17/06/2025
መማር ለምትፈልጉ የማትከስሩበት ነው ተጠቀሙ
Bible study and preaching the Gospel
17/06/2025
መማር ለምትፈልጉ የማትከስሩበት ነው ተጠቀሙ
25/04/2025
ክፍል 7 ፡ የመጨረሻው ዘመን (ቤዛችሁ ቀረቧል) ይህ ቻናል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት የምንማማርበት ነው። ዓላማውም ክርስቲያኖችን ማገልገል ፣ መጽሐፍ ቅዱስ የማጥናት ልምድ የሌላቸውን ለማነሳሳት እና ክርስትናን ላልተረዱት ወንጌል ...
ሕዝ 38፡1-7 እየተፈፀመ ይሆን? ቤተክርስትያን ተነጥቃለች ወይስ ...? በዓለማችን የወንድማማቾች ጦርነት በዝቷል። ምን ተረዳችሁ?
የወንጌል አገልጋይ ሆይ:-
ቲቶ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤
¹²-¹³ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
¹⁴ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
¹⁵ ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።
ሐዋርያት 13 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁸ እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ፤
³⁹ በእርሱ የሚያምን ሁሉ በሙሴ ሕግ በኩል ማግኘት ያልተቻለውን ጽድቅ ያገኛል።
⁴⁰ ስለዚህ ነቢያት እንዲህ ብለው የተናገሩት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤
⁴¹ “ ‘እናንት ፌዘኞች፤ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፤ ጥፉም፤ ማንም ቢነግራችሁ፣ የማታምኑትን ሥራ፣ እኔ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’ ”
እንግዲህ እናንተ የምድር ሰዎች ሆይ ይህን እውነት እንዳትቃወሙ። ብትቃወሙ ዕንባቆም 1:5 ላይ እንደተናገረው እያያችሁ እየጠፋችሁም የእግዚአብሔር ስራውን ይሰራል። ይልቁን እንዲገለጥላችሁ ጸልዩ እንጂ።
Our great hope, Jesus, is coming.
1ኛ ቆሮንቶስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ማንም ራሱን አያታልል፤ ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበበኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ይሁን።
¹⁹-²⁰ የዚህች ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። እርሱ ጥበበኞችን በተንኰላቸው የሚይዝ፤ ደግሞም፦ ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል ተብሎ ተጽፎአልና።
04/02/2024
“የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ትልቁ ጥፋት ይህ ነው፥ የወንጌሉ ዓለም ለእውነት በእውነት መቆም አለመቻላቸው ነው።”
Francis Schaeffer (1912 - 1984)
10 Things You Should Know about Francis Schaeffer The conviction that the Bible held basic answers for basic question would characterize his life and work.
“ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና፥ ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች፥ ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።”
— ዕብራውያን 7፥18-19
“በበዛችሁም ጊዜ በምድርም ላይ በረባችሁ ጊዜ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በዚያ ዘመን፦ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይጠሩም ልብ አያደርጉትም፥ አያስቡትምም፥ አይሹትምም፥ ከእንግዲህ ወዲህም አይደረግም።”
