03/11/2025
Please be a voice for the voiceless ❗️❗️❗️❗️
Share 🔔🔔🔔🔔🔔🔔
We request your voice to raise awareness of the suffering of Ethiopian Orthodox Christians who have faced targeted violence for their Faith.
Please share and stand for human dignity and religious freedom.
World Council of Churches
Human Rights Watch
Amnesty International
United Nations Human Rights
BBC News Africa
BBC World Service
CNN
Fox News
Washington Post
United States Commission on International Religious Freedom
Religious Rehabilitation Group (RRG)
FOX 13 News
Human Rights First
Aljazera Markets أسواق الجزيرة
Fasikaw Kasaw
27/06/2025
♥ !♥
♦•♦•♦•♦•♦•♦•♦•♦•♦•♦•♦•♦•♦
#ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከልብ እናመሰግናለን።
፦
ለመልአከ ጽዮን ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስ
የደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤተ ከርስቲያን አስተዳዳሪ
አሌክሳንድርያ, ቨርጂኒያ
#ጉዳዩ፦ በማኅበራዊ ሚዲያ እርስዎን በተመለከተ ስለ ቀረበው ክብረ ክህነትን የሚመለከት ጉዳይን ይመለከታል።
#ከላይ በርዕሱ እንደተገለጸው በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እርስዎን በቀጥታ የሚመለከት ክብረ ክህነትን የሚያጎድፍ ድርጊት ፈጽመዋል በሚል የቀረበው ዘገባ ህዝበ ክርስቲያኑን ያስቆጣና በስፋትም እያነጋገረ ያለ ጉዳይ መሆኑን ለሀገረ ስብከቱ ከሚመጡ መልእክቶች ተረድተናል። ምንም እንኳን ተበድለናል ብለው በሚዲያ የወጡት አካላት ሚዲያ ከመውጣታቸው በፊት ለሀገረ ስብከታችን በጽሁፍ ያቀረቡት አቤቱታ ባይኖርም በማኅበራዊ ሚዲያ የቀረበው የተበዳይና ያን ተከትሎ ከምእመናኑ ለሀገረ ስብከቱ በስልክም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ የቀረበውን አስተያየት ማከበርና ቀኖና ቤተ ከርስቲያንን ማስጠበቅ የሀገረ ስብከቱ ድርሻ በመሆኑ እርስዎም በሀገረ ስብከታችን በቨርጂኒያ ግዛት የሚገኘው የደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ በመሆንዎ ጉዳዩ በቀላሉ የሚታይ ባለመሆኑ ይህ ደብዳቤ ከተጻፈበት ቀን ጀምሮ በሰባት ቀናት ውስጥ ለቀረበብዎ ጉዳይ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ቀርበው ምላሽ አንዲሰጡ እየጠየቅን በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ የማይቀርቡ ከሆነ ግን ቀኖናዊ ውሳኔ የምንሰጥ መሆናችንን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
።
።
21/06/2025
ሰኖዶቻችን አታሸሹብን።
አትክልተኛው መናኝ የአረንጓዴው ልማት ፈር ቀዳጅ የሊቃውንት ምሳሌ የቀለም ቀንዱ የኔታ ይባቤ ቤተክርስያን የሰጠችን ሰነዳችን ናቸው ።
ሕሊናቸው በእውነት አካላቸው በጾም በጸሎት የታሠረ እውቀታቸው በጉባዔቤት በሊቃውንት አእምሮ የተቸነከረ ከምእመናን ልቡና የተጣመረ የክርስቶስ እስረኛው መናኝ ምናቸው ይታሠራልና። ሰነዳችን አታጣፉብን። የኔታን ስትፈቷቸው ክብሩ ለናንተ ነው ባትፈቷቸው ጥቃቱም ከምትነግሩን አሉባልታ በላይ የሃይማኖታዊ ጥቃት ማረጋገጫ ማህተም ይሆናል። የኔታ ሰነዳችን ናቸው ስንል የቤተክርስቲያን ማስቀጠያ ካርታዎቻችን የጉባዔ ቤትመምህራንና እውነተኛዎቹ የገዳማት አባቶች ናቸው ማለት ነውና ሰነዶቻችን አታሸሹብን።
29/05/2025
[በደብረ ምጥማቅ ከግንቦት 21-25 የአምላክ እናት የድንግል ማርያም መገለጥና ስለውበቷ በኢትዮጵያ ሊቃውንት የቀረበላት ድንቅ ውዳሴ]
✍ በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ (በድጋሚ የተለጠፈ)
♥ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በመዝ ፵፬፥፲፪ ላይ “ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር” (የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ኹሉ በፊትሽ ይማለላሉ) በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት ብዙዎች ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው የአምላካቸውን እናት ለማየት ተመኝተዋል፤ ብዙዎቹም ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው እጅግ አስደናቂ ውበቷን አይተዋል፡፡ ከነዚኽ ውስጥ በደብረ ምጥማቅ የነበሩ ምእመናን ሌሎችም ብዙዎች ንጹሓን ክርስቲያኖች ይገኙበታል፡፡
♥ ልጇ አስቀድሞ በዘመነ ሥጋዌዉ በደብረ ምጥማቅ እንደ ምትገለጽ በገባላት ቃል ኪዳን መሠረት ከኢትዮጵያ፣ ከግብጽ፣ ከአርመንያ፣ ከሶርያ፣ ከሮም፣ ከጽርዕ፣ ከፋርስ ሀገራት ተሰብስበው በደብረ ምጥማቅ ድንኳን ተክለው፤ አጐበር ጥለው ከግንቦት 21 ቀን ጀምረው እስከ 25 ቀን ድረስ በፍጹም ደስታ የድንግልን በዓሏን ያከብሩ ነበር።
♥ “ወድንግልሂ ታስተርእዮሙ በእሉ ኀምስ መዋዕል ዘእንበለ ጽርዐት ምስለ መላእክት ወጻድቃን ወሰማዕት ምስሌሃ” ይላል፤ እመቤታችን ከግንቦት 21-25 ያለማቋረጥ ከመላእክት ከሊቃነ መላእክት፤ በአካለ ነፍስ ካሉ ከነቢያት ከሐዋርያት፤ ከጻድቃን ከሰማዕታት፤ ከደናግል ከመነኮሳት ጋራ ኹና ትገለጽላቸው ነበር፤ አማኒውም ኢአማኒውም ያያት ነበር፤ ክርስትያኖች ይህንን ድንቅ ተአምር እያዩ እምነታቸው ሲጸናላቸው፤ ያላመኑት ደግሞ እያመኑ በመጠመቅ ሀብተ ውልድና ስመ ክርስትናን ይቀበሉ ነበር፡፡
♥ በጒልላቱ ላይ ስትገለጽ በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ ንጽሕት የኾነችው የቅድስት ድንግል ማርያም የፊቷ ውበትና ብርሃን እጅግ ድንቅ ነበርና ካህናቱም ሕዝቡም ኹሉ ልክ እንደ ኤልሳቤጥ “የጌታችን እናት ለእኛ ትገለጪ ዘንድ እኛ ምንድን ነን?” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ ርሷም ያለማቋረጥ ትባርካቸው ነበር፡፡
♥የእመቤታችን ፍቅር በእጅጉ የበዛለት አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ተገልጻ ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት ለርሱም ትገለጽለት ዘንድ በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፉ ላይ፡-
“አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ
ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ
ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ
ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሑ መዓልተ
ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ”
✍ (የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለዐምስት ቀናት ያኽል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያኽል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው) በማለት ተማፅኗታል፡፡
♥ ዳግመኛም ይኸው ኢትዮጵያዊ ሊቅ በተመስጦ፡-
“ሥዕልኪ ጽግይተ ላሕይ ዘከመዝ ትኤድም በዓለም
እፎ ይሤኒ በሰማይ ላሕየ ገጽኪ ማርያም
ሐሤተ ትእምርትኪ እጽገብ አስተርእዪኒ በሕልም
እስመ አውዐየኒ ነደ ፍቅርኪ ፍሕም
አጥፍኦቶ ዘኢይክል ዝናም”
✍ (ማርያም ሥዕልሽ በዓለም እንዲኽ የምታበራ ከኾነ በሰማይ የፊትሽ መልክ ምን ያምር! አንቺን ከማየት የሚገኘውን ደስታ እጠግብ ዘንድ በሕልም ተገለጪልኝ፤ ዝናብ ሊያጠፋው የማይቻለው የፍቅርሽ እሳት አንድዶኛልና) ብሏል፡፡
