26/06/2026
Regional Coordinator for the African Reproducibility Network(AREN) Dr.Musa Mohammed Ali delivered a public seminar at HU - CMHS
June 26/2026
*******//*****
Dr. Musa Mohammed Ali (PhD, Associate Professor), faculty member at Hawassa University and East African Regional Coordinator for the African Reproducibility Network (AREN), delivered a public seminar entitled “Open Science and Antimicrobial Resistance: Building Collaborative Solutions for a Global Threat.” on June 25/2026.
The seminar examined antimicrobial resistance (AMR) as a growing global health challenge that threatens the effectiveness of modern medicine and affects human, animal, and environmental health.
Dr. Musa highlighted major challenges facing AMR research, including fragmented data systems, limited access to scientific evidence, poor reproducibility of research findings, and inadequate interdisciplinary collaboration.
A key focus of the presentation was the role of Open Science in accelerating progress against AMR through enhanced collaboration, transparent research practices, open access to knowledge, and responsible data sharing. Participants also explored the FAIR Data Principles and the One Health approach as important frameworks for addressing complex public health challenges.
Drawing on experiences from the African Reproducibility Network (AREN), Dr. Musa shared examples of how African researchers and institutions are advancing open and reproducible research through capacity building, networking, and collaborative initiatives.
The seminar concluded with a call for stronger partnerships and greater adoption of Open Science practices to support effective responses to antimicrobial resistance and other global health threats.
25/06/2026
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሀኪሞች/መምህራንን ለመቅጠር በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ተፈትናችሁ የተመረጣችሁ በቀጣዬቹ ሦስት(3)የስራ ቀናት በአካል በመቅረብ የቅጥር ፎርማሊቲ እንድትፈጽሙ ያስታውቃል።
23/06/2026
UPCOMING GRAND EVENT Hawassa University THIS WEEKEND!
The 27th Students Convocation!
CONGRATULATIONS TO YOU ALL!
Hawassa University
Ever to Excel!
22/06/2026
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለተማሪዎች በሕይወት ክህሎት በአዕምሮ ጤና እና አደንዛዥ ዕፅ ላይ ስልጠና ተሰጠ።
ሰኔ 16/2018ዓም
********//*******
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ቡድን አስተባባሪነት ለመደበኛ ተማሪዎች የሕይወት ክህሎት አዕምሮ ጤና እና አደንዛዥ ዕፅ ላይ ስልጠና ተሰቷል።
በተመረጡ የኮሌጁ መምህራን የተሰጠው ስልጠና ዋነኛ ዓላማው ተማሪዎቹ አሁን በሚገኙበት የአፍላ ዕድሜአቸው ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም የወደፊት ዕቅዳቸውን ለማሳካት ሱስ ከሚያስይዙ ነገሮችና ሌሎች አደናቃፊ ድርግቶች ተቆጥበው በጽናት በማለፍ ለራሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
በኮሌጁ የመሰብሰቢያ አደራሽ በተሰጠው ስልጠና ሁሉም መደበኛ የህክምናና ጤና ተማሪዎች መጋበዛቸው ታውቋል።
19/06/2026
ለነርሶችና ሚድዋይፎች ለ3 ተከታታይ ቀናት ስሠጥ የቆየ ስልጠና ተጠናቃቀ
ሰኔ 12/2018ዓም
********//******
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ(ሀዩ-ህጤሳኮ) ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በነርሲንግ እና ሚድዋይፈሬሪ ክብካቤ ኦዲት ላይ ለነርሶችና ሚድዋይፎች ከሰኔ 10-12/2018 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየ ስልጠና ተጠናቀቀ።
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የኮሌጁ የጤና ትምህርትና አገልግሎት ኮርፖሬት ዳይሬክቶረት ዳይረክተር ዶ/ር ዘርሁን ተስፍዬ እንደተናገሩት ሆስፓታሉ ስሙን የሚመጥን አገልግሎት እንድሰጥ ከምንጊዜውም በላይ ትኩረት ተደርጎበት እየተሠራ ይገኛል።
በዚህም መሠረት ሙያተኞቹ ንቁ: ብቁና ህሙማንን ተንከባካቢ በመሆን የሚሰጡትን አገልግሎት ከመረጃ: ምዝገባና አያያዝ ጀምሮ በጥራት ኦዲት የተደገፈ እንድሆን ስልጠናው ማስፈለጉን አብራርተዋል።
የህክምና አገልግልሎት ጥራት ኢኖቬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር ተወካይ ዶ/ር መክልት ደጁ እንደተናገሩት በሆስፒታሉ ከሚሰጡት አገልግሎቶች የነርሲንግ እና ሚድዋይፌሪ ክብካቤ አገልግሎት ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን የአገልግሎት ሂደቱ በተቀመጠው መመዘኛ መሰረት መሆኑን የኦዲት ቡድኑ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት እና ክፍሉም ከነርሲንግ እና ሚድዋይፌሪ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ክፍል ጋር በመናበብ እንደሚሰራ አስረድተዋል።
በሆስፒታሉ የህክምና አገልግሎት ጥራት ክትትልና ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያና የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ኤርሚያስ ዳና በበኩላቸው ስልጠናው በዋናነት በነርሲንግ እና ሚድዋይፌሪ ክብካቤ አገልግሎት ኦዲት ላይ ትኩረት ማድረጉንና የነርሶችና ሚድዋይፎች አቅም ለማጎልበት ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።
በኮሌጅ ትምህርትና ህክምና አገልግሎት ጥራት እና ኢኖቬሽን ኮርፖሬት ዳይሬክቶረት አማካይነት በተዘጋጀው ስልጠና ከ40 በላይ ነርሶችና ሚድዋይፌሪዎች መሳተፋቸው ታውቋል።
18/06/2026
የደም ሊገሳ ጥሪ !
