Derartu Tulu Preparatory School Former Student

Derartu Tulu  Preparatory School  Former Student welcome to Derartu Tulu preparatory school students page.it ownership is listed as Government . Thi Derartu Tulu owernship is listed as Government .

Derartu Tulu School is located in the Akaki-Kaliti zone in Addis Ababa region in Ethiopia. This Secondary School in Ethiopia has an enrolment of 1282 with a the total number of teachers being80. The school has students from grades 11->12. The Schools address is PO BOX and their phone number is 0114343278

If you have more information on the school or would like to claim this listing please make a comment or email us. [email protected]

29/05/2025

1,070,000 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ!

"ልጄ ለሞተ ሰው አልቅስለት እዘንለት ራስህንም አሳዝን እንደ ሥርዓቱም መታሰቢያን አርግለት ያገለገለሀን ሰው ሞት ቸል አትበል:: ከልብህ አልቅስለት አጽንተህም እዘንለት እንደ አገሩም ልማድ አልቅስሰት ስለ አገሩም ሕግም አንድ ቀን ሁለት ቀን አልቅስለት::" ሲራክ 38÷15-16

ወንድማችን ዶክተር ተሾመ እሸቱ በአዳማ ሆስፒታል ሲያገለግል የቆየ እንቁ የአጥንት እስፔሻሊስት ሀኪም ነው፡፡
ወንድማችን ብዙ ህሙማንን ያገለገለ ለኢትዮጵያን ብዙ ተስፍ ያለው እንቁ ሀኪም ነበር ።

ነገርግና ምን ሆነ ተገደለ?! ሞቶ አረፈ፡፡

እኔ ይገርመኛል በሀገራችን የአጥንት እስፔሻሊስት ሀኪሞች ትንሽ ናቸው በጣም አናሳ ናቸው፡፡

የሚገርመው 1 የእጥንት እስፔሻሊስት ሀኪም ለ1,070,000 ሰዎች ነው አግልግሎት እየሰጠ ያለው፡፡

ዶክተር ተሾመ እሸቱ ሞተ ማለት 1,070,000 ኢትዮጵያዊያን ሞቱ ማለት ነው፡፡

ትናንት የሞተው አንድ ዶክተር ሳይሆን 1,070,000 ኢትዮጵያዊያን ናቸው፡፡
⚓️ይህን ማን አስተዋለ?!
⚓️እንዴት ማስተዋል አቃተን?!

እንዳትሳሳቱ ትላንት የሞተው 1,070,000 ኢትዮጵያዊያን ናቸው።

ኢትዮጵያ ባድራዋን ዝቅ አርጋ ልታዝን ይገባት ነበር ነገር ግን ገዳይ ሆና ተገኝታለች፡፡ እኛ ጭራሽ ያገለገለንን ሰው ልናዝንልት ይቅርና እንገለዋለን!

ኢትዮጵያዊያ ሆይ ወዴት ነው እየሄድክ ያለሹ/ያለኽው?!
ምንድ ነው እያደረግሽ ያለሽው/ያለኽው?!

©Dn. Dr. Tadesse Fanta Gela (General surgeon)

የመልካምነት እና የደግነት ጥግእኚህን አባት የማያቃቸው እጃቸው ያልፈወሰው በተለይ በአቃቂ እና ቃሊቲ አካባቢ የሚኖር ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም።አሸናፊ ወ/ጨርቆስ ይባላሉ፤ በአቃቂ ወረዳ 02...
02/01/2025

