Tewodros Senior Secondary and preparatory school

Tewodros Senior Secondary and preparatory school Learning is behevioral change!!!

  #ማስታወቂያለ2014 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ተፈታኞች በሙሉየ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የተለቀቀ በመሆኑ ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 ...
27/01/2023



#ማስታወቂያ

ለ2014 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ተፈታኞች በሙሉ
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት የተለቀቀ በመሆኑ ተፈታኞች ከዛሬ ጥር18 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 5፡30 ጀምሮ፡-
• በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም
• በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም
• በቴሌግራም ላይ https://t.me/eaesbot
ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-

• ማንኛውም ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳያስፈልግ እስከ ጥር 26/2015 ዓ.ም ድረስ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ላይ Compliant የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
• የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አድራሻ ላይ ብቻ ይጠቀሙ፡፡ ከተመሳሳይ እና የተዛባ መረጃ ለማሰራጫት ከሚሞክሩ አካላት ራስዎን ይጠብቁ፡፡
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ጥር 18/2015 ዓ.ም
አዲስ አባባ - ኢትዮጵያ

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=559508126215259&id=100064682287722&mibextid=Nif5oz

Educational Assessment and Examinations Services (EAES) among others has a powers and duties of preparing country wide national examinations based on the country's education curriculum and training policy, Administer and ensure the confidentiality and safety of national exams, Establish and administ...

_________ጥር 06/ 05/2015 ዓ/ም____________ በምዕ/ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ትም/ፅ/ቤት ስር በሚገኘው የቴዎድሮስ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ''ለሃገር ግንባታ የምሁራን ሚና'' በሚል ...
14/01/2023

_________ጥር 06/ 05/2015 ዓ/ም____________

በምዕ/ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ትም/ፅ/ቤት ስር በሚገኘው የቴዎድሮስ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ''ለሃገር ግንባታ የምሁራን ሚና'' በሚል ሰነድ ዙሪያ በወረዳው የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደጃዝምች ካሳሁን እና በገለጉ ጉድኝት ሱ/ር አቶ አሰፋ አዲስ አማካኝነት ከመቼውም በተለዬ መልኩ ደስ የሚል የውይይት መድረክ ተደርጓል።

በመድርኩ ለአንድ አገር ዕድገት የምሁራን ሚና አስፈላጊነት ለማናችንም ግልፅ የሆነ ሃሳብ መሆኑን ጠቅሰው፣ ምሁራን ማለት እነ ማን ናቸው? የሚለውንም ጥያቄ ከውይይቱ መግቢያ ላይ በአቶ ደጃዝማች ካሳሁን አማካኝነት ማብራሪያ ተሰጥቷል። በማብራሪያውም፣ መማር ብቻ ለምሁርነት በቂ መስፈርት አለመሁኑን ጠቅሰው አንድ አካል መማሩን ለብሄር ፖለቲካ፣ ጎሳን ከጎሳ ለመከፋፈል፣ ዘርን መሰረት ላደረገ ጥቅም የሚጠቀምበት ከሆነ ተግባሩ ለሃገረ መንግስት ግንባታ የቆመ ካልሆነ ምሁር ሊባል እንደማይችል አስረድተዋል። ምሁር ማለት የሃሳብ ልዕልናው ያደገ ከግለሰብ ይልቅ የቡድን ጥቅምን ያስቀደመ በኢትዮጵያዊነት አስተሳሰብ ራሱን ያካበተ እና የሃገርን ችግር ከመረዳት ባሻገር ለመፍትሄ የታተረ አካል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያ ሃገራችን ካለፉት 210 ዓመታት ጀምሮ በብዙ ውጣ ውረዶች በብዙ ስኬቶችና በብዙ ውድቀቶች እንዳለፈች አብራርተዋል። ዘመናዊ ትምህርት በኢትዮጵያ ከተጀመረበት 100 አመታት በፊት ጀምሮ በኩረጃ ከሌሎች አገራት እዬተቀበልን ስንተገብረው የኖርን አካሄድ በትምህርት ስርዓታችን ላይ አሉታዊ ተፅኖ በምፍጠር ማፍራት የሚገባምንን ጥራት ያለው ምሁር ማፍራት ያላስቻለን መሆኑን አስረድተዋል። ከዚህ ውጭ በእነዚህ 100
አመታት ውስጥ ያለፉትን ምሁራን በነበራቸው አመለካከትና የትግበራ ሁነት መሰረት በ 4 ደረጃዎች ከፋፍለው አስረድተዋል።
የመጀመሪያው የምሁራን ዘመን ፣ ሁለተኛው፣ ሶስተኛውና አራተኛው የምሁራን ዘመን በማለት እና ከ አንድ አስከ አራት ባሉት ደረጃዎች ያለፉት ምሁራን በዘመናቸው ለሃገር ያበረከቷቸውን መልካም ተግባራት ጠቅሰው ባለንበት ዘመን ወይም እኛን የሚጨምረው የምሁራን ዘመን ለሃገር ግንባታ ምን አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚገባው ከገለፁ በኋላ አገራችን ያለችበትን ደረጃ በኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ጋር አዛምደው ገልፀዋል።

