Hawassa Polytechnic College

Hawassa Polytechnic College

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa Polytechnic College, College & University, Hawassa, Awassa.

Hawassa polytechnic is public TVET College established in 1990 E.C to offer technical and vocational education and training for the local community through both formal and non-formal programs aimed to provide morally up right and competent work force for

Operating as usual

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 20/01/2025

የሲ/ብ/ክ/መ/ሥ/ክህ/ኢን/ል/ቢሮ የለኩ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ በመደበኛና በአጫጭር ጊዜ ሥልጠና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ዛሬ ተካሂደዋል።

በስልጠና ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ የክልሉ ሥ/ክህሎት ቢሮ ሥልጠና ዘርፍ ተወካይ ፣ የሌኩ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፣ ሌኩ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ እና ከተማ አመራር አባላቶች ፣ የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ፣ የኮሌጂ ማኔጅመንት አባላት ፣ ግምባር ቀደም አሠልጣኞች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል ።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በሥልጠና አጀማመር ዙሪያ ላይና ስለዚህ መልካም ዕድል መገኘት የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍና በቀጣይ ተጠናክሮ እንድሄዱ መደረግ ስላሉባቸው ክትትልና ድጋፎች ዙሪያ በመነጋገር የሥልጠና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩን በይፋ አከናውኗል ።

በዛሬው ቀንም ከለኩ ከተማ ፣ከሸበዲኖ ወረዳ ፣ ከጎርቼ ወረዳና ከሀዋላ ወረዳ ለመጡ ወንድ =144 ሴት =241 በድምሩ =385 ሠልጣኞች የህይወት ክህሎት ቅደመ ስልጠና መስጠት ተጀምረዋል ።

በመቀጠልም ሠልጣኞች የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታወችን በማሟላት መደበኛ ሥልጠናቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል።
!!
ጥር 12/2017 ዓ.ም
ለኩ

Photos from Sidama National Regional Sate Job,Skill And Enterprises Development Bureau's post 20/01/2025
Photos from Hawassa Polytechnic College's post 16/01/2025

Sidaamu Qoqqowi Loosu Dandootenna lnterprayzootu Latishshi Biiro Manajimentete Miilla Hawaasi Pooli Tekinikete Kolleejjenni Loosamanni Afamanno" Garment Excellence" Mereershi ljaaru Loosinna Maashinnate Shiqo, Diriirsonna qineeso Noo Deerra Toowanyo assitinno.

Miilla qoqqowohono ikko gobbate deerrinnni hoccu loosinni luphiima egennonna fullankera kaima ikkanno yine hananfoonnihu "garment excellence center" Ijaaru loosi yanna agadhino garinni loosamasi qaqajeelshahonna laashshate ikkitanno yannate ledo hadhannonna Value chaine xinta assitino maashinna eansa hagiirsiissinonsata biirote masagaano xawissino.

የሲዳማ ክልል ሥራ ክ/ኢ/ል/ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እየተገነባ ያለው ጨርቃጨርቅ ልህቀት ማዕከል የህንፃ ግንባታ የስልጠናና ማምረቻ ማሽነሪዎች አቅርቦት እንድሁም ፣ የተከላና የዝርጋታ ስራዎችን ጎበኙ።

በሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ የሚመራው የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ቡድን ከሀገር አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ግንባር ቀደም የጨርቃጨርቅ የልህቀት ማዕከል ይሆናል ተብሎ የተጀመረው ማዕከል ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እየተጠናቀቀ ያለ መሆኑና ለሥልጠናና ለማምረቻ የሚሆኑ ማሽነሪዎች መግባታቸውንና የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን እንድሁም እጅግ በጣም የሚደነቅ ስራ ማየት መቻላቸውን ተገልጿል ።

ዓላማችን በ2030 ከምስራቅ አፍርካ ግንባር ማዕከል ማድረግ ነው!

ጥር 8/2017 ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ።
ISO21001:2018 Certified

06/01/2025

ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ ስል የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ መልዕክታቸውን አስተላለፉ።

አቶ መልካሙ አክለውም በዓሉ የሠላም ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ፣ የዕገትና የብልግና እንድሆንልን እንድሁም በሀገራችን በሁሉም አቅጣጫዎች ሰላም የሚሰፍንበት የተመኘነው ሁሉ የሚሳካበት እንድሆንልን እመኛለሁ ስል መልካም ምኞቱን ገልጿል።

መልካም የገና በዓል!