♥ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ይኽነን መገለጧን በእንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ በአድናቆት ፡-
“ኦ ንግሥት ይገንዩ ለኪ ነገሥት ወለኪ ንግሥታት ይትቀነያ
ወኪያኪ የአኲታ ወለስምኪ ይገንያ
ወለኪ ይሰግዳ ወለክብርኪ የሐልያ
ጢሮስ ወሲዶና ሰብአ ግብጽ ወኢትዮጵያ
ፊንቂ ወሮምያ ማሮን ወአርማንያ
በሥነ ጸዳልኪ ይትፌሥሓ ወበላሕይኪ ይትሐሠያ”
✍ (ንግሥት ሆይ ነገሥታት ለአንቺ ያገለግላሉ፤ ንግሥታትም አንቺን ያመሰግናሉ፤ አንቺንም ያሞግሳሉ፤ ለስምሽም ያጐነብሳሉ፤ ለአንቺ የጸጋ ስግደትን ይሰግዳሉ፤ ለክብርሽም ምስጋናን ያቀርባሉ፡፡ ጢሮስና ሲዶና የግብጽና የኢትዮጵያ ሰዎች፣ ፊንቄና ሮምያ፣ ማሮንና አርማንያ በወጋገንሽ ውበት ደስ ይሰኛሉ፤ በደም ግባትሽም እሰይ ይላሉ) በማለት ገልጦታል፡፡
❤ ❖✔ ቅዱስ ያሬድ አባታችንም በማይ ኪራሕ ሳለ እመቤታችን ተገልጻለት ፊቷን ለማየት ታድሏልና ይኽነን በዐይኑ ያየውን ውበቷን በድጓው ላይ እንዲኽ ሲል ጽፎታል፡-
✍️ “አይ ይእቲ ዛቲ እንተ ትወርድ እምሰማይ፤ ብርህት ከመ ፀሓይ፤ አዳም ቆማ ወክሣዳ ከመ አርማስቆስ፤ መዐዛ አፉሃ ከመ ኮል”
(ከሰማይ የምትወርደው እንደ ፀሐይም የምታበራው ርሷ ማን ናት! አንገቷ እንደ ግንብ ቀጥ ያለ ነው፤ የአፏም መዐዛ እንደ እንኮይ ነው) በማለት በተመስጦ የተመለከተውን ውበቷን ተናገረ፡፡
❤ ❖✔ ይኽ የቤተ ክርስቲያን ጌጥ ቅዱስ ያሬድ በዚኽ ሳያበቃ በመላእክት እየተመሰገነች ስለተገለጸችለት ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ያየውን የውበቷን ነገር ሲናገር፦
✍ “እምኀበ መላእክት ትሴባሕ አዳም ሥና፤ መዐርዒር ቃላ ወኲሉ ነገራ በሰላም … እምወርኅ ወእምፀሓይ ይሤኒ ላሕያ …ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ ወከመ ኮል መዐዛ አፉሃ ወከመ ሮማን ቂሐተ መላትሒሃ … "
❤ (በመላእክት ትመሰገናለች፤ ደም ግባቷ ያማረ ነው፤ ቃሏ እንደ ማር የጣፈጠ፤ ነገሯ ኹሉ በሰላም የተመላ ነው … ውበቷ ደም ግባቷ ከጨረቃና ከፀሓይ ይልቅ ያምራል፤ ከንፈሮቿ ፍሕሶ እንደሚባል አበባ ቀይ ናቸው፤ የጒንጯ ቅላትም እንደ ሮማን ቅርፍት ነው) እያለ ሊቁ ማሕሌታይ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይመሰክርላታል።
❤ የእመቤታችን ጣዕመ ውዳሴዋ የበዛለት ኢትዮጵያዊው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በእንዚራ ስብሐቱ ላይ ስለውበቷ በተመስጦ ሆኖ ያቀረበላትን ውዳሴ እነሆ፡-
☞ ☞ “ኦ ፍቅርት ውዕየ ልብየ በእሳተ ፍቅርኪ ወነደ ኅሊናየ እምኀልዮትኪ …” (ውዲቱ ሆይ በፍቅርሽ እሳት ልቤ ተቃጠለ፤ አንቺንም ከማሰብ የተነሣ ኅሊናዬ ነደደ፤ ለምስጋናሽ ቃሌን ከፍ ከፍ አደርጋለኊ፤ አንቺን ለማመስገንም አንደበቴን አከፍታለኊ፡፡ ንግሥት ሆይ አንደበቴ ቅንነትሽን በመናገር ደስ ይለዋል፤ ከንፈሮቼም በቸርነትሽ ጣዕም ነገር ደስ ይሰኛሉ፤ ሰላም እያልኹሽም ለስምሽ አጠራር እኔ እሰግዳለኊ (ኢሳ 49:23)፡፡
❤ንግሥት ሆይ የራስሽ ክፍክፋት ተፈጥሮ እንደ አሞራ ጥቁር የኾነ ጠጒርሽም እንደ ሐር የሚመስል ነው (መሓ 7:6)፤ የራስ ወርቅሽ የቃል ኪዳን ምልክት ነው፤ የንጽሕናሽ ብርሃንም እንደ ጧት ወገግታ ነው (መሓ 6:10)፡፡
❤ ግርምቲቱ ሆይ የቅንድቦችሽ ነበልባል (እሳት) የመብረቅ ፍንጣቂ ነው፤ ዐይኖችሽም እንደ ጨረቃ ምላት ብርሃንን የተመሉ ናቸው (መሓ 6:10)፤ ጆሮችሽም የደስታ በሮች ናቸው (ሉቃ 1:28)፤ የጒንጮችሽ ቅላትም እንደ ሮማን ቅርፍት ነው (መሓ 4:3)፡፡
❤ንግሥት ሆይ አፍሽ የበጎ መዐዛ መስኮት ነው፤ ከንፈሮችሽም የደስታ መፍሰሾች ናቸው (መሓ 4:9)፤ የአፍንጫሽ መዐዛም የበረሓ እንኮይ ነው (መሓ 7:9)፤ የጥርሶችሽ ንጣትም እንደሚያምር በረዶ ነው (መሓ 4:2)፡፡
❤ ምርጢቱ ሆይ የአንደበትሽ ሥር የወተት ምንጭ ነው፤ የንግግርሽ ቃልም እንደ ማር የጣፈጠ ነው (መሓ 4፡12)፤ የእስትንፋስሽ ቃልም የሽቱ ቅመም ብናኝ ነው፤ ጒረሮሽም፣ የማር ወለላ አረፋ ነው፡፡.
❤ የተሸለምሽ ያጌጥሽ ሙሽሪት ሆይ፤ የአንገትሽ መገናኛ (ቅርጽ) እንደ ወርቅ ዘንግ ነው (መሓ 1:11)፤ ትከሾችሽም የሰላምና የቅንነት ማረፊያዎች ናቸው፤ የጀርባሽ ልብስም የብርሃን ሐር ነው (ራእ 12:1)፤ ደረትሽም የዕውቀት አዳራሽ ነው፤ ጉያሽ የመለኮት (የጌታ) ማረፊያ ናቸው፤ እጆችሽም በንጽሕና አንባር የተሸለሙ ናቸው፤ ክንዶችሽም የንጉሥ (የጌታ) መጠጊያዎች ናቸው፤ ክርንሽም የኀይል ረድኤት ቦታ ነው፤ ክንዶችሽም የእሳት ምሳግ ናቸው፤ መኻል እጆችሽም ለመስጠት የተዘረጉ ናቸው፤ በጥፍሮችሽ የተጋረዱ ጣቶችሽ እንደ ወርቅ ፍቅፋቂ ነው::
❤ ሙሽሪት ሆይ ጡቶችሽ እንደ ወይን ፍሬ የተወደዱና ያማሩ ናቸው (መሓ 7:8) ፡፡ ጐኖችሽም በወርቅ ሐመልማል የተሣሉ (ያጌጡ) ናቸው (መዝ 67(68):13)፡፡ የማሕፀንሽ መቅደስ በአበባ (በጸጋ መንፈስ ቅዱስ) የታጠረ ነው፣ (መሓ 7/3) የልቡናሽ ጥልቀትም በቸርነት ቃል፤ ኲላሊቶችሽ የትእዛዝ ጽላት ናቸው፤ ኅሊናሽም የጥበብ መሠረት ነው፤ አንጀትሽም የይቅርታ ሣጥን ነው፤ የውስጥ ሰውነትሽም የቅዱሳን ቅድስት ምልክት ነው፤ የዕንብርትሽ ዙሪያም እንደ ማኅተም ቅርጽ ነው (መሓ 7:3)፤ ማሕፀንሽም የምስጋና ዙፋን ነው::
❤ የድንግልናሽም ምሳሌ፤ የታተመ የነቢያት መጽሐፍ ነው (ኢሳ 29:11)፤ የወገብሽ ትጥቅም የቅድስና ጸጋ ነው፤ ጒልበትሽም የአርያም (የሰማይ) ወገን ናቸው፤ የጭኖችሽ (የእግሮችሽ) አነዋወርም እንደ እብነ በረድ ምሶሶች ነው፤ እግሮችሽም ምሕረትን ለማድረግ የተፋጠኑ ናቸው፤ የማይታበዩ ጫማዎችሽም የጥበብ መድረክ ናቸው፡፡ እግርሽም በቅንነት ጐዳና የጸኑ ናቸው፤ የእግርሽ ጣቶችም በጥፋት ደንጊያ የማይሰነካከሉ ናቸው፤ ጥፍሮችሽም በላያቸው እንደ ብርሃን ብልጭ የሚሉ ናቸው፡፡
❤ የቁመናሽ አካልም እንደ ዘንባባ ያማረ ነው (መሓ 7:8)፤ የመልክሽ ደም ግባትም ለዐይን የተወደደ ነው፤ ድንግል ሆይ እጅግ በጣም አማርሽ፤ ከራስሽ እስከ እግርሽ ክፉ ነገር የለብሽም (መሓ 4:7)፤ ደም ግባትሽን የሚመስለው የለም፤ ኹለንተናሽንም የሚተካከለው የለም፡፡ ምርጢቱ ሆይ መልካም በኾነውና በጎም በኾነው ኹሉ መሰልኹሽ ነገር ግን ምስጋናሽን መጨረሽ አልቻልኹም፡፡)፡፡ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ)
♥ የመልክአ ማርያም ደራሲም የአምላኩን እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን ፊቷን ለማየት ሽቶ በናፍቆት ኾኖ፡-
“ሰላም ለመልክእኪ ዘተሠርገወ አሜረ
ዘያበርህ ወትረ
ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ
አርእዪኒ ገጸ ዚኣኪ ማርያም ምዕረ
ዘኢይሰምዖ ካልእ እንግርኪ ነገረ”
♥ (ኹልጊዜ (ዘወትር) የሚያበራ ፀሓይን ጌጥ ላደረገ መልክሽ ሰላምታ ይገባል፤ ፍቅርን የምትመርጪ (የምታስቀድሚ) አንቺ ፍቅረኛዬ ማርያም ሌላ የማይሰማው ነገርን እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ያንቺን ፊት ግለጪልኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡
♥ በመኾኑም በደብረ ምጥማቅ የተገለጠችላቸው ምእመናን የአምላክን እናት አይተው እንደተደሰቱ፤ ዛሬም ለእኛ በመስቀል ሥር ከልጇ ለተቀበለችን ለአደራ ልጆቿ በረድኤት ትገለጽ ዘንድ አበው ካህናት ሌሊቱን በሰዓታት ምስጋና፦
✍ “ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ወልድኪ ፍቁርኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትባርኪ ላዕሌነ” (ድንግል ሆይ ከተወዳጅ ልጅሽ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ ወደ እኔ ነዪ እኛን ትባርኪ ዘንድ (በእኛ ላይ በረከትን እንድታሳድሪ) በማለት ይማፀኗታል።
[የአምላክ እናት ሆይ ዛሬም ለእኛም በእጅጉ ለምንወድሽ ለልጆችሽ በረድኤት ትገለጪልን ዘንድ እንማፀንሻለን፡፡]
የቴሌግራም ገጼ https://t.me/joinchat/AAAAAFTyR7tztt08pN9U-w
✍ ከመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
👉 በመስቀል ሥር ስጦታችን የተጽናናችሁ የብርሃን ልጆች በአስተያየት መስጫው ላይ እናታችኹን አወድሷት።
23/05/2025
✍️ብልጽግና ዋና ሴራ ስኪያጁን መርጧል!
