የጎ/ቆ/ወ/ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት

የጎ/ቆ/ወ/ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት

Share

በጋራ እንስራ

FDRE Ministry Of Agriculture 22/11/2025

የእንስሳት ጤንነትና ደህንነትን በህግ ማዕቀፍ የመደገፍ ጉዞ

(አዳማ፣ ሕዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

በኢትዮጵያ የእንስሳት ሃብቱ ባለው ሰፊ ፀጋ መነሻነት በርካታ አርሶና አርብቶአደሮች እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ምርታማነትን እያሳደጉ ከራሳቸው አልፈው ለሀገር ኢኮኖሚ ምሰሶ ሆነው ይገኛሉ፡፡

በዚህ ሂደት የእንስሳት ጤናና ደህንነትን መጠበቅ አንዱ ትኩረት ነው፡፡ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ጤናና ደህንነት ችግሮችን ለመፍታት የእንስሳት ልየታ፣ ምዝገባ፣ ክትትል እና የእንስሳት ደህንነት ስርዓትን ዘርግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

የእንስሳት ደህንነትን በዘላቂነት ለመጠበቅም አሰራሮችና የህግ ማዕቀፎችን ከመተግበር ባለፈ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎችን በተከታታይ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ግብርና ሚኒስቴር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አለም አቀፍ የእንስሳት ቀንን በተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መንገዶች አክብሯል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) የእንስሳት ሀብቱ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ በተጨማሪ ለበርካታ አርሶና አርብቶአደሮች የክብርና የሃብት መገለጫዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የእንስሳት ደህንነትና ጤንነትን መጠበቅ ሃገራችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚያስችላት ተናግረዋል፡፡

የእንስሳት ሀብቱን ለማሳደግ የእንስሳቱን ጤንነትና ደህንነት ሳይንሳዊ በሆነ አሰራር መጠበቅ ይገባል፡፡

ለዚህ አጋዥ የሆኑ የህግ ማዕቀፎች መውጣታቸው ደግሞ ዘርፉ ትልቅ ትኩረት ማግኘቱን አመላካች ናቸው፡፡

የእንስሳት ጤንነትና ደህንነት አዋጅን መሰረት በማድረግ የእንስሳት ልየታና ደህንነትን የሚያስጠብቁ የእንስሳትና የእንስሳት ውጤቶች ልየታ፣ ምዝገባና ክትትል እንዲሁም የእንስሳት ደህንነት ስትራቴጂዎች የስራ መመሪያዎች እንዲሆኑ ይፋ ተደርገዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ተዋበ ጫኔ
ፎቶግራፈር፦ ጌታቸው ምትኩ

#ከማምረትበላይ


-------------------------
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ስለግብርና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት👇

📌ድረ-ገጽ፦ www.moa.gov.et

📌ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/MoAEthiopia

📌ዩቲዩብ፦ https://www.youtube.com/

📌ቴሌግራም፦ https://t.me/MoAEthiopianews

📌ቲዊተር፦ https://x.com/MoA_Ethiopia

📌ሊንክድኢን፡- https://shorturl.at/7O6cs

📌ቲክቶክ፦ http://www.tiktok.com/

📌ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/moa_ethiopia/

FDRE Ministry Of Agriculture F.D.R.E Ministry of Agriculture is a Governmental Organization Headquartered in Bole sub-city Ethiopia,Addis Ababa

Photos from North Gojjam Zone Livestock & Fisheries Development Department's post 03/11/2025
02/11/2025

🐂 የሰዎችና የእንስሳት የጋራ በሽታ ‘ብሩሴሎሲስ’ (Zoonotic Disease ‘Brucellosis’)

🚨 ብሩሴሎሲስ 🦠 ማወቅ ያለብዎት ገዳይ የሰዎችና የእንስሳት የጋራ በሽታ!

