20/05/2026
ADET TVET College
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ADET TVET College, College & University, አዴት, Adet.
20/05/2026
Takeoff Sheet (የመጠን መለኪያ ሰነድ) እንዴት እንደሚዘጋጅ – በአጭሩ ላስረዳቹ Mekamu Mohammed
Takeoff Sheet ማለት ከዕቅድ (drawings) እና ከመግለጫ (specifications) መሠረት የሥራ እቃዎችን መጠን ለመለካት እና ለመመዝገብ የሚዘጋጅ ሰነድ ነው። ለዋጋ ግምት (estimation)፣ BOQ እና ለእቃ እቅድ ይጠቅማል።
1. ዕቅዶችን እና መግለጫዎችን ማጥናት
የአርክቴክቸር፣ የስትራክቸር እና የሰርቪስ ዕቅዶችን በጥንቃቄ ይመልከቱ።
መጠኖች፣ ደረጃዎች፣ እቃዎች እና ዝርዝሮችን ይረዱ።
የእቃ አይነት፣ ውፍረት እና ልዩ መስፈርቶችን ይመልከቱ።
ዓላማ: ትክክለኛ መለኪያ ለማድረግ።
2. የሥራ ንጥሎችን መለየት
ፕሮጀክቱን ወደ ሚለኩ ክፍሎች ይከፋፍሉ፣ ለምሳሌ፦
ቁፋሮ (Excavation)
ኮንክሪት ሥራ
የብረት ማጠናከሪያ (Reinforcement)
ግንብ (Masonry)
ፕላስተር
ፊኒሽንግ ሥራ
ዓላማ: ሥራዎችን በስርዓት ለመለካት።
3. ተገቢ የመለኪያ አሃዶችን መምረጥ
የተለመዱ አሃዶች፦
m³ → ኮንክሪት፣ ቁፋሮ
m² → ፕላስተር፣ ስላብ
m → ፓይፕ፣ ቢም
kg → የብረት ማጠናከሪያ
No. → በሮች፣ መስኮቶች
ዓላማ: መደበኛ የመለኪያ ስርዓት ለመከተል።
4. ከዕቅድ መጠን መለካት
እነዚህን ይለኩ፦
ርዝመት (Length)
ስፋት (Width)
ቁመት (Height)
ውፍረት (Thickness)
ፎርሙላዎች፦
መጠን (Volume) = Length × Width × Height
ስፋት (Area) = Length × Width
ዓላማ: ትክክለኛ መጠን ለማግኘት።
5. በTakeoff Sheet ላይ መመዝገብ
የTakeoff Sheet ዋና ኮሎኖች፦
የእቃ ቁጥር (Item No.)
መግለጫ (Description)
ርዝመት (Length)
ስፋት (Width)
ቁመት / ውፍረት
መጠን (Quantity)
አሃድ (Unit)
ማስታወሻ (Remark)
ምሳሌ፦
Item
Description
L
W
H
Quantity
Unit
1
ቁፋሮ
10
2
1.5
30
m³
6. ጠቅላላ መጠን ማስላት
ሁሉንም መጠኖች ይደምሩ።
ለእያንዳንዱ ሥራ ጠቅላላ መጠን ያግኙ።
ዓላማ: BOQ እና ዋጋ ግምት ለማዘጋጀት።
7. ማረጋገጥ (Checking)
መለኪያዎችን እንደገና ይመልከቱ።
የተረሱ ወይም የተደገሙ እቃዎች እንዳይኖሩ ያረጋግጡ።
ዓላማ: ትክክለኛ እና አስተማማኝ ውጤት ለማግኘት።
አጭር ትርጉም (Summary)
Takeoff Sheet የሚዘጋጅበት ሂደት ዕቅዶችን በመመልከት፣ ሥራዎችን በመለየት፣ መጠን በመለካት፣ በሰነድ ላይ በመመዝገብ እና በመረጋገጥ ነው።
10/02/2026
https://www.facebook.com/share/1AR9wA6mMn/
ተጨማሪ ስራዎችን ለማግኘት ሊንኮችን ይከተሉ‼️
https://t.me/Amhara_Job_Finders
https://www.facebook.com/profile.php?id=61560394427130
09/02/2026
👉 የአፈርን የመሸከም አቅም (BEARING CAPACITY) እንዴት እንጨምር??...