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 26/12/2024

Hawaasi pooli Tekinikete kolleeje Jireenyu Paarte safote uurinsha 2kki Doyiicho (6) agani loosu Gumulishi miillate konforaanse harissu.

Barru wosinchina Hawaassi Quchumi jireenyu paarte Poletiku handaari soreessi kalaa Geetu Maamohu afii fanote hasaawira sokkasi sayiisanni soorrote mootimma safantunkunni hanafe gobbate lophonna jireenyu lexxanni dayiinota xawise, dagoomu horaamimma aana soorro dagganno gede gobate gede amandooni mixo baala gumullanni hee'noonita xawisinno.

Konnirano hananfoonni loossa guma gantano gedenna mixote garinni gumulantanno gede assate miilate qeechi jawiidiha ikkinota affe miillanke kaajjodo jireenyu paartenke irkisate jawa qeechansa fultanno gede sokkasi saayisino.

Kolleejete jireenyu paarte safote uurinsha Massagaanchina Latishu mixo loosu harinsho qineesaanchi kalaa Aschalew Adiqohu koforaansete beeqanonna barru wosina ikkitinori Hawaassi quchumi jireenyu paarte Poletiku handaari soreessa Kalaa Geetu Maamohanna Hawaassi quchumi Jireenyu paarte Tantanote handaari soreessi kalaa Abebayew Yoseefiha hawalle keerunni dagini yaatenni barraho miilate shiqanno hasaawu illacha xawisino.

Kollejenihu Qaru Diine ayiiradu kalaa Melkamu Baraasihu afii fanote hasaawanna Barru wosina hawalle keerunni dagginni yaatenni hanafisiisinoha ikkanna kolleejete mareekantanno wo'mante gummara paartete miillanna Albisaano masagaano qeechi jawa ikkasi xawisinno.

Gumuloteno Kollejete jireenyu paarete safote uurinsha (6) gumulishi ripoorte shiqeenna minunni hala'lado hasaawa assinooniha ikkanna, Konni albaanni lame Hiwaasenni masagantannoti kollejete jireenyu paarte miilate kiiro lexxitanni daase korkaatinni 4 hiwaasera tantanantanno gede gumulo sayiimsoonni.

Aanteteno kolleejete gidoonni Haaro jireenyu paarte miilla ikkate hasatto shiqishidhinno miilla hasiiisanno keeno assinanni keeshini gedensaanni wo'ma miilla ikkitanno gede kaajjinshe, barrunita miillate konforaanse iibadu garinni jeefinsoonni.

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 24/12/2024

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕዩን ለማሳካትና የሪፎርም አጀንዳዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል።

ኮሌጁ በ2030 ከምስራቅ አፍርካ 1ኛ ለመሆን አልሞ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱና ዋነኛ የሆነው የGarment እና Textile occupation specialization ሥራ በEASTRIP ፕሮጀክት አማይነት በተገነባውና አካታች አድሱ ህንፃ ላይ ትላላቅ የማሽነሪ ዝርጋታ ዛሬ ተጀምረዋል ።
የማሽነሪ ዝርጋታ ሥራ የእያንዳንዱ ማሽነሪ ስሪቱን ጠንቅቆ በሚያውቁ በሀገረው ባለሙያዎች ማለትም
#ከጀርመን
#ከቻይናና
#ከህንድ በመጡ የዝርጋታ ባለሙያዎች መከናወን ጀምረዋል።

የዝርጋታ ሥራውን በይፋ ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ እያንዳንዱ ማሽን ከተመረተበት ሀገር የመጡ Spatial operators(የዝርጋታ ባለሙያዎች ) ሙሉ በሙሉ የዝርጋታ ሥራ መከናወኑ በቀጣይ ወደ ሥራ ስገባም ያለምንም ማነቆ ወደማምረትና ወደ ማሠልጠን ሥራ በሙሉ አቅም ለመግባት ያስችላል ብለዋል።

