Assosa Online

Assosa Online

Share

እውነተኛ ታማኝ እና ወቅታዊ መረጃዎችን እናደርሳለን፡፡

21/05/2026

⚠️ **ማስጠንቀቂያ፦ ይህ ደብዳቤ የሐሰት (Fake) ነው!**
ሰሞኑን “ከገንዘብ ሚኒስቴር የወጣ የደመወዝ ግብር 15% ቅናሽ ማሻሻያ” በሚል በሰፊው እየተዘዋወረ የሚገኘው ደብዳቤ ሙሉ በሙሉ **የሐሰት (Fake)** መሆኑን የሚያረጋግጡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* ⚖️ **የህግ እና የፖሊሲ እውነታ፦** በሀገራችን የደመወዝ የገቢ ግብር ተመን የሚሻሻለው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚወጣ **የታክስ አዋጅ** እንጂ በገንዘብ ሚኒስቴር የአንድ ገጽ ሰርኩላር ደብዳቤ ብቻ “15% ቅናሽ ተደርጓል” ተብሎ አይደለም። ሚኒስቴሩ ይፋዊ የግብር ተመን የመቀየር ህግ የማውጣት ስልጣን የለውም።
* 📢 **ምንም አይነት ይፋዊ መግለጫ አለመኖሩ፦** እንዲህ ያለ መላውን የሀገሪቱን ሰራተኛ እና የክልል መንግስታት በጀት የሚነካ ትልቅ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ ሲደረግ በገንዘብ ሚኒስቴር ይፋዊ ማህበራዊ ገጾች፣ በኢቢሲ (EBC)፣ በፋና ወይም በሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች በፍጹም አልተገለጠም።
* ✍️ **የሰነዱ የፎርማት ጉድለቶች፦** * የደመወዝ ግብር ማሻሻያ የመሰለ እጅግ ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ሰነድ መለያ ቁጥር (Reference Number) በሰማያዊ ስክሪፕቶ በእጅ አይሞላም።
* በደብዳቤው ላይ ያለው ማህተም እና የሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ፊርማ ከሌላ ሰነድ ላይ ተቆርጦ በዲጂታል መንገድ የተቀናበረ (Superimposed) መሆኑ ያስታውቃል።
* የደብዳቤው ይዘት እና የአማርኛ አገላለጽ የአንድን ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤት መደበኛ የደብዳቤ አጻጻፍ ስታንዳርድ አይከተልም።
ይህ ሰነድ ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሐሰት መረጃ ነው።

20/05/2026

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተሰጠ መግለጫ

ለተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን!

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በሀገሪቱ በሚገኙ በተመረጡ ከተሞች ላይ የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች እስከ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ከደንበኞች የፋይዳ መታወቂያ ጋር እንዲተሳሰር የተቀመጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ በትዕዛዙ መሰረት ደንበኞች እነዚህን ሂሳቦች ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ተደርጓል፡፡

ይህንን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ የማስተሳሰር ጥያቄ ወደ ባንካችን እየቀረበ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ባንካችን ይህንን ጫና በመቋቋም ለደንበኞቻችን በሚፈለገው ፍጥነት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ አሰራሮችን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ለአብነት ከግንቦት 7 እስከ ግንቦት 12 በተለየ ምክንያት እንዳይንቀሳቀሱ ከተደረጉት ሂሳቦች ውጪ የተሳሰሩ ሂሳቦችን ደንበኞች ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም ከ ከግንቦት 12 ጀምሮ ደንበኞች ሂሳባቸውን እንዳስተሳሰሩ የመረጃ ስርዓታችን (system) በራሱ ጊዜ ገደቡን እንዲያነሳ ተደርጓል፡፡

መሰል ፈጣን ምላሾን እየሰጠን የደንበኞቻችንን እርካታ እውን ለማድረግ የምንሰራ መሆኑን እያረጋገጥን በዚህ ሂደት ላሳያችሁት ትዕግስት ከልብ እያመሰገንን በደንበኞቻችን ላይ ለተፈጠረው መጉሏሏት ይቅርታ ለመጠየቅ እንወዳለን፡፡

በተጨማሪም እንዳይንቀሳቀስ ከተደረጉ ሂሳቦች እና ከነዚህ ውጭ በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ አስቀድማችሁ የማስተሳሰር ሂደቱን በባንካችን ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም በበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ (https://cbefayda.cbe.com.et) ሂሳባችሁን ለማንቀሳቀስ እንድትችሉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡

ስለ ትብብርዎ እናመስግናለን!
Via የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

20/05/2026

ምን ይሆን ግን እንዲህ ክፉ ያደረገን ? 🤔
የልጁን እናት በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሎ ቪዲዮ ለቤተሰቦቿ የላከው ግለሰብ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር ውሏል።

ግንቦት 11/2018 ዓ/ም የልጅ እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ አማካኝነት በዛሬው እለት በመሀል አምባ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከሳምንታት በፊት በግዮን ማለዳ በተደጋጋሚ የልጅ እናቱን ገድሎ በመሰወር ለቤተሰቦቿ ቪዲዮ እየለከ እንደሚዝትባቸው መናገራችን ይታወሳል ።

በቀን 12/08/2018 ዓ/ም ከለሊቱ ባልታወቀ ሰዓት ኮልፌ ቀራንዮ ክፈለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው አየር ጤና አካባቢ ሟች አለሚቱ ሸጋው የተባለችውን ነዋሪነቱ አዲስ አበባ የሆነው....