********************************** **
የብልጽግናው ዋና ሴራ አስኪያጅ ባለሙሉ ሥልጣን ሆኖ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተቀምጧል፡፡ በመጨረሻም ሰዎቹ እንደፎከሩት፣ እንደቀሰቀሱት ቤተ ክርስቲያንን ከነሁለንተናዋ ተረክበዋል፡፡ ያ ሁሉ ግርግር፣ ያሁሉ እስር፣ ያ ሁሉ ቅስቀሳ ለዚህ ነበር፡፡
የኢትዮ ፎረሙ ዘገባ ወገባቸውን የመታው፣ ሴራቸውን ቀድሞ ያጋለጠባቸው ለዚህ ነበር፡፡ ያንን ሲያጣጥሉ የነበሩ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች አሁን እርማቸውን ያውጡ፡፡ ሁኔታዎችን ባለመረዳት ጭምር ቤተ ክርስቲያናቸውን አዘናግተዋታልና፡፡ አሳዛኞች፡፡
ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል ቀንደኛ የነበረውን ሰው፣ 'መክፈል ምን ይሠራልሃል፣ ገብተህ ሙሉውን ተረከብ እንጂ' በሚለው የብልጽግና ፈሊጥ ምክንያት ይኸው በቦታው ላይ አስቀምጠውታል፡፡ አሁን ከልካይም፣ ተቆጭም ገልማጭም፣ አምቢ ባይም የላቸውም፡፡ የፈለጉትን የሚሹትን የሚያደርጉበትን ሥልጣን ይዘዋል፡፡ ምክትላቸው ቄስ በላይ ገንዘብ ሠርቆ ታሠረባቸው እንጂ ያኔ ጀምረው ያቀዱት ይኸንን ሙሉ ወረራ ነበር፡፡
ቦታውን የፈለጉት ለቤተ ክርስቲያን ሥራ ሊሠሩላት ሳይሆን ሊሠሩባት፣ ቤተ ክርስቲያንን ሊያዋርዷት፣ ሊዘርፏት፣ ሊቀሟት ነው፡፡ ለብልጽግናም ሰጥ ለጥ ብላ እንድትገዛ ለማድረገ ነበር፡፡ አሁን ቤተ ክርስቲያ በገጣባ አህያ ተወራለች፡፡ ጫካ ሄዶ ሲኖዶስን ከከፈለ ሰው በላይ በክርስትናው ገጣባ አህያ ከየትም አይገኝም፡፡ ገጣ አህያ ደግሞ ጠባዩን ባለፈው አስረድቻለሁ፡፡ ክህደቱ፣ ሸፍጡ፣ ዘረኝነቱ ያመረቅዝበታል እንጂ የሚድንበት አንዳች እድል የለውም፡፡ በድለዳል፣ በጨርቅ ወዘተ ብታለባብሰው የሚሆን አይደለም፡፡
አሁን ያ ጸጉሩ መሸበቱን ለማየት ቆራጩን ሲያጣድፈው ለነበረው ሰው 'ሲወድቅ ልታየው ምን ያስቸኩልሃል እንዳለው' ቤተ ክርስቲያንም ጸጉሯን ተላጭታ፣ ሸበቶውን በግላጭ ፊታችን ወድቆ አየነው፡፡ መልኳ ተቀየረ፣ ያለ ተቆርቋሪ ቀረች፣ አሳልፋ ተሰጠች፣ ሲሞናዊነት ዐይኑን ጨፍኖ መላዋን ወረራት ማለት ነው፡፡
አሁን ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቃትን የተጠናከረ ስደት፣ ሊሆንባት የታቀደውን፣ ማንንም መጠየቅ አያስፈልገንም፣ ራሳችን ፊት ለፊታችን መከራዋን ሲገለጥ አየነው፡፡ ሳዊሮስ መከራ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ሳዊሮስ አሳልፎ ሻጭ ነው፡፡ የምናውቅለት ታሪኩ ይኸ ነው፡፡
አሁን ያኔ 'ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር እርስዎ እኮ ቤቱን ትተውታል፣ እስከዛሬ እኮ እንዲህ አልነበረም' ያለውን ቃል ለመፈጸም፣ ቤተ ክርስቲያንን ለብልጽግና አሳልፎ የሚሰጥበትን ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡
በኦሮሚያ የሚደረግ የቤተ ክርስቲያን ስደት፣ በዐዲስ አበባ የሚደረግ የቤተ ክርስቲያን ወረራ ያለማንም ተቆጭና ገልማጭ ያስፈጽሙታል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ከላይ እስከ ታች፣ ከታጠቀ ኃይል እስከ ስለላ መረብ ተብትበው ተቆጣጥረውታል፡፡ 'ምንም አታመጡም እንዳሉት' አድርገውታል፡፡
አሁን ሁሉም በእጃቸው ነው፣ ዛሬ ደግሞ በጻዕር ላይ የነበረውን ጠቅላይ ቤተ ክህነትንም ፈጽመው ገድለውታል፡፡ ያንን ያደረጉት ደግሞ 'በመንፈስ ቅዱስ ይመራሉ' የተባሉት አባቶች ሲሆኑ በመንፈስ ቅዱስ መመራታቸውን ትተው እነ ከድር በጠቆሟቸው መሠረት የእነ ከድርን አባት የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ (ሴራ) አስኪያጅ አድርገው መርጠዋል፡፡
በእኔ በኩል ቤተ ክርስቲያኔን የተቀማሁት ዛሬ ነው፣ ዛሬ የግመሉን ወገብ የሰበረው የመጨረሻው በትር ቤተ ክርስቲያን ላይ አርፎል አይቸዋለሁ፡፡ ምእመናን ሰሚ እንደሌላቸው፣ ጠላት ደግሞ የፈለገውን ነገር የማድረግ አቅሙን ያሳዩበት ነው፡፡ ሰማያዊቷን ቤተ ክርስቲያን ሊቀሙን ባይችሉም፣ የሰማያዊቷን ቤተ ክርስቲያን ማሳለጫ የሆነችውን የምድራዊቷን ቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ያላቸውን ኃይል ተጠቅመው ከምእመናን መቀማት የቻሉበት ቀን ተደረጎ ይወሰዳል፡፡
አሁን ውሉ ወደማይታወቅ፣ እጅግ በሚያሳስብ ጨለማ ተወርውረናል፣ መዋቅሩም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወድቋል፡፡
ዳሩ ግን ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ ይኖራት ይሆን? ለዚህስ የሚረባረቡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይኖሩ ይሆን? ምእመናን ሰፊ ትግል ይጠይቀናል፡፡ ይኸንን ችላ ብለን የተውን እንደሆነ፣ በመዋቅሯ ሽባነት ስደት፣ ፈተና፣ የመንጋ ነጠቃ መከራ ስትቀበል የቆየችው የነበረችው ቤተ ክርስቲያን፣ አሁን ደግሞ በቅሰጣ ባልሆነ ነገር ግን በሁለንተናዊ ነጠቃ ሙሉ በሙሉ ልናጣት የምንችልበት አጋጣሚ ተፈጥሯል፡፡
አሁን ድርሻው የምእመናን ነው፡፡ እለ ከድር በመረጡላቸው፣ ፖለቲከኞች እንደፎከሩት ባስቀመጡላቸው ሰው ሴራ አስኪያጅነት እየተመሩ ቀጣዩን ሦስት ዓመታት ቤተ ክርስቲያናቸውን በማፍረስ ይተባበራሉ? ሰውየውም ቃል እንደገቡት ቤተ ክርስቲያኗን ከነሁለንተናዋ ለብልጽግና ሲያስረክብ ዝም ብለው ያዩ ይሆን? የሚሉት ጥያቄዎች በቀጣይ የሚታዩ ይሆናሉ፡፡
ሰፊ ትግል፣ ሰፊ ርብርብ የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ወድቀናል፡፡ አሁን መተኛት እንኳን የሚቻለው በአንድ ዐይን ብቻ ይሆናል፡፡ አሁ ይሉኝታ ሊኖር አይገባም፣ አሁን የውጭና የውስጥ የሚባል ጠላት ቀርቷል፣ አሁን ያለው የውስጥ ጠላት ሆኗል፡፡ የውጩም ከነመሣሪያው ውስጥ ገብቶ ተጠቃሏል፡፡
ትግሉም ዋጋ የሚያስከፍል ዋጋም የሚያሰጥ ነው የሚሆነው፡፡
አንቺ ቤተ ክርስቲያን መጽናኛ ይስጥሽ!
