Aleta Wondo High School

Aleta Wondo High School

Share

This Page is the Official page of Aleta Wondo High School

08/11/2021

ዛሬ የሚጀምረውን የ2013 ዓ.ም ሀገራዊ ፈተናን ለምትፈተኑ ተማሪዎች በሙሉ መልካም የፈተና ጊዜን እየተመኘን ፈተናችሁን በፍፁም መረጋጋት እና ስነ- ምግባር በተሞላበት መልኩ እንድትፈተኑ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

መልካም ፈተና
ትምህርት ሚኒስቴር

Photos 26/06/2017
23/09/2016

በ2009 የነባር እና አዲስ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን
1,አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ነባር ተማሪዎች፦ መስከረም 24 እና 25 ዓ.ም
አዲስ ተማሪዎች፦አልተገለጸም
2,ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ነባር ተማሪዎች፥ መስከረም 22 እና 23 2009 ዓ.ም
አዲስ ተማሪዎች፥ ጥቅምት 03 እና 04 2009 ዓ.ም
3,ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ መስከረም 19 እና 20
ለአዲስ ተማሪዎች፦ ከመስከረም 26 እስከ 27
4,አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፥ ከመስከረም 19 እስከ 22
ለአዲስ ተማሪዎች፥ ከመስከረም 29 እስከ 30
5,ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 27-29 2009 ዓ.ም
ለአዲስ ተማሪዎች፦ ከጥቅምት 4-6 2009 ዓ.ም
6,መቀሌ ዩኒቨርሲቲ
ነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 18 እስከ 20 2009 ዓ.ም
አዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
7,ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 23 እስከ 242009 ዓ.ም
ለአዲስ ተማሪዎች፦ ከጥቅምት 03 እስከ 04 2009 ዓ.ም
8,ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 23 እስከ 24
9,መቱ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 20-21
ለአዲስ ተማሪዎች፦አልተገለፀም
10,ሀሮሚያ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 20-22
ለአዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
11,ጅጅጋ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 21 እስከ 23
ለአዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
12,አዲስ አበባ ሳይስንና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 19 እስከ 20
ለአዲስ ተማሪዎች፦ ከመስከረም 26 እስከ 27
13,ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 21 እስከ 22
ለአዲስ ተማሪዎች፦ መስከረም 30 እና ጥቅምት 01, 2009 ዓ.ም
14,ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 19 እስከ 20
ለአዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
15,ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 18 እስከ 20
ለአዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
16,ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 22 እስከ 23
ለአዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
17,ወሎ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ መስከረም 18 እና 19 ሲሆን፥ በቅጣት መስከረም 20
ለአዲስ ተማሪዎች፦ መስከረም 26 እና 27 እንዲሁም በቅጣት መስከረም 28
18,ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ መስከረም 18 እስከ 19
ለአዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
19 ,ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ መስከረም 23 እና 24
ለአዲስ ተማሪዎች፦ አልተገለጸም
20, አዲግራት ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 23 እስከ 25
ለአዲስ ተማሪዎች፦አልተገለጸም
21,ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 24 እስከ 25
ለአዲስ ተማሪዎች፦ ጥቅምት 1 እና 2 ቀን 2009 ዓ.ም
22,አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 18 እና 19
ለአዲስ ተማሪዎች፦ ከመስከረም 25 እስከ 26
23 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
ለነባር ተማሪዎች፦ ከመስከረም 30እና ጥቅምት 01 2009
ለአዲስ ተማሪዎች፦ ጥቅምት 8 እና 9 2009
የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የነባር እና አዳዲስ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

FBC - የ2009 የዩኒቨርሲቲ መድባ ይፋ ተደረገ 22/09/2016

www.fanabc.com/index.php/news/item/18964-የ2009-የዩኒቨርሲቲ-መድባ-ይፋ-ተደረገ.html

FBC - የ2009 የዩኒቨርሲቲ መድባ ይፋ ተደረገ አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ2009 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ተደርጓል። ተማሪዎች ምደባቸውን ውጤታቸውን ባዩበት ድረ ገጽ ማለትም www.nae.gov.et በመግባት መመልከት ይችላሉ ተብሏል። ምደባው ከዛሬ 12...

FBC - የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ተለቀቀ 27/08/2016

fanabc.com/index.php/news/item/18416-የ10ኛ-ክፍል-ሀገር-አቀፍ-ፈተና-ውጤት-ተለቀቀ.html

FBC - የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ተለቀቀ አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ። የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዘርይሁን ዱሬሳ ለፋና ብሮድካስቲ...

