Department of Journalism & Communication, Hawassa University

Department of Journalism & Communication, Hawassa University

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Department of Journalism & Communication, Hawassa University, College & University, Awassa.

27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ እንኳን ለኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሰን ፣አደረሳችሁ!

ኢድ ሙባረክ!

24/05/2026

#አሁን✨



የዓመቱ መዝጊያ ፕሮግራም

በጄሲሳ የበይነመረብ እልፍኝ በዓመቱ መዝጊያ ምሽታችን በሚድያ ስራ አመራር ፣በፍርድ ሂደቶች አዘጋገብ ፣በምርመራ ጋዜጠኝነት ከአለም አቀፍ ተቋማት ስልጠና ካገኘችዉ በ ኢትዮጵያ ሬድዮ ከ1983-2009ዓ/ም ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና አዘጋጅ ሆና ካገለገለችዉ እና በኢትዮጵያ ሬድዮ ብሔራዊ አገልግሎት ለ 16 ዓመታት እንዲሁም በኢቢሲ ለ10 ዓመታት በአጠቃላይ በሚዲያው ለ26 ዓመታት የካበተ ልምድም ካላት የጥያቄ እና መልስ አዘጋጅ ፣የተወዳጁ ዜና ፋይል ዋና ዜና አቅራቢ እና የመጀመሪያዋ ሴት የቀጥታ ስርጭት ዜና አንባቢ ጋዜጠኛ ብርቱካን ሀረገወይን ጋር የሚኖረን የJCSA የበይነመረብ ልምድ ልውውጥ (online talkshow) ተጀምሯል።

ከታች ባለዉ መስፈንጠሪያ ሊንክ ይቀላቀሉ።

👇👇👇👇👇👇
meet.google.com/jvd-kihd-nab

https://t.me/HU_JCSA_Group

24/05/2026

JCSA ONLINE TALKSHOW🎤

የዓመቱ መዝጊያ ፕሮግራም

✨ዉድ የጄሲሳ የበይነ መረብ እልፍኝ(online talkshow) ታዳሚዎቻችን ዓመቱን ሙሉ በርካታ ጋዜጠኞችን እና ከሙያዉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸዉን እንግዶች እየጋበዝን ተሰፍሮ የማያልቅ እዉቀት እና ልምድን ስናገኝበት የነበረዉ የዚህ ዓመት የበይነ መረብ እልፍኛችንን ቀናቶች ቀናትን እየተኩ ለመዝጋት 1 ቀን ብቻ ቀርቶናል።

✨ ታድያ የዚህ ሳምንት የመጨረሻዋ የበይነመረብ እልፍኝ እንግዳችን በሩስያ ሞስኮ በፖለቲካ ሳይንስ እና በ ጋዜጠኝነት እና ስነተግባቦት የተመረቀች እንዲሁም በሚድያ ስራ አመራር ፣በፍርድ ሂደቶች አዘጋገብ ፣በምርመራ ጋዜጠኝነት ከአለም አቀፍ ተቋማት ስልጠና ያገኘች በድጋሜም የስራ ሂደቷን ለማገዝ በቢዝነስ ማኔጅመንት ተመርቃ በ ኢትዮጵያ ሬድዮ ከ1983-2009ዓ/ም ከሪፖርተርነት እስከ ምክትል ዋና አዘጋጅ ሆና ያገለገለች ናት።

➤በኢትዮጵያ ሬድዮ ብሔራዊ አገልግሎት ለ 16 ዓመታት እንዲሁም በኢቢሲ ለ10 ዓመታት በአጠቃላይ በሚዲያው ለ26 ዓመታት የካበተ ልምድም አላት።