02/05/2025
የፈይሳ አዱኛ ጠቅላላ ማኅበር ፈቃድ በጊዜያዊነት ታገደ !
ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም [አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ]
ፈይሳ አዱኛ ጠቅላላ ማኅበር በሰኔ 10 ቀን 2015 ዓም ፈይሳ አዱኛ መንፈሳዊ ማኅበር በሸገር ሲቲና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ተደራጅቶ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲሠጥ የተፈቀደልት መሆኑን የሚታወሰው ይህ ጠቅላላ ማኅበር፤
ማኅበራት ፍቃድ ማውጣት የሚገባቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው መመሪያ መሠረት ከማኀበራት ምዝገባ ክትልና ቁጥጥር መምሪያ መሆን ስላለበት ቀደም ሲል በጊዜያዊነት እንድታገለጉልበት የተሰጣችሁ የአገልግሎት ፈቃድን ሀገረ ስብከቱ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥር 04/2015 በቀን 11/10/2015 ዓ.ም ማኅበሩ ተሰጥቶት የነበረው የአገልግሎት ፈቃድ የተሰረዘ መሆኑን በተጠቀሰው ደብዳቤ ቁጥርና ቀን ገልጾ ማገዱ ይታወሳል።
በመሆኑም ይህ ማኅበር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራት ምዝገባ፣ ክትትልና ቁጥጥር መምሪያ ተመዝግቦ በቁጥር ማ/ም/ክ/ቁ/27/17 በቀን 20/08/2017 ዓ.ም ፈቃድ የተሰጠው መሆኑንና መምሪያው የማኅበራት ምዝገባ ፈቃድ ከሚሰጥበት የውስጥ አሠራር መካከል አንዱ በሀገረ ስብከት ደረጃ በሊቀ ጳጳሱ ለማኀበሩ የተሰጠ ደብዳቤ ወይም የምስክር ወረቀት ማቅረብ ስለሆነ ማኀበሩ ከደቡብ ምዕራብ ሸዋና ከሸገር ሲቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተጻፈ ደብዳቤና የማኀበርነት ዕውቅና የምስክር ወረቀት ማቅረቡን በማረጋገጥ ፈቃዱን መስጠቱን ባወጣው የእገዳ ደብዳቤ ላይ አስታውሷል።
ይሁን እንጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ሲቲ አህጉረ ስብከት ለመምሪያው በቁጥር 2199/2017 በተን 11/08/2017 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ሰፈይሳ አዱኛ መንፈሳዊ ማኅበር የሰጠውን የፈታድ ደብዳቤና የምስክር ወረቀት ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሻረ መሆኑን በመጥቀስ በመምሪያው በኩል ላማኅበሩ የተሰጠው ፈቃድ እንዲሰረዝ ለጠየቀው ጥያቄ መምሪያው ማኅበሩ ከአህጉረ ስብከቱ ፈቃድ አግኝቶ ማስረጃውን ለመምሪያው እስከሚያቀርብ ድረስ ከመምሪያው የተሰጠው የጠቅላላ የማኅበርነት ፈቃድ ለጊዜው የታገደ መሆኑን በማሳወቅ በማኅበሩ ስም ከሚደረግ ማንኛውም እንቅቃሴ ማኅበሩ እንዲታቀብ መንፈሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ በጻፈው ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል።
26/04/2025
ከሀገር አቀፍ የሊቃውንት ጉባኤ ምን እንጠብቅ?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እስካሁን እንድትኖር ታላቁን ሚና የተጫወቱት ሊቃውንት ናቸው። መጻሕፍትን ከሌላ ቋንቋ ተርጉመው በማስተማር ምእመናን ሃይማኖታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ትልቁን ሚና የተወጡ ሊቃውንት ናቸው። በተዘዋዋሪ አሁን በቤተክርስቲያን ላይ ለሚደርሱ ችግሮች ዋና ተጠያቂዎችም ሊቃውንት ናቸው። ምክንያቱም ሊቃውንቱ አንድ ሆነው ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ሁሉም በየራሱ በመሄድ ሕብረታዊነት የሌለበት ግላዊ እይታዎች የልዩነት ምንጭ እስከ መሆን ደርሰዋልና ነው። ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሱ ላሉ ችግሮች ሁሉ መፍትሔው (መድኃኒቱ) ያለ በሊቃውንት እጅ ነው።
የሊቃውንት የአንድነት ጉባኤ ትልቅ ተስፋ ያለበትና ለቤተክርስቲያናችንም ትልቅ የምሥራች ነው። ይህ ከሆነ ከሊቃውንት ጉባኤ ምን እንጠብቅ? በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮች ምን ምን ናቸው መፍትሔያቸውስ? የሚለውን በአጭሩ ለመግለጽ ልሞክር።
፩ኛ፦ ዘረኝነት፦ ይህ ደዌ ከፖለቲካው አልፎ በብፁዓን ጳጳሳት፣ በመምህራን፣ በቀሳውስት፣ በዲያቆናት፣ በምእመናን ሲቀነቀን እንደ ማየት የሚያሳዝን ነገር የለም። ይህ የዘረኝነት አባዜ ከሀገር ወደ ክልል፣ ከክልል ወደ ክፍለ ሀገር፣ ከክፍለ ሀገር ወደ ዞን፣ ከዞን ወደ ወረዳ፣ ከወረዳ ወደ ቀበሌ፣ ከቀበሌ ወደ ቤተሰብ፣ ከቤተሰብ ወደራስ የደረሰ ክፉና ሀገራችንንም ትልቅ ችግር ውስጥ የከተተ ነው። ይህ የዘረኝነት አባዜ በመንፈሳዊ ሹመት ውስጥም ገብቶ ፖለቲካዊ የክህነት ሹመት እስከማየት ደረስን። የብሔር ሲኖዶስ እስከ መቋቋም ደረሰ። የሊቃውንት ጉባኤው በሐዋርያት ቀኖና መሠረት ባለፉት ዘመናት የተፈጸሙ ችግሮችን ሳይቀር አንሥቶ ወጥ መፍትሔ እንደሚሰጥ ተስፋ አደርጋለሁ።
፪ኛ፦ የምንኩስና ጉዳይ፦ መነኮሳት በገዳም ብቻ ተወስነው መኖር እንዳለባቸው መጻሕፍተ መነኮሳት በስፋት ይገልጻል። በመጽሐፈ ገነትም ዓሣ ከውሃ ከወጣ እንደሚሞት ሁሉ መነኵሴም ከገዳም ከወጣ በምግባር የሞተ እንደሚሆን ተገልጿል። በመነኮሳት ምክንያት ምእመኑን አላስፈላጊ ሐሜት ውስጥ ከተትነው። እገሌ ወልዷል፣ እገሌ ልጅ አለው እስከ መባል ተደረሰ። ለምንኩስና የነበረው ክብርም ቀነሰ። ስለዚህ የሊቃውንት ጉባኤው በዚህ ዙሪያ ተወያይቶ ቋሚ ውሳኔ ማስተላለፍ ይገባዋል። ምንኩስናን መሠረት አድርገው የመጡ ችግሮች ሁሉ በዚህ መንገድ እንደሚፈቱ ተስፋ አደርጋለሁ።
፫ኛ፦ አስተምህሮ የሚከለክላቸው ነገር ግን በድንገት የተለመዱ አካሄዶችን ማረም ይገባዋል። ለምሳሌ ሴት ልጅ ወንዶች ባሉበት ጉባኤ መዘመር፣ ማስተማር አይገባትም ይላል ቅዱስ ጳውሎስ። ይህንን በተግባር የሚያስፈጽሙ አድባራትም አሉ። ምናልባት ከሃምሳ ዓመት ወዲህ ግን በሴት ዘማርያት ተጥለቅልቀናል። ይህንን በአንድነት ወስኖ ወይ ቀኖና ሠርቶ ለወደፊቱ የሚቀጥሉበት፣ ወይም የአዘማመር ሂደቱን በሥርዓት የሚያከናውኑበት መንገድ መዘርጋት አለበት።
፬ኛ፦ በቤተክርስቲያን ውስጥ አጥማቅያን የሚባሉ፣ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባሉ፣ እነ እኅተ ማርያም የሚያስጨበጭቧቸው ቡድኖች፣ የቅባት እምነት ተከታዮች፣ የሙስና ሰንሰለቶች በስፋት እየታዩ ነው። እነዚህን የጉባኤ ክርክር የሚያስፈልጋቸውን በጉባኤ ክርክር፣ ሌሎችንም በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ገምግሞ ቋሚ የሆነ የማያዳግም ምላሽ መስጠት ይገባዋል።
