ካምባ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2006 ዓ.ም

ካምባ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2006  ዓ.ም

Share

ካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Photos from ካምባ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2006  ዓ.ም's post 06/06/2026

ተሳታፊዎች የሰርቲፊኬትና የዕውቅና መርሃ ግብር እና #የምርምር እና #ቴክኖሎጂ ውድድር ማጠቃለያ ተካሄደ

ካምባ፣ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም. (ካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)

በካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮምፒውተር የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስደው በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች እና በአክሽን ሪሰርች (Action Research) ሥራዎች የተሳተፉ ባለሙያዎች የሰርቲፊኬትና የዕውቅና ሽልማት መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የካምባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ለተመራቂዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል። በንግግራቸውም እንደ ካምባ ምርጫ ክልል 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላምና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ የሁሉም አካላት ትብብር ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰልጣኞቹም ከዕለታዊ ኃላፊነቶቻቸው ጋር በማስተባበር ለስልጠናው ቅድሚያ በመስጠት ወደ ስኬት መድረሳቸው የሚያስመሰግን መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም፣ “ #ተቋማትንና #ማኅበረሰቡን #ለማገልገል #ያስችላል። ዛሬ ለሰርቲፊኬት በመብቃታችሁ ።” ብለዋል።

በሌላ በኩል አቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኮሌጁ በማታ መርሃ ግብር ለሦስት ወራት የቆየ የኮምፒውተር ስልጠና መስጠቱን ገልጸው፣ ከመደበኛ ትምህርቱ በተጨማሪም አሰልጣኞች በሥራ ቦታቸው ያጋጠሟቸውን ችግሮች ለመፍታት የሚያግዙ የአክሽን ሪሰርች ጥናቶችን በማካሄድ ለዕውቅና መብቃታቸውን አስረድተዋል።

የሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ አቶ #ተበጀ #ተለማ በበኩላቸው፣ ይህ ስልጠና ቀጣይነት ያለው መሆኑን በመግለጽ፤ ስልጠናውን ያልወሰዱ አካላት የኮሌጁ በር ክፍት መሆኑን አስታውቀዋል። አክለውም ፤ “ዘመኑ የሚጠይቀው #ዲጂታል መሆንን ነው፤ ስለዚህ እንላመድ፣ #እንሰልጥን፣ ፣ ” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ኢንዱስትሪ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በሰጡት አስተያየት፣ የተሰራው ቴክኖሎጂ የማህበረሰብ ችግር ከመፍታት አኳያ ላቅ ያለ ድርሻ ያለው በመሆኑ ባለሙያዎች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እንዳለባቸው ሀሳብ ሰጥተዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በዘመናዊ የኮምፒውተር ክህሎቶች፣ በመረጃ አያያዝ እና በቢሮ አፕሊኬሽኖች ላይ ተግባራዊ እውቀት ማግኘታቸው ተገልጿል። በስልጠናው በድምሩ 98 ሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን፣ በመርሃ ግብሩ ላይ አስተያየት የሰጡ ሰልጣኞች ስልጠናው በሙያቸውና በዕለታዊ የሥራ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዳመጣላቸው ገልጸዋል። “ከዚህ በፊት ብዙ የቢሮ ሥራዎችን በእጅ እንሠራ ነበር። አሁን ግን ኮምፒውተርን በብቃት በመጠቀም ሥራዎቻችንን በፍጥነትና በጥራት ማከናወን ችለናል። ስልጠናው የነበረው ተግባራዊ አቀራረብ ለሥራ ቦታችን በቀጥታ የሚጠቅም እውቀት እንድናገኝ አስችሎናል። ወደፊትም ተጨማሪ ስልጠናዎች ቢዘጋጁ በደስታ እንሳተፋለን።” ብለዋል።

