26/07/2023
ድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
"ትምህርት ለትውልድ"
ፊደል የቆጠርንባት፣ የልጅነት ትዝታችንና ፍቅራችን የተቀረፀባት፣ ጥሩና መጥፎን የለየንባት፣ የዜግነት ክብር ብለን የዘመርንባት፣ ከድንቁርና ዓለም ተለይተን እውቀትና ጥበብ የቀሰምንባት፣ ሙሉ ሰው ሆነን ማሰብ የቻልንባት በጥሩ ሥነ- ምግባር ያደግንባት ትምህርት ቤታችን፣ በተለያዩ የትምህርት ጥራት ችግሮች ውስጥ ያለች በመሆኗ ሙሉ እንድትሆንና የመማር ማስተማር ሂደቱም ምቹ እንዲሆን የትምህርት ቤት መሠረት ልማት ለመማር ማስተማር ስራው ዋናው ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ የትውልድ ጉዳይ የሚያሳስበው የቀድሞ ተማሪዎች፣ ባለሀብቶችና ማንኛውም በጎ አድራጎት ድርጂት ድላችን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ በመምጣት የጎደለንን ቁሳዊ ሀብት ታሟሉልን ዘንድ በት/ቤታችን የትምህርት ማህበረሰብና ተማሪዎች ስም እንጠይቃለን፡፡