Arba Minch University Department of Statistics

Arba Minch University Department of Statistics Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arba Minch University Department of Statistics, Education Website, Arba Minch, Arba Minch'.

22/12/2022
25/08/2022

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ትምህርት ዘመን በመደበኛ ፕሮግራም ለተመረቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለተመረቁ ተማሪዎች ወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፣ ሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ በ2015 የትምህርት ዘመን ነፃ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ለ18 ተማሪዎች (AMIT 2፣ AWTI 2፣ CBE 2, CSSH 2, CMHS 2, CAS 2, CNS 2, School of Law 1, school of PBS 1, Sawula campus 2) አወዳደሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚትፈልጉ የ2014 ተመራቂ ተማሪዎች ( መስከረም 29/30 እና ሰኔ 25/26 2014 ዓ.ም የተመረቃችሁ) ከነሐሴ 18-27/2014 ዓ/ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት እንድትመዘገቡ እየገለጽን፡-

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-

1. ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶግራፍ
2. የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/
3. በተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት
4. የማመልከቻ ቦታ፡- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች
ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211
5. ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽበት
ከጳጌሜ1-3/2014 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 5/2015 ዓ.ም፤

ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡-

1. የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች፣ የማኅበራዊ ሳይንስ፣ የቢዝነስና
ኢኮኖሚክስ፣ የሕግ እና የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ተማሪዎች - ዋናው ግቢ
2. የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ነጭ ሳር ካምፓስ
3. የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ዓባያ ካምፓስ
4. የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ኩልፎ ካምፓስ
5. የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች - በሳዉላ ካምፓስ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

24/08/2022

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለፕሬዝደንትነት ውድድር የወጣ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ዩኒቨርሲቲውን በሚቀጥሉት 6 ዓመታት በፕሬዝደንትነት የሚመራውን ኃላፊ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የአመልካቾች ትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስትሬት) ከረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ጋር እና ከዚያ በላይ ሆኖ ከማመልከቻቸው ጋር ቀጥሎ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. Curriculum Vitae (CV)
2. የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት አንድ ፎቶ ኮፒ፤
3. የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ፤
4. በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ፤
5. በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ፤
6. በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ በዝርዝር ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡

ከላይ በተገለጸው መሠረት ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋናው ግቢ አስተዳደር ሕንጻ በቢሮ ቁጥር 209 በአካል ቀርባችሁ ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ [email protected] መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ

25/05/2022
ህዳር 30 2014 አ.ምአርባ ምንጭ--------------------------------------------------------------በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስታቲስቲክስ ትምህርት ክፍል ዉ...
09/12/2021

ህዳር 30 2014 አ.ም
አርባ ምንጭ
--------------------------------------------------------------
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስታቲስቲክስ ትምህርት ክፍል ዉስጥ የሚገኘው Statistical Consulting Service Center ከማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ሰራተኞች "Data Management and Analysis Using SPSS" በሚል ርዕስ የሁለተኛ ዙር ስልጠና ተሰጠ።
---------------------------------------------------------------

ህዳር 11 2014/ አርባ ምንጭበአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስታቲስቲክስ ትምህርት ክፍል ዉስጥ የሚገኘው የStatistical Consulting Service Center ከማህበረሰብ አገልግሎት ዳ...
20/11/2021

ህዳር 11 2014/ አርባ ምንጭ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የስታቲስቲክስ ትምህርት ክፍል ዉስጥ የሚገኘው የStatistical Consulting Service Center ከማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ሰራተኞች "Data Management and Analysis Using SPSS" በሚል ርዕስ የመጀመርያ ዙር ስልጠና ተሰጠ።

31/10/2021

በመቀሌ ፣ በአዲግራት፣በአክሱም ፣በራያና በወልድያ ዩኒቨርስቲዎች ስታስተምሩ ለነበራችሁ መምህራን በሙሉ ወደ ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ጊዜያዊ ምደባ ለመመደብ ያስችለን ዘንድ በሚከተለው ሊንክ ተጠቅማችሁ ከነገ ጀምሮ እስከ እሮብ 24/2/2014 ዓ.ም እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን።
https://forms.gle/uEmVwqqDFQ7dFk5dA

29/10/2021
25/10/2021

ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ነባር ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በሙሉ፡-

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ነባር ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 23-24/2014 ዓ/ም የሚካሄድ ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ጥቅምት 29/2014 ዓ/ም ይሆናል፡፡ በመሆኑም የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም ነባር ቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በየካምፓሶቻችሁ ሬጅስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በአካል ቀርባችሁ ምዝገባ እንድታካሂዱ እየገለጸ ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

05/10/2021
05/10/2021

Address

Arba Minch
Arba Minch'

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch University Department of Statistics posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Arba Minch University Department of Statistics:

Shortcuts

Share