰርክ ሁሉ የሚያስርህ ደግሞ ይመጣል፤ አንተ እንደቀበርክ ሁሉ ቀባርህም ይመጣል፤ የዛሬ ቀባሪ ነገ ተቀባሪ ነው፤ ማንም እራሱን የሚቀብር የለም፤ ሌላውን እንደቀበረ ሁሉ እሱንም ሌላ ሰው ይቀብረዋል፡፡ እና ይህ ሁሉ ያልፋል ብለህ ካሰብክ ሁሉን በልኩ ሁሉንም በገደቡ ታደርጋለህ፡፡ የሌሎችን ታርክ አጥፍተህ፣ የሌሎችን ሀውልት ሰብረህ፣ የሌሎችን ስም አጉድፈህ፣ የሌሎችን ዋጋ አርክሰህ መኖር ትችላለህ ስልጣን እና አቅም እስካለህ ድረስ፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ያልፍና በጊዜው የአንተን ታርክ የሚያጠፋ፣ የአንተንም ሀውልት የሚሰብር፣ የአንተንም ስም የሚያጎድፍ በተራው ሌላ ይመጣል፡፡ የሚተካህን የሚትፈጥረው በዛሬው ተግባርህ ነው፡፡ ክፉ ከሆንክ ክፉ ይተካሃል፣ ርዕቱ ከሆንክ ርዕቱ ይተካሃል፡፡ ይህ ሁሉ ታርክ አልፎ ብትወድቅ ብትነሳም፣ ብትሰበር ብትጠገንም፣ ብትረሳ ብትታወስም፣ ከላይ ሆነህ ወደ ታች እንዳየህ ሁሉ ከታች ሆነህ ወደ ላይ ታያለህ፣ ያሰብከው ቀርቶ ያላሰብከው ቢመጣ ይህም ሁሉ ያልፋል ብለህ አስበው፡፡ ይህም ያልፋል ብለህ ካሰብክ፡- ተስፋ አትቆርጥም፣ ነፍስህ ሳትወጣ አትሞትም፣ ራስህን ለብስጭትና ለቁጣ፣ ለትካዜ አሳልፈህ አትሰጥም፡፡ ከሞት በኋላ ትንሳኤ ከመታሰር በኋላ መፈታት እንዳለ ታያለህ፡፡ የድል ጫፍ ሽንፈት እንደሆነ ሁሉ የሽንፈትም ጫፍ ድል ነው፤ የስልጣን ጫፍ መውረድ እንደሆነ ሁሉ የውርደትም ጫፍ ስልጣን ነው፣ የጤናም ጫፍ በሽታ እንደሆነ ሁሉ የበሽታም ጫፍ ጤና ነው፣ የብርሃን ጫፍ ጨለማ እንዲሁም የጨለማ ድንበርም ብርሃን ነው፡፡ ዓለም ቋሚ አይደለችም፤ ጊዜ ወደ ፊት ብቻ ነው የሚሄደው፡፡ እስር ቤትን የተከሉ አሁን በህይወት የሉም፡፡ ስለዚህ አንተም ዛሬ በታሰርክበት አትኖርም፤ ችግር ሲፈጠር የነበሩ አሁን ግን የሉም ወንድሜ አንተም በዛሬው ችግር ሰምጠህ አትቀርም፤ እንደሚያልፍ ካመንክ ለማለፍ ትጥራለህ፣ እንደማያልፍ ካመንክ ግን ያለህበትን ትቀበላለህ፤ የተቀበልከውንም ላትለውጠው ነገር፡፡ ችግርን ያልፋል ብለህ ካሰብክ ወደ ውጭ ታያለህ፣ ወደ ውጭ ትመለከታለህ፣ ወደ መፍትሄው ታማትራለህ፡፡ ሰው የሚኖረው ከስጋው በላይ ለህሊናው ነው፡፡ ውድቀት ለስጋህ ስትኖር ነው የሚመጣው፤ ክብርና ድል ግን ለህሊናህ ስትኖር ነው፡፡ እባብ ሲደበደብ አናቱን ይከላከላል፡፡ ምክንያቱም አናቱ ደህና ከሆነ ሌላ የተቆረጠ አካል እንኳ ብኖረው ይቀጠላል፤ የተጎዱ አካላትም ይፈወሳሉ፡፡ አናቱ ከተመታ ግን አለቀለት፡፡ ሰውም ህሊናውን ካጣ ሞተ ማለት ያነ ነው፡፡ ህሊናህን ማጣት ካፈልግክ “ይህም ያልፋል!” በል፡፡ የቆምክበት ቦታ የነገው መንገድህ መመልከቻ መነጽር ነው፤ ዛሬ ካለህበት ሰገነት ላይ እንዳትወድቅ መውረጃ ከጉድጓዱም እንዳትሰምጥ መሰላል ነው አሉት፡፡ ንጉሱም ምክራቸውን ሰምቶ በቤተ-መንግስቱ በራፍ፣ በምግብ አዳራሹ፣ በወሂን ቤቱ በር፣ በመኝታውም በዙፋኑም ላይ በትልቁ ጽሁፍ “ይህም ያልፋል!” ብሎ ጻፈና እሱም ሲወጣና ሲገባ፣ ሲመሽና ሲነጋ፣ ሲፈርድና ሲወስን ሁል ጊዜ “ይህም ያልፋል!” ይል ነበረ፡፡
Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Adam Betts, Tigist Nasaru
17/02/2024
Affini Filme maassowa
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Piazza
Awassa