18/09/2026
ቀለም ኢትዮጵያ ዘላቂ መተዳደሪያን ለማጠናከር የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ።
ቀለም ኢትዮጵያ ከBundesministerium für wirtschaftliche Zusammenarbeit und Entwicklung (BMZ) እና TERRA Projekte International e.V. ጋር በመተባበር፣ በቃሉ ወረዳ የሚካሄድና በግብርና እና በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ እንዲሁም የወጣቶችን ሥራ አጥነት ለመቀነስ የሚያስችል አዲስ የ RIPE ፕሮጀክት በይፋ አስጀምሯል።
በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደው የፕሮጀክት ማብሰሪያ ፕሮግራም ላይ እንደተገለፀው ከ2026 እስከ 2030 የሚተገበረው የ RIPE ፕሮጀክት በቃሉ ወረዳ የሚገኙ የገጠር ወጣቶችን እና ተጋላጭ አርሶ አደሮችን ጨምሮ በቀጥታ 12,396 የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚደግፍ ሲሆን፣ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን እና የአካባቢው ባለስልጣናትን አቅምም ያጠናክራል።
ይህ ፕሮጀክት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የወጣቶችን ሥራ አጥነት ለመቀነስ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና አሰራርን ለማስፋፋት ያለመ ሲሆን፤ በእንስሳት እርባታ፣ በዶሮ እርባታ እና በዘላቂ የግብርና ስራዎች ላይ ያተኮሩ ድጋፎችን በማቅረብ ከ250,000 በላይ የማህበረሰብ አባላትን በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋል።
ይህ ወሳኝ ምዕራፍ ደግሞ በቅርቡ በቀለም ኢትዮጵያ የተጀመረውንና በBMZ እንዲሁም በTERRA Projekte International የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄደውን ሌላ ትልቅ ፕሮጀክት ማለትም የዌልነስ (WELLNESS) ፕሮጀክት ያስታውሰናል፡፡
ይህ ፕሮጀክት በአማራ ክልል ከተሞች ውስጥ ለሚገኙ ተጋላጭ ሴቶች ዘላቂ የገቢ ማስገኛ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ፕሮጀክት ሲሆን፤ ከጁላይ 2026 እስከ ጁን 2029 የሚተገበር ነው፡፡የ WELLNESS ፕሮጀክት፤ በደሴ፣ በኮምቦልቻ፣ በባቲ እና በከሚሴ የሚገኙ 409 ተጋላጭ የከተማ ሴቶች ዘላቂ ገቢ እንዲፈጥሩ ለማስቻል ያለመ ሲሆን፣ በንግድ ክህሎት፣ በተግባራዊ ስልጠና እና ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የመነሻ ካፒታል ድጋፍ በማድረግ ሴቶችን ለማገዝ ታስቦ የሚከናወን ነው።
እነዚህ ፕሮጀክቶች በአማራ ክልል ዘላቂ የኑሮ አማራጮችን ለመፍጠር፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጠናከር እና ጠንካራ ማህበረሰብን ለመገንባት ቀለም ኢትዮጵያ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቁ ናቸው።
-----------------------------------------------------------
Kelem Ethiopia Launched a New Project to Strengthen Livelihoods and Resilience
Kelem Ethiopia, in partnership with Bundesministerium für wirtschaftliche Zusammenarbeit und Entwicklung (BMZ) and TERRA Projekte International e.V., has officially launched the RIPE Project (Increasing Productivity in Agriculture, Livestock Farming and Reducing Youth Unemployment) in Kombolcha City.
Running from 2026–2030, the project will support 12,396 direct beneficiaries, including rural youth and vulnerable farmers in Kalu Woreda, while strengthening the capacity of agricultural extension workers and local officials.
The initiative aims to boost agricultural productivity, reduce youth unemployment, and promote climate-resilient farming in which it ultimately supporting over 250,000 community members through targeted livestock, poultry, and sustainable farming interventions.
This milestone builds directly on the momentum of another major project recently launched by Kelem Ethiopia, under BMZ, and TERRA Projekte International Funding support: the WELLNESS Project (Creating Sustainable Income Opportunities for Vulnerable Women in Urban Areas of the Amhara Region).
The WELLNESS Project , running from July 2026 to June 2029, aims in supporting 409 vulnerable urban women in Dessie, Kombolcha, Bati, and Kemisse with business skills, practical training, and start-up support to build sustainable incomes.
While the RIPE Project focuses on rural youth and agricultural development in Kallu Woreda, the WELLNESS Project targets economic resilience for vulnerable urban women across Dessie, Kombolcha, Bati, and Kemisse.
Together, these initiatives reflect Kelem Ethiopia’s commitment to creating sustainable livelihood opportunities, strengthening local capacity, and building resilient communities across the Amhara Region.