Mesele Hailu
Dr Akililu
22/05/2021
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ
ግንቦት 14 ቀን 2013 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የተለያዩ ዝግጅቶቸን ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል። ግንቦት 7 ቀን 2013 ቦርዱ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ምክክር የድምፅ መስጫ ቀን በታቀደለት ግንቦት 28 እና ሰኔ 05 ቀን 2013 መከናወን እንደማይችል በተጨማሪ ከ2-3 ሳምንት ዝግጅት ጊዜ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት በተጨማሪዎቹ ቀናት የሚከናወኑ ይሆናል።
1. ተጨማሪ የምርጫ አስፈጻሚዎች ምልመላን ማጠናቀቅ
በአሁኑ ወቅት ከሚገኙት 138,655 የምርጫ አስፈጻሚዎች በተጨማሪ ቦርዱ 106,345 ምርጫ አስፈጻሚዎችን መልምሎ ማሰልጠን ይኖርበታል፣ ከነዚህ መካከል በቦርዱ መጠባበቂያ ዝርዝር ላይ ተጨማሪ 100,333 አስፈጻሚዎች አሉ። ከእነዚህ ተጨማሪ ምርጫ አስፈጻሚዎች በቦርዱ በተጠባባቂነት የተያዙ ሲሆን ቦርዱ መስፈርቱን የማጣራት እና የማሰልጠን ስራ አጠናቆ ለድምጽ መስጫ ቀን ዝግጁ ያደርጋል። ከፍተኛ የአስፈጻሚ ቁጥር ክፍተት ባለባቸው ክልሎች በልዩ ሁኔታ ለመሙላት ጥረት ያደርጋል።
2. ስልጠና
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለድምጽ መስጫ ቀን ሁሉንም የምርጫ አስፈጻሚዎች ያሰለጥናል። ይህ ስልጠናም
1. የመሪ አሰልጣኞች ስልጠና - 20 ሰዎች በማእከል ደረጃ
2. በዋና አሰልጣኞች ስልጠና- 220 ሰዎች በማእከል ደረጃ
3. በመስክ አሰልጣኞች ስልጠና- 2,200 ሰዎች በ20 ከተሞች
4. በምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች እና ዞን አስተባባሪዎች ስልጠና- 3,781 ሰዎች በ20 ከተሞች
5. የምርጫ ጣቢያ ምርጫ አስፈጻሚዎች ስልጠና - 245,000 ( በአራት ዙር) ደረጃዎች ይከናወናል።
በአራት ደረጃ የሚከናወነው ይህ ስልጠና የሚሰጥባቸው ርእሶች
- የድምፅ መስጫ ቀን ዝግጅት
- ቆጠራ እና ውጤት ገለጻ በምርጫ ጣቢያ ደረጃ
- ውጤት ድመራ ፣ አስተዳደር እና ይፋ ማድረግ በምርጫ ክልል ደረጃ ይሆናሉ። ይህ በየደረጃው የሚደረግ ስልጠና 23 ቀናት ያህል ይፈጃል።
3. የቁሳቁስ እሸጋ እና ስርጭት (ስልጠና እና የድምጽ መስጫ ቀን)
ለስልጠና ቁሳቁስ እሸጋ እና ስርጭት በአጠቃላይ 4 ቀናት ይፈጃል። የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት ከ10 ቀናት በኋላ የሚናቀቅ ሲሆን ከዚያም በተጨማሪ የድምጽ መስጫ ወረቀት፣ ፎርሞች እና ከሌሎች ተገዝተው የተቀመጡ የድምፅ መስጫ ቀን ቁሳቁሶችን በምርጫ ክልል አከፋፍሎ ማሸግ የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመት ከተጠናቀቀ በኋላ አራት ሳምንታት ይፈጃል።
ከዚህ በተጨማሪ ቦርዱ የትራንስፓርት እቅድ ያዘጋጀ ሲሆን ከመራጮች ምዝገባ ልምድ በመነሳት የፌዴራል ተቋማት፣ የክልል መንግስታት እና የሌሎች አካላት ከፍተኛ ትብብር ይጠይቃል። ይህ የኦፕሬሽን ዝግጅት ቦርዱ በሙሉ ሃይሉ አሟጦ በመጠቀም የሚከናወን ይሆናል።