ተጠርጣሪ ደሳለኝ ሽመልስ የተባለው ግለሰብ አንገቷን አንቆ ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ከአካባቢው ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ ከተሸሸገበት...

በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ ከነሸሻጌቸው የወረዳው ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሺን አባላት ጋር በመሆን በጠንካራ ኦፕሬሽን በዛሬው እለት በቀን 11/09/2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል።

ለሚዲያችን መረጃውን ያደረሰው በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው አክብራችሁ መረጃውን ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን ። በግፍ ህይወቷ የተነጠቀው አለሚቱ ሸጋው ፍትህ እንደምታገኝ እናምናለን !

ህዝቡ እንዲሁ ከተባበረ ማንም እህቶቻችን ላይ ጥቃት እያደረሰ መሰወር አይችልም ። የእህታችንን ነብስ ይማርልን

ለተጨማሪ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👇

ቤተሰብ ይሁኑ

20/05/2026
በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መደረጉን የተቃወሙ አሽከርካሪዎች ሥራ አቆሙ - BBC News አማርኛ 18/05/2026

ኬንያውያን አሽከርካሪዎች እና የመኪና ባለንብረቶች ባለፈው ሳምንት የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በመቃወም ሥራ በማቆማቸው በሺህዎች የሚቆጠሩ መንገደኞች እና ንግዶች ተስተጓጉለዋል። በኬንያ ናይሮቢ ዋና ዋና መንገዶች እንቅስቃሴ አልባ ሆነው ያረፈዱ ሲሆን፣ የተወሰኑ መንገደኞች በእግራቸው ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ ተገድደዋል።

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መደረጉን የተቃወሙ አሽከርካሪዎች ሥራ አቆሙ - BBC News አማርኛ በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መደረጉን የተቃወሙ አሽከርካሪዎች ሥራ አቆሙ

18/05/2026

ነብስ ይማር 😭

ሂንሴኔ ተፈሪ ትባላለች። ነዋሪነቷ ነቀምቴ ከተማ ሲሆን፣ በ'ኒው ጀነሬሽን' ኮሌጅ የቢኤስሲ ነርሲንግ (BSc Nursing) የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረች ሲሆን እጅግ ጎበዝ እና በውጤቷ ሌሎች ጭምር የሚቀኑባት እንደነበረች በቅርቧ ያሉ ይመሰክራሉ።

ሂንሴኔ ዛሬ እራሷን አ*ጥ ፍታለች ።
ምክንያቷ ደግሞ የትምህርት ቤት ያልከፈለችው ክፍያ አስራ አምስት ሺህ (15,000) ብር እሷ ላይ የቀረባት ስለነበረ ነው። ክፍያ ያልፈጸመ ደግሞ የ'Exit Exam' ፈተና መፈተን ስለማይችል፣ ከጓደኞቿ መቅረቷ ተስፋ አስቆርጧት ህይ*ወቷን እንድ*ታጠፋ እንዳደረጋት ነው የተነገረው😥
በጣም ያሳዝናል! 😭

16/05/2026

ስለመተከሉ ጥቃት ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል። ቢቢሲ ለቀናት ያጠናከረውን መረጃ እንዲህ ቀርቧል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ወደ መተከል ዞን ዋና ከተማ ግልገል በለስ እየተጓዙ በነበሩ አራት ተሽከርካሪዎች ላይ በዳንጉር እና ጉባ ወረዳዎች መካከል ላይ አይሲድ ቀበሌ ወይም አፍሪካ እርሻ ልማት በተባለ ስፍራ ላይ መሆኑን ቢቢሲ ተረድቷል።

ፀሐይነሽ ህመም ላይ ያሉ እናቷን ለመጠየቅ ሕጻን ልጇን ይዛ ወደ ቡለን ወረዳ እየተጓዘች በነበረችበት ጊዜ ነው ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት ከነ ልጇ የተገደለችው።

"ከዚህ ቀደም አባቷን ሳታይ ስለሞቱባት፤ እናቷን 'ሳላያት እንዳትሞት' በማለት ከ13 ዓመታት በኋላ እናቷን ልታይ እየሄደች ነበር" ሲሉ አንድ የቤተሰብ አባል እናት ከልጇ ጋር እንደወጣች የቀረችበትን አጋጣሚ አስረድተዋል።

የቤተሰብ አጋዥ እና ወንድሞቿን የምታስተምር እንደሆነች የተናገሩት ቤተሰቡ፤ "ያላለቀሰ ሕዝብ የለም" በማለት የእናት እና ልጅ ግድያ በማኅበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘን እና ድንጋጤን መፍጠሩን ገልጸዋል።

ሚስቱ እና ልጁ በታጣቂዎች የተገደሉበት በባለቤቷ በከፍተኛ ሐዘን ምክንያት በመረበሹ ራሱን እና ሌሎችን እንዳይጎዳ በሚል "ታስሮ" እንደሚገኝ የቤተሰብ አባሉ ተናግረዋል።