አቶ አሰፋ አዲስ (ሱ/ር) በበኩላቸው በማስተዳደር ላይ ያለው መንግስት ባሳለፋቸው አራት አማታት ውስጥ በብዙ ምስቅልቅሎሽ ውስጥም ሆኖ ጥሩ ሊባሉ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዎና ማህበራዊ ለውጦችን እንዳበረከተ አስረድተዋል። ከእነዚህም ውስጥ የተፎካካሪ ፓርቲዎች በአመራርነት ቦታ እንዲኖራቸው የተደረገበት ሁኔታ የፍትህ እና የፀጥታ ሃይል እንዲሁም የፍትህ ስርዓት ገለልተኛነት መሆንና በማስተዳደር ላይ ላለው ፓርቲ ጠባቂ ከመሆን ወጥተው ለህዝብና ለሃገር አለኝታነታቸውን ያረጋገጡበት አግባብነት እንደጥሩ ሪፎርም ሊጠቀስ እንደሚገባው አብራርተዋል። ከዚህ ጋር አያይዘው የልልላችን የዘመናት ጂኦግራፊካል ጥያቄ በተፈለገው ምንገድም ባይሆን ታሪካዊ ምህዳሩን ማስጠበቅ የተቻለበት አግባብነት እንዳለም ገልፀዋል። በዚህም ምክንያት ከባለፈው አመት በተጨማሪ ዘጠኝ ያህል ተጨማሪ ወረዳዎች ከ 1995 ዓ/ም በፊት ወደነበሩበት ታሪክ እንደተመለሱ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ከተሰብሳቢው የት/ቤቱ መ/ራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ጥያቄዎችን ተነስተው ፅብረቃ ከተደረገ በኋላ ስብሰባው ተጠናቋል።

የቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የገና በዓልን በት/ቤቱ በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።በበዓሉ እለትም ር/መ/ር ምንውዬለት ስሜ በዓሉን በማስመልከት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግሩም...
08/01/2023

የቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን የገና በዓልን በት/ቤቱ በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።

በበዓሉ እለትም ር/መ/ር ምንውዬለት ስሜ በዓሉን በማስመልከት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግሩም "ጌታችን መድኃኒታችን ኢዬሱስ ክርስቶስ በደሃ ቤት አድሮ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር አሳይቶናል። እኛም ከእርሱ ተምረን ርስ በርስ ልንዋደድ ልንፋቀር ይገባል ብለዋል"

በበዓሉ አብሮ የበዓሉ ተካፋይ የሆነው የት/ቤቱ የሂሳብ መምህር መ/ር ሙሀመድም "እንኳን አደረሳችሁ" በማለት ”በዓሉ ርስ በርስ የምትተሳሰቡበት እና የፍቅር በዓል ይሁንላችሁ" በማለት መልካም ምኞቱን ገልጿል።

በአጠቃላይ በዓል ለሁለት ቀናት በት/ቤቱ እጅግ በደመቀ እና ባማረ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

