Agarfa ATVET College

Agarfa ATVET College

Share

Agarfa Agricultural TVET College is one of the Federally administered colleges under the Ministry of

Photos from Agarfa ATVET College's post 25/04/2026

የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ለሶስት ዓመታት በደረጃ አራት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አሰመረቀ።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

የአጋርፋ ኮሌጅ በሰብል ልማት፣ በመሬት አስተዳደር እና ተፈጥሮ ሀብት ያሰለጠናቸውን በመደበኛ 514 በቅዳሜና እሁድ ፕሮግራም 78 ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመረቀ።

በምረቃው መግቢያ ላይ የክሌጁ ዲን አቶ ፊራኦል ኤደኦ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ ከብዙ ልፋትና ጥረት በኋላ ለዛሬ ቀን ስለበቃችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለው። በሀገራችን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአንበሳውን ድርሻ የምትይዙት እናንተ ስለሆናችሁ የተጣለባችሁን ከፍተኛ ሀላፊነት እንድትወጡ አደራ እላለሁ ብለዋል ።

በምረቃ ስነስረዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የህዝብ ተወካዮች የምክር ቤት ዓባል የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ብረሀነመስቀል ጠና ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ የዘንድሮ ተመራቂዎች ለየት የሚያደርጋችሁ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሚካሄድበት ዋዜማ ላይ የተመረቃችሁ መሆኑ ነው ብለዋል።

የተከበሩ ፕሬዝዳንቱ አክለውም እናንተ የዛሬ ተመራቂዎች ለሀገራችሁ ልማትና እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላችሁ በመሆኑ ተግታችሁ እንድትሰሩ ሲሉ አሳስበዋል።

በስራና ክህሎት ሚንስቴር የቴክኒክና ሙያ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት የተከበሩ አቶ ጌታቸው ደምሴ በበኩላቸው ተመራቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ የወደፊት የስራ አቅጣጫ በመስጠት አጠቃለዋል።

ሚያዚያ 17/2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

Photos from Agarfa ATVET College's post 16/04/2026

የአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ያመረተውን የቀይ ሽንኩርት ምርት ለገበያ አቀረበ።
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

የአጋርፋ ኮሌጅ በሶስት ሄክታር ላይ ካለማውን የቀይ ሽንኩርት ምርት ውስጥ አንድ ሄክታር ላይ ያለውን ለገበያ አቅርቧል።

ኮሌጁ የአከባቢው ማህበረሰሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ በተለያዩ የአከባቢ ገበያዎች በመዘዋወር ገበያ የማረጋጋት ስራ በሰፊው ሰርቷል።

ከኮሌጁ ሰራተኞች አልፍ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጠጥ የሚሰራው ኮሌጁ ቀሪውን ሁለት ሄክታር ለማህበረሰቡ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑን የክፍሉ ሀላፊዎች ገልጸዋል።

ሚያዚያ 2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

Photos from Agarfa ATVET College's post 09/04/2026

የባሌ ዞን የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ የሴቶች ቀን(March 8) በደማቅ ሁኔታ አከበረ።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

የባሌ ዞን የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ከአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ጋር በመተባበር በዞን ደረጃ የሴቶች ቀን(March 8) በአጋርፋ ኮሌጅ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

ሴቶች ከነበረባቸው የጭቆና ቀንበር የተላቀቁበት፣ሀሳባቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን የተጎናጸፉበት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት ያገኙበትነ ቀን በማስመልከት በባሌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ከአጋርፋ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በተለያዩ ፕሮግራሞች የተከበረ ሲሆን በመጨረሻም የፓናል ውይይት በማድረግ ተጠናቋል።

የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የህ/ግ/ኮ/ሥ/አሰፈጻሚ

Photos from Agarfa ATVET College's post 08/04/2026

ከዲንሾ ብሄራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ ለተነሱ የማህበረሰብ አባላት የስንዴ ድጋፍ ተደረገ።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም
አጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ

አጋርፋ ኮሌጅ እየሰጠ ያለው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት በመቀጠል ከዲንሾ ብሄራዊ ፓርክ ለተነሱ የማህበረሰብ አባላት 30 ኩንታል ስንዴ በስጦታ አበረከት።

ተነሽ ማህበረሰቡ ከነበሩበት አከባቢ ፓርኩን ከንክኪ ነጻ ለማድረግ የተነሱ በመሆኑ ለመቋቋሚያ እንዲሆን ታስቦ የተደረገ ደግፍ ነው።

የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

Photos from Agarfa ATVET College's post 07/04/2026

የISO 21001_2025 የትምህርት ጥራት የዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

የአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ
መጋቢት 29/2018 ዓ.ም

በአጋርፋ ኮሌጅ የትምህርት ጥራትን የሚመለከተው የISO 21001_2025 የሰነድ ዝግጅት ምዕራፍ ተጠናቆ ወደ ተግበራ ምዕራፍ ለመግባት የመክፈቻ ፕሮግራም ተካሄደ።