የቢቢሲን ሙሉ ዘገባ ኮሜንት ላይ ባለው ሊንክ ያንብቡ

13/05/2026

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ የሆኑት ገብሩ ካህሳይ (ዶ/ር) በቁጥጥር በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ። የፕሬስ ኃላፊው በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰኞ ግንቦት 3/2018 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ መሆኑን ቢቢሲ ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል።

የቢቢሲን ሙሉ ዘገባ ኮሜንት ላይ ባለው ሊንክ ያንብቡ

12/05/2026

ነብስ ይማር 😭
ዛሬ ቀን 4/9/2018ዓ.ም ከአሶሳ ወደ ግልገል በለስ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት የህዝብ ማመላለሻ ባሶች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከ17 ሰው በላይ ህይወት ሲቀጠፍ ከ51 በላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

Photos from Assosa Online's post 08/05/2026

በአሶሳ ከተማ የግንባታ እቃዎች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን ተከትሎ፣ በግንባታ ስራዎችና በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተገለፀ። የክልሉ መንግስትም ፍትሃዊ የነዳጅ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ በማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰዉን ዘርፈ ብዙ ጫና እንዲቀርፍ ጠይቀዋል።

ቀደም ሲል 2 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው ሲሚንቶ አሁን ላይ ከ 3500 ብር በላይ የደረሰ ሲሆን በተመሳሳይ በአንድ ገልባጭ 70 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው አሸዋ አሁን ከ200 መቶ ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ እየተጠየቀበት ይገኛል።

ለዚህ አስደንጋጭ የዋጋ ንረት ዋነኛው ምክንያት የነዳጅ እጥረት መሆኑን አቅራቢዎች ተናግረዋል።

ክልሉ የድንበር አካባቢ በመሆኑ የጭነት መኪኖች ረጅም መንገድ ተጉዘው እቃ ካወረዱ በኋላ፣ ለመመለሻ የሚሆን ነዳጅ በክልሉ ማግኘት አለመቻላቸው ለአቅርቦቱ መስተጓጎል እና ለዋጋ ንረቱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በከተማዋ የሚገኙ በርካታ የግንባታ ስራዎች በግብዓት እጥረትና በዋጋ መወደድ ምክንያት መቋረጣቸዉንም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።

በአሶሳ ከተማ በቅርብ ጊዜ በርካታ የግንባታ ስራዎች መጀመራቸዉንና አሁን ላይ መቀዛቀዛቸዉን በርካታ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

የክልሉ መንግስት ለነዳጅ አቅርቦቱ ትኩረት በመስጠትና የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከር በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው ሁሉን ጫና እንዲቀንስም ጠይቀዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ከሚመለከታቸዉ አካላት በስልክ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

በዘመናይ የሻለም BGM

07/05/2026

በሰው ላይ ጥቃት በማድረስ የተከሰሰው ድምፃዊ አህመድ ማንጁስ የ300 ብር ቅጣት እንዲከፍል ተፈረደበት።

በሴት ልጅ ላይ አካላዊ ጥቃት በማድረስ ወንጀል የተከሰሰው ድምፃዊ አህመድ ሁሴን ወይንም ማንጁስ ላይ የገንዘብ ቅጣቱን ያስተላለፈው ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ነው።

ድምፃዊው ለዚህ ቅጣት የተዳረገው የካቲት 22 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ከንጋቱ 12 ሰዓት ከ10 ላይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ስታር ሆቴል በተባለው ውስጥ የግል ተበዳይ የሆነችውን መድሃኒት ይልማ ላይ ጥቃት ፈጽሞ ጥፋተኛ በመባሉ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ላይ አብራርቷል።

ፍርድ ቤቱ የቅጣት ውሳኔውን ከመስጠቱ በፊት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት የመረመረ ሲሆን፣ አቃቤ ህግ ወንጀሉ የተፈጸመው በሴት ላይ በመሆኑና ተከሳሽ ድርጊቱን የፈጸመው በምሽት በመሆኑ ቅጣቱ ሊከብድበት ይገባል ሲል አመልክቷል።

ተከሳሽ በበኩሉ ቀደም ሲል የጥፋተኝነት ሪከርድ የሌለበት መሆኑን፣ ድርጊቱን መፈጸሙን አምኖ በመጸጸቱ እንዲሁም የሁለት ልጆች አባትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን በመጥቀስ የሚጣልበት ቅጣት እንዲቀልለት ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ በውሳኔው የአቃቤ ህግን የቅጣት ማክበጃ በመተው፣ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የቅጣት ማቅለያዎች ተቀብሎ የእስራት ቅጣቱን ወደ ገንዘብ ቅጣት ቀይሮለታል።

በዚህም መሰረት ተከሳሹ የ300 ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍል እንደተወሰነበት በፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ላይ ተመልክተናል።

Via ኢትዮጲካሊንክ

ቅጣት ብሎ ዝም 🤔

Want your school to be the top-listed School/college in Asosa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Asosa
Asosa