የመልካምነት እና የደግነት ጥግ

እኚህን አባት የማያቃቸው እጃቸው ያልፈወሰው በተለይ በአቃቂ እና ቃሊቲ አካባቢ የሚኖር ሰው ይኖራል ብዬ አላስብም።
አሸናፊ ወ/ጨርቆስ ይባላሉ፤ በአቃቂ ወረዳ 02 ቴሌ አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው መድኃኒት በሆነው እጃቸው ታሽቶ ድኖ የፈለገውን ገንዘብ ሸጎጥ አድርጎ ከሌለውም እግዚአብሔር ይስጥልኝ ብሎ የሚታሽ ብዙ ነው።
ታዲያ እነዚህን መልካም አባት ሰምኑን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከዚህ በፊት ደግሞ ሸገር FM ዘገባ ሰርተውላቸው ነበር እረ እነደውም የሆነ ወቅት ላይ የአመቱ በጎ ሰው ላይ እንዲታጩ እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር አልተሳካም እንጂ።
አቃቂ አካባቢ ተፅዕኖ ፈጣሪ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ እንዲሁም ቲክቶከር የለም?? ለነገሩ የግድ አቃቂ አካባቢ ብቻ መሆን የለም ደግነታቸው ብሔርን ሰፈርን ጎሣን ያማከለ አደለም። በቃ ንፁህ ደግነት መታደል ነው።
እባካችሁ እኚህን አባት በማስተዋወቅ እና የበኩላችንን አስተዋጽኦ በማድረግ የሚጦሩበትን የሚሸለሙበትን የሚመሰገኑበትን መንገድ እንፍጠር።
አባታችን እድሜና ጤናውን ፈጣሪ ይስጥዎት እናመሰግናለን 🙏🙏🙏
መልካሞች በጠፋበት መልካም ሆኖ መገኘት መታደል ነው።

ለወዳጆቾ ያጋሩ ! ወደ ጋሼ ጋር ሲታመሙ መሄድ ብቻ ሳይሆን የሚገባቸውን ክብር እንስጥ ።ጋሽ አሸናፊ ወልደ ጨርቆስ የ2016 ዓ።ም የዓመቱ በጎ ሰው ተሸላሚ እንዲሆን የተቀመጠውን ምሥል በተቀ...
30/05/2024

ለወዳጆቾ ያጋሩ !

ወደ ጋሼ ጋር ሲታመሙ መሄድ ብቻ ሳይሆን የሚገባቸውን ክብር እንስጥ ።

ጋሽ አሸናፊ ወልደ ጨርቆስ የ2016 ዓ።ም የዓመቱ በጎ ሰው ተሸላሚ እንዲሆን የተቀመጠውን ምሥል በተቀመጡ አድራሻዎች በመላክ ጥቆማ እማ ድምጽ እንስጥ ።

ፍልቅልቋ 😁 “እኔ የገጠር ልጅ ነኝ እናቴ ደግሞ የምንጊዜም ተምሳሌቴ ነች” - አትሌት ደራርቱ ቱሉእንደ አፍሪካ በኦሎምፒክ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ማግኘት የቻለች ቀዳሚያችን ናት፡፡ በፍ...
08/03/2024

ፍልቅልቋ 😁

“እኔ የገጠር ልጅ ነኝ እናቴ ደግሞ የምንጊዜም ተምሳሌቴ ነች” - አትሌት ደራርቱ ቱሉ

እንደ አፍሪካ በኦሎምፒክ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ማግኘት የቻለች ቀዳሚያችን ናት፡፡ በፍልቅልቅነቷ ትታወቃለች፡፡ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከአፏ አይጠፋም፡፡ ብዙዎች በስምምነት ይወዷታል፤ የሀገርን ባንዲራ ከፍ በማድረጓ ያመሰግኗታል፤ ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉ

ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴቶች ብቻ የተመራ ልዑካን ቡድን ወደ ለንደን አቅንቷል፡፡
ታዲያ ከልዑኩ ጋር ያቀናችው ፈር ቀዳጇ አትሌት ደራርቱ ከጉዞዋ ቀደም ብሎ ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡
በቆይታዋም “ለአንቺ ተምሳሌት ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ቀረበላት… (ከረጅም ሳቅ በኋላ) የመጀመሪያዋ ተምሳሌት እናቷ መሆኗን ገልፃለች፡፡