🐄 🔬 ብሩሴሎሲስ ምንድነው? ብሩሴሎሲስ በብሩሴላ ዝርያዎች (Brucella species) የሚከሰት የባክቴሪያ በሽታ ነው። ከብቶችን፣ ፍየሎችን፣ በጎችን፣ አሳማዎችን አልፎ ተርፎም ሰዎችን ያጠቃል!

🧫 🔹 የበሽታው መንስኤ ባክቴሪያዎች:

ብሩሴላ አቦርተስ (Brucella abortus) → በዋናነት በከብቶች

ብሩሴላ ሜሊቴንሲስ (Brucella melitensis) → ፍየሎችና በጎች

ብሩሴላ ሱዊስ (Brucella suis) → አሳማዎች

ብሩሴላ ካኒስ (Brucella canis) → ውሾች

🩺 🔹 የመተላለፊያ መንገዶች: ብሩሴሎሲስ በሚከተሉት ይተላለፋል:

በበሽታው ከተያዘ እንግዴ ልጅ፣ ፅንስ፣ የሴት ብልት ፈሳሾች ወይም ሽንት ጋር ንክኪ ሲኖር።

ያልተቀቀለ (unpasteurized) ወተት ወይም የወተት ተዋጽኦዎችን በመመገብ።

በበሽታው ከተበከሉ የእንስሳት ማደሪያዎች ውስጥ አየርን ወደ ውስጥ በመሳብ (inhalation of aerosols)።

የተበከሉ እንስሳትን በሚይዙበት ጊዜ በቁስል ወይም በጭረት በኩል።

🐮 🔹 በእንስሳት ላይ የሚታዩ ምልክቶች:

በመጨረሻው የሶስት ወራት የእርግዝና ወቅት መጨንገፍ (Abortion in last trimester)

የእንግዴ ልጅ መቅረት (Retained placenta) እና የማህጸን ኢንፌክሽን (metritis)

ተደጋጋሚ መጋባት (Repeat breeding) እና መካንነት (infertility)

የወተት ምርት መቀነስ

በወንዶች ከብቶች → የዘር ፍሬ መመረዝ (Orchitis) እና የዘር ቱቦ መመረዝ (epididymitis)

👨‍⚕️ 🔹 በሰዎች ላይ (የጋራ በሽታ ጠቀሜታው): "የማልታ ትኩሳት" (Malta Fever) ወይም "ተለዋዋጭ ትኩሳት" (Undulant Fever) በመባል ይታወቃል። ምልክቶቹ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ:

የሚለዋወጥ ትኩሳት (Intermittent fever - የሚጨምርና የሚቀንስ)

የመገጣጠሚያ እና የጡንቻ ህመም

ድክመት እና መረጋጋት ማጣት/ድካም

ራስ ምታት እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ⚠️ በቶሎ ካልታከመ ዘላቂ (chronic) ሊሆን ይችላል።

💉 🔹 ምርመራ:

ሮዝ በንጋል ምርመራ (Rose Bengal Test - RBT) → ፈጣን የማጣሪያ ምርመራ

ኤሊሳ (ELISA) / ኮምፕሊመንት ፊክሴሽን ምርመራ (Complement Fixation Test) → ማረጋገጫ

ወተት ቀለበት ምርመራ (Milk Ring Test - MRT) → ለወተት ከብት እርባታ ይውላል

🛡️ 🔹 መከላከል እና ቁጥጥር: ✅ በየጊዜው ምርመራ ማድረግ እና በበሽታው የተያዙ እንስሳትን ማስወገድ (culling) ✅ በብሩሴላ አቦርተስ ኤስ19 (Brucella abortus S19) ክትባት መስጠት (ከ4–8 ወር ዕድሜ ላላቸው ጥጆች) ✅ የተጨነገፉ ነገሮችን በአግባቡ ማስወገድ (በጥልቀት በመቅበር ወይም በማቃጠል) ✅ የእርሻ ቦታ ንጽህናን መጠበቅ እና ፀረ-ተባይ መጠቀም (disinfection) ✅ ጥሬ/ያልተቀቀለ ወተት ከመጠጣት መቆጠብ ✅ የተበከሉ እንስሳትን በሚይዙበት ጊዜ ጓንትና ማስክ መጠቀም