04/01/2023

የትምህርት መረጃ ስርዓትን በማጠናከር በክልሉ የተጀመረውን የትምህርት ጥራት ለማረጋጥ በትኩረት እየተሰራ ነው
የትምህርት ልማት መረጃ አስተዳደር ስርዓት የአንድን ክልል ወይም ሃገር የትምህርት ሁኔታ ከዓለም አቀፍና ሃገር አቀፍ የትምህርት አመልካቾች አንጻር ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ጥልቅ ትንታኔ የሚሰጥበት ስርዓት ነው፡፡ በመረጃዎቹ ላይ ተመስርቶ ግብዓቶችን ለማሟላትና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ጉልህ ጠቀሜታ አለው፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በመረጃ አያያዝ ስርዓት ማሻሻል እና የተቋማትን የውስጥ ገቢን በማሳደግ ጥራት ያለው ትምህርትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡
በዚህም ዓመታዊ የትምህርት መረጃ መጠየቅን በተገቢው መንገድ ለመሙላት እና የትምህርት ተቋማትን የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና ለወረዳ የትምህርት እቅድ ባለሙያዎችን ተሰጥቷል፡፡

በትምህርት ቤቶች ውስጥ ያለውን ሁሉን አቀፍ አቅርቦት በመለየት ለቀጣይ መፍትሄ ለመስጠት ርዕሳነ መምህራን መረጃዎችን በሃላፊነት ማጠናቀር እንዳለባቸው በስልጠናው የተገለፀ ሲሆን የውስጥ ገቢን በማሳደግ የትምህርት ተቋማት ራሳቸውን እንዲችሉ በማስቻል ከተረጅነት ማላቀቅ ዙሪያ የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑንም ነው በስልጠናው የተገለፀው።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን

anrseb.gov.et, Amhara National Regional State Education Bureau, Amhara Education Bureau, Bahirdar,East Gojjam, Weste Gojjam, Agew Awi,South Gondar,Central Gondar,North Wollo,Wag Hemra,North Shewa,Desse,Wollo Oromo, South Wollo, Weste Gondar

02/01/2023
በቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ት/ ቤት በ(21/04/015 ዓ/ም የወላጆች መድረክ ተካሄደ።በመድረኩ በትምህርት ጥራት ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ፅብረቃ በር/መ/ር ምንውዬለት ስሜ ቀርቧል።ከዚህ ጋር ተያ...
02/01/2023

በቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ት/ ቤት በ(21/04/015 ዓ/ም የወላጆች መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ በትምህርት ጥራት ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ፅብረቃ በር/መ/ር ምንውዬለት ስሜ ቀርቧል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ወላጆች ለተማሪዎቻቸው የትምህርት ውጤት መሻሻል ስለሚኖራቸው ሚና እና ማድረግ ስለሚገባቸው ኃላፊነት ጥቆማ ተስጥቷል።

ለትምህርት ጥራት ጉደለት ማነቆ ናቸው የተባሉ ችግሮችንም ር/መ/ሩ አያይዘው ሲናገሩ
👉 የወላጆች ቁጥጥር ማነስ
👉 የተማሪዎች የመማር ፍላጎት እያሽቆለቆለ መምጣት
👉 የተለያዩ ወጣቶች ተመርቀው ስራ አጥ ሆነው መታዬታቸው
👉 እንደ ቴዎድሮስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚታዩ የግብዓት ችግሮች (የመፅሀፍት፣ የላቦራቶሪ እቃወች አለመሟላት፣ ወንበሮች እና የክፍል ግንባታ ማነስ) እና ሌሎችም እንደሆኑ ተጠቅሷል።

የመፍትሔ ሃሳቦችም በወላጆች እና ተሳታፊ አካላት ተንፀባርቀው መድረኩ ለቀጣይም መቀጠል እንዳለበት ተጠቁሞ የእለቱ መድረክ ተጠናቋል።

የቀጠለ...👉👉👉የስርዓተ ፆታ ክበብ ፀሃፊ መ/ርት ክድጃ ምሃመድ በመቀጠል ሴቶች እንዴትና በምን ሁኔታ ላልተፈለገ እንዲሁም እድሜንና የትምህርት ደረጃን ያላማከለ ፆታዊ ትንኮሳ እንደሚጋለጡ አ...
29/12/2022

የቀጠለ...

