20/11/2022
!
ውጥረትን በመፍጠር ረገድ ቀዳሚውን ድርሻ የሚወስደው የአእምሮ መመሰቃቀል እንደሆነ ይታመናል። ባተሌው አእምሮ ሁሌም ውጥረት ይሰማዋል። የተመሰቃቀለ አእምሮ ማለት ግራ መጋባት የሰፈነበት እንዲሁም ውጥረት የነገሰበት ነው። እንዲህ ዓይነቱ አእምሮ በጭራሽ በማይወስናቸው ችግሮች ላይ በቀላሉ ያርፋል።
ከአንዱ ችግር ወደ ሌላው ችግር በጭንቀት ይዘላል እንጂ የተረጋጋ ድምዳሜ ላይ አይደርስም፤ እንዲያውም ከጉዳዩ ጋር በቁም ነገር አይታገልም። በመሆኑም እልባት ያልተሰጠባቸው እና በእንጥልጥል ያሉ ጉዳዮች ይከማቹበታል። በውጤቱም፣ አእምሮ ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ይገባል፤ ተስፋ ወደ መቁረጥም ያመራል።
አእምሮህ ተስፋ ቆረጠ ማለት… አንተም ተስፋ ቆረጥክ ማለት ነው፡፡ እስቲ አእምሮህ ካለበት መመሰቃቀል እንዲወጣ ባለህበት አይኖችህን ጨፍንና ጥልቅ አየር ማግ በማድረግ ለአምስት ሰከንዶች ያህል ይዘህ አቆይተህ ውስጥህ ያለውን ምስቅልቅል ነገር በትንፋሽህ አውጣ፡፡
ተንፍስ… ተረጋጋ፡፡
ሺ አመት አይኖርም… አሁን በዚህች ቅጽበት ዘና በል፡፡ የሕይወት ሁሉ መፍትሄ ያለው ዘና ባለ አእምሮ ውስጥ ነውና አእምሮህን ዘና አድርገው፡፡
5ተኛው ዕትም
19/11/2022