እንዲህ ነበር ያለችው… “እኔ የገጠር የአርሶ አደር ልጅ ነኝ፤ እናቴ ደግሞ ታታሪ ነች፤ ተምሳሌቴ ለእኔ እናቴ ነች፡፡” ምክንያቱም ደሞ ትላለች ደራርቱ፤ ምክንያቱም “እኔ እንደነ አበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴ እና ምሩጽ ይፍጠር ያሉ ጀግኖች አትሌቶችን እያየሁ ቢሆንም ያደኩት ተምሳሌት የምላት ብቸኛዋ ሴት ግን እናቴ ነበረች” ስትል ስሜቷን አጋርታናለች፡፡ ከዚህ ባሻገር የሴቶች ቀን መከበርን አስመልክቶ በሰጠችው አስተያየት የበዓሉ መከበር ለሴቶች ተጨማሪ መልካም ዕድል ይዞ የሚመጣ መሆኑን ትናገራለች፡፡

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሪነት ደረጃ በርካታ ሴቶችን መመልከት እየተለመደ መምጣቱንም በማንሳት ይህም በስራ አፈፃፀም ጭምር የሚታይ መሆኑን አስረድታለች፡፡ በአርሲ በቆጂ የተወለደችው አትሌት ደራርቱ ቱሉ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአመራርነት እያገለገለች የምትገኝ ሲሆን ለሀገሯ ከ15 በላይ የወርቅ፣ ብር እና ነሐስ ሜዳሊያዎችን አስገኝታለች፡፡

መልካም የሴቶች ቀን ንግስታችን አንቺ የኢትዮጵያ ተምሳሌት አራያችንም ጭምር ነው በተለይም በስምሽ በተሰየመው እውቀትን በሚያንፀው ትምህርት ቤት መማር መታደል ነው።

እረጅም እድሜን ከጤና ጋር ይስጥልን።🙏🙏🙏

01/01/2024
  😭አመታዊው የቅዱስ ገብርኤልን በአለ-ንግስ   በቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንግሠው እየተመለሱ የነበሩ የአቃቂ ልጆች በመንገድ ላይ ምን አጋጠማቸው ?ከአቃቂ ባቡር ጣቢያ መገላ ሠፈር 1...
31/12/2023

😭

አመታዊው የቅዱስ ገብርኤልን በአለ-ንግስ በቁልቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንግሠው እየተመለሱ የነበሩ የአቃቂ ልጆች በመንገድ ላይ ምን አጋጠማቸው ?

ከአቃቂ ባቡር ጣቢያ መገላ ሠፈር 18 የሚጠጉ እህት እና ወንድሞች በአንድነት የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ-በዓልን በቁልቢ አንግሠው ሲመለሱ መተሃራ ከተማ መግቢያ ላይ በታጣቂዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል ።

ከእነዚህ መካከል ደግሞ ሁለት እህቶች አንዷ እግሯን አንዷ እጇን በጥይት ተመትው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ተርፈው የመጡ እህቶችና በወቅቱ ድርጊቱን ከተመለከቱ ተጓዦች በተገኘው መረጃ እስከ አሁን ሦስት ወንድሞች በጥይት ተደብድበው ከተገደሉ በኋል የተጓዙበትን መኪና እና አስከሬናቸውን ተቃጥሏል ።

አብረው ከተጓዙት ውስጥ ደግሞ ወደ 13 ገደማ የሚሆኑ እህት እና ወንድሞች ታግተው እስከ አሁን ያሉበት ሁኔታ አልታወቀም ።

ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት በጠዋት ወደ መተሐራ ከተማ በመሄድ ለመጠየቅ ቢጥሩም አስከሬናቸውን ማግኘት እንደማይችልና መለየትም አስቸጋሪ ስለነበረ ቀሪ አካላቸው በአንድነት እንዳረፈ ተገልጾላቸው ተመልሰዋል ።

