Aksum University

Aksum University

Share

Aksum University official page
ልህቀት በጥረት
Excellence Through Perseverance!

Photos from Aksum University CHS & Comprehensive Specialized Hospital's post 19/05/2026
Photos from Aksum University's post 18/05/2026

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሰራተኞች የሚሰጥ የስራ ፈጠራ ስልጠና ተጀመረ
________________//______________

አክሱም ዩኒቨርሲቲ (ግንቦት 10/2018 ዓ.ም)

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የስራ ዕድል ፈጠራና ልማት ማዕከል (CEED) ከስትራቴጂካዊ አጋሩ ከኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) ጋር በመተባበር ለአካዳሚክ እና ለአስተዳደር ሰራተኞች ያዘጋጀው የስራ ፈጠራ ስልጠና ዛሬ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል። ይህ የአቅም ግንባታ ስልጠና እስከ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ይሆናል። የዚህ መርሃ ግብር ዋና ዓላማ በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የፈጠራ ስራዎቻቸውን መደገፍ የሚያስችላቸውን፣ እንዲሁም እነዚህን የፈጠራ ሃሳቦች ወደ ተግባርና ወደ ገበያ ለመቀየር የሚረዱ ክህሎቶችንና አመለካከቶችን ማዳበር ነው።

ስልጠናውን በይፋ የከፈቱት የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙሉጌታ በሪሁ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲዎች የፈጠራ ክህሎት ያላቸው፣ በራሳቸው የሚተማመኑ እና ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች የስራ ዕድል መፍጠር የሚችሉ ብቁ ባለሙያዎችን የማፍራት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ዶክተር ሙሉጌታ አክለውም ዘመኑ የስራ ፈጠራ መሆኑንና ፈጠራ ደግሞ የሚጀመረው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሆነ ጠቅሰው፣ ሰልጣኞች ስልጠናውን በንቃትና በትጋት በመከታተል በተሳካ ሁኔታ እንደሚያጠናቅቁት ሙሉ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

አያይዘውም የስራ ዕድል ፈጠራና ልማት ማዕከሉ በዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ ትኩረት በማድረግ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በስፋት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የማዕከሉ አስተባባሪ መምህር ለአከ ለገሠ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወደ ራስ-ገዝነት እና ዲፈረንሺየሽን (Differentiation) በሚያደርጉት የሽግግር ጉዞ ውስጥ የኢንተርፕረነርሺፕ አስተሳሰብን መላበስ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ይህ ስልጠና የዩኒቨርሲቲው ምርምሮች ወደ ተግባርና ወደ ገበያ የሚወጡበትን መንገድ ለማመቻቸት፣ ተማሪዎች ተቀጣሪ ወይም ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆኑ የስራ ፈጣሪነት መንፈስ እንዲላበሱ ለማድረግ፣ እንዲሁም መምህራን በተማሩበት የሙያ ዘርፍ የራሳቸውን ቢዝነስ ፈጥረው ለተማሪዎቻቸው በተግባር አርአያ እንዲሆኑ ለማስቻል ታላቅ እገዛ እንደሚያደርግ አስተባባሪው ገልጸዋል።

በመጨረሻም መምህር ለአከ፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት (EDI) የዩኒቨርሲቲውን ጥሪ አክብሮ፣ ያለውን እውቀትና ልምድ ለተቋሙ ሰራተኞች ለማካፈል ወደ ስፍራው በመምጣቱ ማዕከሉ ያለውን የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

ልህቀት በጥረት!
አክሱም ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
(ድረ-ገፅ) Official Website:www.aku.edu.et
(ትዊተር) Twitter:
(መፅሀፈ-ገፅ) Facebook:https://www.Facebook.com/aksumuniversity
(ዩ ቱዩብ)YouTube :www.YouTube.com/
(ቴሌግራም) Telegram : https://t.me/aksumuniversity2025
ሊንክድኢን: https://www.linkedin.com/company/aksum-university-official
ፖ.ሳ.ቁ. P.O.Box: 1010