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንስቭ ስፔሻላይዝድ ሪፌራል ሆስፒታል በደም እጥረት ምክንያት በተለይም በወላድ እናቶችና ድንገተኛ አደጋ ተጎጅዎች ላይ የሚፈጠረውን ችግር ለማቃላልና የታካሚዎችን ሕይወት ለማዳን የሚያግዝ የደም ሊገሳ መረሃ ግብር ዓርብ ሰኔ 12/2018ዓም ይካሄዳል።
ስለሆነም ሁሉም የኮሌጃችን መምህራንና ሠራተኞች : ተማሪዎችና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ማኅበረሰብ በሙሉ በዚህ ሰብዓዊና ክቡር ተግባር ላይ በመሳተፍ ደም እንዲለግሱ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
ቦታ :- በኮሌጁ አስተዳደር ሕንፃ ስር
ሰዓት :- ከጧቱ 2:00 ሰዓት እስከ 11:00 ሰዓት
የሚተካውን ደም በመለገስ የማይተካውን ሕይወት
እናድን !
18/06/2026
በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሀኪሞች/መምህራንን ለመቅጠር በወጣው ማስታወቂያ መሠረት የተወዳደራችሁና የስም ዝርዝራችሁ ቀጥሎ የተጠቀሰው አመልካቾች የጽሁፍ ፈተናው ለሰኞ ሰኔ 15/2018 ዓም ከጧቱ 3:00 ሰዓት የተሸጋገረ መሆኑን ያስታውቃል።
15/06/2026
እንኳን ደስ ያለን !
በሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህብረተሰብ ጤና ትምህርት ዘርፍ መምህርና ተመራማሪ ዶ/ር አቻምየለሽ ገ/ጻዲቅ ተክሌ በኮሌጃችን ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሮፌሰር በመሆን በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት ፀድቆላቸዋል ።
Congratulations !
Hawassa University's Executive Congratulations ! Board has approved the promotion of Dr. Achamyelesh Gebretsadik Tekle to the rank of Full Professor in Public Health !
This historic achievement marks her as the first female professor in the history of the College of Medicine and Health Sciences, Hawassa University.
15/06/2026
አስደሳች ዜና!
***//***
ሰኔ 8/2018 ዓ/ም
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ለዘጠኝ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የደረጃ እድገት አፀደቀ!
እንኳን ደስ አለን!!!
EXCITING NEWS!
***//***
June 15, 2026
We are excited to announce that Hawassa University's Executive Board has approved the promotion of nine academic staff to the rank of full professorship!
1. Dr. Achamyelesh Gebretsadik Tekle, Professor of Public Health
2. Dr Alemayehu Muluneh Bitew, Professor of Climate Change and Environmental Science
3. Dr Awdenegest Moges Banjaw, Professor of Soil and Water Conservation
4. Dr. Mihret Dananto Ulsido, Professor of Water Supply and Environmental Engineering
5. Dr. Mulugeta Dadi Belete, Professor of Hydrology
6. Dr. Andargachew Gedebo Abitea, Professor of Plant Breeding
7. Dr Zerihun Girma Woldegebreal, Professor of Wildlife Ecology and Management
8. Dr. Hussein Mohammed Beshir, Professor of Horticultural Sciences
9. Dr. Tarekegn Yoseph Samago, Professor of Agronomy
Congratulations to all of you!!!
Congratulations to all of us!!!
Hawassa University
Ever to Excel!