በተጨማሪም አቶ መልካሙ ሲነገር የገቡ ማሽነሪዎች ሙሉ በሙሉ እሴት ሰንሰለትን (Value chaine) መነሻ ያደረጉ ትላልቅ ማሽነሪ በመሆናቸው ከክር ማምረት ጀምሮ እስከ ሹራዊ ምርት ድረስ ያለውን ሂደት ያጠቃለለ በመሆኑ በተለይ ምርት እያመረቱ መሠልጠንን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።

በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASTRIP project ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ መለሠ ዲዳሞ በበኩላቸው የሠልጣኝ ማደሪያ (Dormitory) ጨምሮ ሁሉንም የሠልጣኞች አገልግሎት አጠቃለው የያዘው ይህ ህንፃ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተሰርቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ መጠናቀቅ መቃረቡና ለሥልጠና ምቹ ለማድረግ ከውጪ የገቡት ትላልቅ ማሽነሪዎች ዝርጋታ በመጀመሩ ደስ እንዳላቸውና ይህም ለኮሌጅ መልካም ነገር መሆኑን አንስተዋል።

አቶ መለሰ አክለውም ከማሽኑ ዝርጋታ በተጨማሪ ለኮሌጅ ውስጥ አሠልጣኞች Installation machine commission and training ወይም ስለ ማሽን ዝርጋታን በተመለከተ ለአሠልጣኞቻችን ጠቅለል ያለ ስልጠና መሰጠቱ በቀጣይ ልገጥሙን የምችል የብልሽትና የጥገና ችግሮችን በራሳችን ለመፍታት አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም የማሽኑ ዝርጋታና የአሠልጣኞች የ Operating system ስልጠና ከ10 እስከ 20 ቀናትን እንደሚፈጅ በማብሰር የኮሌጁ አመራሮች ስራውን በይፋ አስጀምረዋል ።

ዓላማችን የበቃ ዜጋን ማፍራት ነው
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ISO21001:2018 Certified

Photos from የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia's post 16/12/2024
Photos from Hawassa Polytechnic College's post 16/12/2024

Hawaasi Poli Tekinikete kolleeje Loosu Dandoote Ministre, UNCTAD, Master Card Foundation (Seed project ) ispoonserimaninna EDI uurrinsha widoonni hawaassi quchumi giddo addi addi loosira bobbakke heedhanno Interpiraayizootira loosu kalaqo qajeelsha aa hananfoonni.

Qajeelshu beeqaano hawalle keerunni daggini yee hanafisiisinnohu kolleejete 2kki diine kalaa Eyuel Yonehu interprayiizotinke laalchonna laalchimmansa bowirsate hattonno loosu kalaqo ayiimansanna noonsa dandoo mucci assite kee'natenna foonqe noonsa qoxeessa xaaphate jawa kaayyo aano qajeelisha ikkasi xawisinno.

Qajeelishu illachishanno qoxeesubba :-
➢ Dancha hedeweelcho bade afa
➢ Jawaachishano mixo mixira
➢ Gumulate jawaante woyyeessa
➢ Jawaata mashalaqe/tajete bu'a horoonsira
➢ Jeefisaancho mixo qixeessa
➢ Xaaddara dandiitanno yine hendanni mitiimmubba kee'ne kaafo adhanno tidhinanni mixo qineessa
➢ Meesinaatiata gumulate dandoo lossiranna woloota qajeelisha aana illacha tunganiha ikkano yiino.

Konni qajeelishinni wo'munku qajeelshu beeqaano ikkitino intirpirayizootinke lowo egenno cu'mite guumaamma ikkitara agaranni yiinohu kolleejete 2kki soreesi kalaa Eyuel qajjeelshu aninno 6 barrira sufe aamamanoha ikkasi xawise qajeelshu hanafamasi faajjete xawisinno.

በሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስራ ክህሎት ፣UNCTAD እና Master Card Foundatio(Seed project) ስፖንሰርነት ከEDI Institution ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ በለያዩ ሥራ ዘርፍ ለተሠማሩ ኢንተርፕራይዞች የሥራ ፈጠራ ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

የሥልጠና ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የሥልጠና መረሀ ግብሩን ያስጀመሩት የኮሌጁ ም/ዲን አቶ ኢዮኤል ዮኔ ኢንተርፕራይዞቻችን የሥራ ፈጠራ ማንነታቸውንና እምቅ ችሎታቸውን በግልፅና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ አይተው እንድመዝኑ ወይም እንድገመግሙ ለማድረግ ይህ ስልጠና ወሳኝ ነው ብለዋል።

