አርባምንጭ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት Arbaminch City Education Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • አርባምንጭ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት Arbaminch City Education Office

አርባምንጭ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት Arbaminch City Education Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አርባምንጭ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት Arbaminch City Education Office, Education, Arba Mintch.

03/10/2021

የ2013 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ዉጤት ዛሬ በ23/01/2014 ዓ.ም ለትምህርት ቤቶች የተሰራጨ ስለሆነ ዉድ ተማሪዎቻችን ዉጤታችሁን በመዉሰድ ከ24/01/2014 እስከ 26/01/2014 ዓ.ም ድረስ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

የ4ኛ ክፍል ዞናዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ። ሐምሌ 1-2/2013 ድረስ  ሲሰጥ  የቆየው  ፈተና  በሠላም  መጠናቀቁን  የአ/ምንጭ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት  ጽ/ቤት አስታወቀ።
09/07/2021

የ4ኛ ክፍል ዞናዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ። ሐምሌ 1-2/2013 ድረስ ሲሰጥ የቆየው ፈተና በሠላም መጠናቀቁን የአ/ምንጭ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ።

የ2013 ዓ/ም  8ኛ ክፍል ክልላዊ   የፈተና ኘሮግራም
28/06/2021

የ2013 ዓ/ም 8ኛ ክፍል ክልላዊ የፈተና ኘሮግራም

አገር  አቀፍ  የአረንጓዴ  አሻራ  በትምህርት ቤቶች ማስጀመሪያ  ፕሮግራም በአርባምንጭ  ከተማ  ተካሄደ ። በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር  አዘጋጅነት በአርባ ምንጭ  ከተማ  የኢፊዴሪ  ትምህ...
28/06/2021

አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ በትምህርት ቤቶች ማስጀመሪያ ፕሮግራም በአርባምንጭ ከተማ ተካሄደ ።
በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአርባ ምንጭ ከተማ የኢፊዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ከብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ፣ሚኒስቴር ደኤታዎች ፣ የሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያዎች፣ የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያና የአርባምንጭ ከተማ ትምህርት ባለሙያዎች፣የአርባምንጭ ከተማ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መምህራንና ሠራተኞች ተሳታፊ የሆኑበት ታላቅ የአረጒዴ አሻራና ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተከናውኖአል። ፕሮግራሙን በማስመልከት
በትምህርት ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ መልዕክት በተለያዩ አካላት ተላልፏል ።

የብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ብቂላ ሀሪሶ መምህራን ሁለት ውድ የሆኑ አገር የሚገነቡ ተማሪዎች እና አረንጓዴ ችግኞችን በመንከባከብ ትውልድ የመንከባከብ የመቅረጽ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።

የመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ በበኩላቸው ከማህበሩ 5 አላማዎች አንዱ ችግኝ ተከላ ነውና ትውልድ የሚያስቀጥሉ መምህራን ችግኝ ከመትከል ባለፈ የመንከባከብ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማሄ ቦዴ። አረንጓዴ አሻራ በአንጋፋው የአርባምንጭ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መጀመሩ እንዳስደሰታቸው ተናግረው ደቡብ ኢትዮጵያ በባህል የተጠበቁ ደኖች በመኖራቸው አረንጓዴ እንድትሆን አድርጓል ብለዋል።

የአረንጓዴ አሻራ በትምህርት ዘርፍ እንዲጀመር መደረጉ ተማሪዎችና መምህራን ችግኝ እንዲተክሉ በማነሳሳት ለአረንጓዴ ልማት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አቶ ማሄ ተናግረዋል ።

የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ እሸቱ እልቶ በበኩላቸው የአረንጓዴ አሻራ ሲጀመር ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም የመጀመሪያዋ ችግኝ በክቡር የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ከተቸከለች ጀምሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በጋሞ ዞን ከተተከሉ ችግኞች ውስጥ 86 በመቶ መጽደቁን ተናግረዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ የተለያዩ ችግኞች የከተማው ህዝብ በመትከሉ አርባምንጭ የበረሃ ገነት ሆናለች ብለዋል።

የትምህርት ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ ቀንን በአርባምንጭ ከተማ ለማስጀመር ውቢቷን አርባምንጭ ከተማ ለመረጡ የትምህርቱ ዘርፍ አመራሮች አንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

Address

Arba Mintch
NO

Telephone

+251468814075

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አርባምንጭ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት Arbaminch City Education Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category