Photos from Aksum University's post 18/05/2026

7ይ ዓመታዊ ዋዕላ ምርምር ቅዱስ ያሬድን ልሳነ ግዕዝን ብድምቀት ተኻይዱ
___________________//_________________

ኣኽሱም (ዩኒቨርሲቲ ኣኽሱም)፤ 10 ግንቦት 2018 ዓ.ም

ብምትሕብባር ዩኒቨርሲቲ ኣኽሱም፣ ርእሰ ኣድባራት ወገዳማት ኣኽሱም ፅዮንን ቤት ፅሕፈት ባህልን ቱሪዝምን ከተማ ኣኽሱምን ዝተዳለወ 7ይ ዓመታዊ ዋዕላ ምርምር ቅዱስ ያሬድን ልሳነ ግዕዝን ብድምቀት ተሳሳሊጡ ።እዚ ዋዕላ እዚ፣ ዓመታዊ በዓል ቅዱስ ያሬድ (ግንቦት 11) ምኽንያት ብምግባር "ውርሲታት ቅዱስ ያሬድን ልሳነ ግዕዝን ንህንፀት ታሪኽን መፃኢ ፅንዓትን" ብዝብል መሪሕ ቓል ኣብ ኣዳራሽ ቤት ፅሕፈት ባህልን ቱሪዝምን ከተማ ኣኽሱም ተኻይዱ።

እቲ ዋዕላ ብሃይማኖታዊ ፀሎትን ያሬዳዊ መዝሙርን ተዓጂቡ ዝተጀመረ ክኸውን ከሎ፣ ሓላፊ ቤት ፅሕፈት ባህልን ቱሪዝምን ከተማ ኣኽሱም ኣይተ ገብረመድህን ፍፁም ንተሳተፍቲ ናይ እንኳዕ ደሓን መጻእኩም መልእኽቲ ኣመሓላለፎም። ኣይተ ገብረመድህን ኣብ መደረኦም፣ ኣኽሱም ማእኸል ስልጣነ ዓለም ዝነበረት፣ ብምርምር ዘይተወድኡ ሰፊሕ ዝድህሰሱን ዘይድህሰሱን ሓድግታትን ታሪኽን ዝወነነት ቅድስቲ ከተማ ምዃና ኣስሚረምሉ።

ናይ ምርምርን ስግግር ቴክኖሎጅን ምኽትል ፕረዚደንት ዩኒቨርሲቲ ኣኽሱም ዶ/ር መኮነን ኣረጋይ ብወገኖም፣ ንተሳተፍቲ ናይ እንኳዕ ደሓን መጻእኩም መኽፈቲ መደረ ድሕሪ ምቕራብ፣ ኣኽሱም ንዓለም ዘበርከተቶ ስልጣነ ካብቲ ኣብ ኣእማን ተቐሪፁ ዘሎ ሓወልትታት ብተወሳኺ ኣብ ውሽጢ ብርዒ ልሳነ ግዕዝ ዝተሰነደ ዓብዪ ናይ ፍልጠት ውቅያኖስ ምዃኑ ገሊፆም። ቅዱስ ያሬድ ክሳብ ሕዚ ተመራሚርና ክንበፅሖም ዘይከኣልና ረቀቕቲ ስራሕቲ ንዓለም ዘበርከተ ዓብዪ ሊቅ ምዃኑ ዝገለፁ ዶ/ር መኮነን፣ እዚ ዋዕላ እዚ ስነ-ፍልጠታዊ ትንተና፣ ህንፀት ታሪኽን ናይ መፃኢ ፅንዓትን ዝብሉ ሰለስተ ዓበይቲ ዕላማታት መሰረት ብምግባር ዝተዳለወ ምዃኑ እውን ኣረዲኦም። ቁልፊ መልእኽቲ እዚ ዋዕላ ድማ ብክቡር ንቡርእድ ጎደፋ መርሃ—ናይ ርእሰ ኣድባራት ወገዳማት ኣኽሱም ፅዮን ኣመሓዳርን ናይ ማእኸላይ ዞባ ሃገረ ስብከት ስራሕ መካየድን ቀሪቡ እዩ።