በመጨረሻም ኮሌጁ የጀመረውን የአጭር ጊዜ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና ፕሮግራም በስፋት እንደምቀጥል ያስታወቀ ሲሆን፣ ፣ እንደዚህ ዓይነት ስልጠናዎች የሰው ኃይል ብቃትን በማሳደግ ለተቋማት ውጤታማነትና ለአካባቢው ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የካምባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ይስሐቅ ዮሐንስ፣ አቶ ግዳጀ ግምቴ የካምባ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን፣ አቶ ተበጀ ተለማ የኮሌጁ ምክትል ዲንና የሥልጠና ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ ማርቆስ ምልፆ የኮሌጁ ምክትል ዲንና የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ፣ እንዲሁም የኮሌጁ ኢንስትራክተሮችና ተመራቂ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

ካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

#ካምባ
Bezabih Gebeyehu
Yisahak Yohannes
Teka Wude
Tsehay Bekele
Lissanework Kassaye Eka
Enku Yohannes
Tebeje Telema
Markos Milko Mitsa

Photos from ካምባ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2006  ዓ.ም's post 12/05/2026

ለኢንስትራክተር ደስታ ዳታና የተደረገ የጋራ መታሰቢያ

በቀድሞ የሥራ ባልደረባችን ኢንጂነር ደስታ ዳታና ህልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን መግለጻችን ይታወሳል። ዛሬ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም የኢንስትራክተሩ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በቦዲት ከተማ መፈጸሙን ተከትሎ፣ የካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብና መላው ሠራተኞች ከቀኑ 9:00 - 11:00 ሰዓት ድረስ በጋራ በመሆን የባልደረባችንን መልካም የሥራ ዘመንና አርአያነት ስናስብ ውለናል።

ኢንስትራክተር ደስታ በኮሌጃችን በነበራቸው የቆይታ ዘመን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ያለንን ክብር እየገለጽን፣ በድጋሚ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

የካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሠራተኞች

Photos from ካምባ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2006  ዓ.ም's post 11/05/2026

የሀዘን መግለጫ

የኮሌጃችን የቀድሞ ባልደረባ፣ የሙያ ጓደኛችንና ብርቱው መሐንዲስ ኢንስትራክተር ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ስንሰማ በካምባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ ዘንድ ጥልቅና መራራ ሀዘን ተሰምቶናል።

#በኮሌጃችን ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የቢ ደረጃ (B-Level) ኢንስትራክተር በመሆን በታማኝነትና በታታሪነት ሲያገለግሉ የቆዩት የሥራ ባልደረባችን ኢንጂነር ደስታ ዳታ በተቀጠሩበት የሥራ መስክ ለኮሌጃችን ዕድገትና ለተማሪዎቻችን ስኬት ጉልህ አሻራቸውን ያሳረፉ ብርቱ ሰው ነበሩ።

ኢንስትራክተር ደስታ በኮሌጃችን በነበራቸው የሥራ ቆይታ የነበራቸውን የሙያ ፍቅርና ለተሻለ ዕውቀት የነበራቸውን ጉጉት በተግባር ያሳዩ፣ በኢትዮጵያ ቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ (Masters) ትምህርታቸውን አጠናቅቀው ለላቀ አገልግሎት ራሳቸውን ያዘጋጁ ምሁር ነበሩ። ከካምባ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኋላም ወደ ብጠና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ በመቀጠልም በቦዲት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሙያቸው ሲያገለግሉ ቆይተው፣ ባደረባቸው ህመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ሀዘን ነው።

ኢንስትራክተር ደስታ ዳታ በሥራቸው ታታሪ፣ ከሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በቅንነትና በትህትና የተሞላ፣ ለተቋማቸውና ለሙያቸው ታማኝ የነበሩ የሥራ ሰው በመሆናቸው በቆይታቸው ሁሉ መልካም ስም ትተው አልፈዋል።

#እኛ የካምባ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ በሥራ ባልደረባችን ህልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን፤ ፣ #ለልጆቻቸው፣ ፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሲያገለግሉበት ለነበረው #ሠራተኞችና #ሠልጣኞች በሙሉ ፈጣሪ #መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።
የኢንስትራክተር ደስታ ዳታና የሥራ ታታሪነታቸዉ በልባችን ሲታወስ ይኖራል።

ፈጣሪ ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ!

የካምባ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

01/05/2026

KAMBA POLY TECHNIC COLLEGE

01/05/2026

ለሆናችሁ የሥራ ጀግኖች በሙሉ!
(ሜይ ዴይ) በሰላም አደረሳችሁ!