📢 🔹 አስፈላጊ: ❗ ብሩሴሎሲስ በእንስሳት በሽታዎች ህግ መሰረት ሪፖርት የሚደረግ በሽታ (Notifiable Disease) ነው። ❗ ለእንስሳት ውጤታማ ህክምና የለውም → መከላከል ብቸኛው መፍትሄ ነው! 🔥 እራስዎን፣ እንስሳትዎን እና ህብረተሰቡን ይጠብቁ!

ለበለጠ መረጀ

Telegram: Contact @accubreed

31/10/2025

📢 AI እና የእንስሳት እርባታ በኢትዮጵያ: የባለሙያዎችን እገዛ የምትፈልግ የአንዲት ጊደር ታሪክ!
ይህንን አስቸኳይ የባለሙያ ጥያቄ በውስጥ ተጠይቀን ነበር። ጉዳዩን ለመላው ህብረተሰብ እና የእንስሳት ሐኪሞች መማሪያ ይሆን ዘንድ ከጥያቄው ጋር የመፍትሄ ሃሳቡን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፦
1. ❓ የችግሩ ገለጻ (ጥያቄው)
📅 የእርግዝና ታሪክ: በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 3/2017 አ/ም በ AI (ሰው ሰራሽ መዳቀል) የፀነሰችው ጊደር አሁን 10ኛ ወሯ ላይ ትገኛለች።
🚨 አስደንጋጩ ሁኔታ: ጊደሯ እስከ አምስተኛ ወሯ ድረስ መደበኛ የእርግዝና ምልክቶችን ብታሳይም፣ ከዚያ በኋላ የፅንሱ እድገት ተቋርጧል። በተደረገላት የህክምና ምርመራ (Pregnancy Diagnosis - pD) ፅንሱ *በህይወት የሌለና የደረቀ (*Fetal Mummification) ሆኖ ተገኝቷል።

ይህ ሁኔታ የAI ቴክኖሎጂን ስኬት አደጋ ላይ የሚጥልና በእርባታው ዘርፍ ትልቅ ኪሳራ ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ የባለሙያዎችን አስቸኳይ ትኩረት ይሻል።

