Visit Konta

Directions Website

Visit Konta Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Visit Konta, College & University, Konta, Ameya.

አቶ ተመስገን ደጀኔ በኮንታ ዞን የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በመሆን ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።
15/10/2026

አቶ ተመስገን ደጀኔ በኮንታ ዞን የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በመሆን ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

አቶ ወንድማገኝ ኡቴ በኮንታ ዞን የአመያ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።
15/10/2026

አቶ ወንድማገኝ ኡቴ በኮንታ ዞን የአመያ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

የቀድሞ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ለአዲሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የስራ ርክክብ አደረጉ።የኮንታ ዞን ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ባደረገው 4ኛ የሥራ ዘመን 1...
13/10/2026

የቀድሞ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ለአዲሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የስራ ርክክብ አደረጉ።

የኮንታ ዞን ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ባደረገው 4ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የተለያዩ የአመራር ሹመት ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን በዚህም ሂደት የስልጣን ሽግግር ያደረጉት የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ለአዲሱ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ በዛሬው ዕለት የስራ ርክክብ አድርገዋል።

አመራሮቹ ቀጣይ ትኩረት በሚፈልጉ ዞናዊ ጉዳዮች ላይም ምክክር ያደረጉ ሲሆን የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ- ወደ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የባህል ቱሪዝም ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ታውቋል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
‎

የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የዞኑን እምቅ አቅም በመጠቀም የመላው ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ገለፁ።የኮንታ ዞን ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ...
12/10/2026

የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የዞኑን እምቅ አቅም በመጠቀም የመላው ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ገለፁ።

የኮንታ ዞን ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አሰቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ በም/ቤቱ ፊት ንግግር ያደረጉ ሲሆን በዞኑ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

ዞኑ ከተደራጀ ወዲህ በተሰጠው ትኩረት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ የመጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው በቀጣይም በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት በኢንቨስትመንት፣ በገቢና መሠል ዘርፎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

በተለይም በመሰረተ ልማት፣ በተቋማት ግንባታ፣ በህዝብ አገልግሎት እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ድሎች ልብን የሚያሞቁ፣ ተስፋን የሚጭሩ፣ ወኔን የሚፈጥሩና ለቀጣይ ጉዞ መሠረት የሚጥሉ ናቸው ያሉት አቶ ገዛኸኝ ሆኖም ዛሬም የህዝባችን አዳጊ ፍላጎቶች በሁሉም መስክ ከፍተኛ ስራ የሚጠይቁ ናቸው ሲሉም ተናግረዋል።

በቀጣይም ከላይ ከተጠቀሱ ትኩረት አቅጣጫዎች ባለፈ የሰዉ ኃይል እዉቀትን፣ ክህሎትን፣ ጉልበትንና ምርትን በማሳደግ የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ፣ የተፈጥሮ ሀብት ለኢኮኖሚ እድገት ያለዉን ሚና ማሳደግ፣ ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ሴክተሮችን ማነቃቃት፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የበለጠ የሚተኮርባቸው ዘርፎች መሆናቸውንም አብራርተዋል።

ለዚህም አመራር አካላት ሕዝብን ለማገልገል፣ ለውጥን ለመምራት፣ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከርና ልማት ለማምጣት መትጋትና የህዝብ አንገብጋቢ ችግሮች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው መላው የህብረተሰብ ክፍሎች ከትችት ይልቅ ማገዝን፣ ከመጥላላት ይልቅ መደጋገፍን፣ ከመራራቅ ይልቅ መቀራረብን፣ ከመነጣጠል ይበልጥ አንድነትን፣ ትብብርንና የውስጥ አንድነትን በማጠናከር አካባቢያችንን ወደተሻለ የእድገት ደረጃ እናሸጋግር ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዜና ሹመት!ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው ዕለት የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሹመት የሰጡ ሲሆን፣በዚህም መሠረት፥1.አቶ ኤልያስ ሚናሴ -...
12/10/2026

ዜና ሹመት!
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዛሬው ዕለት የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ሹመት የሰጡ ሲሆን፣

