11/02/2022
Arba Minch University Students Union
Arba Minch University Students' Union Official Page
11/02/2022
26/09/2020
ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የክርስትና እምነት ተከታይ ተማሪዎችና የማህበረሰብ አካላት እንዲሁም ለአርባ ምንጭ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለደመራና ለመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ዮ ማስቃላ!!
#የአ/ም/ዩ ተ/ህብረት ጽ/ቤት
👇👇👇
https://t.me/amuSUinfo
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን መቀበል ከመጀመራቸው በፊት የተቋማቱ ዝግጁነት እንደሚረጋገጥ ተገለጸ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ መጀመሪያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መልሶ የመክፈት ሂደትና ዝግጅት በሚል ርዕስ ምክረኃሳብ አቅርበዋል፡፡
በ2012 ዓ.ም የተቋረጠዉን ትምህርት በልዩ ዕቅድ ለማጠናቀቅ በሚሰሩ ስራዎችና ትምህርት ሲጀመር ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች እንዲሁም ቀደም ተብለው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ምን መምሰል እንዳለባቸው በምክረሃሳባቸው ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በጉባኤው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መች እንክፈት ለሚለው ትክክለኛ መልስ እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ በዓለም የጤና ድርጅት መለኪያ መስፈርት መሰረት ደረጃውን ጠብቆ በተዘጋጀ ዝርዝር በጥልቀት የዝግጅት መጠኑ ተፈትሾ ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው ብለዋል፡፡ በዚያ መሰረት የተቋማት ዝግጅት ይፈተሻል። በዳሰሳውም መሰረት መቀበል እንደሚችሉ ፍቃድ ይሰጣል ሲሉ አብራርተዋል፡፡
ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንደገለፁት ቅድሚያ ለተመራቂዎች በመስጠት ተማሪዎችን በመከፋፈል በትንሽ ቁጥር ይጀመራል፡፡ ይህም ከሚታዩ ነገሮች እየተማርን የተማሪ ቁጥር ለመጨመር እድል ይሰጠናል ብለዋል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በምን እንደሚመራ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመሆን ፕሮቶኮል ይዘጋጃልም ብለዋል፡፡
ዩኒቨርስቲዎች የለይቶ ማቆያ ማዕከላት እንደመሆናቸው የክልል መንግስታት ስራ ይጠበቅባቸዋል። አማራጭ የኳረንቲን ቦታዎችን ማዘጋጀትም ግድ ስለሚላቸው እዚያ ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
ተማሪዎችን በማጓጓዝ ሂደት ችግር እንዳያጋጥም ከትራንስፖርት ሚኒስቴርና ጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር እንሰራበታለን ብለዋል፡፡
ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል የሚያስችል እቅድ ካሁኑ አዘጋጅተው ከአስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን ጋር በመወያየት የጋራ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ የበፊቱን አሰራር ይዘን መቀጠል አንችልም፡፡ ዝግጅታችንን ተጋላጭነታችንን አውቀን ተማሪ እንቀበላለን። አንድ ብሎክ ወይም አንድ ካምፓስ ኮቪድ 19 ቢያጋጥም ምን እናደርጋለን ከሚለው ጀምሮ በዝርዝር መስራት እና እያንዳንዱ እቅድ ያለተማሪዎች እገዛ ተፈፃሚ ስለማይሆን ወደነሱ ለማስረፅ መስራት የግድ ይለናል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንዳሉት ጊዜው የተማሪዎች ህብረት ኃላፊነት የሚፈተንበት ነው። የተማሪዎች ህብረት አባላት የመፍትሄ ኃሳብ ሆናችሁ ለተፈፃሚነቱ ከዩኒቨርስቲያችሁ ጋር በትብብር እንድትሰሩ ከእናንተ ይጠበቃል፡፡ ሰላማችሁን ማስጠበቅና ለደህንነታችሁ ዘብ መቆም ለትምህርታችሁ ቀጣይነት ዋስትና ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎች መከፈታቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ተመልሰው እንዳይዘጉም ጭምር የተማሪዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን አስመልክቶም የትኞቹ በዩኒቨርስቲዎች ይቅረቡ የትኞቹ በተማሪዎች ይሟሉ የሚለውን ከተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ውይይቱ ተቋማት የት ላይ እንደሆኑ ለይተን ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ ለመያዝ ታስቦ የተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪዎች በአሁኑ ጊዜ ቁርጠኝነት የሚፈልግ የለውጥ ስራ እየሰራን እንደሆነ መገንዘብ እና በዛው መጠን መፍጠን ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡ ተማሪዎችን ወደትምህርት የመመለስ ሂደት ባለድርሻ አካላትን በተገቢው መንገድ የማቀናጀት ኃላፊነት ተወስዶ መሰራት ያለበት ጉዳይ ነውም ብለዋል፡፡
