Sadiq Mohammed

Sadiq Mohammed

Share

The person who does thief and locked the other FB page and account will be never accept to me

15/04/2026

Gurbaa gadi galoo tana gaati sihii keninaafi qoy
ቀይ ሽብር👇

15/04/2026

Nutis Confirmed janne jira Last KRM
የሶሻል ሚድያ ተፅእኖ ፍጣሪ

Ethiopia, see you soon!!! 🇪🇹🥜

13/04/2026

ወንጀለኛው በእስፔ ተሰቅሏል

13/04/2026

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በአክሱም የተፈፀመውን ጥቃት አወገዘ፡፡ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ‹‹በታሪካዊቷ አክሱም ከተማ ውስጥ በሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ኢሰብአዊ ጥቃት አጥብቀን እናወግዛለን›› በማለት የጀመረ ሲሆን አርብ እለት ሚያዝያ 2 ቀን 2018 የተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ለዘመናት ከቆየው የህዝቡ የመከባበርና አብሮ የመኖር ባህል ጋር የሚቃረን መሆኑን አስረድቷል፡፡

የችግሩ መነሻ ድንገተኛ ሳይሆን በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎችም መድረኮች ላይ የተሰራጨው የጥላቻ ንግግር ውጤት መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው ‹‹ለዘመናት የቆየውን የአዛን ወይንም ድምፅ ማጉያ አጠቃቀም በሀይል ለማስቆም የተወሰደው እርምጃ ህገ መንግስታዊውን የሀይማኖት ነፃነት የሚጥስ ነው›› ብሏል፡፡ መግለጫው በማስከተልም አርብ እለት በጁመአ ስግደት ላይ በነበሩ ሙስሊሞች ላይ የተፈፀመው ጥቃት ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት እንደሌለው ገልፆ በእለቱ በመስጅድ ውስጥ በሀይል በመግባት ቅዱስ ቁርአንን መቅደድና መሬት ላይ መበተንን ጨምሮ በመስጅድ ውስጥ የሚገኙ እቃዎችን እስከመስበር ድረስ የተፈፀሙትን ድርጊቶች ዘርዝሯል፡፡

እንዲሁም በሰላማዊ ምእመናን ላይ አካላዊ ጉዳት ጭምር እንደደረሰባቸው ገልፆ በዘፈቀደ ለተፈፀመው እስርም ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡ ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙ እነዚህን ችግሮች በትእግስት በመቋቋምና ተቃውሞን በሰላማዊ ተክቢራ ብቻ በመግለፅ ላሳየው ጨዋነት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ መግለጫው ጨምሮም መንግስት ይህንን ጥላቻ ያነሳሱና የመሩ፣ በጥቃቱ ላይ የተሳተፉ የፀጥታ ሀይሎችና ሲቪሎችን ተከታትሎ በመያዝ ለፍርድ እንዲያቀርብም ጥሪውን አቅርቧል፡፡

13/04/2026

: #የአሜሪካ ጦር ሀይል መካከለኛው ዕዝ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሰጡትን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ #የኢራን ወደቦችን መውጫና መግቢያ መዝጋት ሊጀምር ነው

አዲስ አበባ — የአሜሪካ ጦር ሀይል መካከለኛው ዕዝ (CENTCOM) ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተላለፈ መመሪያ መሠረት፤ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡና የሚወጡ ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች ለማገድ የባሕር ላይ ከበባ (maritime blockade) ከሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ ጀምሮ እንደሚተገብር አስታወቀ።

የመካከለኛው ዕዝ ከአንድ ሰዐት በፊት ባወጣው መግለጫ፤ የማስጠንቀቂያው ተፈጻሚነት በዓረብ ባሕረ ሰላጤ እና በኦማን ባሕረ ሰላጤ በሚገኙ የኢራን ወደቦችና የባሕር ዳርቻዎች ላይ የሚንቀሳቀሱ የማንኛውም ሀገር መርከቦችን "ያለ አድልዎ" እንደሚመለከት ገልጿል።

ሆኖም ዕዙ አክሎም፤ የአሜሪካ ኃይሎች ወደ ኢራን ወደቦች የማይጓዙ ወይም ከኢራን ወደቦች ያልተነሱ መርከቦች በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ ውስጥ የሚያደርጉትን ነፃ የባሕር ላይ ጉዞ እንደማያስተጓጉሉ አስታውቋል።

ማስጠንቀቂያው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት ለንግድ መርከብ አሽከርካሪዎች ይፋዊ የባሕር ላይ ማሳሰቢያዎች እንደሚሰጥም ሴንትኮም ገልጿል።