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ዲን አቶ ፊራኦል ኤደኦ ለዚህ ደረጃ እስኪደርስ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉትን የISO የታክስ ፎርስ አባላት አመስግነው ከዚህ በኋላ የሁላችንንም ርብርብ የሚጠይቅ ስራ በመሆኑ ሁላችንም በትጋት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የISO 21001_2025 ስልጠና ለወሰዱ አመራር ሰርትፍኬት ተሰጥቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የስነምግባር መከታተያ ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ስራጅ አ/ቃድር በስነ ምግባርና ብልሹ አሰራር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል።

በስልጠናቸው የሙስና ምንነት፣የሙስና አይነቶች፣ የሙስና አነሳሽ ምክንያቶች እና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

Photos from Agarfa ATVET College's post 29/03/2026

በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ደረጃ 2እና 3 የቀበሌ የልማት ጣቢያ ሠራተኞች ለማሰልጠን ተቀበለ።
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

በአጋርፋ ኮሌጅ በግብርና ሚንስቴር እና የስራና ክህሎት ሚንስቴር በመተባበር ለሚሰጠው የሙያ ማሻሻያ ስልጠና የደረጃ 2 እና 3 የቀበሌ የልማት ጣቢያ ሠራተኞች ለማሰልጠን ተቀብሎ ምዝገባ ተካሂዷል።

የኮሌጁን ህግና ደንብ ለማሳወቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ ሲሆን በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ የተገኙት የስልጠና ዘርፍ ም/ዲን የሆኑት አቶ አብርሀም ተስፉ ሲሆኑ የልማት ጠቢያ ሰራተኞችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ መንግስት ባመቻቸላችሁ እድል በመጠቀም በትምህርታችሁን ጠንክራችሁ ደረጃችሁን ለማሻሻል መማር አለባችሁ ያሉ ሲሆን አክለውም የኮሌጁን ህግና ደንብ አክብራችሁ ሥልጠናችሁን መከታተል አለባችሁ ሲሉ አሳስበዋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ ከግብርና ሚንስቴር የመጡ ባለሙያዎችም ተሳትፈዋል።

ሰልጣኞች ከተለያዩ በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እንደሆኑ ተገልጸዋል

መጋቢት 2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ሰራተኞች

Photos from Agarfa ATVET College's post 25/03/2026

በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የሴቶች ቀን በዓል (March 8) በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

በአጋርፋ ኮሌጅ የሴቶች ቀን በዓል (March 8) "የሴቶ ድምጽ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ"በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል።

በበዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ፊራኦል ኤደኦ እንኳን አደረሳችሁ ካሉ በኋላ የማህበረሰቡ ግማሽ የሆኑትን ሴቶችን ያላሳተፈ እድገት የቀጨጨ እንደሆነ ገልጸው ነባር አስተሳሰቦችን በማስወገድ የሴቶችን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ስሜ በበኩላቸው ሴቶች እድል ከተፈጠረላቸው ከተሰጣቸው ሀላፊነትን በላይ የመወጣት አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።

በዓሉ በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ስነ ግጥም፣ ጥያቄና መልስ፣በምልክት የመግለጽ ውድድር፣ ጥሩ ውጤት ላመጡ ሶስት ሴት ተማሪዎች እና ለአንዲት ግንባር ቀደምት ሴት ሰራተኛ ሽልማት በመስጠትና መሰል ዝግጅቶችን በማቅረብ የተከበረ ሲሆን በመጨረሻም በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ዝግጅቱ ተጠናቋል።

መጋቢት 16/2018 ዓ.ም
የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ

Photos from Agarfa ATVET College's post 19/03/2026
Photos from Agarfa ATVET College's post 19/03/2026

የእንኳን ደረሳችሁ መልእክት

አጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ዲን የሆነት አቶ ፊራኦል ኤደኦ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ተኛው የእድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞተቻውን ገልፀዋል

Photos from Agarfa ATVET College's post 19/03/2026

በአጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ ረመዳን 29 እና ረመዳን 30 ለኮሌጁ መስሊም ሰራተኞችና ተማሪዎች የአፍጢር ፕሮግራም ተካሄደ።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

በአጋርፋ ኮሌጅ በኮሌጁ ማኔጅመንት ለሙስሊም ሠራተኞችና ተማሪዎች የአፍጢር ፕሮግራም ተካሄደ።

የአብሮነት ተምሳሌት የሆነው ኮሌጃችን እንደወትሮው ሁሉ ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን አብሮነት በሚያጎላ መልኩ የኮሌጁ ዲን እና የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በደማቀ ሁኔታ አካሂዷል።

በአፍጢር ፖሮግራሙ ላይ የተገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተደረገላቸው ፕሮግራም ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው የኮሌጁን ማኔጅመንትና የህንን ፕሮግራም ላስተባበሩ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መጋቢት 10/2018 ዓ.ም

የኮሌጁ ህዝብ ግንኙነት

Want your school to be the top-listed School/college in Agarfa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Agarfa