ኣብዚ መድረኽ ሰለስተ ኣገደስቲ መፅናዕታውያን ፅሑፋት ዝቐረቡ ክኸውን ከሎ፣ መምህር ፃሃየ ንጉሰ ካብ ኮሌጅ መምህራን ዓድዋ "መዋእለ ህይወትን ኩለመዳያዊ ህላወን ቅዱስ ያሬድ" ብዝብል ርእሲ ፣ መምህር ስብሓት ገ/ሄር ካብ ዩኒቨርሲቲ ኣኽሱም "ንመፃኢ ግዜ ብሕሉፍ ታሪኽ ምውሓስ፦ ያሬዳዊ መበቆላዊ ፍልጠት ምስ ዘመናዊ ሜላታት ተፃዋርነት ንምውህሃድ ዝተዳለወ ኩለመደያዊ ቀመር" ብዝብል ርእሲ ፅሑፎም ዘቕረቡ እንትኸውን፣ መምህር ፍሳሃ ሃይሉ ካብ ዩኒቨርሲቲ ኣኽሱም ድማ "መፅናዕቲ ኣረባብሓ ኣስማትን ፆታ መፍለዪ ምዕላድን ኣብ ልሳነ ግዕዝ" ብዝብል ርእሲ ሰፊሕ ትንተናዊ መብርሂ ሂቦምሉ።

ኣብ መዛዘሚ እቲ ዋዕላ፣ ከንቲባ ከተማ ኣኽሱም ኣይተ ትኩእ ሃይሉ ንኣሰናዳእቲ እቲ ዋዕላን ንኣቕረብቲ መፅናዕታዊ ፅሑፍን ምስጋና ኣቕሪቦም። ኣይተ ትኩእ ኣብ ዘሕለፍዎ መልእኽቲ፣ "ንሕና ተጋሩ ኣኽሱማውያን ኢና፤ ስለዚ ድማ እዚ ዋዕላ ታሪኽናን መንነትናን እንፈልጠሉን ንካልኦት እውን ነፍልጠሉን ዓብዪ መድረኽ እዩ" ኢሎም። ካብ ቅዱስ ያሬድ ከም ተጋሩ ፅንዓትን ተስፋ ዘይምቍራፅን ተማሂርና፣ እዚ ሕዚ ገጢሙና ዘሎ ኩነታት ብትብዓት ክንሰግሮ ከም ዝግባእ ዝፅውዕ ናይ መዕፀዊ መደረ እውን ኣስሚዖም።

ኣብቲ መድረኽ መፅናዕታዊ ፅሑፍ ንዘቕረቡ ክኢላታት ናይ ምስጋና ሰርቲፊኬት ዝተዓደለ ክኸውን ከሎ፣ ዋና ፀሓፊ ቅዱስ ሲኖዶስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትግራይን ናይ ካናዳ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ብፁእ ኣቡነ ኣረጋዊ ብዝሃብዎ ቃለ ቡራኬ እቲ ዋዕላ ብዓወት ተዛዚሙ።

እዚ መድረኽ ብስነ-ፅሑፍን ብቅኔን ተዓጂቡ ከምቲ ናይ ዝሓለፈ ዓመት ብዝደመቐን ብዝሰፍሐን ኩነታት ተኸቢሩ ውዒሉ ።

ብቕዓት ብፃዕሪ!
ዩኒቨርሲቲ ኣኽሱም

ፈፃሚ ህዝባውን ዓለም-ለኻውን ርክባት!
(ወግዓዊ ድሕረ-ገፅ) Official Website: www.aku.edu.et
(ትዊተር) Twitter:
(መፅሓፈ-ገፅ) Facebook:h ttps://www.Facebook.com/aksumuniv
(ዩቲዩብ) YouTube :www.YouTube.com/ University 2025
(ቴለግራም) Telegram : https://t.me/aksumuniversity2025
ሊንክድኢን: https://www.linkedin.com/company/aksum-university-official
(ሳንዱቕ ቁፅሪ ፖስጣ) ሳ.ቁ.ፖ P.O.Box: 1010

