Arba Minch University

Arba Minch University

Share

Arba Minch University was established by government proclamation (Council of Ministers 111/2004) Civil, Mechanical & Electrical Engineering.

ARBA MINCH UNIVERSITY PROFILE

AMU’s historical foundation dates back to late 1990s. Mandated to address water-related issues, the then Arba Minch Water Technology Institute (AWTI) was established in 1986. AWTI then used to offer short and long-term trainings, conducting research and rendering consultancy services in the water sector. In 1997, it got restructured as Arba Minch Technology Institute

Photos from Arba Minch University's post 11/06/2026

በግራንት ፕሮፖዛል አጻጻፍ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የፐብሊኬሽንና ግራንት ማኔጅመንት አስተዳደር፣ ለካምፓሱ መምህራን በግራንት ፕሮፖዛል አጻጻፍ (Grant Proposal Writing) ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከሰኔ 1 እስከ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ሰጠ።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ወንድወሰን ጆረኔ እንደገለጹት፤ መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው መምህራን ከአገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ የምርምር ፕሮጀክቶች ያላቸውን ተሞክሮ እንዲለዋወጡ ለማስቻል ነው። የግራንት ፕሮጀክቶችን ማዘጋጀትና የገንዘብ ድጋፍ (ፈንድ) ማፈላለግ ተቋማዊ ግዴታ ጭምር መሆኑን ዲኑ አብራርተዋል።

"ቴክኖሎጂዎች በፍጥነት እያደጉ ባለበት በዚህ ዘመን ራስን ማሻሻል ተፈላጊነትን ይጨምራል" ያሉት ዶ/ር ወንድወሰን፤ መምህራን ምርምሮችን እንደወትሮው ከማሳተም ባለፈ ያሉትን ዕድሎችና የልምድ ልውውጦች በመጠቀም ፕሮጀክቶችን ማምጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። በዚህም አገርን፣ ተቋምን፣ ማህበረሰብንና ራስን ተጠቃሚ በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን መትጋት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በአገሪቱ በምርምር ያልተዳሰሱ በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን የጠቆሙት ዲኑ፣ መምህራን ከስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ወደ ተግባር እንዲለውጡ በማሳሰብ መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የፐብሊኬሽንና ግራንት ማኔጅመንት አስተዳደር አስተባባሪ ዶ/ር ታዬ ታደሰ በበኩላቸው፣ ስልጠናው በርካታ ልምዶችን መቅሰም ያስቻለ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ስልጠናው ልዩ ትኩረት፣ ክትትልና ቀጣይነት እንዲኖረው እንደሚፈለግ የገለጹት ዶ/ር ታዬ፤ በቀጣይም ከአነስተኛ ድጋፍ በማሳደግ ወደ 'ግራንድ' (ታላላቅ) ፕሮጀክቶች መሸጋገር ይጠበቃል ብለዋል። የተሰሩ ምርምሮችን ወደ መሬት የማውረድ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፣ ስልጠናው በጋራ የመስራት ባህልን እንደሚያጎለብት አስረድተዋል።

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አሰልጣኝ ዶክተር መስፍን ጥላሁን፣ ያላቸውን ልምድ በማካፈላቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፤ የግራንት ፕሮፖዛል ሲዘጋጅ በዓለም ላይ ያሉ ዕድሎችን በማሳየት የሪሰርች አቅምን መገንባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በስልጠናውም ስኬታማ የግራንት ፕሮፖዛል መጻፊያ ቴክኒኮችንና ዘዴዎችን፣ የገንዘብ ድጋፍ ምንጮችን (Sources) እና ጥሪዎችን (Calls) የመለየት ስልቶችን፣ ፕሮፖዛል ሲጻፍ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎችና አወቃቀሮችን (Structures) እንዲሁም የምርምር ሃሳቦችን ከዓለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) ጋር አጣጥሞ የማቅረብ ጥበብን በስፋት ማብራራታቸውን አሰልጣኙ ጠቅሰዋል። መምህራን ያገኙትን ክህሎት ተጠቅመው መስራት ከቻሉ ለዩኒቨርሲቲውና ለምርምር ስራዎቻቸው ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት ትልቅ አጋዥ እንደሚሆንም አክለዋል።