➤የጥያቄ እና መልስ አዘጋጅ ፣የተወዳጁ ዜና ፋይል ዋና ዜና አቅራቢ እና የራሷ የሆነ ወዝ እና ለዛ ያላት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት (ከጠቅላይ ሚኒስቴሮች እና ፕሬዝደንቶች )ጋር ወደተለያዩ የዓለም ሃገራት ሄዳ የቀጥታ ስርጭት ዘገባዎችን ያዘጋጀች የመጀመሪያዋ ሴት የቀጥታ ስርጭት ዜና አንባቢ ጋዜጠኛ ብርቱካን ሀረገወይን ናት።

መርሀ ግብሩ የሚካሄድበትን የgooglemeet ሊንክ የመወያያ ሰዓቱ ሲቃረብ ከታች ባለዉ በJCSA የቴሌግራም ግሩፕ የምናጋራቹ ይሆናል።
👇👇👇👇👇👇

እዉነቱን በኃላፊነትና በሚዛናዊነት እንነግራችኋለን!!



https://t.me/HU_JCSA_Group

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 23/05/2026

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን የሚዲያና ኢንፎርሜሽን አጠቃቀም ክህሎትን ለማሳደግ ያለመ ስልጠና በአለታ ወንዶ ከተማ ተሰጠ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህረበሰብ አገልግሎት አካል የሆነውና በጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህራን ተቀርፆ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሚዲያና መረጃ አጠቃቀም ክህሎት ለማሳደግ ያለመ ፕሮጀክ ሶስተኛ ዙር ስልጠና በአለታ ወንዶ ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሰጥቷል።

በስልጠናው ከአለታ ወንዶና ህዳሴ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመረጡ 40 ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ወቅቱን የዋጀና የመረጃና የሚዲያ አጠቃቀም ክህሎታቸውን ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑን በስልጠናው የተሳተፉ ተማሪዎች ገልፀዋል።

በስልጠናው የሚዲያና መረጃ ምንነትና ባህሪያት፣ የሚዲያና መረጃ አጠቃቀም ክህሎት አስፈላጊነትና ደረጃዎች፤ የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያስከትሉት ጉዳትና የሀቅ ማጣራት ክህሎት ላይ አትኩሮ ተሰጥቷል።

በሰልጠናው የሀቅ ማጣሪያ ዘዴዎችን (Fact checking tools) በመጠቀም በበይነ መረብ የሚሰራጩ መረጃዎችን በራሳቸው ማጣራት የሚችሉበት ክህሎት የሚጨምር መሆኑ ተመላክቷል።

ስልጠናውን የፕሮጀክቱ መሪ መልሰው ደጀኔ (ዶ/ር)፣ መ/ር ዮናታን ዘብዴዎስ፣ መ/ር ያረጋል መኩሪያና መ/ር እያዩ ዓለማየሁየ ሰጡ ሲሆን የሚዲያና ኢንፎርሜሽን ሊትሬሲ ክበብ (MILC) አባላት ተማሪዎች በረዳት አሰልጣኝነት ተሳትፈዋል።

በፕሮጀክቱ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዙር ስልጠናዎች በሀዋሳና በይርጋለም ከተሞች ከሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 120 ተማሪዎች መሰልጠናቸው የሚታወስ ሲሆን በመጪዎቹ ቀናት ከበንሳ ዳየ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተውጣጡ 40 ተማሪዎች በስልጠናው ይሳተፋሉ።

በየስልጠናዎቹ መጠናቀቂያም በየትምህርት ቤቶቹ የሚዲያና ኢንፎርሜሽን ሊትሬሲ ክበባትን በማቋቋም በጋዜጠኝነትና ኮምንኬሽን ትምህርት ክፍል ስር በሚንቀሳቀሰው የሚዲያና ኢንፎርሜሽን ሊትረሲ ክለብ ጋር ለማስተሳሰር ተችሏል።

ፕሮጀክቱ በሲዳማ ክልል አራት ከተሞች ከሚገኙ ስምንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ክህሎትን ለማሳደግ ታልሞ የተቀረጸ ነው።

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 23/05/2026



የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ት/ት ክፍል ተማሪዎች ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ጎብኝተዋል።