የገሚሱ ቤተሰብ በሃዘን ገሚሱ በጭንቀትና በቁጭት ከፍተኛ ሃዘን ላይ ይገኛሉ ። የተቀሩትን ወንድሞች እና እህቶች ያሉበት መስማትም ምን እንደሆኑ ማወቅ ባለመቻሉ ጭምር የከተማ ህዝብ በሙሉ በሃዘን ላይ ይገኛል ።

ለመላው ቤተሰብ እንዲሁም የከተማ ህዝብ በሙሉ ብርታት እና መጽናናት ይሁን ! ።

#መረጃው ከአቃቂ ከተማ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ ነው ! ።

ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በአንደኝነት ከፍተኛ ውጤት የመጣበት ስኩል ኦፍ ኢንዲያና ሲሆን (640) በሁለተኝነት ደግሞ ደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይከተላል (634)
12/10/2023

ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በአንደኝነት ከፍተኛ ውጤት የመጣበት ስኩል ኦፍ ኢንዲያና ሲሆን (640) በሁለተኝነት ደግሞ ደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይከተላል (634)

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ከፍተኛ የተባለውን ውጤት ያመጡትን ብቻ ለመጥቀ...
12/10/2023

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ከደራርቱ ቱሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ፡፡

ከፍተኛ የተባለውን ውጤት ያመጡትን ብቻ ለመጥቀስ ያህል፡

1ኛ, አቤል ደምለው - 634

2ኛ, እዮቤድ ወልደአብ - 606

3ኛ, ሰመሀል ሀብተኪሮስ - 571

4ኛ, ቤተልሔም ታደሰ - 545

26/09/2023

የአቃቂ ልጆች የበዓል ቀንዎን በባላገሩ ቲቪ ያሣልፋ!!
መልካም የመስቀል እና መውሊድ በዓል 🕌💒

ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የበጎ ሰው 2014 ልዩ ተሸላሚ!!..ይገባታል!!🙏🙏🙏
04/09/2022

ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የበጎ ሰው 2014 ልዩ ተሸላሚ!!..ይገባታል!!🙏🙏🙏

ደራርቱ ቱሉ ገመቹደራርቱ ቱሉ የተወለደችው በቆጂ በምትባል የኢትዮጵያ መንደር ነው። በትምህርት ቤቷ በተዘጋጁ ሩጫዎች ውስጥ ጎልቶ መታየት ጀመረች እና ትኩረቷን በፍጥነት ወደ ሀገር አቀፍ ደረ...
17/08/2022

ደራርቱ ቱሉ ገመቹ

ደራርቱ ቱሉ የተወለደችው በቆጂ በምትባል የኢትዮጵያ መንደር ነው። በትምህርት ቤቷ በተዘጋጁ ሩጫዎች ውስጥ ጎልቶ መታየት ጀመረች እና ትኩረቷን በፍጥነት ወደ ሀገር አቀፍ ደረጃ አሰፋች።

እ.ኤ.አ. በ 1989 በስታቫንገር (ኖርዌይ) በተካሄደው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፋ 23ኛ ሆና አጠናቃለች። ከጥቂት አመታት በኋላ በ1992 በአምበሬስ በተካሄደው ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ በማግኘት የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሴት ሆነች።

እ.ኤ.አ. በ 1991 በቶኪዮ የዓለም ሻምፒዮና ተሳተፈች ፣ የመጀመሪያዋ ትልቅ ውድድሯ መሆኑ ነው፣ በ10,000 ሜትር ስምንተኛ ሆና አጠናቀቀች። በቀጣዩ አመት በ1992 የባርሴሎና ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ ከሰሃራ በታች ካሉ አፍሪካውያን የመጀመሪያዋ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።

