Hawassa College of Health Science-ሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Hawassa College of Health Science-ሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa College of Health Science-ሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ, College & University, Besides to Tabor Mountain, Awassa.

Hawassa Colleges of health science is one of Oldest and Famous college in creating competent Health professional in Sidama region formely it belongs to SNNPR but now be tot Hawassa town besides to TMt

14/11/2025

ለሚመለከተው ሁሉ፣
የኑሮ ውድነት ታሳቢ በማድረግ በቅርቡ መንግሥት ደሞዝ ጭማሪ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን፣የተደረገው ጭማር የሲዳማ ክልል ፋይናንስ ቢሮ እሮብና ሀሙስ ለሁሉም ሠራተኛ ይከፈላል ተብሎአል በተባለው መሠራት ለሌሎች መስርያ ቤት ክፍያ ተፈጽሞአል፣ነገር ግን መልካም አስተዳደር ችግር ያለበት የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እስከ አሁን መክፈል ይቅርና የጭማር ደብዳቤ ስላልተሰጣቸው ቅረታቸውን አቅርበዋል ፣
ችግሩ ሳይባባስ፣መማረና ማስተማር ሳይቋረጥ ፣በአስቸኳይ እንድከፈልልን በአጽንኦት እንጠይቃለን ።

Photos from Hawassa College of Health Science-ሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ's post 12/11/2025

በወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ የጤና ሚንስትር የተሰጠ መግለጫ ✍️👇

06/11/2025

በስነምግባር የታነፀ ብቁ የጤና ባለሙያ መሆን ይፈልጋሉ ? እንግዲያዉስ በአንጋፈዉ ኮለጃችን ፈጥነው ይመዝገቡ!
ሀ.ጠ.ሳ.ኮ

04/11/2025

👉የሪህ በሽታ ምንድን ነው❓

በዓላትን ተገን አድርገዉ ከሚከሰቱ በሽታዎች መካከል አንደኛዉ ሪህ ሲሆን በበዓላት ወቅት ከአመጋገባችን ጋር በተያያዘ የሚከሰት ነዉ፡፡ በሽታው ከበዓላት መምጣት ጋር ተያይዞ በብዛት ቢስተዋልም በአዘቦት ቀንም ሊከሰት ይችላል፡፡

የሪህ በሽታ በማንኛውም ሰው ላይ የሚከሰት የበሽታ ዓይነት መሆኑን እና የሚከሰተውም ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ በሚከማችበት ወቅት እንደሆነ የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ሪህ በጣም ከተለመዱት የአርትራይተስ በሽታ ዓይነቶች አንዱ ሲሆን ከፍተኛ ህመም ሊያስከትል ይችላል።

የሪህ በሽታ በመገጣጠሚያዎች አካባቢ፣ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ በአውራ ጣታችን ላይ ድንገት በሚከሰት ከፍተኛ የሕመም ስሜት፣ እብጠት እና ቅላት ባህሪው ይታወቃል።

በሽታው የሚያስከትለው ሕመም በድንገት የሚከሰት እና ብዙውን ጊዜ በሌሊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅስ ዓይነት ሲሆን በተለይ የአውራ ጣት በእሳት የተቃጠለ ያህል ሊሰማ ይችላል።

የሪህ ችግር አንድ ጊዜ ከጀመረ በኋላ የመከላከያ እርምጃዎችን ካልወሰድን የመመላለስ ባህሪም አለው።

የሪህ በሽታ መንሥኤዎች ፦

ሪህ የሚከሰተው ዩሪክ አሲድ የተባለው ኬሚካል በአጥንት መገጣጠሚያዎች ውስጥ በሚከማችበት ወቅት ነው። ዩሪክ አሲድ በመገጣጠሚያዎች ላይ ሲከማች እብጠትን እና ከፍተኛ ሕመምን ያስከትላል።

ዩሪክ አሲድ የሚፈጠረው ሰውነታችን ፒዩሪን የተባለ ንጥረ-ነገርን በሚሰባብርበት ጊዜ እንደሆነ የጤና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ፒዩሪን በተፈጥሮ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም በበሬ ቀይ ሥጋ እና ጉበትን በመሳሰሉ ተዋፅኦች ላይ ይገኛል።

