22/11/2018
የጥሩ ወላጅ ባሕርያት
--------------
--ልጅን መውደድ፦ በጭፍን ሳይሆን ሃላፊነት በሚሰማው መልክ መውደድ፤ ሲያጠፉ ማረም እና ስህተታቸውን እንዲረዱ መርዳት።
--የልጆን ችግር እንደራስ መመልከት፡-ጥሩ ወላጅ ከልጃቸው አንጻር በማሰብ ጫና ከማሳደር ወይም ሲወድቁ ከማሾፍ ይልቅ በተገቢው መልክ ማበረታታት።
--ወጥነት:- የወላጆች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ፣ ህግ እና ደንቦች፣ እና ልጆቻቸውን የሚቀጡት ቅጣት ወጥነት ሊኖራቸው ይገባል። ወጥነት ያላቸው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ለልጆች የደህንነት ስሜት እና ጥሩ ልማዶችን እንዲያዳብሩ ይረዳል።
--መነጋገር ወይም መግባባት:- ጥሩ ወላጆች ከልጃቸው ጋር በተሳካ ሁኔታ በመነጋገር ልጆቹ የአስተሳሰብን ሂደት እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል። በተጨማሪም ከወላጆቻቸው በመማር ልጆቹ የመነጋገር ወይም የመግባባት ችሎታቸውን ያሻሽላሉ።
--በንቃት ማዳመጥ፦ ወላጆች ትኩረት በመስጠት፣ በንቃት በማዳመጥ፣ ለልጆቹ ሃሳብ እውቅና በመስጠት እና ተሞክሯቸውን እንዲካፈሉ መርዳት ወይም ማበረታታት ያስፈልጋል።
--መረዳት፦ ወላጆቹ ልጃቸው የሚናገሩትን ሲሰሙ፣ ጭንቀታቸውን፣ ፍራቻዎቻቸውን እና ሀሳባቸውን ሲረዱ፤ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ መተማመን እና እምነት መጣል ይችላል።
--ትዕግስት፦ ከባድ ቢሆንም ወላጆች ሁል ጊዜ ከልጆቻቸው ባህሪ በስተጀርባ ያለውን ምክንያት በትዕግስት መረዳት ያስፈልጋል።
ምንጭ:-
ልጅን መውደድ፦ በጭፍን ሳይሆን ሃላፊነት በሚሰማው መልክ መውደድ፤ ሲያጠፉ ማረም እና ስህተታቸውን እንዲረዱ መርዳት። የልጆን ችግር እንደራስ መመልከት፡-ጥሩ ወላጅ ከልጃቸው አንጻር .....