በዚህም መሰረት 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የሚካሄደው በ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይሆናል። ይህም ሆኖ ድምጽ መስጠት ሂደቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከናወንባቸው የማይችልባቸው የምርጫ ክልሎች እና የምርጫ ጣቢዎች የሚኖሩ ሲሆን
1. የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች ፣ በጸጥታ ችግሮች
2. የመራጮች ምዝገባ ተጀምሮ የተቋረጠባቸው ቦታዎች
3. የመራጮች ምዝገባ ላይ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበባቸው ወይም ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ ላይ ጉልህ የአሰራር ችግር በማየቱ ማጣራት የወሰነባቸው ቦታዎች
በተለያዩ ምክንያቶች (በጸጥታ እና በመራጮች ምዝገባ አቤቱታ) ድምጽ መስጠት ሂደቱ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ተግባራዊ ሊሆን የማይችልባቸው የምርጫ ክልሎችን ቦርዱ የለየ ሲሆን እነሱም የሚከተሉት የምርጫ ክልሎች ናቸው።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል (4 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመባቸው ቦታዎች
1. መተከል ምርጫ ክልል
2. ሺናሻ ልዩ ምርጫ ክልል
3. ካማሽ ምርጫ ክልል
4. ዳለቲ ምርጫ ክልል
ሶማሌ ክልል (14 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበባቸው እና የማጣራት ሂደቱ ላይ የሚወሰኑ
1. አራቢ የምርጫ ክልል
2. ደግሃመዶ ምርጫ ክልል
3. ጎዴ የምርጫ ክልል
4. ጂግጂጋ 1 የምርጫ ክልል
5. ጂግጂጋ 2 የምርጫ ክልል
6. ቀብሪደሃር ምርጫ ክልል
7. ቀላፎ ምርጫ ክልል
8. ዋርዴር ምርጫ ክልል
9. ፊቅ ምርጫ ክልል
10. ገላዲን ምርጫ ክልል
11. ደገሃቡር ምርጫ ክልል
የመራጮች ምዝገባ ሂደት በክልሉ መስተዳድር የተቋረጠባቸው
1. አይሻ ምርጫ ክልል
2. ኤረር ምርጫ ክልል
3. ሽንሌ ምርጫ ክልል
ኦሮሚያ ክልል ( 7 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ( በጸጥታ ችግር)
1. ቤጊ ምርጫ ክልል - ምእራብ ወለጋ
2. ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል - ምእራብ ወለጋ
3. አያና ምርጫ ክልል - ምስራቅ ወለጋ
4. ገሊላ ምርጫ - ምስራቅ ወለጋ
5. አሊቦ ምርጫ ክልል -ሆሮ ጉድሩ
6. ጊዳም ምርጫ ክልል- ሆሮ ጉድሩ
7. ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል- ሆሮ ጉድሩ
አማራ ክልል (8 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው (በጸጥታ ችግር)
1. ማጀቴ (ማኮይ) ምርጫ ክልል
2. አርጎባ ልዩ ምርጫ ክልል
3. ሸዋሮቢት ምርጫ ክልል
4. ኤፌሶን ምርጫ ክልል
5. ጭልጋ 1 ምርጫ ክልል
6. ጭልጋ 2 ምርጫ ክልል
7. ላይ አርማጭሆ ምርጫ ክልል
8. ድልይብዛ ምርጫ ክልል
ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል (3 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው (በጸጥታ ችግር)
1. ቀይ አፈር መደበኛ
2. ሱርማ ልዩ ምርጫ ክልል
3. ዲዚ ልዩ ምርጫ ክልል
ሐረሪ ክልል (2 ምርጫ ክልል)
የመራጮች ምዝገባ ከፍተኛ የተዛባ አሰራር የታየባቸው እንዲሁም በህግ የተያዘ ጉዳይ
1. ጀጎል ልዩ ምርጫ ክልል+ ጀጎል መደበኛ ምርጫ ክልል
2. ጀጎል ዙሪያ እና ሁንደኔ ምርጫ ክልል
ልዩ መግለጫ
በጋምቤላ ክልል ዲማ ምርጫ ክልል እና አኮቦ ምርጫ ክልል ከፍተኛ የመሰረተ ልማት እና የመጓጓዥ ችግር ከፍተኛ በመሆኑ በልዩ ሁኔታ የክልል እና የፌደራል መንግስትን ከፍተኛ እገዛ ይጠይቃል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 14 ቀን 2013 ዓ.ም
[Edited]
27/04/2021
/የህዳር በሽታ/
።==========================።
በዚህች ቀን የሰማይ ሰራዊት ሁሉ አለቃቸው መልአከ ምክሩ የምክሩ አበጋዝ ይለዋል የቅድስት ሥላሴ መንጦላእትን የሚከፍትና የሚዘጋ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመበት ቀን ነው።
በህዳር ወር በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ህዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡ ተያይዞም በዕለቱ የህዳር ሲታጠን ታሪክ ይነሳል፤
አፍሪካን የጎዳው ከባዱ የእንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ በአገራችን ከህዳር 7 እስከ ህዳር 20 ቀን 1911 ዓ.ም ለአስራ አራት ቀናት ገደማ የቆየ ነበረ በሽታው በህዳር ወር የተከሰተ በመሆኑ ህዝቡ የህዳር በሽታ እያለ ጠራው :፡
ብላቴን ጌታ መርስዔ ሀዘን ወልደቂርቆስ የሃያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ በተሰኘው መጽሀፋቸው እንዳሰፈሩት፤ ወረርሽኙ እስከ አርባ ሺህ ኢትዮጵያዊንን ለሞት ዳርጓል፤
በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ዘጠኝ ሺህ ዜጎች በበሽታው ሞተዋል፡፡
በተለይም ህዳር 12 ቀን 1911 ዓ.ም በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሞቱበት በመሆኑ በቀኑ የጽዳት ዘመቻ እንዲደረግ በአዋጅ ተነግሮ ስለነበር፣ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ይህ ነገር እንደባህል ተወስዶ በየዓመቱ ህዳር 12 ቀን የጽዳት ዘመቻ ይደረግ ጀመር፤ ይህም በተለምዶ ህዳር ሲታጠን የምንለው ነው፡፡
ከበዓሉ ረድኤት ያሳትፈን አገራችንን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን አሜን።
26/06/2020
[ለሁላችሁም ምስጋናን በአክብሮት ስለማቅረብ]
🌞 መልካምና ቅን ልብ ያለው ሰው ሁሌም አንድ ሰው መልካም ነገር ሲሠራ ማበረታታት ልማዱ ነውና እጅግ መልካም የሆነ ሕሊና ስለነበራችሁ ሁላችሁም ደስታችሁን አክብሮታችሁን ስለላካችሁልኝ እኔም በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ሁላችሁንም እጅ እነሣለሁ።