የፔዳጎጂ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት የስልጠናው ተሳታፊ ዶ/ር ማቱሳላ ሆጃ በሰጡት አስተያየት፤ ስልጠናው የውጭ አገራትን በጀት ለምርምር እንዴት ማምጣት እንደሚቻልና የምርምር ንድፍ (Research Design) እንዴት ማዘጋጀት እንዳለብን አቅጣጫ አሳይቶናል ብለዋል። ያገኘነውን ልምድ ተጠቅመን የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታ ምርምር ለማድረግ አቅም አግኝተናል ሲሉም አክለዋል።

ሌላኛዋ ሰልጣኝ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህር መሰረት አሰፋ በበኩሏቸው፣ ስለ ምርምር አጻጻፍና የግራንት ፈንዶችን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ጥሩ ልምድ ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል። በተለይም ሴት መምህራን ምርምር ሲሰሩ ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ተለይተው የተዘጋጁ አሰራሮች እንዳሉ ስልጠናው በተጨባጭ እንዳሳወቃቸውና ተጨማሪ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

በመረሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ለስልጠናው ተሳታፊዎች የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ /Spring of Wisdom

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

11/06/2026

የሐዘን መግለጫ

አቶ ፍጹም እንዳለ ከአባታቸው ከአቶ እንዳለ ታፈሰና ከእናታቸው ከወ/ሮ አበባ ሰለሞን ሕዳር 11 ቀን 1984 ዓ.ም በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ተወለዱ፡፡

አቶ ፍጹም እንዳለ ከየካቲት 01 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመኪና ረዳት ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

አቶ ፍጹም እንዳለ በደረሰባቸው ድንገተኛ አደጋ በተወለዱ በ34 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ አቶ ፍጹም እንዳለ ባለትደርና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ፍጹም እንዳለ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፣ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ /Spring of Wisdom

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

11/06/2026

CALL FOR APPLICATIONS: SHORT COURSE TRAINING FOR PHD STUDENTS

Arba Minch University, in collaboration with the VLIR-UOS Institutional University Cooperation (AMU–IUC) project, is organizing a capacity-building training for PhD students who are doing their PhD in Ethiopian universities under the TISP7 project (Transversal institutional strengthening sub-project 7).

1. Training Overview
The training focuses on PhD research skills and gender-inclusive academic practices. It is scheduled to take place from July 27 to August 1, 2026, in a hybrid format.

The program brings together selected active PhD students from five Ethiopian universities:

• Arba Minch University (AMU)
• Wachamo University
• Hawassa University
• Wolaita S**o University
• Werabe University

2. Training Topics
The training will cover the following areas:
• Formulating the central research question in PhD studies
• Planning and time management in doctoral research (student–supervisor responsibilities)
• Gender and diversity-sensitive research approaches (theory and practice)
• Academic presentation skills (PPT and oral communication)
• Challenges in PhD writing
• Qualitative research: challenges and opportunities
• Quantitative research: challenges and opportunities
• Inclusive stakeholder engagement in PhD research

3. Trainers
The training will be delivered by distinguished professors from Belgian universities (including KU Leuven, university of Brussels and the University of Antwerp) as well as experienced Ethiopian academics.

4. Participant Selection
A total of 26 PhD candidates will be selected:
• Arba Minch University: 10 candidates (5 female, 5 male)
• Each of the other universities (Wachamo, Hawassa, Wolaita S**o, Werabe): 4 candidates each (2 female, 2 male)
Eligible applicants should be first- or second-year PhD students who are interested in participating in the training.

5. Application

Applicants are advised to refer to the following eligibility criteria for further details.

