17/03/2022
አሜሪካንና ቡችሎቿን የNATO አገራት ማን ይቅጣቸው? ለነሱስ ማእቀብ ይኖር ይሆን? የስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ያደረገው አስደንጋጭ ጥናት መሰረት ፤ ግማሹ የአሜሪካ ህዝብ የዘር ማጥፋትንም ሆነ የጦር ወንጀልን በአገሪቱ ወታደሮች እስከተፈፀመ ድረስ ፈቃደኛ ናቸው።
* በ1999 አመት ጅማሬ ምክኒያት የሚፈበርከው NATO ታላቋን አገር ዩጎዝላቪያን ለ78 ቀናት 28,000 ሚሳኤልና ቦንብ አዘነበባት። ተቋማት ፈረሱ ታላቅ የነበረችው ዩጎዝላቪያም በብሄር ተከፋፍላ ወደ 9 ብጥስጣሽ አገራት ተለወጠች። በወቅቱ ዢኑዋ እንደዘገበው 2500 ንፁሃን ሲገደሉ 79ኙ ህፃናት ነበሩ። ኔቶ ግን አንድም ሰው አልሞተበትም ነበር።
* ብዙ የተወራለትና አሜሪካና ኔቶ በሽንፈት ለቀው የወጡበት የአፍጋኒስታን ወረራ እስከ 71,000 የንፁሃንን ሂወት እንደቀጠፈ ተዘግቧል።
* በ Abu ghraib የኢራቁ ማሰቃያ ማጎሪያ ምን ይደረግ ነበር? በቃላት ሊገለፅ በማይችል መልኩ የአሜሪካ ወታደሮች እስረኞችን እስከሞት ያሰቃዩ ነበር። በሙስሊሙ ማህበረሰብ ፀያፍ የሆኑ ድርጊቶችን በመፈፀም ስነልቦናቸውላይ ይጫወቱ ነበር። (ከታች ፎቶዎችን ይመልከቱ)
* በ2019 በዩ.ኤስ አየር ሃይል Abu Kamal ሶሪያ ጥቃት ደርሶ ነበር። በአከባቢው የሽብርተኛ እንቅስቃሴ እንዳለ ያመነው ኳታር የሚገኘው የአሜሪካ ጦር ኮማንድ ሴንተር በቦታው ንፁሃን ሰዎች እንደነበሩ ቢያውቅም ጥቃቱን አዘዘ። 2 ግዙፍ ቦንቦች ከአየር ተጣሉ ከ80 ሰዎች በላይ ሲሞቱ 16ቱ ብቻ ታጣቂዎች ነበሩ የቀሩት ህፃናት እናሴቶች ነበሩ።
- [ ] ይህን ለምሳሌ ይሆን ዘንድ አነሳሁ እንጂ አሜሪካ ከሁለተኛው አለምጦርነት በኋላ ከ80 በላይ አገራት በጦር መምዝ አልያም በመበጥበጥ ተሳትፋለች። የሚገርመው እነዚህ በሰው ፍጡር ላይ የሚደረጉ ወንጀሎችን የሚፈፅሙት አብዛኛው Secret Americans Death Squad አባላት ሲሆኑ በወንጀልም አይጠየቁም ነበር።
- [ ] በዩክሬን እየተደረገ ያለውንጦርነት በቀጥታ በመቀስቀስ NATO ተጠያቂ ነው። የUSSR መፍረስን እንዲሁም የምዕራብ እና ምስራቅ ጀርመንን መቀላቀል ተከትሎ ኔቶ ወደ ምስራቅ ወደ ሩሲያ ድንበር እንደማይስፋፋ በእንግሊዝ ፣ አሜሪካ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመንና ሩሲያ የተደረገውን ስምምነት NATO 14 ጊዜ የጣሰ ሲሆን። በቅርብ በማንአለብኝነት ዩክሬንን ለመቀላቀል ከ2008ጀምሮ እንቅስቃሴ አደረገ። ይሄም የኔቶ ኒውክለር ሚሳኤሎች ሩሲያ ድንበር ላይ ለማጥመድ የተደረገ ጥረት በመሆኑ ሩሲያ ራስን መከላከል ነው በሚል ወረራውን አድርጋለች። አይዞሽ ከጎንሽ ነን ሲሉ የነበሩ የኔቶ አባላትም ዩክሬንን ካዷት። ተንታኞች እንደሚሉት ቀድሞውንም በጅ አዙር ጦርነት ሩሲያን ለመጉዳትና ከአለም ለማግለል የተጠቀሙበት ነው። ዩክሬንም ብትፈርስ ግድ አይሰጣቸውም ይላሉ።
- [ ] ታዲያ የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት አፍሪካን ይጎዳ ይሆን? ስንዴ፣ ማዳበሪያ፣ ዘይት . . . በሌላ ፅሁፍእንገናኝ! ሰላም!
