Bakkalcho Jireenyu Maate ባካልቾ የብልፅግና ቤቴሰብ

Bakkalcho Jireenyu Maate   ባካልቾ የብልፅግና ቤቴሰብ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Bakkalcho Jireenyu Maate ባካልቾ የብልፅግና ቤቴሰብ, College & University, Hawassa, Awassa.

20/06/2026

ሲዳማ ቡና የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!
****************

ሲዳማ ቡና ሁለት ጨዋታ እየቀረው የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

በ36ኛ ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ነገሌ አርሲ አንድ አቻ ተለያይቷል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብርሀኑ በቀለ ለሲዳማ ቡና፣ በረከት ወልዴ በፍጹም ቅጣት ምት ለነገሌ አርሲ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ከጨዋታው አንድ ነጥብ ያገኘው ሲዳማ ቡና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳክቷል።

በሊጉ ታሪክም ይሄንን ክብር የወሰደ 11ኛው ክለብ ሆኗል።

በ2002 ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው እና ባለፉት አስራ ሰባት አመታት በሀገሪቱ ከፍተኛው የሊግ ዕርከን ላይ ሲወዳደር የቆየው ሲዳማ ቡና አስረኛ የክለቡ አሰልጣኝ በሆነው ያሬድ ገመቹ እየመራ ዋንጫውን ወስዷል።

ክለቡ በቀጣይ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያን የሚወክልም ይሆናል።

Photos from Tewodros Tadesse Kawiso's post 20/06/2026
20/06/2026

በጉልበት የተገለጠ ምስጋና፡ የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች መንፈሳዊ የድል አከባበር::

የዘንድሮው የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡናን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ሻምፒዮን በማድረግ ደማቅ ታሪክ አስመዝግቧል። የሲዳማ ቡና ተጫዋቾች ውድድሩ ሊጠናቀቅ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሯቸው ነው የሊጉን ዋንጫ ማንሳታቸውን በይፋ ያረጋገጡት።

ይህ ድል ክለቡ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያሳየውን ጠንካራ የቡድን መንፈስ እና የሜዳ ላይ የጨዋታ የበላይነት በግልጽ ያሳየ ነው።

ከስፖርታዊ ብቃታቸው ባሻገር ግን የሻምፒዮንነቱ መረጋገጥን ተከትሎ በሜዳ ላይ የታየው ትዕይንት የብዙዎችን ልብ የነካ ልዩ ክስተት ነበር።

ዳኛው ጨዋታውን ሲያጠናቅቅ ተጫዋቾቹ የተለመደውን የደስታ አገላለጽ ወደ ጎን በመተው መንፈሳዊ ትህትናን መርጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ በእጆቻቸው በመያዝ ከጎል መረቡ ስር አንስተው እስከ ሜዳው መሀል መስመር ድረስ በጉልበታቸው በመጓዝ ለፈጣሪያቸው ጥልቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህ አስደናቂ ክስተት ተጫዋቾቹ ላባቸውን አፍስሰው ላገኙት ስፖርታዊ ስኬት የፈጣሪ ጸጋ ወሳኝ መሆኑን በተግባር ያሳዩበት ነው።

የዘንድሮው የፕሪሚየር ሊግ ፍጻሜ ሲዳማ ቡና ዋንጫውን ከማንሳቱ በተጨማሪ፣ ስፖርታዊ ፉክክር ከመንፈሳዊ ትህትና ጋር የተዋሃደበት ውብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ሆኖ ተመዝግቧል።

🙏🙏🙏❤️❤️❤️

📷Aku Images

⚽️⚽️⚽️

ጉርሻ Page

🌴🌴🌴

Photos from Hawassa City Administration Government Communication Affairs Department's post 05/06/2026
03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

Photos from Sidama National Regional State Office of the President's post 01/06/2026
Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Hawassa
Awassa