መርከበኞች ይፋዊ የ"መርከበኞች ማሳሰቢያ" (Notice to Mariners) ስርጭቶችን እንዲከታተሉ እና በኦማን ባሕረ ሰላጤና በሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ አካባቢ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ከአሜሪካ የባሕር ኃይል ጋር የሬዲዮ መስመር 16 በኩል ግንኙነት እንዲያደርጉ መክሯል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል በኢስላማባድ የተካሄደው ንግግር ያለ ስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት በጨመረበት ወቅት ነው።

ከጥቂት ሰዓታት በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አሜሪካ ወደ ሆርሙዝ የባሕር ሰርጥ የሚገቡ ወይም የሚወጡ መርከቦችን "መተላለፊያ መከልከል" (blockading) ልትጀምር እንደምትችል አስጠንቅቀው ነበር።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ"ትሩዝ ሶሻል" ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የአሜሪካ ኃይሎች በባሕር ሰርጡ ለማለፍ የሚሞክሩ "ማናቸውንም መርከቦች የመዝጋት ሂደቱን በአስቸኳይ ይጀምራሉ" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም፤ “ሁሉም [መርከቦች] እንዲገቡ እና እንዲወጡ የሚፈቀድበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፤ ነገር ግን ኢራን እስካሁን ይህ እንዲሆን አልፈቀደችም" ሲሉ ጽፈዋል።

በተጨማሪም የአሜሪካ የባሕር ኃይል "ለኢራን የመሻገሪያ ክፍያ (toll) የከፈለ ማንኛውንም መርከብ በዓለም አቀፍ የባሕር ክልል ውስጥ መተላለፍ እንዲያስቆም" መመሪያ መስጠታቸውን ገልጸው፤ "ሕገ-ወጥ ክፍያ የሚከፍል ማንኛውም አካል በባሕር ላይ አስተማማኝ ጉዞ አይኖረውም" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

12/04/2026

ብሪታንያ በሆርሙዝ ወሽመጥ የታቀደውን የትራምፕ የባህር ላይ እገዳ እንደማትቀላቀል አስታወቀች

​የብሪታንያ መንግስት ዶናልድ ትራምፕ በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ ለመጣል ባቀዱት የባህር ላይ እገዳ (Naval Blockade) ላይ እንደማትሳተፍ በይፋ አስታውቃለች።

​እንደ ዘገባው ከሆነ፣ ብሪታንያ ይህን ውሳኔ ያሳለፈችው በአካባቢው ያለውን ውጥረት ላለማባባስና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን ላለመጉዳት በማሰብ ነው። የሆርሙዝ ወሽመጥ ለዓለም አቀፍ የነዳጅ ንግድ ቁልፍ መተላለፊያ እንደመሆኑ መጠን፣ እንዲህ ዓይነቱ ወታደራዊ እርምጃ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት በለንደን በኩል ተፈጥሯል።

​ዩናይትድ ስቴትስ አጋሮቿ በዚህ የባህር ላይ ዘመቻ እንዲተባበሯት ጥሪ ብታቀርብም፣ ብሪታንያ ግን የራሷን የባህር ኃይል ደህንነት በተናጠል እንደምታስከብርና ከትራምፕ አስተዳደር እቅድ ጋር እንደማትሰለፍ ገልጻለች።

12/04/2026

Aksum abshir isinif qaqabaa jirra

Photos from OBN አማርኛ's post 12/04/2026
11/04/2026

አርሰናል በበርንማውዝ ተሸነፈ ‼

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በኢምሬትስ ስታድየም፣ አርሰናል በሜዳውና በደጋፊዎች ፊት በበርንማውዝ 2 ለ 1 ተሸንፎ ነጥብ ጥሏል።

ለአርሰናል በፍፁም ቅጣት ምት ዮኮሬሽ ጎል ሲያስቆጥር፣ ለበርንማውዝ ክሩፒ እና ስኮት ኳስን ከመረብ አገናኝተዋል። በዚህም በርንማውዞች ለ13ኛ ጊዜ ያለመሸነፍ ጉዟቸውን አስቀጥለዋል።

ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው አርሰናልን በ61 ነጥብ እየተከተለ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ ነገ እሁድ ከቼልሲ ጋር ወሳኝ ጨዋታውን ያደርጋል።

"ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የፌስቡክ ገጻችንን 'Follow' ያድርጉ።

ሊንኩን ተጭነው ቤተሰብ ይሁኑ፦ 👇

https://www.facebook.com/AMECODessie

"መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ያድርጉ - ስለመረጡን እናመሰግናለን!”

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

#አርሰናል

አሚኮ ደሴ AMECO Dessie Broadcasting & media production company

Want your school to be the top-listed School/college in Asebe Teferi?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Ciro
Asebe Teferi
304050

Opening Hours

09:24 - 05:00