ዛሬ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (May 1, 2026) በመላው ዓለም እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ የሰራተኞች ቀን በታሰበበት በዚህ ዕለት፤ ለሀገር እድገት ዋጋ ለምትከፍሉ የሥራ ጀግኖች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

የኢትዮጵያ መሠረቱ በሠራተኛው ብርቱ ትጋት፣ ጥረትና ጽናት ላይ የተመሰረተ ነው። ዛሬ በየዘርፉ የሚመዘገቡ ስኬቶች የሀገራችን ዋልታና ማገር የሆኑ የሠራተኞች እውቀት፣ ክህሎትና ጽናት ድምር ውጤቶች ናቸው።

ውድ #ኢንስትራክተሮች እና ፤

ኮሌጃችን በ #መደበኛ እና (Short-term) ስልጠናዎች እንዲሁም በ ሂደት ጥራቱን የጠበቀ ውጤት እንዲያመጣ የምታሳዩት ትጋት ለተቋማችን ኩራት ነው።

“ ፤ ለኢንዱስትሪ ሰላምና ለምርታማነት መሠረት ነው”

የሚለው የዘንድሮው መሪ ቃል የኮሌጃችንም ቁልፍ አጀንዳ ነው። የእናንተ ደህንነት፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና ሰብዓዊ ክብር ሲጠበቅ ለፈጠራና ለላቀ ጥራት ያላችሁ ተነሳሽነት እንደሚጨምር እናምናለን።

በቀጣይ የስራ ዘመናችሁ ሁሉ ውጤታማ እንድትሆኑ፣ የምታፈሩት ለሀገራችን ብልጽግና ትልቅ አቅም እንዲሆን መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።

በተጨማሪም ከኮሌጃችን ውጭ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ ተሰማርታችሁ ለሀገር ዋጋ ለምትከፍሉ፦
በ ህይወት ለምታተርፉ፤
በ እና በሰላም ጥበቃ ላይ ለምትተጉ፤
በ ትውልድን በመቅረጽ ላይ ላላችሁ፤
በ #ኢንዱስትሪ፣ በ #ግብርና እና በሌሎችም የሙያ ዘርፎች ለምትለፉ ባለሙያዎች በሙሉ፤

እንኳን ለዓለም አቀፉ የሠራተኞች ቀን አደረሳችሁ!
! ✊🛠️📖

#የሰራተኞችቀን #ቴክኖሎጂሽግግር #ምርታማነት #ኢትዮጵያ #ካምባ

11/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን፡- የካምባ ከተማ አስ/ር ከንቲባ አቶ ተካ ውዴ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ ለጌታችንና ለመድሃንታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን እላለሁ።

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የመተሳሰብና የመቻቻል እንዲሆንልን እመኛለሁ።

እግዚአብሔር አምላክ በውድ ልጁም እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችንና በኃጢአታችን ሙታን የነበረንን ዓለም ሳይፈጠር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መርጦ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ በመካከላችን ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው አፍርሶ ከክርስቶስ ጋር ህይወት ሰጠን።

እርሱ ስለ በደላችን ቆሰለ፣ ስለ መተላለፋችንም ደቀቀ በመስቀል ላይም ሞቴ፣ ሞትንም ድል አድርጎ ተነሳ።

የትንሳኤ በዓል ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጨለማን በብርሃን ያሸነፈበትና ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ለእኛ ለሰው ልጆች አዲስ ተስፋ ተምሳሌት እንደመሆኑ የማይታለፉ የሚመስሉናተስፋ የሚያስቆርጡ በውስጣዊና በውጫዊ ጫና የተፈጠሩ አሁናዊ ፈተናዎችን በድል ማለፍ እንደሚቻል አመላካች ነው።

የትንሳኤ በዓልን ስናከብር ክርስቶስ በመስቀሉ ያሳየውን ፍቅር እያስታወስን ከክፋትና ከተንኮል ይልቅ ትህትናን በመላበስ በመተሳሰብና እርስ በርሳችን በመጠያየቅ ለተቸገሩ ወገኖች ካለን ነገር በማካፈልና የተገኘውን በጋራ በመቋደስ ፍቅራችንን እየገለጽን ልናሳልፈው ይገባል።