16/05/2026

👉ማስታወቂያ👈

የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ
👇👇👇

15/05/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተና የሚለማመዱበት አድራሻ ይፋ ሆኗል።

-------------------------- // -------------------------

(ግንቦት 07/2018 ዓ.ም) ደጋግሞ መለማመድ የእውቀትን እና የክህሎትን ጉድለት ይሞላል፤ በራስ መተማመንን ያሳድጋል ሲል አገልግሎቱ ገልጿል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በበይነ መረብ (CBT) ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

በዚህም ሁሉም ተፈታኞች በተደለደሉበት ክልል ወይም ከተማ አስተዳደር ትይዩ ባለው ማስፈንጠሪያ በመጠቀም USER Name በሚለው ላይ የፈተና አዳራሽ መግቢያ ካርድ ላይ ያለውን አድሚሽን ቁጥር በማስገባት እና Pass word በሚለው ላይ 1234 በማስገባት መጠቀም እንደሚችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ፈተናውን ለመለማመድም በዴስክቶፕ ኮምፕዩተር፣ በላፕቶፕ ኮምፕዩተር፣ በታብሌት፣ በስልክና በመሰል የኤልክትሮኒክስ መሣሪያዎች ማንኛውንም ዓይነት ኢንተርኔት አማራጭ በመጠቀም ከግንቦት 07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከፈተናው ድረስ መለማመመድ እንደሚችሉም ገልጿል።

ተፈታኞች አዲሚሽን ካርድ ከየትምህርት ቤታቸው ማግኘት እንደሚችሉ የተገልጸ ሲሆን በየጊዜው ተማሪዎች የሚለማመዱባቸውን ፈተናዎች በተከታታይ የምንሰጥ መሆኑንም አገልግሎቱ አብራርቷል።
በመሆኑም መምህራን ፣ የትምህርት ቤት አመራርና ወላጆች ተፈታኝ ተማሪዎች እንዲለማመዱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን።

ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
ዩቱዩብ- https://www.youtube.com/-of-education-ethiopia
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

14/05/2026

👉 Call For 7th Research Conference On St. Yared And Geez Language.👈
👇👇👇

12/05/2026

📢 NOTICE TO ALL NEWLY MATCHED RESIDENTS 🎓🏥
Aksum University CHS & Comprehensive Specialized Hospital is pleased to announce the official admission and registration schedule for all newly deployed Residency Program students for the 2026 G.C academic year.
📅 Reporting Date:
May 17, 2026 G.C
📅 Registration Dates:
May 18–19, 2026 G.C
📍 Venue:
CHS & Comprehensive Specialized Hospital Administration Office, Referral Campus, Aksum University
📄 Required Documents
✔️ NGAT examination certificate
✔️ Official transcript transfer proof
✔️ Clearance letter from previous workplace
✔️ Degree certificate and student copy
✔️ Academic credentials (Grades 8–12)
✔️ Sponsorship letter (if applicable)
✔️ Four passport-size photographs
⚠️ All documents are strictly required for admission and registration.
📞 For further information:
Dr. Mebrahtu G/silassie – 0914537006

Welcome to Aksum University College of Health Sciences and Comprehensive Specialized Hospital and best wishes as you begin your residency training journey!

12/05/2026

Today, on International Nurses Day, we proudly honor and celebrate the incredible nurses of Aksum University CHS & Comprehensive Specialized Hospital

Every day, our nurses serve with unwavering dedication, compassion, courage, and resilience. They are the heart of patient care — saving lives, comforting families, promoting health, preventing disease, and standing at the frontlines during every challenge.

Your commitment, sacrifice, and humanity continue to inspire us all. The impact you make in the lives of patients and the community is immeasurable.

On this special day, we extend our deepest gratitude and appreciation to all nurses for your tireless service and professionalism.

