የመንግሥቱ ድምጽ - Yemengistu Dimts

የመንግሥቱ ድምጽ - Yemengistu Dimts This Page is always dedicated to teaching and sharing insights about the second coming of Christ

21/10/2024
👉 “እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ለቍጣ የዘገየ፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት...ነው።ዘጸአት 34:6👉 "ለቁጣ የዘገየ" የምለው የእግዚአብሔር ባህርይ የእግዚአብሔርን ፍጹም...
18/10/2024

👉 “እግዚአብሔር፥ እግዚአብሔር መሐሪ፥ ሞገስ ያለው፥ ለቍጣ የዘገየ፥ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት...ነው።
ዘጸአት 34:6
👉 "ለቁጣ የዘገየ" የምለው የእግዚአብሔር ባህርይ የእግዚአብሔርን ፍጹም የሆነ ትዕግስትን የሚያመለክት ቃል ነው። አንዳንድ ጊዜ እኛ ታግሰናል የሚንላችውን ሁነታዎችን ወደኋላ ቢንመለከታቸው አብዛኛዎቹ መለወጥ ስላልቻልናቸው አይናችንን ጨፍነን ጥርሳችንን ነክሰን አሜን ብለን የተቀበልናቸው ነገሮች ናቸው እንጅ ትዕግስትን የሚያሳዩ አይደሉም። አጸፋውን መመለስ ስላቃተን ወይም አጸፋው ሌላ ጣጣ ያመጣብናል ብለን ያለፍናቸው ነገሮች ትዕግስትን አያመለከቱም። የእግዚአብሔርን ትዕግስት ከሁሉም ቻይነቱ፣ ከሁሉም አዋቅነቱ እና ከሉዓላዊነቱ አንጻር ከተመለከትክ እመነኝ ትደነቃለህ። በእግዚአብሔር ላይ የሚከፈቱ አፎች፣ የሚደረጉ በደሎች፣ የሚጣሱ ድንበሮች ስትመለከት "ለቁጣ የዘገየ" የሚለውን ቃል በቀላል ምዛን ላይ አታስቀሚጠውም። እሩቅ መሄድ አይጠበቀብንም እኛን ራሳችንን ምን ያህል እንደታገሰን ሁላችንም ራሳችንን እናውቃለን።
👉 አንድ በጣም መገንዘብ ያለባችሁ ነገር እግዚአብሔር ለቁጣ ይዘገያል ይላል እንጅ አይቆጣም አይልም። ቁጣ የእግዚአብሔር ሌላኛው ገጹ ነው፣ ያን ገጽ ግን ፈጥኖ አይገልጠውም። እግዚአብሔር ታጋሽ ነው። መልካም ቀን!

15/10/2024

ፍጥረትን ከፈጠረ በኃላ ራስህን ቻል ብሎ እሩቅ ያልቆመ ይልቁንስ "በሥልጣኑ ቃል የሚደግፍ" ጌታ፤ እኛንም አድኝቸዋለሁና ከዚህ በኃላ ራሳችሁን ቻሉ አይለንም። በጸጋ ጀምረናል በጸጋ እንጨርሳለን።

12/10/2024

ክርስቲያን ኃጢአትን ልሰራ ይችላል ነገር ግን በኃጢአት ልደሰት ፈጽሞ አይችልም።

ከተገለጠው ድርጊታችን በላይ የልብ አካሄዳችን የነገ ፍሬያችንን ይወስናል!የተገለጠው ድርጊታችን ለሰው ይታያል!ልባችን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ታይቶ ይመዘናል!ምንም ነገር ስናደርግ የምናደርግ...
09/10/2024

ከተገለጠው ድርጊታችን በላይ የልብ አካሄዳችን የነገ ፍሬያችንን ይወስናል!የተገለጠው ድርጊታችን ለሰው ይታያል!
ልባችን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ታይቶ ይመዘናል!
ምንም ነገር ስናደርግ የምናደርግበት መንፈስ ከድርጊታችን በላይ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ አለው!
ያልተኖረ የታይታ ብቻ ገፅታ ምን በሰው ዘንድ ጎሽ ቢያሰኝና ቢገነባ ጊዜ ቆጥሮ ባዶነቱ ይገለጣል ከትወና ሕይወት አያልፍም!እግዚአብሔር እያዘነ የምንገነባው ገፅታ የትም አያደርሰንም!
በልባችን እንለወጥ!ብልህ እንጂ ብልጣብልጥ አንሁን!
ሳይረፍድ ብዙ ሳንከስር የእውነት እንሁን! የእውነት እንኑር! አንሸነጋገል! የእውነት ልብና ቅንነት ገፅታችን ይሁን!እርሱ ጎሽ ይበለን ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው!

በእውነት መንፈስ ተባረኩ!

Via Hana

እግዚአብሔርን "ቅዱስ ነህ" ስንል፤ ኃጥአት የማትሰራነህ እያልን አይደለም፣ ስጀመር he has no ability to do sin, ተፈጥሮው አይደለም። ቅዱስ ነህ ስንል፤ ልዩ ነህ፣ ከማንም እ...
09/10/2024

እግዚአብሔርን "ቅዱስ ነህ" ስንል፤ ኃጥአት የማትሰራነህ እያልን አይደለም፣ ስጀመር he has no ability to do sin, ተፈጥሮው አይደለም። ቅዱስ ነህ ስንል፤ ልዩ ነህ፣ ከማንም እና ከምንም ጋር አትወዳደርም፣ የሚመስልህ በሰማይ በምድር ከምድርም በታች የለም፣ በአጠቃላይ "You are unique" እያልን ነው። ስንቀደስ ምንም እንኳ የውጭ ሰውነታችን አጠገባቸን ካለው አብሮን ከሚሠራው፣ ከሚያገለግሉው፣ ከሚኖረው ሰው የተለየ ባይሆንም በውስጣዊ ሰውነታችን (በአስተሳሰብ፣ በመፈሳዊ ጥንካረ፣ በሞራል ልህቀት) ከሎሎች የተለይን እንሆናለን። ቅድስና ልዩነትን ይፈጥራል፣ ቅድስና በጣም ከሚትወዳቸው ሰዎች ጋር ያጋጫል፤ ምክንያቱም መቀደስ መለየት ስለሆነ። ተለይ ልዩ ትሆናለህ!

08/10/2024

የእግዚአብሔርን ቃል ከመከተል ውጭ plan B የለንም፣ የእኛ plan A-Z የእግዚአብሔር ቃል ነው። የእግዚአብሔር ቃል አማራጭ መንገድ ሳይሆን ፍጹምና ብቸኛ የሕይወታችን መሪ ነው።

ያ  መሢሕ … የተሰኘ የመስከረም ገቱ ቁጥር 3 አልበም ነሃሴ 26 (sep 1) በሁሉም ሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርም እንደምለቀቅ መስኪ አሳውቃለች። በጉጉት እንጠብቃልን!
16/08/2024

ያ መሢሕ … የተሰኘ የመስከረም ገቱ ቁጥር 3 አልበም ነሃሴ 26 (sep 1) በሁሉም ሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርም እንደምለቀቅ መስኪ አሳውቃለች። በጉጉት እንጠብቃልን!

Address

Piassa
Awassa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የመንግሥቱ ድምጽ - Yemengistu Dimts posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to የመንግሥቱ ድምጽ - Yemengistu Dimts:

Shortcuts

Share

Category