በሌላ በኩል በዓሉ ሀይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ ተከብሮ እንድጠናቀቅ መላው የከተማችን ማህበረሰብ ከጸጥታው ጎን በመሆን የተለመደውን ትብብር አጠናክሮ ልቀጥል ይገባል።

በዲጋሚ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የመቻቻል፣ የአብሮነትና የወንድማማችነት እንዲሆንልን እመኛለሁ።

አቶ ተካ ውዴ
የካምባ ከተማ አስ/ር ከንቲባ
ሚያዝያ 03/2018ዓ.ም

11/04/2026

‎መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፦ አቶ ይስሃቅ ዮሐንስ

‎​እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

‎ትንሣኤ የመሥዋዕትነት፣ የጽናት እና የተስፋ በዓል ነው።

‎ትንሣኤ ከጽናት በኋላ የሚገኝ ድል ነው። ከፊቱ የጅምላ ፍርድ አለው፤ ከፊቱ ውግዘት አለው፤ ከፊቱ ግርፋት አለው፤ ከፊቱ መራቆት አለው፤ ከፊቱ መከዳት አለው፤ ከፊቱ የፀሐይ መጨለም፣ የጨረቃ ደም መልበስ፣ የከዋክብትም መርገፍ አለው።

በዚህ ሁሉ ግን በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ክርስቶስ በጽናት ቆመ። ስለ ዓላማ ሲባል መከራን ታገሠ። ስለ ሰው ልጅ ሲባል ሁሉን እየቻለ በጽናት ተጓዘ።

‎ትንሣኤ ተስፋ ነው። ፈተናው እንደሚያልፍ ተስፋ ይሰጣል። ዓርብን ላየ እሑድ የሚመጣ አይመስልም ነበር። የመቃብሩን ድንጋይ ላየ የሚነሣ አይመስልም ነበር። ማኅተሙን ላየ የሚፈታ አይመስልም ነበር። ጨለማውን ላየ ብርሃን ሩቅ ይመስል ነበር። ሁሉም ግን ተገለበጠ። ታሪክን የታሪኩ ጌታ ለወጠው።

‎ተስፋችን በደጅ ነው። ዓርብ ላይ እሑድን እናየዋለን። ከሞት ባሻገር ሕይወትን፣ ከመቃብር አልፈንም ትንሣኤን የምንመለከት ነን። የሚጨበጥ ሕልም የጠራ ምናብ አለን። ስለዚህም ወጀብና አውሎ ነፋስ አያስደንቀንም። ዛሬ ለነገ፣ ሞት ለትንሣኤ ቦታ እንደሚለቁ የምናውቅም፣ የምናምንም ነን።

‎ በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ ያዘኑትን በማፅናናት፣ የታመሙትን በመጠየቅ እና ማዕዳችንን ለሌላቸው በማካፈል ሊሆን እንደሚገባ አደራ ለማለት እወዳለሁ።

‎ የመረዳዳትና የመተሳሰብ ባህላችንን አጠናክረን በመቀጠል የሁላችንም በዓል እንዲሆን እናድርግ እያልኩ፤ ላሳስብ እወዳለሁ።

‎ አቶ ይስሐቅ ዮሐንስ
‎ የከምባ ከተማ አስ/ር የመንግስት ዋና ተጠሪ
‎ሚያዝያ 2018 ዓ.ም

Photos from ካምባ ቴክንክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ 2006  ዓ.ም's post 10/03/2026

ከጋሞ ዞን አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

​በዞናችን በተለያዩ አካባቢዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት፣ በተለይም በደጋማ አካባቢዎች በተከሰተ የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ወገኖቻችን ህይወት በማለፉ የዞኑ አስተዳደር የተሰማውን መሪር ሀዘን ገልጿል ።

​በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የዞኑ ህዝብ መጽናናትን ይመኛል።

​አስተዳደሩ በአሁኑ ወቅት በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳትና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን፤ ህዝባችንም መሰል ተፈጥሯዊ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

Photos from የደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ  South Ethiopia bureau of Labor & Skills's post 06/03/2026
Want your school to be the top-listed School/college in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address


Arba Minch'