Happy International Nurses Day! 💙

Photos from Aksum University's post 09/05/2026

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የIFMIS ዲጂታል ሥርዓት ትግበራ የርክክብና የሽኝት መርሃ-ግብር ተከናወነ
_______________//_________________

አክሱም ዩኒቨርሲቲ፡ ግንቦት 01፣ 2018 ዓ.ም

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የIFMIS (Integrated Financial Management Information System) ዲጂታል ሥርዓት አጠቃቀምና አፈጻጸም ዙሪያ ከገንዘብ ሚኒስቴር ከመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር የውይይት፣ የርክክብና የሽኝት መርሃ-ግብር በትናንትናው ዕለት በድምቀት ተከናውኗል።

በዚህ ጉልህ መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ነጋሽን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊዎችና ከገንዘብ ሚኒስቴር የተወከሉ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው የምክክርና የርክክብ ሂደቱን አከናውነዋል።

የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብርሃም ነጋሽ በመርሃ-ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የIFMIS ሥርዓት ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመን የሚተገበር የተቀናጀ የዲጂታል መፍትሄ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህ ሥርዓት ሀብትና ጊዜን በቁጠባ በመጠቀም ረገድ ያለውን ፋይዳ በመጥቀስ፣ ቀደም ሲል በነበሩ የአሰራር ሂደቶች ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም ሥርዓቱ ተደራሽነትን ባረጋገጠ መልኩ ተግባራትን በቅልጥፍና እና በብቃት ለመከወን እንደሚያስችል በመጠቆም፣ ይህ ዲጂታል የሥራ ሥርዓት በዩኒቨርሲቲው ተግባራዊ እንዲሆን የላቀ ድጋፍ ላደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር እና ላለፉት ስድስት ወራት በትጋት ሥልጠና ሲሰጡ ለቆዩ ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል የገንዘብ ሚኒስቴርን በመወከል በመድረኩ ላይ የተገኙ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች በበኩላቸው፤ በዩኒቨርሲቲው በነበራቸው ቆይታ የታዘቡትን የሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነትና ለለውጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

የIFMIS ሥርዓት የሀገራዊ "ዲጂታል ኢትዮጵያ" ፖሊሲ ዋና አካል መሆኑን በመግለጽ፣ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ ሐሳቦችንም አቅርበዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለሥርዓቱ ቀጣይነትና ስኬታማነት አስፈላጊውን የቴክኒክና የሙያ ድጋፍ ለማድረግ ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑንም በዚሁ መድረክ አረጋግጠዋል።
ይህ የርክክብ መርሃ-ግብር ከተሳታፊዎች በቀረቡ ገንቢ አስተያየቶችና በቀጣይ የትብብር አቅጣጫዎች ላይ በተደረገ ውይይት የታጀበ ሲሆን፤ ላለፉት ስድስት ወራት ስልጠና ሲሰጡ ለነበሩ ባለሙያዎች የዕውቅና እና የምስጋና ሰርቲፊኬት በመስጠት ተጠናቋል።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊውን የIFMIS ዲጂታል ሥርዓት በሥራ ላይ ካዋሉ ግንባር ቀደም የመንግስት ተቋማት ተርታ መሰለፉ ይታወቃል።

ልህቀት በጥረት!
አክሱም ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

(ድረ-ገፅ) Official Website:www.aku.edu.et
(ትዊተር) Twitter:
(መፅሀፈ-ገፅ) Facebook:https://www.Facebook.com/aksumuniversity
(ዩ ቱዩብ)YouTube :www.YouTube.com/
(ቴሌግራም) Telegram : https://t.me/aksumuniversity2025
ሊንክድኢን: https://www.linkedin.com/company/aksum-university-official
ፖ.ሳ.ቁ. P.O.Box: 1010

Photos from Aksum University's post 08/05/2026

Aksum University Hosts Annual Research Conference on Heritage and Tourism
________________//______________
AKSUM, Tigray, Ethiopia — Under the strategic theme "Bridging History and Future: Sustainable Heritage Management for Tourism Revitalization," Aksum University’s Institute of Archaeology and Tourism (IAT) officially convened its annual research conference on April 30, 2018 E.C. The event was organized through a close collaboration between the IAT and the university’s Research, Publication, Ethics, and Dissemination Directorate, bringing together senior management, academic staff, and students.
The proceedings began with a welcome address from Mr. Woldu G/slasie, Vice Director for Research, Community Service, and Technology Transfer at the IAT.