* ሶስት አይነት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከያ ቴክኒኮች አሉ - mechanical, chemical & other stabilization techniques
A) ሜካኒካል ውስጥ :-
1. Compaction - አፈሩን ስንጠቀጥቀው density/ unit
weight ይጨምራል ያ ማለት ደግሞ አፈርን የመሸከም አቅም ጨመረ ማለት ነው::
2. Excavation and Replacement – expansive soil ከሆነ ወይም ሌላ አስቸጋሪ አፈር ከሆነ ይህን መጠቀም እንችላለን
3. Mixing of Different Soils - ሳይታችን ላይ ያለው አፈር
coarse ወይም fine ብቻ ከሆነ ወይም ደግሞ አፈሩ አንድ አይነት
ብቻ ፀባይ ካለው ከተለያዩ አፈሮች ጋር በመደባለቅ የተሻለ የአፈር
ፀባይ ማግኘት እንችላለን
B) ኬሚካል :-
1. Lime stabilization - ይህንን የምንጠቀመው በአብዛኛው ለexpansive soil ነው፡፡ አፈሩን ከ Lime ጋር በመደባለቅ
plasticity መቀነስ እንችላለን፡፡ የlime መጠኑ ከሚያስፈልገው በላይ ከበዛ ግን B.C. ይቀንሳል፡፡
2. Cement stabilization - ሲሚንቶን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ concrete
pavement ስር መጠቀም እንችላለን በአብዛኛው ለአየር መንገዶች ፤ ለአውራ ጎዳናዎች ፤ ግድቦችን ከሽርሸራ ለመከላከል
ወ.ዘ.ተ. መጠቀም እንችላለን፡፡
3. Asphalt stabilization - አስፓልትን ከአፈር ጋር በመደባለቅ የተሻለ ውጤትን የምናገኝበት ዘዴ ነው በተለይም ለcohesive አፈሮች፡፡ አፈሩን water proof በማድረግና ውሃማነትን በመቀነስ
B. Cን መጨመር እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ይህንን ድብልቅ ለመንገዶች እንደ base course መጠቀም እንችላለን፡፡
C) ሌሎች የአፈርን ባህሪ ማስተካከያ መንገዶች:-
1. Drainage - ፓይፖችን አፈር ውስጥ በመቅበር ወይም ጉድጓዶችን በመጠቀም ground water የምንቆጣጠርበት ነው
2. Precompression - ግንባታ ከመጀመራችን በፊት አፈሩ ላይ ሎድ በመጫን ኮምፓክት የምናደርግበት ዘዴ ነው
3. Dynamic Stabilization
ሀ) Blasting - ቦምብ ወደውስጥ በመቅበር በፍንዳታው አፈሩ ይጠቀጠቃል::
ለ) Compaction Piles - ፓይሎችን ወደውስጥ በማስገባት አፈሩ ወደ ጎን እንዲሸሽና እንዲጠቀጠቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
ፓይሉን ስናስወጣውም በተቦረቦረው ጉድጓድ ውስጥ የተሻለ አፈር በማስገባት የአፈርን የመሸከም አቅም ማስተካከል እንችላለን፡፡
4. Injection And Grouting - አፈሩን በሲሚንቶ ወይም በተለያዩ chemical ውህዶች በpressure በመምታት ground
water ና settlement መቆጣጠር እንችላለን፡፡
የተሻለውን ዘዴ ለመምረጥ የአፈሩንና የአካባቢውን ሁኔታ ፤ ኢኮኖሚ ፤ ሴፍቲና የመሳሰሉትን ነገሮች ማጤን አለብን፡፡
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Telephone
Website
Address
አዴት
Adet