የሪህ በሽታ ምልክቶች :-

*የመገጣጠሚያ ላይ ህመም
*የመገጣጠሚያ አካባቢ መቆጣት (አካባቢው ላይ ሙቀት፣ መቅላት እና ማበጥ)
*በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የመገጣጠሚያ ህመም (ለመንቀሳቀስ መቸገር)
*በመገጣጠሚያ አካባቢ የማቃጠል ስሜት መኖር
*ቁርጥማት፣ ትኩሳት እና ብርድ ብርድ ማለት የሚጠቀሱ ምልክቶች ናቸው

ለበሽታው አጋላጭ ነገሮች :-

*ፆታ (ወንዶች ዮሪክ አሲድ በብዛት ስለሚያመርቱ በወንዶች ላይ የመከሰት እድሉ ይጨምራል)
*እድሜ (ሴቶች ላይ ካረጡ በኋላ የዮሪክ አሲድ ማምረት ይጨምራሉ)
*አልኮል መጠጦች (ዮሪክ አሲድ ከሰውነት በበቂ ሁኔታ እንዳይወገድ ያደርጋሉ
*የዩሪን መጠኑ ከፍተኛ የሆኑ የአመጋገብ ስርአት (ስጋ፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ አሳ…..)

*የሰውነት ክብደት

የሪህ በሽታ መከላከያ መንገዶች :-

*አመጋገብ ማስተካከል (የዩሪክ ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን አለመመገብ ወይም ለጊዜው መቀነስ)
*አልኮል መጠጦችን አለመጠጣት
*የስውነት ክብደት መቆጣጠር
*መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
*በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ሊትር ውሃ መጠጣት የሚመከር መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

የሪህ በሽታ ሕክምና :-

የሪህ በሽታ ሕክምና ሁለት ዓይነት ሲሆን አንደኛው ሪህ የሚያስከትለውን የእብጠት እና የሕመም መጠን ማስታገስ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ በደም ውስጥ የሚገኘውን የዩሪክ አሲድ መጠን በመቀነስ በሪህ በሽታ ምክንያት የሚከሰተውን ጉዳት መቀነስ እንደሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጤና መረጃ የሚታወቀው የማዮ ክሊኒክ መረጃ ያመለክታል።

04/11/2025

በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ :-
መምህር፣ ይሁን ፣ተማሪ፣ እንድሁም ድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች፣ የደረሰባችሁ ማንኛውንም በደል፣መልካም አስተዳደር ችግር በውስጥ መስመር (inbox)ላኩልን ።

03/11/2025

ሀገር አቀፍ ደረጃ በጥራትና ፣በስነምግባር የታነፀ የጤና ባለሙያ በማፍራት የሚታወቀው Hawassa Health College እንድሁም በሀገራችን የሚገኙ የጤና ሳይንስ ኮሌጆች ፎረም ስብሳቢ የሆነው አንጋፋው የHawasssa Health Science College )🤔በጣም ውስብስብ ችግር ውስጥ ገብቶአል ፣መማርና ማስተማር አሽቆልቁሏል ፣የተማሪዎች ውጤት እጅግ በጣም ወድቆአልና ፣የሚመራው አካል በተገቢው መምራት ተስኖዋት ቢሮ መግባት ከዛ ወረ ለቃቅማ መውጣት ፣ከመምህኖች ጋር መጋጨት ሆነዋ ስራዎ፣ያለ እየመሰለ ልወድቅ ተቃርበዋል ።
ስለዚህ የሚመለከተው አካል ቢፈትሽና እርምንት እርምጃ ቢወሰድ እንላለን ።

02/11/2025

በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ነገር ያሳስበናል ፣ምክንያቱም እንደ አንዱ ዜጋና #ሀጤሳኮ ማህበረሰብ አካል ስለሆነም ።
በዝርዝር እመለስበታለሁ !

01/11/2025
Photos from የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ-አማርኛ ልሳን's post 01/11/2025
01/11/2025

"መንግስት ጤና አገልግሎቱ ላይ የተለያዩ ድጋፎችን ያደርጋል፡፡"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ከሰጡት ማብራሪያ

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

Photos from Sidama National Regional State Health Bureau's post 12/10/2025
Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Besides To Tabor Mountain
Awassa