ጥያቄው፦ የጊደሯን ሕይወት ለመታደግ እና ለቀጣይ እርባታ አገልግሎት እንድትውል ለማድረግ፣ የደረቀው ፅንስ ከቀዶ ሕክምና (Surgery) በፊት በህክምና ዘዴ (Medical Treatment) እንዲወገድ የሚረዳ መፍትሄ በአስቸኳይ እንጠይቃለን።
2. 💊 የባለሙያ ምላሽ እና መፍትሄ (ሕክምናው)
ጊደሯ የደረሰባት ችግር "የደረቀ ፅንስ" (Fetal Mummification) በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ይህም የፅንሱ ፈሳሽ ተመጥጦ የፅንሱ አካል በደረቅ መልክ በማህፀን ውስጥ የሚቀርበት ሁኔታ ነው።
✅ ከቀዶ ሕክምና በፊት ተመራጭ የሕክምና ዘዴ:
የደረቀ ፅንስን ከቀዶ ሕክምና ውጭ ለማስወገድ በአብዛኛው በዘርፉ ባለሙያዎች የሚመከረው እና ውጤታማ የሆነው ሕክምና የሆርሞን ሕክምና (Hormone Therapy) ነው።
ዋና የሕክምና ስልት
* የፕሮስታግላንዲን (PGF_{2\alpha}) መርፌ:
* ዓላማ: ይህ መድኃኒት ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዲቆይ ያደረገውን Corpus Luteum (CL) የተባለውን የእርግዝና መከላከያ ሆርሞን አምራች አካል ያጠፋል (Luteolysis)।
* ውጤት: CL ሲጠፋ የፕሮጄስትሮን (Progesterone) መጠን ስለሚቀንስ የማህፀን በር እንዲከፈት እና የማህፀን ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ በማድረግ የደረቀው ፅንስ እንዲወገድ ያደርጋል።
* የፅንሱ መውጣት:
* የፕሮስታግላንዲን መርፌ ከተሰጠ በኋላ በአብዛኛው ከ2 እስከ 4 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የደረቀው ፅንስ ከማህፀን ይወጣል።
* በአንዳንድ ሁኔታዎች የማህፀን በር በቂ ከሆነ ፅንሱ በእጅ (Manual Removal per Vaginam) ሊወገድ ይችላል።
* የተደገመ ሕክምና: ፅንሱ በመጀመሪያው መርፌ ምላሽ ካልሰጠ፣ ከ48 እስከ 72 ሰዓታት በኋላ ሁለተኛው የፕሮስታግላንዲን መርፌ ሊሰጥ ይችላል።
* ተጨማሪ የሕክምና ድጋፍ: አንዳንድ ጊዜ የእንስሳት ሐኪሞች የማህፀን በር እንዲሰፋ ለማገዝ ከፕሮስታግላንዲን ጋር ኤስትሮጅን (Estrogen) ሆርሞን ሊጨምሩ ይችላሉ።
3. 💡 ማጠቃለያ እና ማስጠንቀቂያ
ይህ ዓይነቱ ሕክምና ለጊደሯ ሕይወት ወሳኝ በመሆኑ እና ከፍተኛ የእውቀት ልምድ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ሕክምናው ሊሰጥ የሚችለው በእንስሳት ሕክምና ባለሙያ (Veterinarian) ብቻ መሆን አለበት።
* መድኃኒቱን በራስዎ አይስጡ! ትክክለኛው የመድኃኒት መጠን እና የሕክምና ዕቅድ የሚወሰነው የጊደሯን የጤና ሁኔታ በትክክል በመረመረ የእንስሳት ሐኪም ብቻ ነው።

www.anrslivestock.gov.et 30/10/2025

በኮርማ ማስጠቃት ወይስ በአርቴፊሻል ኢንሲሚኔሽን???
የቱ የተሻለ ነው??

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ) በተፈጥሮአዊ መንገድ ማስጠቃትም ሆነ በአርቴፊሻል ኢንሲሚኔሽን ሁለቱም የራሳቸው የሆነ ጥቅም አላቸው። የተሻለ ተብሎ የሚወሰነው የታሰበው እቅድ ላይ እና የፋርሙ ሁኔታ ላይ ነው።

1.የአርቴፊሻል ኢንሲሚኔሽን ጥቅሞች

ዝርያ ማሻሻል:- በዚህ መንገድ ማዳቀል የተሻለ የተባለውን ምርጥ ዝርያ መርጠህ ያለገደብ በራስህ ፋርም ውስጥ ዘሩ እንዲወለድ ማድረግ ትችላለህ።

በሽታ:- በአርቴፊሻል ማዳቀል ከከብት ወደከብት የሚተላለፉ እንደ ቪብሮ/Vibro/, ቦቫይን ሄርፕስ ቫይረስ/ Bovine Herpes Virus እና ሌሎችም አይነት በሽታዎች አይኖረውም ምክንያቱም የኮርማው ዘር በላብራቶሪ ስቶር ሲደረግ ቅድሚያ ጥንቃቄዎች ስለሚደረጉ።

ወጪ:- በአርቴፊሻል የማዳቀል ስራ ከኮርማ ነፃ ስለሆነ ኮርማውን በፋርም ውስጥ አሰቀምጦ ከሚደረጉ የመኖ: የሰው ሃይል እና የቤት ወጪዎች ነፃ ያደርጋል።