በእንግሊዝ ዱራም የሃገር አቋራጭ የዓለም ሻምፒዮን ሆና እስከታወቀችበት ጊዜ ድረስ በጉልበቷ ላይ የደረሰባት ጉዳት እስከ 1995 ድረስ ከውድድሩ እንድትርቅ አድርጓታል።

እ.ኤ.አ. በ 2000 በሲድኒ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ተሳተፈች ፣የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታ የተሻለ የግል ጊዜዋን እሳየች እና 30፡17፡49 የሆነ አዲስ የኦሎምፒክ ሪከርድ አስመዝግባለች። በሚቀጥለው አመት የለንደን ማራቶን አሸነፈች እና ከዚያም በ 10,000 ሜትር የመጀመሪያውን የአለም ሻምፒዮና በኤድመንተን አሸንፋለች።

በ 32 ዓመቷ ማንም ሳያምንባት በ2004 የአቴንስ ኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ በመሳተፍ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

ደራርቱ ቱሉ በአሁኑ ወቅት በሴት አፍሪካውያን ሯጮች በተለይም በኢትዮጵያውያን የበላይነት ፈር ቀዳጅ ተደርጋ ትጠቀሳለች። በታሪክ ከምርጥ የርቀት ሯጮች አንዷ ስትሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ውጤት ያስመዘገበች ከሰሃራ በታች የመጀመሪያዋ አትሌት ነበረች።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አባል የሆነችው ደራርቱ ቱሉ በኢትዮጵያ አርሲ ደጋማ አካባቢዎች ከብት በመጠበቅ ነው ያደገችው። እስከ 16 ዓመቷ ድረስ ከወትሮው በተለየ ፈጣን ሯጭ እንደነበረች አላወቀችም።

የአፍሪካ ተስፋ

እ.ኤ.አ. በ1992 የ10ሺ ሜትር የኦሎምፒክ ፍፃሜ ውድድር የደቡብ አፍሪካዋ ኤላና ሜየር ከ6ኪሜ ሩጫ በኋላ ዙሩን አክርራ መምራት ብትጀምርም ጀግናዋ ደራርቱ ቱሉ ግን አንገት ለአንገት ተናንቃ የመጨረሻው ዙር ከመጀመሩ በፊት ደራርቱ ወደ መሪነት በመግባት በ30 ሜትር ርቀት ማሸነፍ ችላለች። የኦሎምፒክ ሜዳሊያ ያስገኘችው የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካዊት ሴት ደራርቱ እና ደቡብ አፍሪካዊቷ ሜየር ለአዲስ አፍሪካ ተስፋን ለሚያሳይ የድል ዙር እጅ ለእጅ ተያይዘው ሄዱ።

በ1996 ኦሎምፒክ ሁለት ኢትዮጵያውያን ወደ መድረኩ ቢመለሱም ተስፋ አስቆራጭ በሆነ አራተኛነት አጠናቀዋል። ሆኖም የሩጫ ህይወቷ ገና አልተጠናቀቀም። በ2000 የሲድኒ ጨዋታዎች ደራርቱ እንደገና በ10,000ሜትር ከስምንት አመታት በፊት ያሳለፈችውን መልሳ በመምራት የፍፃሜውን ዙር በማሳየት እና የቡድን አጋሯን ጌጤ ዋሚን በማሸነፍ ግልፅ ድል ተቀዳጅታለች። ደራርቱ በኦሎምፒክ የርቀት ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማስመዝገብ የመጀመሪያዋ ሴት ሆናለች። እ.ኤ.አ. በ2004 በአቴንስ ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች (የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ ቻይናዊቷ ሁዪና ዢንግ፣ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ፣ የደራርቱ የሀገሯ ልጅ እጄጋየሁ ዲባባ)።

Address

Ak'ak'i Besek'a

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251114343278

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Derartu Tulu Preparatory School Former Student posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Derartu Tulu Preparatory School Former Student:

Shortcuts

Share

Category