06/03/2022
።። ።።።።።። ። የነጭ የበላይነት የሚታወጅበት ጦርነት
"White Races Of The World In a Final Crusade Against Semitics!” Andriy Biletsky የዩክሬን አዞቭ special operations አሬንጅመንት መሪ።
ምናልባት ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ ተበሳጭተው ይሆን? እውነታው ግን እንዲህ ነው፤ በቅድሚያ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ያለምንም ሀፍረት ከዘገቡት ጥቂቶቹ
*BBC ~ "አውሮፓዊ የሆነ ሰማያዊ አይንና ወርቃማ ፀጉር ያለው (ልእለሰቡ የአውሮጳ ነጭ) ሲገደል ማየት ልብ ይሰብራል" ይላል ቢቢሲ የጋበዘው እንግዳ።
*NBC~ "እነዚ ስደተኞች ከሶርያ የመጡ አደሉም። ክርስቲያኖች ፣ እንደኛው ነጭ፣ እኛኑ የመሰሉ ናቸው" ሪፖርተሯ
CBS ፣ AL JAZEERA ሳይቀሩ ለዩክሬን ዋና ነጮች ሲያለቅሱ ከርመዋል። ስለስደተኞች ሰብአዊነት ሳይሆን የቆዳ ቀለማቸውን እያነሱ ዘግበዋል።
የዩክሬን ጦር በግልፅ ናዚዝም እና የነጭ የበላይነት መመሪያ ያደረገ እስኪመስል ድረስ white supremacy ይፎከርበታል። አንድሬ ቢሌትስኪ ግልፁን የተናገረ ሲሆን በስሩ 25,000 ጦር አባላትን ይመራል። ዋና አላማውም የሴም ህዝባችን ማጥፋት ነው ይበል እንጂ በዚ ጦርነት በዩክሬን የነበሩ ጥቁሮች፣ ህንዶች ባጠቃላይ ወደ ፖላንድና አዋሳኝ አገሮች ድንበር እንዳይሻገሩ እና በዩክሬን ወታደሮች ሲደበደቡ እና ቶርች ሲደረጉ እያየን ነው።
NATO አንቺ ቁጭ በይ እና እኛ ዙሪያሽን እንክበብ የማለት ያህል መስፋፋት ሩሲያን አደጋ ላይ የሚጥል ሀቅ መሆኑ አይካድም። አለም እንዲህ ለምእራባውያን ያጨበጨበውና ለዩክሬን ያሽቃበጠው፤ Lybia በኔቶ ስትወድም፣ ሶርያ ወደ ድንጋይ ዘመን ስትመለስ፣ ኢራቅ ስትጠፋ ፣ አፍጋኒስታን ስትወድም፤ ሰሜን ኮሪያ፣ ኩባ፣ ቬንዝዌላ፣ ኢራን፣ ኤርትራ በምእራቡ የኢኮኖሚና የመገለል ውርጅብኝ ሲደርስባቸው አለም አልነበረም እንዴ?