፭ኛ፦ ሥርዓት ተኮር ልዩነቶችን ማጥበብ፦ ከጊዜ ብዛት የተነሣ አንዱ መምህር የፈቀደውን ሌላው ሲከለክል፣ አንዱ ያወገዘውን ሌላው ሲፈቅድ እያየን ነው። ይህ ደግሞ ምእመናንን እስከመከፋፈል የደረሰ ስለሆነ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሔ ቢሰጠው። ቀላል ምሳሌ ላንሣ በዘመነ ዮሐንስ የነቢያት ጾም ህዳር 14 ነው መጀመር ያለበት አይ አይደለም ህዳር 15 ነው በሚል የተፋቱ ባልና ሚስቶች ሳይቀር አሉ። የእነርሱ ልዩነት ምንጭ ደግሞ መምህራን ናቸው። ይህንን የመሳሰሉ በርካታ የሥርዓት ልዩነቶችን ስለምእመናን ሲባል ወጥ ሥርዓት ማድረግ ይገባል።
፮ኛ፦የቤተክርስቲያን መጻሕፍት በሊቃውንት ጉባኤ ታይተው በአንድ ማተሚያ ቤት ወጥተው ለሕዝቡ መድረስ ይገባቸዋል። ገዳማት፣ ጉባኤ ቤቶች፣ ደብሮች በየራሳቸው የቤተክርስቲያንን መጻሕፍት ማሳተም የለባቸውም። ከዚያ ይልቅ በማእከላዊነት በጠቅላይ ቤተክህነት በኩል መታተም ይገባቸዋል። የአንድምታ መጻሕፍት በአፄ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያ ሊቃውንት መክረውባቸው በሕብረት እንደተዘጋጁ ሁሉ አሁንም በአንድነት ከጉባኤ ጉባኤ ሳይለያይ ወጥ እንዲሆን በጋራ ቢዘጋጁ። በገድላትም፣ በትርጓሜ መጻሕፍትም በሌሎችም ፖለቲከኞች ለራሳቸው ዓላማ እየመዘዙ ምእመናንን የሚለያዩባቸውን ቃላት መርምሮ ከምን አንጻር እንደተነገሩ አብራርቶ ለቀጣዩ የልዩነት ምንጭ እንዳይሆኑ መፍትሔ መስጠት ይገባል።
፯ኛ፦ ሀገራችን ካለችበት ችግር አንጻር ብዙ የወንበር መምህራን ከጉባኤው እንደማይገኙ ይታወቃል። ቢሆንም ግን ባሉበት ቦታ ሆነው በስልክ፣ በጽሑፍ ሐሳባቸውን ልከው እንዲነበብና የእነርሱም ሐሳብ እንዲታይ ቢደረግ። በትግራይ ብዙ መምህራን እንዳሉ ይታወቃል። ተጠርተው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም። ነገር ግን የእነርሱንም ሐሳብ መቀበል የሚቻልበት መንገድ ቢፈጠር። ለተፈጠረው የቀኖና ጥሰት ቀኖናዊ መፍትሔ እንዲሰጠው ሊቃውንቱ የመፍትሔ ሐሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። በዚህ መልኩ እስከ መቼ እንቀጥላለን?! ጠንካራና የተናበበ ኦርቶዶክሳዊ ሕብረት እንዲፈጠር ቢወያዩ።
፰ኛ፦ አሁን በጠቅላይ ቤተክህነት ያሉ የሊቃውንት ጉባኤ አባላት እያንዳንዳቸው የወንበር መምህራን የነበሩ፣ በየራሳቸውም ትልልቅ ጥራት ያላቸው መሆናቸው ግልጽ ነው። ነገር ግን በእኛ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ዙሪያ በሌሎች ቤተ እምነቶች ብዙ ስሑታን መጻሕፍት ሲጻፉ ከሊቃውንት ጉባኤው ግን ብዙ ጊዜ መልስ ሲሰጥ አናይም። ስለዚህ የሊቃውንት ጉባኤው እንዳለ ሆኖ አቅም ያላቸው ታላላቅ ሊቃውንትንም ቢጨምርና በቤተክርስቲያን ላይ ለሚደርሱ የተሳሳቱ ትምህርቶች ወቅታዊና አፋጣኝ ምላሽ የሚያገኙበትን ሁኔታ ቢያመቻች። እንደ ሐሳብ በሀገራችን ያሉ የወንበር መምህራን ሁሉ ከዋናው የሊቃውንት ጉባኤ በተጨማሪ ኢመደበኛ የሊቃውንት ጉባኤ አባላት ቢሆኑና በየጊዜው ያላቸውን ሐሳብ የሚያቀርቡበት ሁኔታ ቢመቻች።
፱ኛ፦ የመምህራን ምደባን በተመለከተ፦ በአቋቋም፣ በድጓ፣ በመጻሕፍት፣ በቅኔ፣ በዝማሬ መዋሥእት፣ በቅዳሴ በየጊዜው ብዙ መምህራን ይመረቃሉ። ነገር ግን ከተመረቁ በኋላ የሚያያቸው አካል የለም። ስለዚህ ቤተክርስቲያን የመምህራን ቋሚ የደመዎዝ ስኬል አዘጋጅታ ሁሉንም መምህራን መያዝ ብትችል። በበረኃ፣ አሕዛብ በሚበዙበት ቦታ፣ በገጠር ተቀጥረው ሕዝቡን ለሚያስተምሩ መምህራን ልዩ ጭማሪ ደመዎዝ በመስጠት ክርስትና እንዲስፋፋ ያለውም እንዲጸና ቢደረግ። ጉባኤ ቤቶች ወቅቱን የዋጁ ይሆኑ ዘንድ አንድ ደቀመዝሙር እስኪመረቅ ድረስ ከመደበኛው ትምህርት በተጨማሪ ልዩ ልዩ ሥልጠናዎችን እንዲሰለጥን ቢደረግ።
፲ኛ፦ ያለንን የሰው ሀብት መጠቀም የምንችልበት መዋቅር ቢዘረጋ፦ ይህንንም ስል ቤተክርስቲያን ብዙ ዶክተሮች፣ ብዙ ኢንጂነሮች፣ ብዙ መምህራን፣ ብዙ ፓይለቶች፣ ብዙ ተመራማሪዎች፣ ብዙ ወታደሮች፣ ብዙ ጀነራሎች፣ ብዙ ፖለቲከኞት፣ ብዙ ዳኞች፣ ብዙ አርበኞች፣ በጠቅላላው በልዩ ልኑ ሙያ ተሠማርተው የሚገኙ ልጆች አሏት። እነዚህን ሁሉ የምትይዝበት መዋቅር ግን የላትም። እኒህን ምሁራን የምትይዝበት ልዩ መዋቅር ዘርግታ ክርስትናን የተረዱ ሁሉም በየሙያቸው ለሀገር የሚጠቅሙ እንዲሆኑ ማድረግ የምትችልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ቢቻል። ሌላው የተቸገሩ እናት አባቶች፣ እናት አባት የሞቱባቸው የሙት ልጆች፣ በጠቅላላው ኑሮ ከብዷቸው በመንገድ የወደቁ ክርስቲያኖችን በቋሚነት የሚረዳና ሁሉም ክርስቲያን ከችግር ወጥቶ በአንድነት መንፈስ የሚኖርበትን መንገድ ማመቻቸት ቢቻል። ድርጅት መክፈት ካስፈለገ መክፈት። በሕብረታዊነት ካሰብን አንዱ እየተቸገረ አንዱ ደስ ብሎት የሚኖር ክርስቲያን መኖር የለበትም።
እነዚህንና የመሳሰሉ ጉዳዮችን ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ያለውን ተደራራቢ ችግር ነቅሎ የሚጥል መፍትሔ ከሊቃውንቱ እንደሚገኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ቀሪውን የልጅነቴን ለመወጣት ያህል መምህራን ቢገናኙ ሊፈቷቸው የሚችሉ ልዩነት የሚመስሉ ግን ያልሆኑ፣ በምእመናን ዘንድ ግን ልዩነት የሚመስሉ፣ ከጉባኤ ቤት ጉባኤ ቤት ልዩ ልዩ አገላለጽ ያላቸው 93 ጉዳዮችን በአሥር ገጽ ጸፌ ለሚመለከተው አካል አስገብቻለሁ።
መምህሮቻችን ሊቃውንቱ ለሚገናኙበት ዕለት እንኳን አደረሰን።
አንድ ጌታ
አንድ ሃይማኖት
አንድ ጥምቀት
አንድ ኅብረታዊ አረዳድ
እናንተም የምትጨምሩት ካለ እስኪ ግለጹት። ችግሮቻችንን በትክክል ማወቅ ራሱ የመፍትሔው ግማሽ ነው ይባላልና።
© በትረ ማርያም አበባው
26/04/2025
"ገድል ይነገራል እንጅ አይሰበክም" - ምን ይሉት አቃቂር ነው?
የሰሞኑን አነጋጋሪ አባት በሌላ ቪድዮ በተመሳሳይ አዳራሽ እንዲህም ብለዋል።
"ገድለ ቅዱሳን ይነገራል ይተረካል እንጅ አይሰበክም። ድርሳን ይነገራል ይተረካል እንጅ አይሰበክም። ነገር ግን ለዘለዓለሙ የሚሰበከው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።"
ሲጀመር ስብከት ማለት ምንድን ነው? በመንገር፣ በመተረክ እና በመስበክ መካከል ያለውስ ልዩነት? ይነገራል ይተረካል እንጅ አይሰበክም ማለት ለምን አስፈለገ? ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ማለትስ ጓዙ ምንድን ነው?
ስብከት ምን ማለት ነው?