CRITERIA FOR ELIGIBILITY AND APPLICATION: PhD TRAINING ON GENDER INCLUSIVITY AND SUCCESSFUL PHD COMPLETION

1. Eligibility Criteria

Applicants must meet the following requirements:
• Must be a first-year or second-year PhD student in Ethiopian Universities.
Exception: If suitable female candidates are not available in this category, female university staff that have conducted research, published articles, and are preparing to begin PhD studies may be considered.
• Must be able to fully and voluntarily participate in the training scheduled from July 27 to August 1, 2026, held in an isolated setting in Arba Minch.
• Should demonstrate interest in gender inclusion, time management, and addressing challenges in PhD milestones.
• Priority will be given to applicants with professional experience in their respective fields.

2. Application Process

• Invitations will be issued through the university Academic Program Office and/or Postgraduate Office.
• Applicants must submit:
o A CV in EU format
o A short statement of interest outlining:
 Academic and professional background
 Work experience
 Motivation for attending the training
• Selection will ensure gender balance (50% female and 50% male participants).

3. Application Submission

Applications should be sent electronically to:
[email protected]

[email protected]

With a copy (CC) to:
[email protected]

4. Evaluation and Selection

•Applications will be reviewed by a committee jointly established by the Postgraduate School of Arba Minch University and the AMU–IUC Project, based on the stated selection criteria.
•Only selected candidates will be contacted via email.

5. Note

•The AMU–IUC project will cover accommodation, transport (Bus), and per diem costs for participants from Outside of Arba Minch University.

10/06/2026

Join us for a High-Level Scientific Seminar featuring Dr. Lawrence Banks, Director-General of ICGEB.

📅 16 June 2026 | ⏰ 8:30 AM – 12:00 PM
📍 Arba Minch University, Main Campus, New Hall

We look forward to welcoming researchers, faculty, students, and partners.

Photos from Arba Minch University's post 10/06/2026

በኤችአይቪ/ኤድስና በሥነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ላይ ያተኮረ ሥልጠናና በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የደም ምርመራ መርሐ ግብር ተካሄደ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲና ‹‹በራስ መተማመን ኤችአይቪ ፖዚቲቭ ወጣቶች›› ሀገር በቀል ልማት ማኅበር ትብብር ከኤችአይቪ/ኤድስና ከሥነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ተፅዕኖዎችን ለመቀነስና ለመከላከል ያለመ ሥልጠናና በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ የደም ምርመራ መርሐ ግብር ከግንቦት 24-30/2018 ዓ/ም ተከናውኗል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ሠናይት ሳህሌ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወጣት እንደመሆናቸው ለኤችአይቪ/ኤድስና ለሥነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ተናግረው በተለያዩ ሁኔታዎች እየጨመረ የመጣውን የወጣቶች ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲያስችልና ተማሪዎችም ራሳቸውን ዐውቀው ቀጣይ ሕይወታቸውን በጥንቃቄና በአግባቡ እንዲመሩ ለማስቻል ሥልጠናው ያግዛል ብለዋል፡፡

ሥልጠናና የኤችአይቪ/ኤድስ የደም ምርመራውን ከጋሞ ዞን የመጡ የሕክምና ባለሙያዎች ሰጥተዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - [https://www.amu.edu.et/](https://www.amu.edu.et/)
ቴሌግራም - [https://t.me/arbaminch_university](https://t.me/arbaminch_university)
ፌስቡክ - [https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/](https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/)
ዩቲዩብ [https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA](https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA)

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ /Spring of Wisdom

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Photos from Arba Minch University's post 09/06/2026

የዕጩ ዶ/ር ማሙሽ ተክሌ የPhD መመረቂያ ጽሑፍ ግምገማ (Public Defense) ተካሄደ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት (School of Graduate Studies)፣ በውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (Water Technology Institute) ስር በሚገኘው የሃይድሮሊክ እና ውኃ ሃብት ምህንድስና ፋኩልቲ (Faculty of Hydraulic and Water Resource Engineering) በሃይድሮሊክ ምህንድስና (Hydraulic Engineering) የባለሙያ ማደጊያ የዶክትሬት ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ዕጩ ዶ/ር ማሙሽ ተክለ አሰፋ የ3ኛ ዲግሪ (PhD) መመረቂያ ጽሑፍ ግምገማ (Public Defense) ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ተካሂዷል።

