18/08/2026
የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የክረምት በጎ ፍቃድ የሥራ አካል የሆነውን የአቅመ-ደካሞች ቤት ግንባታ ተረከበ።
(ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም አሶሳ)
የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የክረምት በጎ ፈቃድ የሥራ አካል አንዱ የሆነውን የአቅመ-ደካሞች ቤት ግንባታ፤ በኮሌጁ የገንዘብ ምንጭ ለመገንባት ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አንድ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ አሙና አብዱልዋሂድ
እና ሌሎች የወረዳው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ደረጃውን የጠበቀ ሁለት ክፍል ቤት ለመገንባት የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ ግዛቸው በጋንፄ በዛሬው እለት የተረከቡ ሲሆን፤በርክክቡ ወቅትም አቶ ግዛቸው በታቀደለት የጊዜ ገደብ ሰርተው እንደሚያስረክቡ ገልጸዋል።
ዘገባው የኮሌጁ የህዝብ ግንኙነት ነው!
==============//=========