የጥሬ ቃሉ ፍች
መስበክ ማለት:- ማብሠር፣ ማስተማር፣ በታላቅ ቃል መጮኽ፣ ማሰማት፣ መልፈፍ፣ መለፍለፍ፣ ዐዋጅ መንገር፣ ማዜም፣ መዘመር፣ ማውራት፣ መመስከር ተብሎ ይተረጎማል።
ስብከት ማለትም ትምህርት፣ ዐዋጅ፣ ወሬ፣ ታሪክ ማለት ነው ይላሉ አለቃ ኪዳነ ወልድ።
ከዚህ ትርጉም ስንነሣ የስብከት ዐውዱ ሰፊና ብዙ መኾኑን እንረዳለን። በአመዛኙ ለቃለ እግዚአብሔር የተመደበ ቢኾንም ስለ ሌላ ነገርም ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። በአጭሩ መልእክት ማስተላለፍን ይመለከታል። በቃል የሚከናወን እንደኾነ በታላቅ ቃል መጮኽ ከሚለው መረዳት ቢቻልም በጽሑፍም ሊኾን ይችላል። ለምሳሌ "ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው፡ ይላል" የሚለው የጠቢቡ ቃል በጽሑፍ እንጅ በቃል የተላለፈ አይደለም። መክ ፩: ፪።
መንገር፣ መተረክ እና መስበክ
መስበክ
ከቃሉ ፍች እንደተረዳነው በመስበክ፣ በመንገር እና በመተረክ መካከል የትርጉም ልዩነት የለም።
አቡኑ በመናገር፣ በመተረክ እና በመስበክ መካከል የነገረ መለኮት ልዩነት ያለ አስመሰሉት እንጅ ቃላቱ ተመጋጋቢ፣ ተገናዛቢ፣ ተተካኪ አቻ ትርጉም ያላቸው ናቸው። ገድልንም ኾነ ድርሳንን ይነገራል ይተረካል እንጅ አይሰበክም ሲሉ የሰማይና የምድር ያኽል ያራራቋቸው መስሏቸው ከኾነ አያጣሏቸው አንድ ናቸው ነው መልእክታችን።
ክርስቶስን መስበክ ማለት ስለ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት እና መድኃኒትነት ማስተማር፣ መንገር፣ መመስከር፣ መተረክ፣ ማዜም፣ መጻፍ ማለት ነው። ገድላትና ድርሳናት እንዲሁም ሌሎች አዋልድ ከዚህ ተልእኮ ውጭ አይደሉም። ሥራቸው ክርስቶስን መስበክ ነው። አቡኑ ራሳቸው ይቅርታ በጠየቁበት መድረክ ይኽን ብለዋል እና ብዙ ማስረጃ ማቅረብ አያስፈልገኝም። ውዳሴ ማርያም የሚወድዱት ጸሎት እንደኾነ ከነገሩን ጋር ነገረ ክርስቶስ የተብራራበት ታላቅ መጽሐፍ እንደኾነ መስክረዋል። እውነት ነው! ታዲያ ምኑን ነበር "ሌላውን ድርሰት ተውት" ያሉት?
ገድላት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በቃልም በተግባርም ከመስበክ አልፈው በሞታቸው የሰበኩ የመሰከሩ ቅዱሳን ዜናዎች ናቸው። ክርስቶስን በሕይወትና በሞት ከመስበክ በላይ ምን ዓይነት ክርስትና አለ?
"የክርስቶስ ክብር በሕይወቴም ቢኾን በሞቴም ቢኾን በሰውነቴ ይገለጣል" እንዲል። ፊል ፩: ፳።
መቼም ኢየሱስ ክርስቶስ ይሰበካል ሲሉ ከወንጌል ልዩ ማለታቸው አይኾንም ብለን እንገምታለን። ባልነገሩን ላይ ማመን አስቸጋሪ ቢኾንም ከግማሽ ተሩብ በላይ ሔደን እንዳይርቁ እናቅርባቸው በሚል። ለማንኛውም ወንጌል ይሰበካል ለማለት የሚከተሉትን የመጽሐፍ ክፍሎች ማየት ይበቃል።
+ ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ኹሉ ይዞር ነበር። ማቴ ፱: ፭።
+ እንዲህም አላቸው ወደ ዓለም ኹሉ ሒዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ማር ፲፮: ፲፭።
ይኸው ስብከተ ወንጌል በሌላ አገባብ ወንጌል ማስተማር ወይም ትምህርተ ወንጌል እየተባለ ተነግሯል። ለምሳሌ ቀጥሎ ያሉትን የመጽሐፍ ክፍሎች እንመልከት:-
+ ይህን ከንቱ ነገር ትታችሁ ሰማይና ምድርን፥ ባሕርንም በውስጣቸውም ያለውን ኹሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እናስተምራችኋለን። ሥራ ፲፬: ፲፭።
+ ነገር ግን የእግዚአብሔርን የጸጋውን ወንጌል እንዳስተምር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበልሁትን ሩጫዬን እንድጨርስና መልእክቴንም እንድፈጽም ነው እንጂ ለሰውነቴ ምንም አላስብላትም። ሥራ ፳: ፳፬።
+ ወንጌልን ለማስተማር አላፍርምና። ሮሜ ፩: ፲፮።
+ በወንጌልም ትምህርት አንድነት ይኖረኝ ዘንድ ስለ ወንጌል ትምህርት ኹሉን አደርጋለሁ። ፩ቆሮ ፱: ፳፫።
ይኸው የቃለ ወንጌል ትምህርት በቃል ፍቺው እንደተነገረው ወሬም ይባላል።
+ "ቀድሞ ምእመናንን ያሳድድ የነበረው እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን የሃይማኖት ትምህርት ዛሬ ይሰብካል ሲባል ወሬዬን ይሰሙ ነበር" እንዲል። ገላ ፩: ፳፫።
+ እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም። ማር ፲፮: ፲፫።
+ የኢየሱስንም ወሬ ሰምታ በስተኋላው በሰዎች መካከል መጥታ ልብሱን ዳሰሰች። ማር ፭: ፳፯። ዜናውን ለማለት። ዜናውም ወንጌል ነው።
+ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ። መዝ ፺፭: ፪።
ማስተማርና መስበክ፣ ትምህርትና ስብከት የሚሉት ቃላት እንዲሁም ወሬ እርስ በእርስ ተተካኪ፣ ተወራራሽ፣ ተዛማጅ መኾናቸውን በዚህ እንረዳለን። ዘርዘር ሲል ትምህርትና ስብከት የዘርፍ ልዩነት አላቸው። ትምህርት ዕውቀት ሲኾን ስብከት ጥሪ ነው።
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መስበክ ለአፍታ የማይቋረጥ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀዳማዊ ተልእኮ ነው።
"ኹል ጊዜም በቤተ መቅደስና በቤት ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደኾነ ማስተማርንና መስበክን አልተዉም" እንዲል። ሥራ ፭: ፵፪። እንዲሁም "እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ስንፍና ነው" እንደተባለ። ፩ቆሮ ፩: ፳፫።
መተረክ እና መንገር
እነዚህ ኹለቱ ፍጹም አንድነት ያላቸው ናቸው። ይኽንንም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ክፍሎች ማየት ይጠቅመናል።
+ መቼም ቢኾን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው። ዮሐ ፩: ፲፰። በ፳፻ እትም ተረከው የሚለው ገለጠው ተብሏል። ግእዙ ነገረነ ይለዋል። አንድ ናቸው ማለት ነው።
+ እነርሱም በመንገድ የኾነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው። ሉቃ ፳፬: ፴፭። በ፳፻ እትም ተረኩላቸው የሚለው ነገሯቸው ተብሏል። ግእዙ ወነገርዎሙ ይለዋል።
+ በርናባስ ግን ወስዶ ወደ ሐዋርያት አገባውና ጌታን በመንገድ እንዴት እንዳየውና እንደ ተናገረው በደማስቆም በኢየሱስ ስም ደፍሮ እንዴት እንደ ነገረ ተረከላቸው። ሥራ ፱: ፳፯። እንዴት እንደ ነገረ ሲል እንዴት እንደ ሰበከ እንዴት እንደ አስተማረ ማለቱ ነው። ተረከላቸው ሲልም ዘረዘረላቸው ነገራቸው ማለቱ ነው።
ወንጌል ማስተማር ወንጌል መስበክ እንደሚባለው ኹሉ ወንጌል መንገርም ይባላል።
"ነገር ግን እንደምታውቁት በፊልጵስዩስ አስቀድመን መከራ ተቀብለን ተንገላትተንም፥ በብዙ ገድል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንናገር ዘንድ በአምላካችን ደፈርን" እንዳለ ሐዋርያ። ፩ተሰ ፪: ፪።
ዐዋጅ መንገር
ቅዱስ ዮሐንስ ዐዋጅ ነጋሪ ወይም ቃለ ዐዋዲ ሲባል ሰባኪ ማለት ነው። እርሱም፥ “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደ ተናገረ የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ እያለ በምድረ በዳ የሚሰብክ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” በሚለው ተገልጧል። ዮሐ ፩: ፳፫።
ሰባኬ ወንጌል ቅዱስ ጳውሎስም ዐዋጅ ነጋሪነቱን ይጋራዋል። "እንግዲህ ከሰማችሁት ከሰማይ በታች በመላው ዓለም ከተሰበከው እኔ ጳውሎስም ዐዋጅ ነጋሪና መልእክተኛ ኾኜ ከተሾምኹለት፥ ከወንጌል ትምህርት ተስፋ የመሠረታችሁ አቋም ሳይናወጥ ጨክናችሁ በሃይማኖት ብትጸኑ. . ." በማለት። ቆላ ፩: ፳፫። ደግሞም በሌላ ስፍራ "በኀይሉ አጋዥነት እንደ ሰጠኝ እንደ ጸጋው ስጦታ መጠን እኔ መልእክተኛና ዐዋጅ ነጋሪ የኾንኹለት" በማለት ተናግሮታል። ኤፌ ፫: ፯።