በዕለቱ የውስጥና የውጭ ገምጋሚዎች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በተካሄደው የምርምር ግምገማ (Public Defense) መድረክ ላይ፣ የዕጩ ዶክተሩ የምርምር ሥራ አስፈላጊውን የአካዳሚክ መስፈርት በሙሉ አሟልቶ በመገኘቱ በአማካሪና ገምጋሚ ቦርዱ ሙሉ ድምፅ ተቀባይነት አግኝቶ ጸድቋል።

የዕጩ ዶ/ር ማሙሽ ተክሌ አሰፋ የምርምር ጽሑፍ ”Modeling Climate and Land-Use Change Impacts on Hydrology and Sediment Yield, and Erosion Mitigation in the Kessem Watershed” በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን፣ የምርምር ሥራው በዶ/ር ቦጋለ ገብረማርያም ነካ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) እና በዶ/ር ኤልያስ ገበየሁ አየለ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ዋናና ረዳት አማካሪነት (Supervisor & Co-supervisor) የተመራ ነበር።

የዕጩ ዶ/ር ማሙሽ ተክሌ የምርምር ውጤት እና አጠቃላይ የትምህርት አፈጻጸም በቀጣይ ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ሲጸድቅ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በይፋ የሚያገኙ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - [https://www.amu.edu.et/](https://www.amu.edu.et/)
ቴሌግራም - [https://t.me/arbaminch_university](https://t.me/arbaminch_university)
ፌስቡክ - [https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/](https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/)
ዩቲዩብ [https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA](https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA)

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ /Spring of Wisdom

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

09/06/2026
Photos from Arba Minch University's post 09/06/2026

የዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ መለሰ የPhD መመረቂያ ጽሑፍ ግምገማ (Public Defense) ተካሄደ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት፣ በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (AMIT) ስር በሚገኘው የሲቪል ምህንድስና ፋኩልቲ በስትራክቸራል ምህንድስና (Structural Engineering) የጋራ የክትትል የዶክትሬት ፕሮግራም (Joint Supervision PhD Program) ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩት ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ መለሰ ዲቻ የ3ኛ ዲግሪ (PhD) መመረቂያ ጽሑፍ ግምገማ (Public Defense) ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ተካሂዷል።

በዕለቱ የውስጥና የውጭ ሀገር ገምጋሚዎች በተገኙበት በተካሄደው የምርምር ግምገማ (Public Defense) መድረክ ላይ፣ የዕጩ ዶክተሩ የምርምር ሥራ አስፈላጊውን የአካዳሚክ መስፈርት በሙሉ አሟልቶ በመገኘቱ በአማካሪና ገምጋሚ ቦርዱ ሙሉ ድምፅ ተቀባይነት አግኝቶ ጽድቋል።

የዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ መለሰ የምርምር ጽሑፍ ”Structural Performance of Reinforced Concrete Members Incorporating Banana Fiber and Diatomaceous Earth Slurry Treated Recycled Aggregate” በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን፣ የምርምር ሥራው በፕሮፌሰር ክሪሽናራጅ ራማውሳሚ (Dr. Krishnaraj Ramawsamy) እና በፕሮፌሰር ሳንዲፕ ቻውዳሪ (Dr. Sandeep Chaudhary) ዋናና ረዳት አማካሪነት የተመራ ነበር።

የዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ መለሰ የምርምር ውጤት እና አጠቃላይ የትምህርት አፈጻጸም በቀጣይ ለዩኒቨርሲቲው ሴኔት ቀርቦ ሲደቅቅ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በይፋ የሚያገኙ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityccd/
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የጥበብ ምንጭ /Spring of Wisdom

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Photos from Arba Minch University's post 09/06/2026

Internal Vacancy Announcement

Want your school to be the top-listed School/college in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


P. O. Box 21
Arba Minch'
00251