This was followed by an opening keynote from Dr. Desta G/tekle, Special Advisor to the Vice President for Research and Technology Transfer. Dr. Desta emphasized the university's unwavering commitment to academic excellence and framed heritage preservation not just as a scholarly pursuit, but as a vital tool for the broader regional recovery of Tigray.

The heart of the conference consisted of rigorous research presentations that explored the intersection of archaeological preservation and the socio-economic impacts of recent regional conflicts.

One major study focused on the conceptualization of the Adwa battlefield for potential registration as a UNESCO Tangible Heritage site, while another provided a sobering analysis of archaeological management challenges, including the pressures of war, development, and looting within the Central Zone.

Furthermore, the audience examined a detailed tourism impact assessment regarding businesses in Aksum, Adwa, and Abyi Addi, as well as critical findings from rescue archaeology and urgent preservation efforts in the Hahayle and La’elay Adyabo weredas.

Following an engaging Q&A session that delved into the practicalities of revitalizing the tourism sector, the event concluded with an official certificate ceremony to recognize the contributors' academic efforts.

In his closing remarks, Dr. Berihu Teklu, the Research, Publication, Ethics, and Dissemination Director, underscored the indispensable role that sustainable heritage management plays in bridging the gap between Tigray's storied past and its economic future.

Excellence Through Perseverance!
Contact and Media Information
For more information, you may visit our official website at www.aku.edu.et or connect with us on our social media platforms. We are active on Twitter at and on Facebook at facebook.com/aksumuniversity. Detailed video coverage and updates are available on our YouTube channel, , and you can join our community on Telegram via t.me/aksumuniversity2025. For professional inquiries, please visit our LinkedIn page under Aksum University Official or contact us via P.O. Box 1010, Aksum, Ethiopia.
Public and International Relations Executive Office
Aksum University

Photos from Aksum University's post 08/05/2026

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በአካቶ ትምህርትና ተደራሽነት ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ተካሄደ
******************//****************

አክሱም ዩኒቨርሲቲ፦ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ሥነ-ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል አስተባባሪነት "በአንድነት ለአካታችነት፦ ተደራሽና ምቹ የትምህርት አካባቢን መፍጠር" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ ተካሂዷል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ገብረየሱስ ብርሃነ መርሃ ግብሩን በንግግር ሲከፍቱ እንደገለጹት፤
"ክቡራን እንግዶች፣ ክቡራን መምህራን እና ውድ ተማሪዎች፤ አስቀድሜ በዚህ ወሳኝ በሆነው የአንድነት ለእኩልነትና አካታችነት ወርክሾፕ ላይ በመገኘታችሁ የተሰማኝን ጥልቅ ደስታ መግለጽ እወዳለሁ። ወደዚህ የዕውቀትና የለውጥ መድረክ እንኳን በደህና መጣችሁ። ይህ ወርክሾፕ በዩኒቨርሲቲያችን ውስጥ እያንዳንዱ ግለሰብ እኩል ዕድል እንዲኖረው፣ እንዲከበርና ተጠቃሚ እንዲሆን ያለንን ጽኑ ቁርጠኝነት በተግባር የምናሳይበት ትልቅ መድረክ ነው። ለእኛ አካታችነት ተራ ቃል ብቻ ሳይሆን ሁላችንም የምንጋራው የሞራልና የሙያ ኃላፊነት ጭምር ነው። ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራትና የብቃት ማዕከል ብቻ ሳይሆኑ፣ ልዩነት የሚከበርበት፣ እኩልነት በተግባር የሚታይበትና አካታችነት ለሌሎች ተምሳሌት የሚሆንበት መድረክ መሆን አለባቸው።

አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የማህበረሰባችን የማይነጠሉና ወሳኝ ክፍሎች ናቸው። በመሆኑም በትምህርት ጉዟቸው ላይ የሚገጥሟቸውን ማንኛውንም ዓይነት አካላዊ፣ ማህበራዊም ሆነ መዋቅራዊ መሰናክሎች ማስወገድ የሁላችንም ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል።