ንዑስ ማጠቃለያ
መንገር፣ መተረክ እና መስበክ ልዩነት የላቸውም። ነገረ ክርስቶስ በኹሉም ቃላት እንዴት በተለዋዋጭ እንደተነገረ ከማስረጃ ጋር ዐይተናል። መስበክ የሚለውን ቃል የተለየ አድርጎ ለማሳየት መታሰቡ እንግዳ ነገር ነው። ያውም ደግሞ ለክርስቶስ ብቻ የተገባ አድርጎ ማሳየቱ ልክ አይደለም። ለክርስቶስ ብቻ የተገቡ የምንላቸው ከምሥጢረ ሥጋዌ ጋር የተያያዙ መገለጫዎች አሉ። እነዚህም ተዋሕዶ፣ ሥግው ቃል፣ ቅቡዕ፣ መሲሕ፣ ኢየሱስ፣ አማኑኤል፣ ክርስቶስ የመሳሰሉት ናቸው። ከእነዚህም አንዳንዶቹ እንደ ዐውዳቸው ወይም በተለየ ቅጽል እና ገላጭ ለሌላ ሊነገሩ ይችላሉ። ለምሳሌ ሐሳዊ መሲሕ እንደማለት። ስለዚህ የማይገባ ልዩነት በመፍጠር የሰውን ልብ መክፈል በተለይ ታስቦበት ከኾነ አደገኛ ነው እንላለን።
የንስሐ ስብከት
ምንም እንኳ ንስሐ ዓላማው ሰዎችን ወደ ጌታችን የማቅረብ ቢኾንም የተነሣው ሰዋስዋዊ የቃላት አጠቃቀም ጉዳይ ስለኾነ ስብከት ማለት በቀጥታ ስለ ጌታችን መናገር ብቻ አለመኾኑን ለማሳየት ነው።
ስለዚህ ጌታችንን ከመስበክ ባሻገር የንስሐ ስብከትም አለ የሚለውን እንመለከታለን። ነቢዩ ዮናስን ለሰብአ ነነዌ ያቀረበውን የንስሐ ጥሪን ማየት ይቻላል። “ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሒድ፥ ክፉታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ” እንዲል። ዮና ፩: ፪። ይኽንንም ጌታችን የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚች ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፋረዷታል፤ ያሳፍሯታልም፤ ዮናስ በሰበከላቸው ጊዜ ንስሓ ገብተዋልና፤ እነሆ፥ ከዮናስ የሚበልጥ በዚህ አለ" በማለት አስተምሮበታል። ሉቃ ፲፩: ፴፪። ጌታችን ቃሉ ለእኔ ብቻ ነው አላለም።
ከዚህም በላይ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ጥሪ ስብከት እየተባለ መጠራቱን መመልከት ይቻላል።
+ በዚያም ወራት መጥምቁ ዮሐንስ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” ብሎ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ። ማቴ ፫: ፩።
ስብከት በሌላ ዐውድ
ብዙ መዘርዘር ሳያስፈልግ ቃሉን ልጥቀስ።
"እግዚአብሔር ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ በጥርሳቸው ሲነክሱ በሰላም ይሰብካሉ፥ በአፋቸው ግን አንዳች በማይሰጥ ሰው ላይ ሰልፍን ያስቡበታል።" ሚክ ፫: ፭።
ቃላት እንደ ዐውዳቸው ይተረጎማሉ እና ስብከት የሚለው ቃል ለጌታ ብቻ ነው ብሎ ደምድሞ መናገር አይገባም። ወደሌሎች "የብቻ" ገደሎች የሚያንደረድር ቁልቁለት እንዳይኾን ከመጠንቀቅ ጋር።
ገድል ወይም ድርሳን ይነገራል ይተረካል እንጅ አይሰበክም ማለት ለምን አስፈለገ?
ዋናው ችግር ያለው እዚህ ላይ ነው። ገድልና ድርሳንን ለማጣጣል የተደረገ ስልታዊ አቀራረብ መኾኑ ነው። በዚህ አነጋገር የተነጻጸሩትን አካላት እንመልከት። ገድል እና ድርሳን በአንድ ወገን ኢየሱስ ክርስቶስ በሌላ ወገን። ሲጀመር ንጽጽሩ ሕፁፅ ነው። ግእዛን የሌላቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ከፈጣሬ ዓለማት ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ማነጻጸር ባልተገባ።
ኢየሱስ ክርስቶስን ማክበር ቢቻለን ከምናውቀው ከምናደርገውም በላይ ቢደረግ የደስታችን ወሠን ከአድማስ ይሻገራል። ከአጓጉል ንጽጽሩ (wrong comparison fallacy or faulty comparison) ጀርባ ክብረ ነክነት አድብቷል። እንደዚህ ያለውን የአፕልና ብርቱካን ንጽጽር ይሉታል። ይኽስ ከዚያም ያልፋል። ባይኾን ወንጌልና ገድል፣ ድርሳን እና መጽሐፍ ቅዱስ ብለው ቢያነጻጽሩ በተሻለ። ግን እርሱም ቢኾን ፍርደ ገምድል ድምዳሜን አይሻም።
ለኢየሱስ ክርስቶስ የምንሰጠው ክብር ከምንም ከማንም በላይ እንደኾነ ለክርክር አይቀርብም። የእርሱን ክብር እና ሥልጣን የሚገዳደር ኹሉ ርጉም ነው። እኛ በዚህ ሃይማኖታዊ ሥነ ልቡና የተዋቀርን መኾናችን ይታወቃል። ስለዚህ ክርስቶስን በአንድ ወገን ሌላ አካልን በሌላ ወገን አድርጎ የሚያቀርብ ንጽጽር ቢኖር ፈጥነን የምንቆምበት ረድፍ የቱ እንደኾነ ይታወቃል። ከፍቅራችን የተነሣ ማን ከእርሱ ሊወዳደር ይችላል? በማለት ብዙ ማሰብ ሳያስፈልገን ብያኔ ለመስጠት አንቸገርም። በዚህ ጊዜ ለሌላው ተነጻጻሪ ወገን እምብዛም መጨነቅን አንታገስም። ቶሎ ሊነካብን አይገባም ወደሚለው የሚሰለፍ ሥነ ልቡና አለን።
በዚህ ስስ ብልታችን ሲመጡብን ሳናውቀው ወይም ከችኮላ የተነሣ የምንቃወመውን ስንደግፍ ልንገኝ እንችላለን። በተለይ ተነጻጻሪ ኾኖ የቀረበው አካል እንደ ገድል እና ድርሳን ዓይነት ሲኾን የሚያሳድረው ተጽእኖ በቀላል አይታይም። በተለይም በተደጋገመ ቁጥር በረዥም ጊዜ ወደ ማናናቅ ወደ ማጣጣል ወደ ማቅለል ይወስዳል። ስለዚህ ንጽጽሩ ደግነት ይጎድለዋል። በስቅለቱ ቪድዮም "ድርሰትና ተረቱን ተውት" ያሉበት ዐውድ ከዚህ ጥመት የተቀዳ ነው።
ከገድልና ድርሳናት ጀርባ ቅዱሳን አሉ። ከቅዱሳት መጻሕፍቱ በላይ ተናጋሪው መምታት የፈለጉት ቅዱሳኑን ነው። ልክ እመቤታችን ቤዛ አትባልም እንዳሉት ኹሉ ቅዱስ ገብርኤልና ቅዱስ ሚካኤልም ቤዛ አይባሉም ያሉበትን ዐውድ ወደዚህ ስቦ ማየት ይገባል።
አቀራረባቸው ክርስቶስ ብቻ (Sola Christus) መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ (Sola Scriptura) ለሚሉ አካላት የተመቸ ስለኾነ የኦርቶዶክስነትን አጥር በአፍራሽነት ይነቀንቃል። ችላ የማይባለውም ለዚህ ነው። ስብከት በእግዚአብሔር ቃል ሲኾን ምንጩም አንድ ነው። መጻሕፍተ ቅዱሳት ወይም መጽሐፍ ቅዱስ።
መጽሐፍ ቅዱስ የገድልም የድርሳንም እስትግቡእ ነው
መጽሐፍ ቅዱስ በአጭሩ ብዙ ዓይነት ይዘት ያላቸው የልዩ ልዩ መጻሕፍት እስትግቡእ (ስብስብ) ነው። የትምህርት፣ የትእዛዝ፣ የታሪክ፣ የትንቢት፣ የመዝሙር፣ የድርሳን፣ የገድል፣ የተአምር . . . ወዘተ ይዘት ያላቸው ናቸው።
ወደ ርእሳችን ለማትኮር የሐዋርያት ሥራ ማለት ምድቡ ከገድል ነው። የሐዋርያትን ተጋድሎ እስከ መታሰር፣ መገረፍ፣ መሰደድ፣ እና ሰማዕትነት ይዘረዝራል። ገድል ነው ብሎ ቆርጦ የሚጥለው አለን? ኦሪት ዘጸዐት ገድለ ሙሴ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ቢዘረዘር በብዙ ቦታዎች የተሰባጠሩ ብዙ ገድለ ቅዱሳን አሉበት። ገድለ አብርሃም፣ ገድለ ዳዊት፣ ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ፣ ገድለ ጳውሎስ እያልን ልናወጣ እንችላለን። የገድል ይዘቱ ኹሉ ስለ እግዚአብሔር እግዚአብሔር በመረጣቸው ቅዱሳን የተደረገ ሃይማኖታዊ ተጋድሎ ነው።
ድርሳን ደግሞ ቅዱሳን መላእክት ከእግዚአብሔር እየተላኩ የሰው ልጆችን የጠበቁበትን የተራዱበትን የተንከባከቡበትን ሕይወት የሚያሳይ መጽሐፍ ነው። ለዚህም ራዕየ ዮሐንስን በመጽሐፍ ደረጃ መጥቀስ ይቻላል። ለአብነት በመጽሐፈ ሄኖክ፣ በነቢዩ ዳንኤል፣ በነቢዩ ሕዝቅኤል፣ በመጽሐፈ ጦቢት፣ በነቢዩ ዘካርያስ፣ በወንጌል፣ በሐዋርያት ሥራ እና በኦሪት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት ተጽፏል። (ድርሳን ተብለው የሚጠሩ መጻሕፍተ ሊቃውንትም አሉ። እንደ ድርሳን ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ድርሳነ ቄርሎስ።)
ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የገድልና የድርሳን እስትግቡእ ነው ማለት ነው። ገድልን መቃወም መጽሐፍ ቅዱስን መቃወም ነው። ድርሳንን መቃወም መጽሐፍ ቅዱስን መቃወም ነው።
ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ማለትስ ጓዙ ምንድን ነው?
