18/09/2023
በክፍለ ከተማው ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ2016 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለት ተጀመረ፡፡
ኮልፌ ኮሙኒኬሽን መስከረም 07/2016 ዓ.ም
በክፍለከተማው የ2016 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለት በሁሉም ትምህርት ቤት መጀመሩን አስመልክቶ በክፍለ ከተማው የሚገኘውን ወይራ ቅድመ አንደኛ ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተገኘን ሲሆን ትምህርት ቤቱ እስከ አሁን 2 ሺ 23 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በ2016 ትምህርት ዘመን መማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለት አስጀምሮዋል፡፡
የ2016 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር የማስጀመሪያ መርሃ ግብርም በትምህርት ቤቱ የተካሄደ ሲሆን በመርሃ ግብሩ የወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸናፊ ብርሀኑና ሌሎች የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
የወይራ ቅድመ አንደኛ ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ተካልኝ እጅጉ የ2016 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በክረምት ወቅት ‹ትምህርት ለትውልድ› መርሃ ግብር አማካኝነት የትምህርት ቤቱን ምድረግቢና የመማሪያ ክፍሎችን የማስዋብ ስራ ፤ወንበሮችና በሮችን የመጠገን ከመምህራን እና ወላጆች ጋር በ2016 ትምህርት አጀማመር ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀው የ2016 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደት በዛሬው እለት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
በትምህርት ቤቱ የ7 ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ተማሪ ማራያዊት ሱለይማን እና ተማሪ ዮሀንስ ኩምሳ ከክረምት እረፍት በኋላ በአዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቱ ተማሪዎችን ለመቀበል ያደረገው ዝግጅት እንዳስደሰታቸው ገልጸው ትምህርታቸውን በጥሩ ዲስፒሊንና ስነምግባር ለመከታተል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
በእለቱም ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ቁሳቁስ ተበርክቶላቸዋል፡፡
04/09/2023
ለወይራ ት/ቤት ነባር ተማሪዎች
ለ2016 የትምህርት ዘመን ለምዝገባ በወጣው መርሃግብር መጥተው ያልተመዘገቡ ተማሪዎችን በ30/12/2015 ዓ.ም ከሰዓት ከ8:00 ጀምሮ ብቻ የምንመዘግብ መሆኑን አውቃችሁ ምዝገባ ያመለጣችሁ መጥታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።
30/08/2023
ማሳሰቢያ
ውድ የተማሪ ወላጆች/አሳዳጊዎች ለ2016 የተማሪዎች ምዝገባ ሲመጡ ለአሞላል ፍጥነት እንዲረዳንና ከዚህ በታች ያሉ መጠይቆችን እንዲዘጋጁበት ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
ተማሪን የሚመለከት የሚሞላ መረጃ
* የተማሪ ሙሉ ስም ከአያት
* የትውልድ ቀን / ወር / ዓ.ም
* እድሜ
* ተማሪ በት/ቤታችን ትምህርት የጀመረበት ዓ.ም
* የተማሪ የትውልድ ቦታ (ከተማ / ዞን /ወረዳ )
* ተማሪ አሁን የሚኖርበት(ከተማ / ወረዳ /ቤት ቁጥር)
* የወላጅ ስልክ ቁጥር
ወላጅ ወይም አሳዳጊን በሚመለከት የሚሞላ መረጃ
* የወላጅ/አሳዳጊ ስም ከነአያት
* የጋብቻ ሁኔታ
* የወላጅ/የአሳዳጊ የትውልድ ቀን /ወር / ዓ.ም
* ስራና የስራ ቦታ
* የእናት ስም ከነአያት
* የወላጅ ወይም አሳዳጊ መኖሪያ አድራሻ
(ወረዳ /ክፍለ ከተማ / ከተማ )
04/07/2023
ከወለደች በ3ኛዋ ቀን የተፈተነች እናት!!
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ወይራ ቅድመ መደነኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከወለደች ሶስት ቀን የሆናት የ8ኛ ክፍል የማታ ተማሪ ለምለም ተፈራ በመጋቢ እናቶች እንክብካቤ እየተደረገላት ፈተናዋን በሰላም አጠናቀቀች። በተጨማሪም
የወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ባለሞያዎችም ለተማሪያችን እና ለልጅዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል በማድረጋቸው ምስጋናችንን እናቀርባለን።
04/07/2023
በወይራ ትምህርት ቤት ለ2 ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሰላም ተጠናቋል። በት/ቤቱ ተማሪ የሆኑ የቀን እና የማታ ተማሪዎችን ጨምሮ 4 የግል ት/ቤት ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን ፈተናው ከተጠናቀቀ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ የመትከል መርሀ ግብርን ተከናወኗል።
02/07/2023
ወይራ ቅድመ አንደኛ ት/ቤት በ25/10/2015 ዓ.ም በሁለቱም የማስተማሪያ ቋንቋ ለሶስት አመታት በመማር ያጠናቀቁ ተማሪዎችን አስመርቋል።
እንኳን ደስ አላችሁ!
Baga gammaddan!