Arbaminch Polytechnic and Satellite Institute

Arbaminch Polytechnic and Satellite Institute

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Arbaminch Polytechnic and Satellite Institute, College & University, Arbaminch, Arba Minch'.

"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል ርዕስ የቴክኖሎጂ፣ ክህሎት እና ምርምር ውድድር በአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢኒስቲትዩት ተቋም 27/03/2025

"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል ርዕስ የቴክኖሎጂ፣ ክህሎት እና ምርምር ውድድር በአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳታላይት ኢኒስቲትዩት ተቋም ይህ ዜና በአርባምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳይንስ ተቋም (አርባምንጭ ፖሊቴክኒክ) የሚካሄደውን የቴክኖሎጂ፣ ክህሎት እና ምርምር ውድድርና ማሳያ (ኤግዚቢሽን) አፅንኦት የሚሰጥ ሲሆን፣ ውድድ...

Photos from Arbaminch Polytechnic and Satellite Institute's post 11/03/2025

በአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንሲትዩት ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የክህሎት፣የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ውድድር ተጠናቀቀ፡፡ አርባ ምንጭ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም

በአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳተላይት ኢንስቲትዩት (Arbaminch Polytechnic and Satellite Institute) ለሁለት ቀናት የቆየው የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና ተግባራዊ የጥናት እና ምርምር ውድድር ተካሄዷል። ይህ ውድድር መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም ተጠናቅቋል።

በውድድሩ ወቅት ተማሪዎች፣ መምህራን እና ተመራማሪዎች የተለያዩ የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት እና የምርምር ፕሮጀክቶችን አቅርበዋል። የውድድሩ ዋነኛ ዓላማ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ እና በሳይንሳዊ ምርምር ውስጥ ያላቸውን ችሎታ እና ፈጠራ ማሳየት፣ ተግባራዊ ችግሮችን መፍታት እና የኢትዮጵያን ልቀት በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስክ ማሳደግ ነው።

ውድድሩ ለሁለት ቀናት በመካሄድ ላይ የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ ተሳታፊዎች ፕሮጀክቶቻቸውን ለአስተያየት አቅርበዋል፣ እንዲሁም የተለያዩ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስራዎችን በማካፈል እርስ በርስ ዕውቀትን ለማስተዋወቅ ተችሏል። ውድድሩ በተሳካ ሁኔታ ከጨረሰ በኋላ፣ አሸናፊዎች ተለይተው ማበረታቻ ሽልማት እና ሰርቲፊኬት ከኮሌጁ ዲን አቶ በዛብህ በርዛ ተቀብለዋል ።

በአጠቃላይ፣ ይህ ውድድር በአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክ እና ሳተላይት ኢንስቲትዩት የቴክኖሎጂ እና የምርምር አቅም ለማሳደግ የሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ምሳሌ ነው። ይህ አይነት ውድድር በተማሪዎች መካከል የፈጠራ አስተሳሰብን ለማበረታታት እና በአገራችን ውስጥ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ልማትን ለማፋጠን አስተዋጽኦ ያበረክታል።

Photos from Arbaminch Polytechnic and Satellite Institute's post 25/01/2025

የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ተነሳሽነትን የተላበሰ እና ለሥራ ፈጠራ የተዘጋጀ የሰው ኃይል በመፍጠር የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ማፋጠን እንደሚቻል ተገለፀ ።
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባይነህ አበራ ተነሳሽነትን የተላበሰ እና ለሥራ ፈጠራ የተዘጋጀ የሰው ኃይል በመፍጠር የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ለማፋጠን የሙያ ቴክኒክ ስልጠና ኮሌጅ የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
አክለውም ያለንን የሰው ሀብት ምርታማ ለማድረግ ፣ የሥራና ክህሎት ስልጠናዎች ላይ በትኩረት ልሰራ እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህም አካታች ትምህርት ሥልጠና ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል።
ተቋሙ በጥንካሬ ያስመዘገባቸውን በማስቀጠል እና ድክመቶቹ ላይ የእርምት እርምጃ በመውሰድ በቀጣይ ለውጤታማነት መትጋት እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።
ወጣቱ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆን የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባልም ብለዋል
የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስቲትዩት ዲን አቶ በዛብህ በረዛ በበኩላቸው የቴክኒክና ሙያ አዲሱን ኢንተርፕርነር እሳቤ መሠረት በማድረግ በሀገር ደረጃም ቀድሞ ከተቋቋሙ ተቋማት አንዱ እንደመሆኑ በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ በመልካም ተሞክሮ ልምድ እያጋራ በዘርፍ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መቆየቱን ተናግረዋል።
ተቋሙ ከተያዘለት ስራ ማስኬጃ በጀት 65 በመቶውን ለስልጠና እንደሚውል እና በሁሉም ዲፓርትመንት ደረጃ ተቋማዊ ምዘና 85 በመቶ ውጤታማ መሆኑንም በሪፖርታቸው አመላክተዋል

Photos from Arbaminch Polytechnic and Satellite Institute's post 24/08/2024

ዛሬ ማለትም ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም ለ መላው የቴክኒክና ሙያ አሰልልጣኝ መምህራን ከ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጥ ስልጠና መንግስት ያዘጋጀ በመሆኑ ትግበራውን በተመለከተ በስልጠናው ላይ አስተባባሪ እንዲሆኑ የተመረጡ አካላት በ አርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳታላይት ኢንስትቲዩት ዋና ዲን አቶ በዛብህ ባርዛ ቢሮ በመገኘት ከ አዘጋጅ አካላት ጋር በ online በይነመረብ (Video Conferencing) ውይይት አድርገዋል።

በመሆኑም አሰልጣኝ መምህራን በተዘጋጁ ዩኒቨርሲቲዎች ምድባቸውን በማወቅ ከ ነሀሴ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 3/2016 ዓ.ም ድረስ በስልጠና እንደሚቆዩ ተገልጿል። ስለዚህ ሁሉም የአርባ ምንጭ ፖሊቴክኒክና ሳታላይት ኢንስትቲዩት አሰልጣኝ መምህራን በአጠቃላይ ከወዲሁ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላና ብርድልብስ በመያዝ ለመገኘት ዝግጅት እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

Photos from የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia's post 18/05/2023
12/06/2022

Levels and their respective qualifications in the EtQF structure.

Want your school to be the top-listed School/college in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Arbaminch
Arba Minch'