በአጭሩ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ማለት እግዚአብሔርነቱን፣ ሥጋዌውን፣ ትምህርቱን፣ አረአያነቱን፣ ተአምራቱን፣ መድኃኒትነቱን (ሕማሙን ሞቱንና ትንሣኤውን)፣ ቸርነቱን እና ትእዛዙን መግለጥ፣ ማወጅ፣ በሕይወት መኖር ማለት ነው።
እንግዲህ በእውነት ክርስቶስን የሚሰብክ ካለ ጌታችንን ስለ ባሕርይ አባቱ አብ ስለ ባሕርይ ሕይወቱ መንፈስ ቅዱስ ሲሰብክ ያገኘዋል። ስለራሱም ሲያስተምር ያገኘዋል።
ደግሞም እንጅ ስለ ቅዱሳኑ ሲሰብክ ያገኘዋል። እርሱ ስስት የሌለበት ቸር አምላክ ሲኾን አድሮባቸው የሚኖሩ ቅዱሳን በሚፈጽሙት ገድል ደስ እያለው ሲሰብካቸው እንሰማዋለን።
ድንግል ማርምን እነኋት እናትህ ያለው ማን ነው? በቀራንዮ ዐውደ ምሕረት ላይ የስብከቱ መጨረሻ ያደረጋትን የእመቤታችንን ነገር አዳመጥኸውን? ዮሐ ፲፱: ፳፯። ወይስ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከእርሱ የሚበልጥ አልተነሣም ሲል ሰማኸውን? ማቴ ፲፩: ፲፩። ወዲህስ ቅዱስ ጴጥሮስን "አንተ ብፁዕ" ነህ ባለበት የፊልጶስ ቂሣርያ ዐደባባይ ነበርህን? ማቴ ፲፮: ፲፯። በደማስቆ ጎዳና ገስግስ እስቲ። አሳዳጁን መልሶ ምርጥ ዕቃ ሲለው ትሰማው እንደኾን። ሥራ ፱: ፲፭።
ስንቱን እዘረዝረዋለሁ። እዚያው ገብቶ መዋኘት ነው እንጅ። እናማ አንተ ክርስቶስን ለመስበክ ያብቃህ እንጅ ክርስቶስ ቅዱሳንን ሲሰብክ ታገኘዋለህ። እንዲህ እያለ "እውነት እላችኋለሁ፤ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርሷ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል።” ማቴ ፳፮: ፲፫። ዐየኸው የቅድስቲቱ ባለሽቱዋ የማርያምን ነገር ንጉሡ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በሚሰበክበት ኹሉ እንዲሰበክ ሲያዝዝ። ገድሏን ስበኩት ብሏል የጌቶች ጌታ!
ትእዛዙን አክብረን እርሱን ስንሰብክ ቅዱሳንን እንሰብካለን። እኔን ብቻ አትስበክ እያለህ አንተን ብቻ ካልክ እያፈነገጥህ እንጅ እየሰበክኸው አይደለም።
ማጠቃለያ
ይኽንን የምንለው አንዳንዶች እንደሚያጮኹት እርሳቸውም ልብ የሰጡት እንደኾነ እንደታዘብነው አቡነ ገብርኤልን ለመግፋት አይደለም። የተዋሕዶ አጥር ሲነቀነቅ ቆሞ ማየት ስለማይገባ እንጅ። የተዛቡ ነገሮችን ለመናገር ያላቸው ድፍረት እንዳናጣቸው ያሳቅቃቃል። ሮሜ ፰: ፴፬ንም ጀምረው ተውት እንጅ አነካካቸው ያሳስባል። ለጊዜው በቀጨኔ መድኃኔ ዓለም ያስተማሩትን ሰምቼ ለማጣፋት ምክንያት አግኝቻለሁ። እዚያ ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ አይደለም ብለዋልና። በጓዳ ሌላ በዐደባባይ ሌላ መኾን የሐራጥቃ ባሕርዪ መኾኑን ባላጣውም ፖለቲካዊ ነገር እየተደረተበት ጨርሰው እንዳይርቁ በርግገው እንዳይሔዱ ለመጠንቀቅ ወደድሁ። ሽል ከኾነ ይገፋል ቂጣም ከኾነ ይጠፋል ይሉ የለ!
በጸሎት ከማሰብ ጋር ተዋሕዷዊ አቋማችንን እናጠንክር።
ይቆየን።
በዓባይነህ ካሴ
25/04/2025
አባ ገብርኤል "የእናንተ ዐውድ አይመለከተኝም
የእኔን ዐውድ ተረዱኝ" ዓይነት አስተያየት ሰጥተው ተመለከትኩ። አንድ ነገር ግን እንዳደንቅ ፍቀዱልኝ። አንደበተ ርቱዕነታቸው አስደምሞኛል። በዚህ አንደበተ ርቱዕነት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትን ቢያስተላልፉበት ደግሞ የበለጠ ያማረ ይሆን ነበር።
ብፁዕ ሆይ ሰው ሁሉ ለምን ብሎ የተቃወመዎት በእርስዎ ዐውድ መሳት ሆኖ ሳለ ዐውዴን ተረዱኝ ማለትዎ ለምን ይሆን?
ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ቤዛ ነሽ አሉ ለዓለም
ብለን ስንዘምር የእርሷ ቤዛነት የክርስቶስን ቤዛነት የሚተካ ነው ወይም የሚተካከል ነው ብለን እንዳልሆነ ሳይረዱ ወደመተቸት ሄዱ። እርሷን ቤዛ ስንላት እግዚአብሔር በሰጣት ጸጋ በጸጋ ቤዛ ሔዋን፣ ቤዛ ኃጥኣን በመሆኗ ነው። "ለኃጥኣን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ" እንዲል። ከእግዚአብሔር በተሰጣት የምልጃ ጸጋ ሰውን የምታስምር ስለሆነ ቤዛዊተ ኵሉ ዓለም እንላታለን። ይህንን ሳይረዱ በተሐድሶዎች ቅኝት አዙረው ቤተክርስቲያን የማትለውን እንደምትል አስመስለው ሲተቹ ስናይ እንዴት የተባለበትን ዐውድ ሳይረዱ ይናገራሉ ብለን ዐውዱን ለማሳየት ጻፍን።
ሌላው ግን አንዳንዱ ወደ ስድብ አምርቶ አስተውያለሁ። ስድብ ተገቢ አይደለም። የሰው ልጅ ከተሳሳተ ስሕተቱን በማስረጃ ማስረዳት በቂ ነው። ከተሳደብን ግን እኛም የጥፋቱ ተባባሪ ስለምንሆን በተቻለ መጠን ላለመሳደብ መጣር ይገባል። እውነት ያለ ስድብ በእውነትነቷ ብቻ ስትነገር የሁሉንም ኅሊና ትገዛለች። ስድብ ከተቀላቀለባት ግን ትደበዝዛለች። ስለዚህ በተቻለን አቅም እውነትን ያለምንም ስድብ መግለጽ መልመድ አለብን።
ብፁዕ ሆይ በትርጓሜም በነገረ ማርያም ትምህርትም ስለፈያታዊ ዘየማን የተነገረውን እንደማይቀበሉ ጽፈዋል። በትርጓሜም በነገረ ማርያምም የተገለጸውን ጉዳይ ለምን እንደነቀፉት በቂ ማብራሪያ መስጠት ይገባዎታል። በቤዛ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጉዳዮች ከኦርቶዶክሳዊው አስተምህሮ ያፈነገጠ ንግግር አድርገዋል። በዚህ በግልጽ ይቅርታ ቢጠይቁ መልካም ነው።
አንዳንዶች ደግሞ አቻ ፍለጋ ሲሯሯጡ አይቻለሁ። የተሳሳተ እኩልነትን (False equivalence) ፈጥረው እገሌ በዚህ ጉዳይ እንዲህ ብሎ ነበር። እርሱ ዝም የተባለ ብሔሩ እንዲህ ስለሆነ ነው የሚሉ አሉ። ስሕተትን በብሔር መደበቅ አይገባም። እኔ እንዲህ ስለሆንኩ ነው የሚለውም ተገቢ አይደለም። ጉዳዩን በኦርቶዶክሳዊ መነጽር ማየት ይገባል።
© በትረ ማርያም አበባው