በዚ ጦርነት ሌላው አሳፋሪ ነገር እንደ ኬኒያ ያሉ አገሮች በሎንዶን ያሉ የነጭ ጌቶቻቸውን ትእዛዝ ለማክበር ይመስላል ከምእራባዉያን ጎን ተሰልፈዋል።
"ይህ እርምጃ ከዩክሬን ናዚዝምን ለማስወገድና የሩሲያን ደህንነት ለማስከበር ነው" ፑቲን
ከአድዋ ጀምሮ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጎናችን የቆመች አገር ሩሲያ!
ፑቲኒዝም ይለምልም! ምንጭ WION እና CRUX
30/06/2020
https://www.youtube.com/watch?v=bMncyN_C-pQ
A New Continent Is Discovered on Earth In the Pacific Ocean
How to Stop Water Polution. In case you're wondering what water polution has to do with a new continent discoevered in the Pacific Ocean, here's the answer t...
29/06/2020
ትዝብት
የህዝብ ትራንስፖርት በተለየም የአምበሳ, የፐብሊክ ትራንስፖርት፣ የተማሪዎች ባስ እና የሸገር ባሶች, በሙሉ የወንበር አቅማቸው እየጫኑ ይገኛሉ። መንግስት በአንጻሩ ከ4 ሰው በላይ መሰብሰብ እንዳይቻል አውጇል፣ ታክሲዎች በግማሽ እንዲጭኑ አስገድዷል፣ ታዲያ የህዝብ ትራስንስፖርት ላይ ለምን በግማሽ መጫን አልተተጋበረም፣ ጎን ለጎን ቁጭ በሎ መሄድ አሁን ካለው ችግር ጋር እንዴት ይጣጣማል። የቤት መኪኖች በወንበር ልክ ከመጫን እና የህዝብ ትራንስፖርት በወንበር ለክ መጫን የትኛው የበለጠ በሽታውን ያስፈፋል። ቢታሰብበት መልካም ይመስለኛል
22/06/2020
ለኤርትራ መገንጠል ከኤርትራውያን የበለጠ ሲለፉ የነበሩት ፦
፨ ግብፃዊው የ UN ሴክሬታሪ ጄነራል ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ
፨ ሱዳን ፥ ግብፅ እራሷ እና
፨ በትህነግ የሚመራው ኢህአዴግ ነበሩ
ያኔ የትኛውምንም ኢትዮጵያዊ ትስማማለህ ወይስ ምን ይሻላል ብሎ ያማከረው አልነበረም ። ተማክረው የወሰኑትም ቢሆኑ በህዝብ ድምፅ ይሁንታን ያገኙ አልነበሩም ።
ጠቢባን እና ዘመኑ ያፈራቸው ታላቅ የፖለቲካ መሪዎች ተብለው ፎቷቸው በየጎዳናው ፥ በየቁልፍ መያዣው ፥ በየቤቱ እና በየግድግዳው የተለጠፈላቸው፤ ህይወታቸው ሲያልፍ የደጀ ሰላም ግድግዳዎች በምስላቸው ያሸበረቀላቸው ፥ ድንኳን በየቀበሌው ተጥሎ የተለቀሰላቸው እናም ሞተው እንኳ "ራእያቸው" ሲመራን የነበሩት እነዛ መሪዎቻችን ስለ አሰብ ሲጠየቁ ,,," ግመል ያጠጡበት" ነበር ያሉን።
