26/04/2025
የመ/ሐ/ከ/ሁ/ደ/መ/ት/ት ቤት የቴክኖሎጂ ቀንን በማስመልከት ከ 'Project Initiative Ethiopia' ጋር በመተባበር የተማሪ ወላጆች ባሉበት ደማቅ ፕሮግራም አቅርቧል።
ፕሮግራሙን ያስጀመሩት የት/ት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሀቢብ ያሲን ቴክኖሎጂ የመጪው ትውልድ መፃዒ እድል የሚወሰንበት መሆኑን አውስተው ት/ት ቤቱ የቴክኖሎጂ ስራዎችን እንደሚያበረታታ ገልፀዋል።
የአ/ከ/ት/ፅ/ቤት ሐላፊ አቶ ሀቢብ ሐንፈሬ ከተማሪ ወላጆች ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተው መሐመድ ሐንፈሬ ት/ት ቤት የሚያስፈልጉትን የእድሳት ስራ እንዲያከናውን ወላጆች በቻሉት እንዲያግዙና ስራውን ለማስጀመር ጥሪ አቅርበው ሌሎች እገዛ ሊያደርጉ ከሚችሉ ባለድርሻ አካላት ጋርም እንደሚነጋገሩ ገልፀዋል።
ወደፊት ኮሚቴ በማቋቋም ለት/ት ቤቱ አዲስ አካውንት በመክፈት በት/ት ቤቱ የተማሩ፤የት/ት ቤቱ ወዳጆችና የከተማችን ነዋሪዎች በፈቃዳቸው አሻራቸውን የሚያሳርፉበት መንገድ እንደሚመቻች ተጠቁሟል።