የተቋሙ የይዘትና የቴክኒክ ክፍል ባለሙያዎች የተቋሙን አጠቃላይ አደረጃጀት፣ ተልዕኮና ዓላማ እንዲሁም የቴክኖሎጂ አቅምና አተገባበር የተመለከቱ ገለጻና ማብራሪያዎች ለተማሪዎች ሰጥተዋል።

የዜናና የፕሮግራም የሥራ ክፍሎች፣ የሬድዮና ቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች፤ እንዲሁም የፋና ላምሮት እና የዲጂታል ሚዲያ ስቱዲዮዎችም የጉብኝቱ አካል ነበሩ።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች ስለትብብራችሁና ስላደረጋችሁልን መስተንግዶ ከልብ እናመሠግናለን!

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 22/05/2026



የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ት/ት ክፍል ተማሪዎች በአዲስ አበባ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት የሚያደርጉትን ትምህርታዊ ጉብኝት ቀጥለዋል።

ተማሪዎቹ ሸጎሌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC)የሚዲያ ኮምፕሌክስ ጎብኝተዋል።

በEBC የሚዲያ ኮምፕሌክስ በነበራቸው ቆይታ የተቋሙን ሙዝየም ጨምሮ ፤ የዜናና የፕሮግራም የሥራ ክፍሎች፣ የሬድዮና ቴሌቪዥን ስቱዲዮዎች፤ እንዲሁም የይዘት ዝግጅት ሂደቶችን ተመልክተዋል።

የEBC አመራሮችና ሠራተኞች ስላደረጋችሁልን መስተንግዶ ከልብ እናመሠግናለን!

ዘጋቢ:- እፁብድንቅ አብርሃም (የ3ኛ ዓመት የጋዜጠኝነትና ኮሙንኬሽን ትምህርት ክፍል ተማሪ)

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 21/05/2026

ትምህርታዊ ጉብኝቱ እንደቀጠለ ነው

ተማሪዎቻችን በኢትዮጵያ የግል ፕረስ ታሪክ ለረዥም ዓመታት የዘለቀውን ሪፖርተር ጋዜጣን ጎብኝተዋል።

የሪፖርተር ባልደረቦች ከጋዜጣው ምስረታ ጀምሮ እስከዛሬ ስለደረሰበት ደረጃ እንዲሁም ስለ ይዘት ዝግጅትና ተያያዥ ጉዳዮች ለተማሪዎች ገለጻ አድርገዋል።

ሪፖርተር ጋዜጣ በአማረኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የሚታተሙ ሁለት ጋዜጦችን ለአንባቢያን በማድረስ ላይ ይገኛል።

ጋዜጣው 30ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን በያዝነው ዓመት ማክበሩም የሚታወስ ነው።

የሪፖርተር ጋዜጣ አመራሮችና ሠራተኞች ላደረጋችሁልን ቀና ትብብር የላቀ ምስጋና እናቀርባለን 🙏

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 21/05/2026

የተማሪዎች ትምህርታዊ ጉብኝት በአፍሪካ ሬነሰንስ ቴሌቪዥን (Arts)

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪዎች በቀጠለው ትምህርታዊ ጉብኝት የአፍሪካ ሬነሰንስ (Arts) ቴሌቭዥንን ጎብኝተዋል።

ተማሪዎች በጉብኝታቸው የተለያዩ የሥራ ክፍሎችንና ስቱዲዮዎችን የተመለከቱ ሲሆን ስለ ስራ ሂደቱም በየክፍሉ ባለሙያዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የአርትስ ቴሌቪዥን አመራሮችና ሠራተኞች ስለቀና ትብብራችሁ ከልብ እናመሠግናለን🙏

ዘጋቢ:- ፀሐይ አበበ
3ተኛ ዓመት የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪ

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 20/05/2026

የተማሪዎች ትምህርታዊ ጉብኝት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምኒኬሽን ትምህርት ክፍል የ 3ተኛ አመት ተማሪዎች አዲስ ሚዲያ ኔትወርክን ጎብኝተዋል

