የአፋር ወጣቶች

የአፋር ወጣቶች

Share

Information

Photos from የአፋር ወጣቶች's post 19/11/2024

ለበጎ ስራ ተመልሻለሁ 🙏🙏🙏
ወንድማችን ፍፁም ግርማ (ፍፄ) በጠና ታሟል። በእርግጥ ካመመው ወራቶት ተቆጠሩ። በሽታውን የሰው ፊት ሳያይ "እርዳታ እናሰባስብ" ብንለው እንኳን "ቆይ!"ብሎ ብቻውን ለመታገል ሞከረ ሞከረ ሞከረ ግን አሁን ከአቅሙ በላይ ሆነበት። "አቃተኝ አግዙኝ" ሲል እንዴት ልብ ይሰብራል። ከራሱ አልፎ ለሰዎች፣ ለመጪው ትውልድ የሚተርፍ ልጅ በድንገት በበሽታ ወድቆ እጅ አጠረው። በሽታ ክፉ ነው። ተሯሩጦ እንዳይበላ አስሮ ያስቀምጣል። በህመም ምክንያት በተቋረጠ ገቢ ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃል። ፍፄ ይህን ተቋቁሞ ህመሙን በሆዱ ሸሽጎ ነበር። ዛሬ ግን እስከ 2 ሚሊየን ብር የሚፈጅ የውጭ ሀገር ህክምና እንደሚያስፈልገው ሲሰማ "አሁን ተራው የእናንተ ነው" አለን። ከፈጣሪ በታች ለሰው መድኃኒት ሰው ነው። እናም ፍፄ እኛን ላለማስቸገር ብዙ ታግሎ አቃተኝ ካለ እኛ አለንልህ ልምለው ይገባል።
ነገ እኛም ተረኞች ነን እናም የአቅማችንን በማውጣት ፍፄን እንታደገው።
ይሄንን የእርዳታ መስጫ አማራጮች ተጠቅመን እናግዘው የላካችሁበትን ፎቶውን ብትልኩልን ሌሎችን ያበረታታል።
👉ንግድ ባንክ 1000222130143
👉አቢስንያ 36211725
👉ቴሌብር 0911395229/0913246683
ፍፁም ግርማ አሸብር

ሼር አድርጉት🙏

29/11/2023

የሀገር ግንባታ የዘመናትና የማያልቅ የትውልድ ቅብብሎሽ ውጤት ነው።

ሀገር የትውልዶች ትስስር ውጤት ናት። የትውልድ ቅብብሎሽ ሲባል፣ በትውልዶች መካከል በሚኖር ጠንካራ ተግባቦት የሚፈጠር፣ የጠንካራ እሴት መወራረስ ነው።

በዚህ አይነት መንገድ መልካም ያልሆኑ እሴቶች እየታረሙ፣ ጠንካራ ሀገራዊ እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ፣ ዘመኑን እየዋጁ ሲሄዱ፣ ሀገር እየተጠናከረ ይመጣል።

ትውልዶች የሚያልፉበት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ የተለያየ ከመሆኑ የተነሳ፣ በትውልዶች መካከል የሚኖር ልዩነት አይቀሬ ነው።

አልፎ አልፎም ልዩነቱ ወደ ተቃርኖና የለየለት ጠላትነት ሊለወጥ ይችላል። በትውልዶች መካከል ያለውን ልዩነት ተረድቶ ለማስማማትና ለማቻቻል አለመሞከር በትውልዶች መካከል የትስስር ክፍተት ይፈጥራል።

ይህ የትውልድ ትስስር ክፍተት እየሰፋ ሲሄድ በሀገር ጥንካሬ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል። በቀደመውና በተተኪው ትውልድ መካከል ያለው የዕሴትና የባህሪ ልዩነት እጅግ የሰፋ ሲሆን ፣ በማህበረሰብ መካከል የጥቅም ግጭት በመፍጠር አፍራሽ ሀገራዊ ሁኔታ ይፈጥራል።

አንዱ የአንዱን ሁኔታ የሚገነዘብ ሳይሆን፣ ተተኪው የቀደመውን አምርሮ የሚጠላ፣ የቀደመው ተተኪውን የሚያብጠለጥል በመሆኑ፣ ባለው ላይ የመገንባት ሳይሆን የማፍረስ ባህል እንዲፈጠር ያደርጋል።

ትውልድ አብሮ የተገመደና የተቋጠረ ብቻ ሳይሆን እንደ ወንዝ ሳያቋርጥ የሚፈስስ የዘመንና የክሥተት ውጤት ነው። ሊሸከሙትና ሊያሻግሩት የማይችሉትን የምልከታ መነጽሮቹን አውልቆና የአተያይ አድማሱን አስፍቶ ፤ የራሱን ፈተና በማሸነፍ ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለ ሀገርን ማስረከብ ፤ የዚህ ትውልድ ጊዜ የማይሰጥ የቤት ስራ ነው።
የመደመር ትውልድ ገፅ 23 -25

Photos from የአፋር ወጣቶች's post 04/09/2022

ኢንጂነር ሃይደር መሀመድ በዛሬው ቀን ርክክብ አድርጓል
መልካም የስራ ዘመን ይሁንልህ ወንድሜ

Want your school to be the top-listed School/college in Awash?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


Awash