👉👉👉የስርዓተ ፆታ ክበብ ፀሃፊ መ/ርት ክድጃ ምሃመድ በመቀጠል ሴቶች እንዴትና በምን ሁኔታ ላልተፈለገ እንዲሁም እድሜንና የትምህርት ደረጃን ያላማከለ ፆታዊ ትንኮሳ እንደሚጋለጡ አብራርተዋል። በመድረኩ ሴት ተማሪዎቻችን ለዚህ ችግር ሚጋለጡበትን መንገድ ሲያብራሩ፣
ሴት ተማሪዎች ላልተፈለገ ወሲብ፣ ሚጋለጡት በ ሦስት መንገድ እንደሆነ ተናግረዋል።
እነዚህም፦

👉. በራስ ፍላጎት ወይም ተነሳሽነት
👉. በመታለል ወይም በአቻ ግፊት
👉. በአስገድዶ መደፈር ሲሉ በ 3 መንገድ አብራርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ 3 የችግሩ መፈጠሪያ መንገዶችን ሴት ተማሪዎች እንዴት ማስዎገድ እንደሚችሉ አስረድተዋል። ለምሳሌ ያህል ወንዶች እንዴት እንደሚቀርቧቸውና እንዴት ወዳልፈለጉት ጣጣ ውስጥ እንደሚከቷቸው እንዴት እንደሚያጠምዷቸው በምን ሰዓት እንደሚያጠቋቸው በጥልቀት አስረድተዋል።

💃💃💃በመድረኩ ሌላ የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑትና የስርዓተ ፆታ ክበብ አባል የሆኑት መ/ርት የሽዬ አያናው ወቅቱ በቴዎድሮስ ከተማ እና አካባቢው ባህል መሰረት ከገና በዓል በኋላ ባሉት ወራት ሰርጎች በከፍተኛ ሁኔታ ይፈፀማሉ እና ያለ ፍላጎቷ ከትምህርት አለም ወጥታ ለትዳር ምትሰጥ ሴት ተማሪ ከመካከላችሁ ትኖራለች እና ወረቀት ቆራርጠን እንበትናለን ፅፋችሁ ስጡን በማለት ሃሳባቸውን ገልፀዋል።

💃💃💃ሌላ የስርዓተ ፆታ ተሳታፊ የሆኑት መ/ርት ገነት ተገኘ ሁላችንም በኢኮኖሚ ችግር ትምህርታቸውን ሊያቋርጡ የሚችሉ ሴት እህቶቻችን በክበቡ ስም ገንዘብ በማዋጣት ማገዝና መታደግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

💃💃💃 በመድረኩ ተሳታፊ የሆነችውና የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪ የሆነችው ተማሪ የሻሽወርቅ ወሌ '' እኔ ከዚህ ትምህርት ቤት ስማር 4 ዓመቴ ነው እንደዚህ ዓይነት መድረክ ተፈጥሮልን አያውቅም። በጣም ደስ ብሎኛል። መድረክ ከተከፈተልንማ ብዙ ሃሳቦች አሉን። በማለት ሃሳቧን ጀምራለች። ሌሎች ክበቦችም ልክ እንደዚህ ቢሰሩ መልካም ነው በተለይ የቋንቋና ሚኒሚዲያ ክበብ የእንግሊዝኛ ቋንቋ በእንግሊዝኛ የመናገር ችሎታን ለማዳበር በር ከፋች ነውና ልክ እንደስርዓተ ፆታ ክበብ የሚታ ነገር ቢሰራ ብላለች። ከዚህ በተጨማሪ ''ይህ የእኛ ሴቶች ነፃ መድረክ ነው ምንም ወንድ የለም ያሉት ሴት አስተማሪዎቻችን እና እኛ ሴት ተማሪዎች ነን። ስለዚህ ልብ ለልብ ተነጋግረን እየደረሰብን ስላለው ችግር መነፋገር አለብን ብላለች።