ተማሪዎቹ በጉብኝታቸው ወቅት በድርጅቱ ውስጥ የሬዲዮ የቀጥታ ስርጭት፣ የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን ስቱዲዮዎችን፣ የፕሮዳክሽን ስቱዲዮዎችን እንዲሁም የስራ ሂደቶችን ተመልክተዋል። በድርጅቱ ሰራተኞችም ስለ ጋዜጠኝነት እና ስለ ተግባራዊ ክህሎቶች የተመለከተ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አመራሮች እና ሰራተኞች ስላደረጋችሁልን መስተንግዶ እናመሰግናለን።

ዘጋቢ ቤዛዊት ዘውዴ:
የ3ኛ ዓመት የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ተማሪ

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 20/05/2026

የተማሪዎች ትምህርታዊ ጉብኝት በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል የ3ኛ አመት ተማሪዎች የሚዲያ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል። አንጋፋው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትንም የጉብኝታቸው ጅማሮ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት በነበራቸው ቆይታም በይዘት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚውና በየክፍሎቹ ዋና አዘጋጆችና ባለሙያዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ላለፉት 85 ዓመታት ያህል እያገለገለ የቆየ ሲሆን በዓሉ ግርማ ፣ ስብሃት ገ/ እግዚአብሔር ፣ ማሞ ውድነህን ጨምሮ በርካታ አንጋፋ ጋዜጠኞችና ደራሲያን የሰሩበት አንጋፋ ተቋም ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ላደረጋችሁልን ቀና ትብብር ከልብ እናመሠግናለን 🙏

ዘጋቢ: በእውቀቱ አዝመራው

(የ3ኛ ዓመት የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ተማሪ)

Photos from Department of Journalism & Communication, Hawassa University's post 19/05/2026

በጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህራን የተቀረጸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የሚዲያና መረጃ አጠቃቀም ክህሎት የማሳደግ ፕሮጀክት ሁለተኛ ዙር ስልጠና በይረጋለም ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ተሰጠ።

ከይርጋለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ከጽናት አካዳሚ ለተውጣጡ 40 ተማሪዎች የተሰጠው ይህ ስልጠና የሚዲያና መረጃ ምንነትና ባህሪያት፣ የሚዲያና መረጃ አጠቃቀም ክህሎት አስፈላጊነትና ደረጃዎች፤ የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያስከትሉት ጉዳትና የሀቅ ማጣራት ክህሎት ላይ አትኩሮ ተሰጥቷል።

ሰልጣኞቹ የሀቅ ማጣሪያ ዘዴዎችን (Fact checking tools) በመጠቀም በበይነ መረብ የሚሰራጩ መረጃዎችን በተግባር እንዲያጣሩ ማድረግም የስልጠናው አንዱ አካል ነበር።

ስልጠናውን የፕሮጀክቱ መሪ መልሰው ደጀኔ (ዶ/ር)፣ መ/ር እያዩ ዓለማየሁ፣ መ/ር ዮናታን ዘብዴዎስ እና መ/ር ያረጋል መኩሪያ የሰጡ ሲሆን የሚዲያና ኢንፎርሜሽን ሊትሬሲ ክበብ (MILC) አባላት ተማሪዎችም በረዳት አሰልጣኝነት ተሳትፈዋል።

በፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ከታቦርና አዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች መሰልጠናቸው ይታወሳል።

በየስልጠናዎቹ መጠናቀቂያም በየትምህርት ቤቶቹ የሚዲያና ኢንፎርሜሽን ሊትሬሲ ክበባት ተቋቁመዋል።

ፕሮጀክቱ በሲዳማ ክልል አራት ከተሞች ከሚገኙ ስምንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ክህሎትን ለማሳደግ ታልሞ የተቀረጸ ነው።

Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Awassa