የሥልጠናውም በሚከተሉት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ማለትም :-
➮ መልካም አጋጣሚዎችን የመለየት
➮ አበረታች ግቦችን የማስቀመጥ
➮የአፈፃፀም ብቃትን የማሻሻል
➮በርካታ የመረጃ ምንጮችን የመጠቀም
➮ የትግበራ/የአፈፃፀም እቅድ የማዘጋጀት
➮ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን የመገምገምና እርምጃ በመውድ እና
➮ግላዊ ኃይልን/አቅምን በማሳደግ ሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ ሥልጠና እንደምሆን አስገንዝበዋል።

በኢንተርፕራይዞቻችን ላይ ትልቅ ለውጥ ፣ ስኬትና መሻሻል ያመጣል ተብሎ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና ለ6 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ በማብሰር የሥልጠና መረሀ ግብሩን አስጀምረዋል ።

ሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ!

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 11/12/2024

የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከቻይናው ግዙፉ Yiyang Vocational and technical college ጋር በትብብር ለመስራት የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ ።

የYiyang vocational and technical college Vice Prident የሆኑት professor Wu Zili የተመራው ኮሚቴ የኮሌጁን ነባራው ሁኔታ፣ የአሠለጣጠን ሂደትና የሪሶርስ አቅም ተዘዋውረው ጎብኝቷል።

በProfessor Wu Zili የተመራው ኮሚቴ ከጉብኝቱ በኃላ ባዩት ነገር መደሰታቸውንና ኮሌጁ በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሆነ አይተናል በማለት በዚህም እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በ vice prisident Wu Zili በኩል ገልፀዋል ።

መነሻውን በጉብኝን ያደረጉት የሁለቱም ኮሌጅ አመራሮች በመሰባሰብ የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለድጋፍ የለያቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች ፣ የድጋፍ ፍላጎት እንዲሁም የኮሌጁን ነባራዊ ገጽታ የሚያሳይ አጭር የውይይት ሰነድ በIndustry Liaison Specialist አቶ ለማ ቡናራ ቀርበዋል።

በመቀጠልም የYiyang Vocational and Technical College ከሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ጋር በትብብር ለመስራት የለያቸውና ባቀዳቸው ፕሮግራም ዙሪያ እንድሁም የYiYang Vocational and Technical ኮሌጅ አጠቃላይ ገጽታን የሚያሳይ አጭር ሰነድ በዶ/ር ድቅነህ ገብሬ ያቀርበዋል ።

የቻይናው ግዙፉ Yiyang Vocational and Technical college ከሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር ለመሥራት ካቀዳቸው ፕሮግራሞች መካከል :-
✅ Automotive occupation ላይ
✅ Fashion Design occupation
✅ E-commerce /Digital marketing
✅ Academic exchange for faculty and students
✅ Overseas skills training programs in collaboration with domestic and international Enterprises
✅Faculty training and professional skills training in partnership with foreign institutions.
✅Development of international vocational education standard and curriculum standard እንድሁም ከተለያዩ በቻይና የግል ኩባኒያዎች ጋር በትስስር ለመሥራት እንዳቀዱ አስረድተዋል።

የሁለቱም ኮጅሌጅ አመራሮች በትብብር ለመስራት በተዘጋጀው የስምነት ሰነድ (MOU) ላይ በጋራ ተፈራርመዋል ።

በመጨረሻም የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ ለዓመታት ገደማ ያልተቋረጠ የድጋፍና የሁለትዮሽ በጋራ የመስራት ጥያቄ በዛሬው ቀን እንድህ ባማረ ሁኔታ ለመጀመር በጋራ በመፈራረማችን እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ በማለት በራሱና በኮሌጁ ሥም ለእንግዶቹ ምስጋናቸውን አቅርቦ የዕለቱን ፕሮግራም አጠቃለዋል።

ዓላማችን የበቃ ዜጋን ማፍራት ነው
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ISO21001:2018 Certified

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 05/12/2024

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከEASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለተማራቂ ተማሪዎች Career Development ስልጠና እሰጠ ይገኛል።