በዚህም መሠረት፥
1.አቶ ኤልያስ ሚናሴ - የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣
2.አቶ ቀበሌ መንገሻ - የኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር፣
3.ወ/ሮ ውዳለም ፍቃዱ - የመንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣
4.ኢንጅነር አብዲዩ መኮንን - የመስኖ ልማት ተቋማት ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር፣
5.አቶ አማኑኤል አለሙ - የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣
6.ዶክተር ለማ መሰለ - አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር፣
7.ወ/ሮ ዬሺሀረግ ደበበ - የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣
8.አቶ ቆጭቶ ማሞ - ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር፣
9.ዶ/ር ዐቢይ አንደሞ - የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር፣
10. ኢንጅነር ተዎድሮስ ተክሌ - የኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ባለስልጣን
11. አቶ ወሰን ጨምሶ - ጤናና ጤና ነክ አገልግሎትና ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣
12. አቶ አስራት መኩሪያ - ቡና ሻይ ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣
13. አቶ ግዛው ጋጊያቢ - ማዕድን ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር፣
14. ዶ/ር ጌታቸው ወሊያብ - ማዕድንና ኢነርጂ ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር፣
15. አቶ ታደሰ አይበራ - ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የስልጠና አውታሮች ማስተባበሪያ ምክትል ኮሚሽነር፣
16. አቶ ታሪኩ ታረቀኝ- ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ሀላፊ ምክትል ኮሚሽነር፣
17. ኢንጅነር ዩሐንስ ዋዳ - ማዕድንና ኢነርጂ ኤጄንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የማዕድን ጥናት ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ፣
18. አቶ ወንዱ ታደሰ - የኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣
19 ም/ኮማንደር አስናቀ ሀብቴ - ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር፣
20 ም/ኮማንደር ታከለ ታደሰ - ፖሊስ ኮሚሽንጨየወንጀልና ትራፊክ ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር፣
21 አቶ በላይ አየለ - መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የግብአት አቅርቦትና ንብረት አስተዳደርስራ ዘርፍ ኃላፊ፣
22.አቶ ጌታቸው አቱሞ - መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና ዲዛይንና ኮንትራት አስተዳደር (ሪጉላቶሪ) ስራ ዘርፍ ኃላፊ፣
23 ኢንጅ እሸቱ ኦሞሼ - መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የመንገድ ግንባታና ጥገና(ኦፕሬሽን) ስራ ዘርፍ ኃላፊ፣
24 አቶ አፈወርቅ አለሙ - መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክሬክተርና የግንባታ ክትትልና ኮንትራት አስተዳደርዘርፍ ኃላፊ፣
25 አቶ በላይ ኮጃብ - ቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ባለስለጣን የቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ልማትና ጥበቃ ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር፣
26 አቶ መብራቱ መርክነ - አደጋ ስጋት ስራ አመራር የአደጋ ስጋት ምላሽ የፈንድ አስጸዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ፣
27. አቶ መቱ አኮ - አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር፣
28 ኢ/ር ሰብሌ ወዳጆ - የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር፣
29 አቶ አዛሪያስ አየለ -ማዕድን ኮርፖሬሽን የማዕድን ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር፣
30 አቶ አማኑኤል አሰፋ -ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ሥራ አስፈጻሚ፣
31 አቶ አክልሉ ስምኦን - ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ፣
32 አቶ ተዘራ ሽጉጤ- ደቡብ ምዕራብ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ፣
33 ኢ/ር አያለዉ አደሎ - ደቡብ ምዕራብ የግንባታ ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚ፣
34 አቶ ዳዊት ደስታ - ደቡብ ምዕራብ ምርጥ ዘር ድርጅት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ፣
35 ዶ/ር ካሳሁን ወዳጆ - ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ምክትል ስራ አስኪያጅ
36 አቶ አክልሉ ሀይሌ - የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን በምክትል ቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደርባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር፣
37 አቶ አስራት አዳሮ - የመሶብ አንድ የአንድ ማዕከል አገልግሎትበምክትል ቢሮ ላፊ ማዕረግ የመሶብ አንድ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር፣
38 አቶ አህመዲን አወል - የመሶብ አንድ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በምክትል ቢሮ ላፊ ማዕረግ የመሶብ አንድ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር በመሆን ተሹመዋል።

የኮንታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ካቢኔ አካላት ሹመት አፅድቋል።በዚህ መሠረት:-1. አቶ ወንድማገኝ ወጁ - የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ፣2. አቶ እስራኤል ጮንቄ...
12/10/2026

የኮንታ ዞን ምክር ቤት 4ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ካቢኔ አካላት ሹመት አፅድቋል።