💃💃💃 የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ መስቀል በለጠ ሃሳቧን ስትገልፅ ''ሴት እህቶቻችን በኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ከሚያቋርጡብን ከምንበላው ቀንሰንም ቢሆን እያንዳንዳችን ሴቶች ሁሉ 10 ብር በማውጣትና በማሰባሰብ ድጋፍ ልናደርግላቸው ይገባል ስት ሃሳቧን ገልፃለች። ሌሎች ተሳታፊና ከ680 በላይ የሆኑ ሴት ተማሪዎችም ሃሳቧን በከፍተኛ ጭብጫቦ አድንቀውላታል።
በመጨረሻም የክበቡ ተጠሪ የሆኑት መ/ር ትዕግስት ድረስ ለተማሪዎችየሃሳብ መቀበያ ወረቀት በመቆራረጥና በመስጠት እንዲሁም የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ውይይቱ ሊደመደም ችሏል።

©©© የቴዎድሮስ /2ኛ/ደ/ት/ቤት©©©                                ቀን 20/04/2015ዓ/ም   👉👉  በቴ/2ኛ/ደ/ት/ቤት በስርዓተ ፆታ ክበብ አማካኝነት በት/ቤቱ ሴት...
29/12/2022

©©© የቴዎድሮስ /2ኛ/ደ/ት/ቤት©©©

ቀን 20/04/2015ዓ/ም
👉👉 በቴ/2ኛ/ደ/ት/ቤት በስርዓተ ፆታ ክበብ አማካኝነት በት/ቤቱ ሴት ተማሪዎች የትምህርት ጉዞ ላይ እየተፈጠሩ ባሉ መሰናክሎች ዙሪያ ሁሉም የት/ቤቱ ሴት መ/ራንና ሴት ተማሪዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በችግሮች ዙሪያ ያሉ የውይይቱ መሰረታዊ ሃሳቦች ቀደም ሲል በክበቡ ተጠሪዎች ሴት መ/ራን እና በትምህርት ቤቱ ር/መ/ር ውይይት ከተደረገባቸው በሗላ ከተማሪዎች ጋር የውይይት መድረክ በመፍጠር ልክ እንደ እናትና ልጅ የልብ ለልብ ውይዩይት ተካሂዷል።
በውይይቱ መድረኩን የመግቢያ ንግግር በማድረግ የከፈቱት የሥርዓተ ፆታ ክበብ ተጠሪ መ/ርት ትዕግስት ድረስ እንደገለፁት ``ሴት ልጆች ተምረን በማናቸውም የሙያ ዘርፍ እኩል ልክ እንደ ዎንዶች መስራትና ሃገራችን ካለችበት ደረጃ ወደ ተሻለ ከፍታ ከፍ ማድረግ እንደምንችል በብዙ መንገድ አሳይተናል`` ብለዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ዘመናት የተለያዩ ሴት ልጆች ሃገራትን በማስተዳደር ከፍተኛ ጀብዱ ስርተዋል ካሉ በኋላ:

👉 የአሜሪካዋን የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንት ሄላሪ ክሊንተን
👉 የጀርመኗን ማራሂተ መንግስት አንጌላ መርኬልን
👉 የእንግሊዟን ንግስት ኤልሳቤጥን
እንዲሁም ወደ አገራችን ድንቅ እንስቶች በመምጣት
👉 የተከበሩት ገነት ዘውዴ የትም/ት ሚኒስተር ሆነው እንዳገለገሉ
👉 የተከበሩት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሃገራችን በፕሬዝዳንትነት እያገለገሉ መሆናቸውን
👉 የጤና ሚኒስተር ሆነው እያገለገሉን ያሉትን የተከበሩ ሊያ ታደሰን እና ሌሎችንም ድንቅ ሴቶችን በማንሳት የት/ቤቱን ሴት ተማሪዎች በሞራል አነሳስተዋል።

ከዚህ በመቀጠል ሴት ተማሪዎች ተምረው መድረስ ካሰቡት ደረጃ እንዳይደርሱ ብዙ ጎታች የሆኑ ችግሮች እንዳሉባቸው እና ከእነዚህ ጎታች ችግሮች እንዴት መውጣት እንዳለባቸው በመግለፅ ውይይቱን ከፍተዋል። ይሄን በተመለከተ የክበቡ ተጠሪ መ/ርት ትዕግስት ድረስ ሃሳባቸው ሲያብራሩ፣ ችግሮቹን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ በማለት በ 3 ከፋፍለው አስረድተዋል።