የEASTRIP ፕሮጀክት Industry Liaison Specialist የሆኑት አቶ ለማ ቡናራ ከየሙያው የተወጣጡ ተማራቅ ሠልጣኞችን ኮሌጁን በመወከል እንኳን በጣችሁ በማለት የ3 ቀን የሥልጠና ቆይታቸው ሚን እንደሚመስልና የሥልጠናውን ዓላማ በተመለከተ Orientation በመስጠት አስጀምረዋል ።

አቶ ለማ አክለውም ተማራቂ አሠልጣኞቻችን ሥልጠናቸውን ካጠናቀቁ በኃላ ወደ ሥራ ዓለም ለመቀለቀል የሚያገኙትን ሚቹ አጋጣሚዎችን ሁሉ እንደ ዕድል በመጠቀም ወደ ሥራ የሚገባበትን መንገድ የሚያሳይ ሥልጠና እንደሆነም በአጽንኦት አንስተዋል ።

ሥልጠናው በውስጡ ሠፋፊ ይዘቶችን የያዘ እንመሆኑ ቀለል ባለ መንገድ
👉 የንግድ እቅድ አዘገጃጀት
👉 የCV አዘገጃጀት
👉 የሥራ ፈጠራ ክህሎት የሚያሳድግና ተግዳሮቶችን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ለማወቅ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን በመግለጽ ከኮሌጁ ተመርቆ የሚወጡ ሠልጣኞቻችን ሁሉም ወደ ሥራ የሚገውበትን መንገድ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ሠልጣኞችን እንደየሙያቸው በመደልደል ግንባር ቀደም የሆኑና የብዙ ጊዜ ልምድ ያላቸው ሞዴል አሠልጣኞችን በመመደብ ለ3 ተከታታይ ቀናት እንድሰጥ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ሥልጠናው እየተሰጠ ይገኛሌ።

ዓላማችን የበቃ ዜጋን ማፍራት ነው
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ISO21001:2018 Certified !

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 04/12/2024

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ድኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የክትትልና ድጋፍ ቡድን ሲዳማ ክልል በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሥራ ጉብኝት አደረገ ።

የክትትልና ድጋፊ ቡድኑ ከክልሉ ሥራ ክህሎትና ኢን/ል/ቢሮ አመራሮችና እና ከኮሌጁ አመራሮች ጋራ በመሆን በተለያዩ ወርክ ሾፖች የተሠሩ ተግባራትን ጎብኝተዋል።

የክትትል ቡድኑ በዋናነት ከተመለከታቸው ተግባራት መካከል
✅ የሪፎርም ስራዎች ያሉበት ደረጃ
✅ የዞንንግና ድፍረንሼሽን ትግበራ
✅ የሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሥራ ዕድል ፈጠራ
✅ በክረምቱ አሠልጣኞች ሥልጠና የመጡ ለውጦች ዙሪያ
✅ የፈጠራ ስራዎችና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማምረት የህብረተሰቡን ችግር ከማቅለል ሥራዎች ጋር ተያይዞ
✅ ኮሎጁ የውስጥ ገቢን ከማሳደግ ጋር የሠራቸው የምርት ማምረት ሥራና ሌሎች ሥራዎችን ጎብተዋል።

በመጨረሻም የክትትልና ድጋፍ ቡድኑ መሪ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተሰሩ ተግባራት የሚበረታቱና ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን በማሰብሰር መጠናከር በሚገባቸው በትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የበለጠ እንድሰራ በማለት ጉጥኝቱን አጠቃለዋል ።

ዓላማችን የበቃ ዜጋን ማፍራት ነው
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ISO21001:2018 Certified !

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 17/11/2024

የሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከEDI ጋር በመተባር በኮሌጁ በተለያየ ደረጃ የአመራርነት ድርሻ ላላቸው ሠራተኞች ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የpublic Entrepreneurship And Innovation Ecosystem Building ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ።

ስልጠናውን ስከታተሉ የነበሩት በኮሌጁ የየደረጃው አመራሮችም ስልጠናው እጅግ ጠቃሚ ፣ እራሳችን ያለንበትን ያየንበትና በቀጣይ በየደረጃው ለምንተግበረው ተግባራት innovative በሆነ መንገድ ችግሮችን እየፈታን አዳድስ ስራዎችንና አሠራራሮችን እየነደፍን ለመሄድ አቅማችንን የገነባ ነውም ስሉ አስተያየታቸውን ሰተዋል።