እርግጥ ነው ዛሬ የኤርትራ የባህር በሮች እና በነዚ አገራት ፥ ተቋማትና ግለሰቦች በግፍ ተነጥቀን ለኤርትራ የተሰጠብን አሰብ ከግመል ማጠጫነት የተሻለ ጥቅም አይሰጥም። እኛ ግን ደማችንን ለጅቡቲ እያጠጣን /እየለገስን እንገኛለን። ይባስ ብሎ በአለም ካሉት የባህር ሃይል ጥንካሬ ካላቸው ምርጥ አስር አገራት አንዷ ከሆነችው ከግብፅ ጋር የጦርነት እሰጥ አገባ ውስጥ ነን። ስለ ጅቡቲ ካነሳን አይቀር የባህር በሯን ለቻይና ፥ ጃፓን ፥ አሜሪካ ፥ ፈረንሳይ እና ለመሳሰሉት ሃያላን አገራት የጦር መንደሮችን (military base ) እያከራየች ትገኛለች። ሱማሊያ ለኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ለሆነችው ቱርክ ፤ ሱማሊላንድም ወዳጅ ይሁኑ ጠላት በቅጡ ለማናውቃቸው ነገር ግን ሁሌም የግብፅ አንጀት ለሆኑት ኤምሬትስ እና ሳኡዲ አረቢያ አጎብዳጅ ሆናለች። ሱዳንም ኢትዮጵያ በታሪክ ካሏት ታሪካዊ ጠላቶች ሁሉ አቋሟ ማይታወቅ እና አቅፎ አሳልፎ እንደሚሰጥ አይነት ወዳጅ ነች።
በአለም ላይ ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይዛ እና ለዘመናት ከጠላት ጋር ስትታገል የኖረች የባህር በር የሌላት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። የኛን ገማሽ ህዝብ ይዞ እንኳ የባህር በር የሌለው ሌላ አገር የለም።
ስለዚህም ስለባህር በር የምንነጋገርበት ከዚህ የተሻለ ግዜ የለም ። ምንም ጥያቄው እንዳይነሳ በፖለቲካው መንደር ባይፈልግም ፤ ምንም መፍትሄ አልባ አድርገው ብዙዎች ቢተውትም ነገር ግን የማንሸሸው ugly truth ነው።
ይህን ፅሁፍ ስጀምር ዋናው ጉዳዬ አባይ ነበር። ግብፅ ያንን ሁሉ ሴራ ስትሰራብን ጎረቤቶቼ ብላ አላዘነችልንም። ወደብ አልባ እንድንሆን ጥራም ተሳክቶላታል። እኛ ግን ሃላፊነት የሚሰማን ህዝቦች ነን። ማንም ኢትዮጵያዊ ፤ ጨፍጫፊ መሪ እንኳን ዙፋን ላይ ቢቀመጥ አባይን ጨርሶ የማቆም ህልም እንኳ ኖሮት አያውቅም ወደፊትም አይኖርም ። ይሁንና አባይን ለማልማት ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ እና ፊርማ ማግኘት አይጠበቅብንም ። እንደውም ግደቡ ማለቁ ላይቀር ፖለቲከኞቻችን የከፋፈሉንን ግብፅ አንድነታችንን እንድናጠናክር ውለታ እየዋለችልን ነው።
, ቸር እንሰንብት!
20/06/2020
* የግብፅን ዲፕሎማሲ ተፅዕኖ እንዴት መወጣት እንችላለን ?