25/08/2016

ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።
በዚህም መሰረት በመደበኛ እና በማታ በተፈጥሮ ሣይንስ የትምህርት መስክ ፈተና ወስደው ለወንድ 354 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ለሴት ደግሞ 340 ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ።
በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ በመደበኛ እና በማታ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ደግሞ ለወንድ 330 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ሆኗል።
በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ሁሉም የታዳጊና አረብቶ አደር ሴት ተማሪዎች 335 እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንደዚሁም ሁሉም የታዳጊ ክልልና የአርብቶ አደር አካባቢ ወንድ ተማሪዎች ከፍተኛ የትምሀርት ተቋማትን ለመቀላቀል 340 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
በማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚቀላቀሉ የግል ተፈታኞች ለወንድ 360 እና ከዚያ በላይ ፣ ለሴት ደግሞ 355 እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
በማህበራዊ ሳይንስ ለታዳጊና የአርብቶ አደር ሴት ተማሪዎች 315 እና ከዚያ በላይ፤ ለወንዶች ደግሞ 320 እና ከዚያ በላይ፤ በተፈጥሮ ሳይንስ ለታዳጊና የአርብቶ አደር ሴት ተማሪዎች ለወንዶች 340 እና ከዚያ በላይ፣ ለሴቶች ደግሞ 335 እና ከዚያ በላይ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ሆኗል።
መስማት ለተሳናቸው የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ለሁለቱም ፆታ 297 እና ከዚያ በላይ ሲሆን፥ በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ደግሞ ለሁለቱም ጾታ 275 እና ከዚያ በላይ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ሆኗል።
ሁሉም አይነስውራን (ወንዶችም ሆነ ሴቶች) 200 እና ከዚያ በላይ ካስመዘገቡ በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ይመደባሉ።
በግልም ሆነ በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማታም ሆነ በቀን እንዲሁም በርቀት ትምህርታቸውን መከታተል የሚፈልጉ ተማሪዎች 295 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
ብሄራዊ ፈተናውን 246 ሺህ 570 ተፈታኞች የወሰዱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 50 በመቶዎቹ 350 እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል።
106 ተፈታኞች ደግሞ 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 21ዱ ሴቶች ናቸው።
በሌላ በኩል የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከሶስት ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል። www.fanabc.com/index.php/news/item/18372-የ2009-ዩኒቨርሲቲ-መግቢያ-ውጤት-ይፋ-ሆነ.html

15/08/2016

የ12ኛ ክፍል የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና ዉጤት ይፋ ሆነ፡፡ የሚከተለዉን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ፡፡ 
52.169.230.16/Home/Student

NEAEA Ethiopia APK Download - Free Education APP for Android | APKPure.com 29/07/2016


ይህ የአንድሮይድ መተግብርያapp ነጥባቹ(ውጤት) ሲለቀቅ በቀላሉ ለማየት ያስችላቿል፡፡
Size 1.2MB
ዳውንሎድ ለማድረግ ይህን link ሊንክ ይጫኑ https://m.apkpure.com/neaea-ethiopia/com.habeshaandroid.neaea መልካም ዕድል ለአለታ ልጆች

NEAEA Ethiopia APK Download - Free Education APP for Android | APKPure.com Download NEAEA Ethiopia apk 1.0 and all version history for Android. Android App National Educational Assessment and Examination Agency (NEAEA App)

ፊቼ-ጫምባላላ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር መዘጋጀታቸውን የሸበዲኖ ወረዳ በቄጣላ ሥነሥርዓት ዙሪያ ውይይት... | Aleta Wondo High School 21/06/2016

awhs.yu.tl/post-title-7.xhtml

ፊቼ-ጫምባላላ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር መዘጋጀታቸውን የሸበዲኖ ወረዳ በቄጣላ ሥነሥርዓት ዙሪያ ውይይት... | Aleta Wondo High School ዘንድሮ የሚከበረውን የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ-ጫምባላላ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር መዘጋጀታቸውን የሸበዲኖ ወረዳ በቄጣላ ሥነሥርዓት ዙሪያ ውይይት ያካሄዱት የሀገር ሽማግሌዎች ተናግረዋል፡፡ የቄጣላ ሥነሥርዓቱ ፍፁም