ተማሪዎችን ከመመለስና የኮቪድ 19 ለይቶ ማቆያ ቦታዎችን ከማዘጋጀት አንፃር የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስታት እያንዳንዱ የራሱን ኃላፊነት ወስዶ እንዲሰራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ እንደከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፋዊና አገራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ ምርምር ላይ የተገኘውን እውቀት ተጠቅመን ለአገር የሚውል አድርገን መጠቀምም ይገባናል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ስራውን በማስፈፀም ሂደት ኃላፊዎች የኮሙኒኬሽን ክፍተት እንዳይኖር በመነጋገር ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመው አመራር የሁሉ ነገር ቁልፍ እንደመሆኑ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ነገ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል የተባለ ሲሆን ከዚያም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቋማቱን ለመክፈት ያበቃሉ ተብለው የተቀመጡ ዝርዝሮችን በመያዝ በዩቨርስቲዎች በመገኘት ብቁ መሆን አለመሆናቸው ታይቶ አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ ብቻ እንዲከፍቱ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ወደኃላ የቀራችሁ ዩኒቨርስቲዎች ካላችሁ ፈጥናችሁ ዝግጅታችሁን አጠናቅቁ ብለው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ጉዳዩንም እንደፕሮጀክት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለባቸው አስበዋል፡፡
ከተሳታፊዎች የተለያዩ ስጋት ናቸው ተብለው የተነሱ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ለመፍታት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
መልካም ዜና
የጤና ሚኒስቴር የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ
********************************
የጤና ሚኒስቴር ዓለምአቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር እንደየአከባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረ ሀሳብ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አቅርበዋል።
ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ግን እነዚህን መስፈርቶች በአግባቡ መከናወናቸው የሚያረጋግጥ ግብረ ኃይል በየትምህርት ቤቶቹ ሊቋቋም ይገባል ብለዋል ሚኒስትሯ።
የሰዎችን ቁጥር በመመጠን እና የኮቪድ -19 መከላከያ መስፈርቶችን በመተግበር ስብሰባ፣ ሲኒማ፣ ቲያትር፣ የስፖርት ዝግጅቶች፣ ማህበራዊና ሐይማኖታዊ በዓላት፣ የአደባባይ በዓላት፣ ሊፈቀዱ እንደሚገባም የጤና ሚኒስቴር ምክረ ሀሳቡን አስቀምጧል።
የጤና ሚኒስቴር በማንኛውም ሁኔታ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ በመላ ሀገሪቱ አስገዳጅ ሊሆን ይገባል ብሏል፡፡
16/09/2020
ለአምዩ ተማሪዎች፡ የማኔጅመንትና የአስተዳደር ሰራተኞች፡ መምህራን፡ እንዲሁም ለ40ምንጭ ቤተሰቦች ሁሉ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ!
#መልካም አዲስ ዓመት!
AMU-SU wishes ahappy NEW YEAR 2013 to all AMU students, Managements & administrative staffs, instructors and to family of ArbaMinch.
New Year!🌼እንቁጣጣሽ🌼
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the school
Website
Address
Arba Minch
Arba Minch'