በመዝጊያው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ ፣ በፈጠራ የታገዘ የአገልግሎት አሠጣጥና በስራ ላይ ያሚጋጥሙ ማነቆችን እንደ ምቹ አጋጣሚ ተጠቅሞ በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የመንግስት ሠራተኛውን ሥነ-ምህዳር ማስፋት ያስፈልጋል ፣ብለዋል።

ለዚህ እንደኮሌጅ የተመሩ የፈጠራ ሥራዎችን የፈጠራ ሀሳቦችን ለማገዝ የተጀመሩ ሥራዎች ማለት -Incubation center
-Women Entrepreneur Development program
-Income Generation program እና ሌሎች የተጀመሩ ተግባራት እንዳሉ ጠቅሶ አሁን እንደ ኮሌ የተሻለ የፈጠራ ሀሳብና Business plan ይዞ የሚመጡትን በማወዳደር innovative ሥነ-ምህዳርን ለማስፋት ኮሌጁ የአንበሳውን ድርሻ በመቀበል እንደሚያግዝም ቃል ገብተዋል

በመሆኑም የEDI አሠልጣኞችንና ውድ ጊዜያቸውን ሰውቶ በእረፍት ቀናቸውን ጭምር ለስልጠናው ትኩረት ሰጥቶ የተከታተሉትን የኮሌዱን አመራር በሙሉ አመስግነዋል።

በመጨረሻም በስጠናው የተሻል ተሳትሮ የነበራቸውን በመሸለምና ለሁም ሠልጠናኞች የስልጠና ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት በመስጠት ለ3 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና መጠናቀቁን አብስሯል።

Photos from Hawassa Polytechnic College's post 09/11/2024

የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከEASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በ2017 ለ2ተኛ ዙር ለአሠልጣኞችና ለባለሙያዎች ስሰጥ የቆየውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና በተሳካ ሁኔታ አጠናቀቀ።

በማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሳ ኮሌጁ ከEASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የአሠልጣኞችንና አጠቃላይ የሠራተኞቹን አቅም በእውቀት ፣ በክህሎትና በአመለካከት በመንገንባት ውጤታማ የሆነ የመማር ማሠልጠን እንድሁም ውስጣዊ የምዘና ሥርዓትን ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሆነ የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ በራሣ አንስተዋል ።

የኮሌጁ ዲን አቶ መልካሙ ሲያነሳ ኮሌጃችን በተለይ ISO2001:2018 Certified (ምስክርነት ያገነኘ) እንደመሆኑ መጠን የምንሰጠው ስልጠናም ሆነ አገልግሎት የዓለም አቀፍ ስታንዳርድን የጠበቀ መሆን እንዳለበት አንስቶ አሠልጣኞቻችንና ሠራተኞቻችን በዛው ልክ የተዘጋጁና የበቁ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በኮሌጁ የEASTRIP ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ
በኮሌጁ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የተያዩ ስለጠና የተሰጠ ብሆንም በመማር ማሠልጠኑ ውጤታማነትና ጥራት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ መሆኑን አንስቶ በኮሌጁ እስካሁን ከ157 በላይ የሚሆኑ አሠልጣኞች ውጤታማ የአሠለጣጠን ስነ-ዜደ ስልጠና እንደወሰዱና ከአጠቃላይ አሠልጣኞችም ከ70% በላይ ተደራሽ መደረጉን ገልጸዋል ።

አቶ መለሠ አክለውም የተሠጠውን ስልጠና በሚጠበቀው ደረጃ ወደ ታች ወርዶ በመማር ማስተማርና በምዘና ስርዓት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በሟሟላት እንደሀገር በሚጠበቀው ደረጃ ውጤት ለማስመዝገብ የትምህርት ክፍሉ ባለሙያዎች ፣ የድፓርትመንት ተጠሪዎች ፣ የምዘና ኮሚቴዎችና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ በአተገባበሩ ላይ ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ተግባር እንድገባ አሳስበዋል ።

በኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት Industry Liaison Specialist. የሆኑት አቶ ለማ ቡናራ አጠቃላይ የሥልጠና ሂደትን እየመራ ፣ እያሰለጠነና እያወያየ በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቀ በኃላ በፕሮጀክቱ ድጋፍ የትምህርት እድልን ከማመቻቸት ጀምሮ የሠራተኞችን አቅም ለመገንባት የተሰሩ ሥራዎችን ሪፖርት ካቀረቡ በኃላ ከከሌጁ ዲን ጋር በመሆን ለሠልጣኞች የስልጠና ማጠናቀቅያ ምስክር ወረቀት በመስጠት ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ባማረ መልኩ ተጠናቀዋል።

በዚህ ዙሪ ስልጠና የተሠጡባቸው ርዕሶች :-
✅Outcome-based training delivery
✅Ethiopian occupational standard (EOS)
✅Analysing unit of competency
✅ UC and Learning Module (LM) R/ship
✅practical learning module preparation
✅TTLM Preparation &plan training session
✅Teaching methodology
✅Effective Teaching
✅Learning Domains
✅ Assessing, Measuring and Evaluation
✅ Table of specification
✅ Item analysis
✅ Internal Assessment implementation and Grading System. በሚሉና ሌሎች ርዕሶች ላይ ለ10 ተከታታይ ቀናት በጥልቀት ስልጠና ስሰጥ ቆይቷል።

ዓላማችን የበቃ ዜጋን ማፍራት ነው
የሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ISO2001:2018 Certified !

29/10/2024
Photos from Hawassa Polytechnic College's post 07/10/2024

*******እንኳን ደስ አላችሁ********
የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማት ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የእውቅና ሴረተፍከት ሽልማት ያበረከተ ስሆን፣ ኮሌጃችን ካሉት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች 1ኛ ደረጃ በመያዙ የእውቅና ሰርተፊኬት አግኝቷል።

16/09/2024

*******Congratulations********
Tsiyon Adane from Hawassa Polytechnic College ICT department attained Best of Nation recognition in France skill Competition.

10/09/2024

🌻🌻🌻🌻እንኳን ለ2017 አድስ ዓመት🌻🌻🌻
🌻ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/ሰን!!!🌻
ኮሌጃችን በምስራቅ አፍሪካ በጋርመንት እና ቴክስታይል ሙያ የልህቀት ማዕከል በመሆን ሠልጣኞችን ተቀብሎ ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየሰራ ይገኛል። በስልጠና ጥራት ሁለም ቀዳሚ የሆነው ኮሌጃችን በዓለም አቀፍ በሥልጠና አሰጣጥ ጥራት ትግበራ ISO 21001:2018 Education Management System በሀገራችን ቀዳሚ በመሆን ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ተሸላሚ በመሆን ከድርጅቱ ዋና ዳይረክቴር እጅ በቀን 4/13/2016 ዓ/ም የእውቅና ሴርተፊኬት በማግኘት ደስተኛ ሆነን የምናከብረው በዓል መሆኑ ለየት ያደርገዋል፣ በዚህም መሠረት ኮሌጃችን በ2017 ዓ/ም ነባር እና አድስ ሠልጣኞ ተቀብሎ በዘርፉ የበቃ ተወዳዳሪ እና ስራ ፈጣሪ ትውልድ በማፍራት ከሀገር አልፎ ለምስራቅ አፍሪካ አስተዋጽኦ ለማበርከት ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ስንገልጽ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማናል።
🌻🌻🌻 አድሱ አመት 🌻🌻🌻🌻
🌻🌻የደስታ🌻🌻
🌻🌻🌻🌻የሠላም፣ 🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻የፍቅር፣🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻🌻🌻አብሮ የመስራት፣ 🌻🌻
🌻የብልጽግና እንድሆን እንመኛለን!!🌻
🌻🌻ሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ🌻🌻
🌻🌻🌻🌻ዲን ጽ/ቤት🌻🌻🌻🌻

Want your school to be the top-listed School/college in Awassa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Videos (show all)

ሰላም  ‹‹ የጥበበኞች አምባ ›› የተሰኘው ዶክመንተሪ ስርጭትዛሬ ቅዳሜ ማታ 3፡00 ሰዓት ላይ በዋልታ ቴሌሺቪን ይተላለፋል እንድትከታተሉት በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ Greetings. Doc...
Hawassa PTC Learning Workshop Vs JP Garment Ethiopia PLC. Simulating the learning workshop at the college level helps th...
ሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የምክክር መድረክ፤

Location

Telephone

Address

Hawassa
Awassa