14/06/2016

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን መለወጡን የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከግንቦት 22 ጀምሮ ለአራት ቀናት ሊሰጥ የነበረው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በፈተና ወረቀቶች መውጣትና ቀድሞ በማህበራዊ ድህረ ገፅ መሰራጨቱን ተከቶሎ ፈተናው መቋረጡንና የድጋሚ ፈተና ቀን ከሰኔ 27-30/2008 ዓ.ም እንደሚሰጥ ለህዝብና ለተፈታኝ ተማሪዎች ማሳወቁ የሚታወቅ ነው፡፡
ይሁንና ይህ ጊዜ ከረመዳን ፆም ወር ጋር የተገናኘ መሆኑን በመግለፅ የኢትዮጵያ አስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለተማሪዎች ከፆም በኋላ እንዲሆን ያቀረበውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ ከክልሎች ጋር በተደረገው ምክክር ጥያቄው የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃሳብ መሆኑን ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለመገንዘብ መቻሉን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት ሌሎች ተማሪዎችና ወላጆቻቸውም የጓደኞቻቸውንና የወላጆቻቸውን ጥያቄ ይጋሩታል የሚል እምነት በመያዝ ፈተናው ከሐምሌ 4 ሰኞ እስከ ሐምሌ 7 ሐሙስ 2008 ዓ.ም ድረስ እንዲሰጥ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ሁሉም ዝግጅቶች በተሟላና በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተፈፀሙ መሆኑንና በእለቱ ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ.ም ሁሉም ተማሪዎች የመለያ ካርዳቸውን /ID - Card/ በመያዝ በተመደቡበት ትምህርት ቤታቸው እንዲገኙ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪ አስተላልፋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውንና መምህራንን በማስተባበር ተማሪዎች በተረጋጋ መንገድ የትምህርት ክለሳ እንዲያደርጉ ፣ የምክር አገልግሎት እንዲያገኙና እንዲያደርጉ እንዲሁም ወላጆችም ቀጣዩን አንድ ወር ልጆቻቸውን እንዲደግፉ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

FBC - ሰበር ዜና: ትናንት ተቋርጦ የነበረው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል 31/05/2016

ሰበር ዜና: ትናንት ተቋርጦ የነበረው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ተቋርጦ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።
የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ ከሰኔ 27 ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ድረስ ፈተናው ይሰጣል።
የ12ኛ ክፍል ፈተና ኮድ 14 የእንግሊዝኛ ፈተና መውጣቱ በመረጋገጡ እና ሌሎች ፈተናዎች ላለመውጣታቸው ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባለመኖሩ እንዲሰረዝ መደረጉን ትናንት ሚኒስትሩ መግለፃቸው ይታወሳል።
አሁን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት እና አሰጣጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ጥበቃ የሚከናወን እንደሚሆንም ነው ሚኒስትሩ የገለፁት።
ሀገር አቀፍ ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥናትና ምርምር ማዕከል አማካኝነት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚዘጋጅ ያስረዱት አቶ ሽፈራው፥ ባለሙያዎቹ ተፈታኝ የስጋ ዘመድ እንደሌላቸው ተረጋግጦ በፈተና ዝግጅት እንዲሳተፉ እንደሚደረግም ተናግረዋል።
ፈተናው በመቀጠልም በተደራጀ እና ምስጢራዊነቱን በጠበቀ መልኩ የህትመትና የስርጭት ስራው እንደሚከናወንም ነው ያረጋገጡት።
በፈተና ስርቆት ተግባሩ ላይ የተሳተፉ አካላትም ህጉ በሚፈቅደው መሰረት አስፈላጊውን ማጣራት በማካሄድ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ እንደሚደረግም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
አቶ ሽፈራው ተማሪዎች በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለፈተና ዝግጀት በማድረግ በተጠቀሰው ጊዜ ፈተናውን እንዲወስዱ አሳስበዋል።
ምንጭ☞fanabc.com/index.php/news/item/16365-ሰበር-ዜና-ትናንት-ተቋርጦ-የነበረው-ወደ-ከፍተኛ-ትምህርት-ተቋም-መግቢያ-ፈተና-ከሰኔ-27-እስከ-30-ይሰጣል.html

FBC - ሰበር ዜና: ትናንት ተቋርጦ የነበረው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ተቋርጦ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ። የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለይም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እ...

FBC - እንኳን ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ድረገፅ በደህና መጡ፡፡ 30/05/2016

ሰበር ዜና: የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተቋረጠ አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መቋረጡን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሃሙስ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና እስካሁን ኮድ 12 የእንግሊዝኛ ፈተና መውጣቱ በመረጋገጡ ነው እንዲቋረጥ የተደረገው ብሏል። ለመላው ተፈታኞች እና ቤተሰቦቻቸው ሚኒስቴሩ ይቅርታ ጠይቋል።
ምንጭ= ☞fanabc.com

FBC - እንኳን ወደ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ድረገፅ በደህና መጡ፡፡ ክፍት የስራ ማስታወቂያዎች  Associate, Internal Audit(Re-Advertised) Job by Ethiopian Agricultural Commodities Warehousing Services Category: Admin, ...

Want your school to be the top-listed School/college in Aleta?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Wendo
Aleta
SHOWMAP,CHECK-INSANDSTARRATINGSONTHEPAGE