የአለም አቀፉ ፖለቲክስ 'ለሆዴ ባባ' አይነት ወይም 'ለከንፈር መምጠጥ' ምንም ቦታ የለውም። ለዚህም ነው ለኢትዮጵያ የወቅቱ የመሽኮርመም እና የምንኩስና ቅድስና ጉዞ ለማንም ግድ ማይሰጠው።
ፖለቲካ በአለምአቀፋዊው እውነታ ሳይሆን የፕሮፓጋንዳ እና የጩኸት ብዛት ነው። ፖለቲካ አስመሳይነት እና በድሎ እንኳን ቀድሞ መጮህ ነው።
በአገራችን ስመጥር ሰዎችን የመግፋት እና በገዢው ፓርቲ መሪዎች ብቻ የሚዘወር የዲፕሎማሲ አባዜ የት እንዳረሰን ሁላችንም ያየነው ነው። ከኔ በላይ የዲፕሎማሲ እውቀት እና እስራቴጂ ላሳር የሚለው የባፉት አምስት አስር አመታት ጉዞ በአለምአቀፋዊው ክብር አናት የነበረችውን አገራችንን አሁን ከጎኗ የሚቆም ወዳጅ እንኳ እንድታጣ አድርጓታል ። አሁንም ግን ግዜው አረፈደም ። በተለይም ከአባይ ወንዝ ግድብ ጋር በተያያዘ ልትከተል ይገባል የምለውን ስትራቴጂ ከአለም Geopolitics እና የሃይል አሰላለፍ አንፃር የግሌን ሃሳብ አቀርባለሁ ።
# 1 - ከአረቡ አለም እና ከመካከለኛው ምስራቅ አምርረው ግብፅን የሚጠሉ እና በጠላትነት የፈረጇት አገሮች አሉ? አዎ በአለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው AL Jazeera ባለቤት የሆነችው ካታር እና ቱርክ ዋንኞቹ ናቸው። ግብፅ ከነዚ አገራት ጋር የተካረረ ፀብ ውስጥ ትገኛለች። የሱኒውን አለም ለሁለት የከፈለው ይህ ፀብ ከእጅ አዙር ጦርነት እያለፈ ሲሆን በተለይም በሊቢያ እየተካረረ መቷል። ግብፅና አጋሮቿ የቤንጋዚውን የጦር መሪ ጄነራል ሀፍታርን በመደገፍ ቱርክ እና ካታር የትሪፖሊውን the so called 'UN backed Government ' በመደገፍ የጦዘ ጦርነት ውስጥ ናቸው። ይህ proxy war በሊቢያ ብቻ ሳይወሰን በቅርቡ በሱዳን የተካሄደውን የመንግስት ለውጥ እንዲሁም የአልጄሪያው አመፅ ውስጥ ሁሉ አለበት።
ቱርክ ቀጥታ የውትድርና እርዳታዋን ለትሪፖሊ መስጠት ከጀመረች በኋላ ግብፅ በሊቢያ የከፋ ሽንፈትን እየቀመሰች ትገኛለች።
ስለዚህ ኢትዮጵያ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ከነዚ አገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በማጥበቅ ግብፅን መፃረር።
# 2 - አለም አቀፍ ሚዲያዎችን በተቻለ አቅም መጠቀም ። ይህ አገርን ከማስተዋወቅ ይጀምራል ። ግብፅ በበርካታ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች እራሷን በብዙ ታስተዋውቃለች። በዚህም ብዙ ርቀት ቀድማናለች። ለምሳሌ ቱሪዝሙን ስናስተዋውቅ ስለአባይ ወንዝ መናገር። ይጠቅማል ።
#3 - ኢትዮጵያ በእጇ ያላት ትልቅ ሀይል AU ነው። የአፍሪካ ህብረት ምንም "ጥርስ አለባ" በመባል ቢታወቅም ለዲፕሎማሲያዊ ጉዳይ ግን ከፍተኛ ጥቅም አለው። እዚህ ህብረት ውስጥ ከግብፅ ይልቅ ኢትዮጵያ የተሻለ አቅም አላት ። ያንን መጠቀም ብልህነት ነው።
# 4 - የዲፕሎማሲ ስትራቴጂን ከፖለቲካው እና የጎጥ ኮታ ማሟያነት በተቻለ አቅም መነጠል። በአገር ውስጥ እና በውጭ ያለውን ኢትዮጵያዊ regardless of ther ethnicity and political view ለጋራ አላማ ማሰለፍ። በየቴሌቭዥኑ ተቃዋሚዎችን በጅምላ ከመፈረጅ መረጃ የተገኘበትን ባንዳ ነጥሎ እውነተኛውን ከጎን ማሰለፍ።