ይህ ወርክሾፕ በዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ውስጥ ግንዛቤን ከማሳደግ ባለፈ፣ አካታችነትን በተግባር ለመደገፍና ለማበረታታት ትልቅ ዕድል ይፈጥርልናል።

ስለሆነም በአንድነት እንማር፣ እርስ በርስ እንተዋወቅ፣ እንዲሁም ለጋራ ለውጥ በቅንጅት እንሥራ። ሁሉንም አካታች የሆነ የትምህርት አካባቢ መፍጠር ዩኒቨርሲቲያችንን ያጠነክረዋል፤ ለማህበረሰባችንም የሚኖረውን ሚና የላቀ ያደርገዋል።

በመጨረሻም ይህንን እጅግ አስፈላጊ ዝግጅት በከፍተኛ ጥረት ላዘጋጁት የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል አባላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ሁላችንም አብረን እንማር፣ አብረን እንሥራ፤ ማንም ወደኋላ የማይቀርበትንና ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ዩኒቨርሲቲ በጋራ እንገንባ።" የሚል መልእክት አስተላልፏል።

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ጎይትኦም ወ/ሊባኖስ በበኩላቸው መድረኩ የተዘጋጀው አካል ጉዳተኞች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑና በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ሦስት ዋና ዋና የመወያያ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን፤ መምህር ግደይ ገ/መድህን የልዩ ፍላጎት ድጋፍ ማዕከል አመሰራረትና ዓላማን በሚመለከት፣ መምህርት አሰፉ አዲስ በአካቶ ትምህርት ተደራሽነትና ምቹ ትግበራ ዙርያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ፣ እንዲሁም መምህር ለአከ መኮነን የአካል ጉዳተኞችን የሚመለከቱ ሕጎችና ደንቦች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። እነዚህን ጽሁፎች መነሻ በማድረግም ከተሳታፊዎች ጋር ጥልቀት ያለው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በተጨማሪም በመድረኩ ላይ የማዕከላዊ ዞን የዓይነ ስውራን ማህበር ሊቀመንበር መምህር የማነ የውሃንስ፣ ከዞኑ ዓቃቢ ሕግ ጽህፈት ቤት አቶ አበበ ጎደፋይ እና በትግራይ ክልል የአካል ጉዳተኞች ተሟጋችና ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑት ወ/ሪት ታሪክ ታደሰ ተገኝተው የግል ተሞክሯቸውንና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ለተሳታፊዎች አጋርተዋል።

በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙሉጌታ በሪሁ ባስተላለፉት የመዝጊያ መልዕክት፤ ዩኒቨርሲቲው አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ከማስተማር ባለፈ ምን ያህሉ ሥራ አግኝተዋል ወይም ሥራ ፈጥረዋል የሚለውን መከታተልና መደገፍ እንዳለበት አሳስበዋል።

ለዚህም ሥራዎችን በትክክል በሰነድ በማስፈር በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚገባ ጠቁመው፣ መድረኩ ለወደፊት ሥራዎች ትልቅ ተሞክሮ የሰጠ መሆኑን በመግለጽ ዝግጅቱን ተጠናቀዋል ።

ልህቀት በጥረት!
አክሱም ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

(ድረ-ገፅ) Official Website:www.aku.edu.et
(ትዊተር) Twitter:
(መፅሀፈ-ገፅ) Facebook:https://www.Facebook.com/aksumuniversity
(ዩ ቱዩብ)YouTube :www.YouTube.com/
(ቴሌግራም) Telegram : https://t.me/aksumuniversity2025
ሊንክድኢን: https://www.linkedin.com/company/aksum-university-official
ፖ.ሳ.ቁ. P.O.Box: 1010

Want your school to be the top-listed School/college in Aksum?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

http://www.aku.edu.et/

Address


Aksum University
Aksum

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:30
Tuesday 08:00 - 17:30
Wednesday 08:00 - 17:30
Thursday 08:00 - 17:30
Friday 08:00 - 17:30