🌞 በፀሐይ ግርዶሽ ዙርያ ከዓመት በፊት በአንድሮሜዳ መጽሐፍ እና በማሕበራዊ ሚዲያዎች ከምርጡ ሳይንቲስት ከዶክተር ጌትነት ፈለቀ ጋር ስንናገርና ግርዶሹም እየተቃረበ ሲመጣ ብዙዎች ወዳጆቼ ባይሆንስ የሚል ሐሳብ ውስጥ በመግባት በጣም አስበውልኝ እንደነበር አሁን ተረድቻለሁ። ለዚህም ሐሳባችሁ የኢትዮጵያ አምላክ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ።
🌞 ዕውቀት፣ እውነት ጨርሶ የማያቃቸው ጥቂቶች ግን ጨርሶ አይፈጠርም በማለት ካልተከሠተ ነቀፋን ትችትን ለማዝነብ ዝግጅት ላይ ነበሩ። ነገር ግን ከፀሐይ ጋር ያለን ቀጠሮ የማይዛነፍ በብዙ ምስጢር የተሰናሰለ በሳድሲት፣ በኃምሲት፣ በራብዒት፣ በሣልሲት፣ በካልዒት፣ በኬክሮስ የተቀመረ መሆኑን ከዕውቀት መራቅ ክፉ ነውና አልተረዱትም። ቢሆንም በዚህ አልከፋም ብርሃን ዕውቀትን እንዲያገኙ ለነርሱ ከመጸለይ በቀር።
🌞 ፀሐይ በጨረቃ ተጋርዳ ብትጨልምም መልሳ ከተጋረደችበት ወጥታ ብርሃኗን አንጸባርቃለች ዛሬም የኢትዮጵያ ምርጥ የአባቶቻችን ጥበብና ዕውቀት ሥልጣኔና ምስጢር እንዳይገለጽ ብዙ ጨለማዎች ተጋርደው ለዘመናት ቆይተው ነበር።
🌞 ነገር ግን ላስተዋለ ሰው ፀሐይ ኢትዮጵያችን ያላትን የራሷን ምስጢር እንዳታወጣ የጋረዷትን ጨለማዎች ሁሉ በከፍተኛ ፍጥነት አርቃ በልዕልና ብርሃኗ ላይ ለመቀመጥ ትላንት [ሀ] ወይም [፩] ብላ ቀመሯን ጀምራለች። ምልክቷንም አሳይታለች።
🌞 ፀሐይ ኢትዮጵያን የሚመጥናት ዕውቀት፣ ከፍታ፣ ሥልጣኔ፣ እውነት፣ እምነት፣ አመክንዮ፣ ፍቅር፣ ብርሃን ነው እንጂ ዝቅታ፣ ውርደት፣ ሐሰት፣ ድንቁርና፣ ማታለል፣ ጠብ ክርክር፣ ምቀኝነት፣ ጨለማ አይደለምና ከዚህ በኋላ ማንም ላይጋርዳትና ላያዋርዳት በከፍታ ሰገነቷ ላይ የምታበራበትና እንደ ጥንቱ ዓለምን በሥልጣኔ የምትመራበት ጊዜዋ ነው።
🌞 ፀሐይ ትላንት በጨለማዋ ሰዓት ከጎንና ከጎንዋ ሜርኩሪና ቬነስን አድርጋ በምሥራቅ አቅጣጫ ከፊት ለፊቷ ደግሞ ማርስን፣ ጁፒተርን፣ ሳተርንን አሰልፋ እንደታየች ፀሐይ ኢትዮጵያም በመከራዋ ሰዓት ምርጥ ልጆቿን የምትሰበስብበት ደጋፊዎቿን ከፊቷ የምታቀርብበት ሰዓቷ ነው።
🌞 ግርዶሹና ጨለማው ከፀሐይዋ ፊት ለፊት የተጋረደው ለጥቂት ሰዓት ነው። ብርሃኗ ግን ዘላቂ ነው። አሁንም ፀሐይ ኢትዮጵያችን ከፊት ለፊቷ የሚመጣባትን ፈተናን መሻገሯና ማብራቷ ለወዳጆቿ ደስታ ለሚጠሏት ግን አስደንጋጭ መርዶ ነው።
🌞 የሠኔ 14ቱ ግርዶሽ መቼም በምድራችን የማይደገም ነው ምክንያቱም መስመሩን የሠሩት ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ መሬት ብቻ ሳይሆኑ ሰመር ሶልስቲስ፣ ስካይ ክሮስ፣ የሚልክዌይ (የፍኖተ ሐሊብ) ማዕከል፣ ጋላክቲክ ፕሌንና ሁሉም ፕላኔቶች መሆናቸውና ሳክሪድ ጂኦሜትሪን በሰማይ ላይ መሥራታቸው በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ አስተዋይ ልብ ያለው ሰው አእምሮውን አስፍቶና በጥበብም ተራቅቆ ለሚመረምር በቅርብ ሊሆን ያለውን የዓለምን ሁኔታ በደንብ ይረዳበታል እላለሁ።
🌞 ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ የዕውቀትና የእውነት ብቻ ተባባሪዎች እንድትሆኑ እንጂ የድንቁርናና የሐሰት ተባባሪ መቼም እንዳትሆኑ ወንድማዊ ምክሬን አቀርባለሁ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Telephone
Website
Address
Monopol
Awassa