ደህንነት:- በአርቴፊሻል የማራባት ስራ በኮርማ ለማስጠቃት ከሚደረግ ግብግብ ነፃ ስለሆነ ላሟም ሆነች ባለቤቱ ደህንነታቸው ይጠበቃል።

ቅድመ እውቅና

አርቴፊሻል ኢንሲሚኔሽን የተሳካ እንዲሆን ሙያዊ ዕውቀት ይፈልጋል።

አርቴፊሻል ኢንሲሚኔሽን ውጤታማ እንዲሆን ላሟ ከፍተኛ የስሪያ ግለት ጊዜ ላይ መሆኗን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

2.በተፈጥሮአዊ /ኮርማ ማስጠቃት

የባለሙያ ወጪ ይቀንሳል:- ኮርማ በራሱ ተፈጥሮአዊ መንገድ ግለት ላይ ያሉ ላሞችን እየመረጠ በሰው እገዛም ሆነ በራሱ ያጠቃል። ይህም በፋርሙ ዉስጥ ሊኖር የሚችልን ስሪያ ላይ ያለች ላምን ተከታትሎ የመለየትን ስራ ሰራተኞችን ይቀንሳል እና የግለት ጊዜያቶች ባክነው እንዳያልፉ ይረዳል።

የስሪያ ጊዜ ላይ ላሞችን መለየት የፋርሙ ስኬት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። አንድ ላም ግለት ላይ ባለች ጌዜ የግድ ዘር መያዝ እና ወደ እረግዝና መግባት አለባት: ዙሩ ካለፋ ድጋሚ ከአንድ ወር እስከ 3 ወር ድረስ ቆይታ ግለት ታነሳለች ይህ ማለት ከ1 ወር እስከ 3 ወር የምታስወጣው ወጪ ያለምንም ጥቅም ኪሳራ ነው ማለት ነው። ስለዚህ እዚ ላይ ኮርማውን ላሞቹ መሃል በመልቀቅ ስሪያ ላይ ያለችውን እንዲለይ ማድረግ ይቻላል።

ገቢ ያመጣል:- ዘሩ ቆንጆ ከሆነ በኮርማው ማስጠቃት ክፍያ አለው።

ኮርማ የመያዝ ቅድመ ዕውቅና

ወጪ:- ዘሩ ምርጥ ካልሆነ በማጥቃት ደረጃ ከሌላ ፋርም ገቢ ካላመጣ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ወጪው የበለጠ ሊሆን ይችላል።

ደህንነት:- ለማጥቃት የተቀመጠ ኮርማ በውስጡ ያለው የወንድ ሆርሞን/ Testestrone/ በጣም ከፍ ያለ በመሆኑ እና ባለው ግዙፍ ሰውነት አደገኛ ሊሆን ይችላል: ለማኔጅመንት ቀላል የሚባል አይሆንም።

በሽታ:- በኮርማ ማስጠቃት ከላይ የተጠቀሱትን ተላላፊ በሽታዎች ተጋላጭ ያደርጋል።

ዘር:- በኮርማ ብቻ ማስጠቃት በፋርሙ ውስጥ ከላው ዘር ሌላ የተሻለ ዘር እንዳይኖር ይገድባል ።

ምክር

በጣም ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ላሞች ባሉበት በሰፋፊ ፋርም ውስጥ ኮርማ ቢኖር ይመከራል ምክንያት ለግለት /Heat detection / ኮርማው በተሻለ መልኩ መለየት ስለሚችል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ http://www.anrslivestock.gov.et/
ዩትዩብ፦ https://youtube.com/channel/UC3z_W2ex69Ra-Pt0ED_hyjg
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/AmharaLivestockandFisheriesResourcesDevelopment/
ቴሌግራም፦ ht

www.anrslivestock.gov.et Joomla! - the dynamic portal engine and content management system