💃💃💃 ሴት ልጆች ከማህበራዊ ጉዳዮች አንፃር እየደረሱባቸው ያሉ ችግሮች በሚኖሩባቸው አካባቢ ሊፈጠርባቸው ለሚችል ያልተገባ ወይም እድሜንና የት/ት ደረጃን ያላማከለ ፆታዊ ግንኙነት ዙሪያ ሴቷን መክሮ ከመመለስ ይልቅ ስድብና ማንቋሸሾች እንዳሉ እና ይሄ ደግሞ ሴት ልጆችን በማሸማቀቅ ከትምህርታቸው ወደ ኋላ እንደሚላቸው አብራርተዋል። ከዚህ ባሻገር ሴት ልጆችን ያለፍላጎታቸው አስገድዶ መዳር፣ መድፈር፣ የጉልበት ብዝበዛዎች እና ሌሎችም እየተፈፀሙባቸው እንደሆነ ገልለዋል። በተለያዩ ጊዜያ ከሚሰሙ ጭምጭምታዎች በመነሳት ሴት ተማሪዎች በተፈጠረባቸው እድሜንና የትምህርት ደረጃን ያላገናዘበ ፆታዊ ግንኙነት ሳቢያ በሚፈጠር ያልተገባ እርግዝና፣ ከማህበረሰብ ትችትና ሰቆቃ ራሳቸውን ለማዳን ሲሉ ለብዙ ስነልቦናዊ እና አዕምሮአዊ ጉዳት እንደሚዳረጉ ጫካ ውስጥ የማይቻለውን ችለው ብቻቸውን አምጠው እንደሚዎለዱም ጭምር ጠቁመዋል። ከዚህ ባሻገር ለአባላዘር በሽታ መጋለጥም እንዳለ አበክረው አስረድተዋል።

👤 ከኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ጋር በተያያዘ ብዙ ሴት ልጆች የተመጣጠነ ምግብ፣ አልባሳት፣ ትራንስፖርት የንፅህና መጠበቂያ እንዲሁም ልዩ ልዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ማሟላት ባለመቻል ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ሴት ተማሪዎችም ብዙዎች እንዳሉ አብራርተዋል።

ከፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የትምህርት ጥራት መጓደል ሤት ተማሪዎች በሚያመጡት ውጤት ደስተኛ ባለመሆን እና ተስፋ በመቁረጥ ከትምህርት አለም ራሳቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ማግለልን የሚመርጡበት አጋጣሚም እንዳለ አክለው አብራርተዋል።

~ይህን ሁሉ ካሉ በኋላ ለችግሮቹ መንስኤ የሆኑትን ጭብጦች ከተረዳን በመመካከርና መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ሴት ልጆችን ከትምህርት ገበታቸው እንዳይዎጡና በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤትአስወመዝግበው ካሰቡት ኣላማ እንዲደርሱ ማድረግ እንችላለን ብለዋል።

ተማሪዎችን በተለያዩ መርጃዎች መደገፍ የሁሉም መምህራን ኃላፊነት ነው። መምህራን ተማሪዎቻቸው ብቁ እንዲሆኑ እስከታች ድረስ ወርደው የመስራት ኃላፊነት አለባቸው። በዛሬው እለት (29/03/20...
08/12/2022

ተማሪዎችን በተለያዩ መርጃዎች መደገፍ የሁሉም መምህራን ኃላፊነት ነው። መምህራን ተማሪዎቻቸው ብቁ እንዲሆኑ እስከታች ድረስ ወርደው የመስራት ኃላፊነት አለባቸው።

በዛሬው እለት (29/03/2015 ዓ/ም) በቴዎድሮስ ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት በአራቱም የክፍል ደረጃዎች ማለትም ከዘጠኝ እስከ አስራሁለተኛ ክፍል ድረስ ባሉት የክፍል ደረጃዎች የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል። ተማሪዎች በእንደዚህ አይነት ዝግጅቶች መሳተፋቸው አቅማቸውን ለማወቅ እና አንዳቸው ከአንዳቸው ለመማር ትልቅ እድል ሊፈጥርላቸው እንደሚችል ተመላክቷል።

Address

Wisdom
Amara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tewodros Senior Secondary and preparatory school posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category