— ኤርምያስ 3፥16
07/01/2024
እኚህ አባት አቡነ ጎርጎሪዮስ ይባላሉ። ከጎን ያለው ፎቶ ወጣት ሳለው የተነሳሁት ነው። ከአቡነ ጎርጎሪዮስ ከተማርኳቸው ትምህርቶች አንዱ ስለታቦት ነበር። በዚያን ጊዜ ለእኔ መንፈሳዊ ትምህርት የመጀመሪያዬ ስለነበር ነጭ ወረቀት ላይ የመጻፍ ዓይነት ነበር። ስለታቦት፡-
በኢትዮጵያውያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን ብቻ ያለ ስርዓት መሆኑን ተምሬአለሁ። ከአምስቱ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ ብቻ ይህንን ስርዓት ስታካሂድ አንዳቸውም አልተከተሏትም፤ ምክንያቱም የግድ አይደለም ደግሞም አላመኑበትም ማለት ነው። ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የሌለውን ስርዓት ለመፈጸም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መዋሸት ያስፈልጋል። ይህንን ከባድ ውሸት በድፍረት የፈጸመች ሀገር ብትኖር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ሕዝቡም አንባቢ እና ጠያቂ ስላልነበረ ለተሸከሙት እንጨት ሲያሰግዱት ይሰግዳል ፣ ጠፋ ተሰረቀ ሲሉት ለፍለጋ ይወጣል። በዝዋይ ገብርኤል ገዳም በአቡነ ጎርጎርዮስ ከተማርኩ በኋላ አዲስ አበባ አቡነ ገብርኤልን አግኝቼ ስለታቦቱ ጠይቄያቸው ነበር ምላሻቸው የኢትዮጵያ ባህል ነው እንጂ ዶግማ አይደለም ብለውኛል። ታዲያ ለምንድነው የእናቴን ሽንኩርት መክተፊያ የሚያክል ነገር በቄስ አሸክመው የሚያሰግዱን? የሚል ጥያቄ በውስጤ ብቅ ቢልም በሰዓቱ መጸሐፍ ቅዱስን በሚገባ ስላልተረዳሁ በአንደበቴ ማውጣት አልቻልኩም ነበር። ነገር ግን መጽሐፉን ሳነብ ያገኘሁት የብሉይ ኪዳን ታቦት ከላይ በምስል እንደለጠፍኩት አራት ካህና የሚሸከሙት ትልቅ ሳጥን መሰል ነገር እንደነበር ስረዳ የአገራችን ታቦታት ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ የሌለውና ወደ ጣዖት አምልኮ የሚጠጋ እንደሆነ ተረዳሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሰዎች ወይም በመላእክት ስም የተቀረጸ ታቦት አላገኘሁም። በአጸደ ስጋ በሌሉ ሰዎችና መናፍስት በሆኑ መላእክት ስም ቅርጽ ሰርቶ ማምለክ የመናፍስት ጠሪና የባለብዙ አማልክት ተከታይ የሆኑ የሕንዶች ዓይነት ልምምድ ነው። ይህን እውነት አባቶች በደንብ ያውቁታል። ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ከዚህ ጉድ ራሷን ብታጠራ እና ንጹውን የክርስቶስን ወንጌል መስበክ ብትጀምር ከአፍሪካ አልፎ ለዓለም በደረሰች ነበር። አሁንም አልረፈደም!
አቡነ ጎርጎሪዮስ ትልቅ ባለውለታዬ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስን እንድወደው እና የዕለት ተዕለት ምግቤ እንዲሆን መነሻ የሆኑኝ እኚህ አባት ናቸው። ዛሬ በሕይወት ቢኖሩ የምጠይቃቸው ብዙ ነገር ነበረኝ ግን ለዚህ አልታደልኩም።
ቀጥሎ እውቀት ለጨመሩልኝ ለእነ አቡነ ገብርኤል እና አቡነ መልከጼዴቅ ትልቅ ክብር አለኝ።
ለኦርቶዶክስ ቤ/ክ ለዓለም የሚተርፍ የተሐድሶ ዘመን እንዲፈጥንላት ጸሎቴ ነው።
ወይትባረክ ለእግዚአብሔር!!!
“ብዙ ኀዘን የማያቋርጥም ጭንቀት በልቤ አለብኝ ስል በክርስቶስ ሆኜ እውነትን እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ ሕሊናዬም በመንፈስ ቅዱስ ይመሰክርልኛል።”
— ሮሜ 9፥1-2
07/01/2024
ዛሬ በቤተክርስቲያን ዘማሪያን እንደዚህ ደምቀው በምስጋና፣ በውዳሴና በአምልኮ እየመሩን በእግዚአብሔር መንፈስ በሀልዎቱ ውስጥ እንድንሆን አድርገውናል። ዘመናችሁ ይባረክ!!! ባርኳቸው
| Monday | 16:00 - 20:00 |