29/10/2025

# # #ዝርያ ማሻሻል የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል በ3 ዋና ዋና ተግባራት የሚከናወን ሲሆን እነሱም በመደበኛ ማዳቀል፣በሲንክሮናይዜሽ እና በተሻሻለ ኮርማ ድቀላ ሲሆኑ በዞናችን ውስጥም እየተተገበሩ ይገኛሉ፡፡
* ሲንክሮናይዜሽን
የወተት ላሞችን ድሪ ፍላጎት ማቀናጀትና በርካታ ቁጥር ያላቸውን የላሞች/ጊደሮች የመኖ ውሀና ሌሎች ሁኔታዎች በተመቻቸላቸው ጊዜ እንዲወልዱ በማድረግ ሁሉም የተወለዱ ጥጆች በቂ ውሀ :ወተት ጠጥተው አንድም ሳይሞቱ እንዲያድጉ በህይወት ዘመናቸው ምርታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የጥቂ ጊዜ በሆርሞን አማካይነት የመቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ነው ፡፡በዚህ ቴክኖሎጂም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የድሪ ፍላጎት ያላሳዩ ላሞችም ወደ ፍላጎት እንዲመጡ ከማድረጉም በተጨማሪ የላሞችን የኮርማ ፍላጎት ዑደት በአማካይ 21 ቀን የነበረውን ከ2-5 ቀን ያሳጥራል፡፡ቴክኖሎጂው ሆርሞንን በመውጋት የድሪ ፍላጎት ማነሳሳት እንጂ በራሱ ድቀላ ባለመሆኑ ሆርሞኑ በተወጋ 2-5 ቀናት ውስጥ ሁሉም አ/አደሮች ላሞቻቸውን ወደ ድቀላው ጣቢያ በማቅረብ እንዲዳቀሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የቴክኖሎጂው አስፈላነት ፡- - የላሞች የኮርማ ፍላጎትን ቀን ማሳጠር፣የሚወለዱ ጥጆችን በተሸሻለ አባላዘር ለማዳቀል፣የሚወለዱ ጥጆች መኖ አቅርቦቱ በተመቻቸ ጊዜ እንዲወልዱ ለማስቻል፣ዘመናዊ የወተት ከብቶች እርባታን ለማስፋፋት፣አንድ ላም በወለደች በ2 ወር ውስጥ እንድትጠቃ ለማስቻል እና ወዘተ ናቸዉ ፡፡
የቴክኖሎጂው አተገባበር፡- - ቴክኖሎጂው እንደሚከተለው የሚተገበር ይሆናል
መስፈርቱን የሚያሟሉ ላሞችን መመልመል(ይህም ጥሩ የሰውነት አቋም ያላቸው፣አራት ጡት ያላቸው፣ከበሽታ ነጻ የሆኑ፣መውለድ የሚችሉ)
የቀረቡ ከብቶች በአዳቃይ ባለሙያው አማካኝነት እርግዝና ምርመራ ይደረግላቸዋል
እርግዝና ያላቸው ሆርሞን ሳይወጉ እንዲመለሱ ይደረጋል
በምርመራው ወቅት የኮርማ ፍላጎት ላይ ያሉት እንዲዳቀሉ ይደረጋል
እርግዝና የሌላቸው ላሞች የህይወት ታሪክ ተመዝግቦ ሆርሞን ይወጋሉ
ሆርሞን ከተወጉ በኋላ ላሞቹ የኮርማ ፍላጎት በሁለተኛው ወይም በሶስተኛው ቀን ስለሚያሳዩ ግድ ወደ ድቀላ ጣቢያ መምጣት አለባቸው
አንዳንድ ላሞች ድብቅ ፍላጎት ስለሚያሳዩ ሁሉም ሆርሞን የተወጉ ላሞች በሶስተኛው ቀን የግድ ወደ ማዳቀያው ጣቢያ መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
ላሞቹ ከተዳቀሉ በኋላ ከ17-21 ቀን ድረስ ክትትል በማድረግና ከሀገረሰብ ኮርማ በመጠበቅ ወደ ፍላጎት ከመጡ ወደ ድቀላው ጣቢያው መውሰድ ያስፈልጋል
ፕሮግራሙ ውጤታማ ለማድረግ ፕሮግራሙ ከመተግበሩ በፊት ሊደረጉ የሚገባቸው ነጥቦች ፡-
ሲንክሮናይዜሽን በራሱ ብቻውን ዉጤት ወይም ስኬት ባለመሆኑ አብሮ የሚሄድ ተግባራት አንድ ላይ ሊከናወኑ ይገባል፡፡እነዚህም
ተሳታፊ አ/አደር መመልመል(ፍቃደኛ የሆነ፣ኤክስቴንሽን የሚቀበል፣መኖ ያለማ)
የማዳቀያ ጣቢያዎችን ክራሽ ማዘጋጀት እና መጠገን
በአ/አደሩ ዘንድ ግንዛቤ በንቅናቄ መፍጠር
አስፈላጊውን ሎጀስቲክ ተግባሩን ለሚያከናውኑ ባለሙያዎች ማመቻቸት ዋነኛዎቹ ናቸው፡፡