በዚህ መሠረት:-

1. አቶ ወንድማገኝ ወጁ - የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ፣

2. አቶ እስራኤል ጮንቄ - የሰላም ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ፣

3. አቶ አምባዬ አባቴ - ፋይናንስና ኢኮኖሚ መምሪያ ኃላፊ፣

4.አቶ ይስሐቅ ደሳለኝ - ኢንዳስትሪና ኢኖቬሽን መምሪያ ኃላፊ፣

5. አቶ አበበ ደምሴ - የባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ፣

6. አቶ ጣልአርገው መኮንን - የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ፣

7. አቶ ግርማ ይልማ- የውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ፣

8.ወ/ሮ ድንቅሽ በፍቃዱ- የሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ፣

9. አቶ ኢዮብ ስለሺ- ፐብሊክ ሰ/ስ/ሰ/ሀ/ል/ መምሪያ ኃላፊ፣

10. አቶ ታሪኩ ኬሃሞ- የጤና መምሪያ ኃላፊ፣

11. ወ/ሮ ጤናዬ አወል- ከተማ ልማትና ኮ/ሽን መምሪያ ኃላፊ፣

12. አቶ ማስረሻ ሀደሮ- ንግድና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ፣

13. አቶ አጥናፉ አበራ- የትምህርት መምሪያ ኃላፊ፣

14. አቶ ባሻ በላይነህ- ግብርና አካ/ጥ/ህ/ስ/ልማት መምሪያ ኃላፊ

15. አቶ አግደው አሰፋ- የፕላን መምሪያ ኃላፊ፣

16. አቶ መስፍን ጎበዜ- የስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ፣

ሆነው በመሾም ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።የዞኑ ዋና አስተዳደሪ ሹመት የክልሉ መንግስት ተወካይና ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር በየነህ በላቸው ያ...
12/10/2026

አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳደሪ ሹመት የክልሉ መንግስት ተወካይና ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር በየነህ በላቸው ያቀረቡ ሲሆን በጉባኤው አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ቃለ መኃላ ፈፅመዋል።

በዞኑ ውስጥ ያሉ እምቅ የቱሪዝም ሀብቶችን የማልማትና የማስተዋወቅ ስራ በስፋት እየተሰራ ይገኛል። አቶ አበበ ደምሴበኮንታ ዞን ባ/ቱ/ስ መምሪያ አዘጋጅነት "ሀገርን እንወቅ" በሚል መርሃ-ግብ...
11/10/2026

በዞኑ ውስጥ ያሉ እምቅ የቱሪዝም ሀብቶችን የማልማትና የማስተዋወቅ ስራ በስፋት እየተሰራ ይገኛል። አቶ አበበ ደምሴ

በኮንታ ዞን ባ/ቱ/ስ መምሪያ አዘጋጅነት "ሀገርን እንወቅ" በሚል መርሃ-ግብር የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ጉብኝት ተደርጓል።

በጉብኝቱ የዞኑ ባ/ቱ/ስ መምሪያ አመራርና ማኔጅመንት አባላት፣ የተቋሙ አጠቃላይ ባለሙያዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ መስህቦችን ጉብኝት አድርገዋል።

ፓርኩ 1,410 ስኩዌር ካሬ ኪ.ሜ. ስፋት ያለው ሲሆን ከ800 በላይ የሚሆን የአፍሪካ ዝሆን መንጋ፣ የጎሽ እና ሌሎች ከ40 በላይ አጥቢ የዱር እንስሳትን ጨምሮ ብዙ ዓይነት አዕዋፋትና እፅዋት እንደዚሁም 6 ሐይቆች፣ ፍል ውሃዎች፣ 11 የሚሆኑ ወንዞች እና ሌሎች ተፈጥሮ ሀብቶች የሚገኙበት ብሔራዊ ፓርክ ነው።

በጉብኝቱ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት
የኮንታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ ደምሴ በዞኑ ያሉ እምቅ የቱሪዝም ሀብቶችን የማልማትና የማስተዋወቅ ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በፓርኩ ውስጥ ያሉ የቱሪዝም ሀብቶችን ተደራሽ ለማድረግ በመንግሥትና በግል ባለሀብቶች ሰፊ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው እኚህን ድንቅ ሀብቶች ሁሉም ኢትዮጵያዊም ሆነ የውጭ ዜጋ መጥቶ መጎብኘት ይገባልም ብለዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ለቱሪስት ምቹ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ በመግለፅ በአካባቢም ሆነ ከአካባቢ ውጭ ያሉ ቱሪስቶች መሰል ጉብኝት በማካሄድ መጎብኘት እና የ
ማስተዋወቅ ይገባቸዋል ብለዋል።

በዕለቱ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በተቋሙ በኩል የተዘጋጀ የጥያቄና መልስ ውድድር ተደርጎ ለአሸናፊዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
‎

ሹመት ብዙ ምቾት፣ ብዙ እንቅልፍ፣ ብዙ ድሎት ያለው ሳይሆን ብዙ ሀላፊነት እና ድካም ያለው ጉዳይ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
08/10/2026

ሹመት ብዙ ምቾት፣ ብዙ እንቅልፍ፣ ብዙ ድሎት ያለው ሳይሆን ብዙ ሀላፊነት እና ድካም ያለው ጉዳይ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

‎ያለፉትን ስብራቶች መርምረን፣ በፍጥነት እና በፈጠራ መንገድ ሪፎርም እያደረግን፣ የሚመጣውን ዓለም ለመቃኘት እየተዘጋጀን ነው።‎‎ #የመደመርመንግሥት
05/10/2026

‎ያለፉትን ስብራቶች መርምረን፣ በፍጥነት እና በፈጠራ መንገድ ሪፎርም እያደረግን፣ የሚመጣውን ዓለም ለመቃኘት እየተዘጋጀን ነው።
‎
‎ #የመደመርመንግሥት

Address

Konta
Ameya

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Konta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share