Photos from የጎ/ቆ/ወ/ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት's post 22/10/2025

በጎንጅ ቆለላ ወረዳ እን/ዓሣ ሀ/ል/ጽ/ቤት በአሁኑ ወቅት የተከሰተውን የዶሮ በሽታ ወደ ወረዳው እንዳይገባ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ለዶሮ አሳዳጊዎችና አረቢወች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት 12/02/2018 ተሰጠ።

Photos from የጎ/ቆ/ወ/ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት's post 21/10/2025

እንስሳትን በመከተብ የራሳችን ጤና እንጠብቅ

Photos from የጎ/ቆ/ወ/ እንስሳት ሃብት ልማት ጽ/ቤት's post 21/10/2025

‎ የእንስሳት ክትባት እየተሰጠ መሆኑ ተገለፀ፡፡

‎ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም(ጎንጅ ቆለላ ኮሙኒኬሽን)
‎በሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ እንስሳትን ከተለያዩ በሽታዎች ለመከላከል የእንስሳት ክትባት እየተሰጠ መሆኑን የወረዳው እንስሳትና አሳ ሀብት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

‎ክትባቱን ሲሰጡ ያገኘናቸው የጎንጅ ዙሪያ ቀበሌ የእስሳት ጤና ባሙያ ወይዘሮ ብዙአየው ከፋለ እንደገለፁት ፤በበጀት ዓመቱ 2500 እንስሳትን ከተለያዩ በሽታዎች ለመከላከልና ለመጠበቅ የአባሰንጋ ክትባት ለመስጠት ታቅዶ እስከ አሁን ባለው የስራ እንቅስቃሴ ለ8መቶ እንስሳቶች ክትባት መስጠት መቻሉን ተናግረዋል፡፡ ይህ ክትባት የሚሰጠው በሽታው ላልተከሰተባቸውና ክበድ ላለሆኑ እንስሳት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

‎የአባሰንጋ በሽታ ተላላፊና ገዳይ በመሆኑ በሽታው ከመከሰቱ በፊት ማንኛውም ማህበረሰብ በእንስሳት ላይ የማንቀጥቀጥ፣የሙቀት መጨመርና የሆድ ንፋት ምልክቶች በሚታዩበት ጊዜ ወደ እንስሳት ህክምና ቦታ መውሰድ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

‎እንስሳትን በወቅቱ በማስከተብ ጤንነታቸውን በመጠበቅ ለውጤታማነታቸው ትልቅ ሚና እንዳለውም ባለሙያዋ አሳስበዋል፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Alem?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Gonji
Addis Alem
12345