Kotebe University of Education

Kotebe University of Education

Share

Kotebe University of Education (KUE) is Ethiopia’s only public university mandated to produce competent education professionals.

A premier first-generation institution, established in the 1950s.

24/04/2026
Photos from Kotebe University of Education's post 22/04/2026

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 'የቃልኪዳን ቤተሰብ' ፕሮጀክት ምሥረታ አካሄደ
*********** *********** ***********
(ኮትዩ፣ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም) - ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ ተማሪዎች የቃልኪዳን ቤተሰብ እንዲኖራቸው የሚያስችለውን ፕሮጀክት ምሥረታ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን ፣ የሃይማኖት አባቶች እና ተማሪዎች በተገኙበት አካሂዷል።

ምሥረታውን በንግግር የከፈቱት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ፣ የቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት ባህሎችን፣ ቋንቋዎችን፣ ወግና ልማዶችን የምንለዋወጥበት ትልቅ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

በመርሐግብሩ ላይ በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ ምክትል ዲን ወ/ሮ ምኞት ጌታቸው፣ የፕሮጀክቱን ዓላማና ይዘት የሚገልጽ ጽሑፍ አቅርበዋል። በዚሁ ወቅትም የሃይማኖት አባቶች የፕሮጀክቱ አካል በመሆን የቃልኪዳን ቤተሰብ ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት በመግለጽ፣ አስፈላጊው ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል።

በመድረኩ መዝጊያ ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ፣ ይህ የቃልኪዳን ቤተሰባዊነት መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞችንም ሊያሳትፍ እንደሚገባ ጠቁመው፣ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ለማድረግ ፕሮጀክቱ በስፋት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተጀመረና ተሞክሮውም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት አገኝቶ እየተተገበረ መሆኑም ተመላክቷል።

- የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Photos from Kotebe University of Education's post 22/04/2026

KUE Awards ELIP Completion Certificates to Academic Staff
⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆ ⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆ ⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆⋆
(KUE, April 22, 2026) – Kotebe University of Education (KUE), through its Languages Improvement and Development(LIDC), has awarded English Language Improvement Program(ELIP) completion certificates to 114 academic staff across two cohorts. The ceremony was held at the university’s G+3 Hall in the presence of awardees and university officials.

Welcoming participants, Dr. Getachew Baye Head of the center, addressed the gathering and emphasized the significance of the training in strengthening instructors’ English language competence. He also presented the rationale, objectives, implementation process, and post-training evaluation report, followed by feedback and discussion with participants.

In his closing remarks, Dr. Allebachew Kemiso, Vice President for Academic Affairs, congratulated the awardees and highlighted the importance of Continuous Professional Development (CPD) programs such as the English Language Improvement Program (ELIP). He noted that such initiatives play a crucial role in bridging skill, pedagogical, and technological gaps among academic staff. He further encouraged instructors to embrace such opportunities to acquire up-to-date knowledge and skills and to actively engage in training sessions.

Finally, certificates were awarded to trainees, trainers, and coordinators who contributed to the successful implementation of the program across both cohorts.

► Public and International Relations Executive Office




Follow Us for More Information:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/

Photos from Kotebe University of Education's post 17/04/2026

የዩኒቨርሲቲው 14ኛው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከበረ
************ ************ ************

(ኮትዩ፣ ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም) - የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 14ኛው የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ቀን ከተለያዩ 20 የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ባቀረቡት የውድድር ፕሮጀክቶች እና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ታግዞ ተከብሯል፡፡

ተማሪዎቹ ያቀረቡትን የፈጠራ ውጤቶች የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ከሚሶ፣ የምርምርና የማኅበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ ሙሉጌታ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ለሁለት ቀናት የተካሄደው የአውደ ርዕይ እና ውድድር መርሐግብር በተጠናቀቀበት ወቅት የምርምርና የማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ ሙሉጌታ፣ ፕሮጀክት እንድትሠሩ ዕድል የፈጠረላችሁ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው የውድድር መድረክ በመሆኑ፣ የዚህ ዓይነቱ ዕድል የፈጠራ ሥራ እንድትሠሩ፣ ነገሮችን በአንክሮ እንድትመለከቱና እንድትመራመሩ፣ የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት ጥረት እንድታደርጉ፣ የወደፊት ህይወታችሁን እንድታልሙና በመስኩ ትልቅ ሰው እንድትሆኑ መልካም አጋጣሚ በመሆኑ የጀመራችሁትን የፕሮጀክት ፈጣራዎች በቀጣይም ወደ ተግባር መለወጥ ይጠበቅባችኋል ብለዋል፡፡
ይህ ዓይነቱ የተማሪዎች የፈጠራ ውድድር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ረገድ ለሀገሪቱ በጣም ጠቃሚ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ቴዎድሮስ፣ ስልጠናውን እና ውድድሩን ያዘጋጀውን የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ STEAM ማዕከል እንዲሁም ለፕሮጀክቱ እና ለፈጠራ ሥራዎቹ መሳካት ግብዓትን ከማሟላት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ያመቻቸውን STEM Synergy ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡

የ STEM Synergy የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኢንጂነር አብዮት ላቀው፣ ድርጅታቸው ወጣቶች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ እና በሂሳብ የላቀ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የተለያዩ መርሐግብሮችን ማመቻቸት፣ ስልጠና መስጠት፣ በዘርፉ የጽንሰሃሳብና የተግባር እውቀት እንዲቀስሙ የሚተጋ በመሆኑ ይህንንም ዓላማ ለማሳካት ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ስኬታማ ሥራዎችን እየሠራ በመሆኑ ለዩኒቨርሲቲው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቅርቡም በመርሐግብሩ ላይ ለሚሳተፉ ሴት ወጣቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመሆን ስልጠና መስጠቱን ያስታወሱት ኢንጂነር አብዮት፣ ዋና ዓላማውም ወጣቶችን ማብቃት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ማድረግ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ STEAM ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ስንታየው ዓለሙ በበኩላቸው፣ በፈጠራ ሥራዎቹ ውድድር ላይ ከ20 የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመጡ ተማሪዎች መወዳደራቸውን ጠቅሰው፣ የፕሮጀክቶቹም ሃሳብ የሀገሪቱን የግብርና ምርት ለማሻሻል፣ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር፣ የትራንስፖርት ችግሮችን ለመቅረፍ፣ የጤና አገልግሎቶችን ለማፋጠን፣ ታዳሽ ኃይሎችን ለመጠቀም እና የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት የሚያግዙ በመሆናቸው የፈጠራ ውጤቶቹም ሆኑ የፈጠራው ባለቤት የሆኑት ተማሪዎች ተስፋ የሚጣልባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በውድድሩ ላይ ለተሳተፉ እና በውድድሩ ላሸነፉ ተማሪዎች ሠርተፍኬት እና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Photos from Kotebe University of Education's post 16/04/2026

በተማሪዎች መካከል የሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ
*************** *************** ***************

(ኮትዩ፣ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም) - በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች መካከል የሚካሄደው የእግር ኳስ ውድድር የአይቲ እና ማትስ ትምህርት ክፍሎች ከሳይኮሎጂ እና ስፔሻል ኒድ ትምህርት ክፍሎች ጋር ባደረጉት ጨዋታ ተጀመረ።

በመክፈቻ ሥነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ ባደረጉት ንግግር፣ የስፖርት ውድድሩ ከማሸነፍና መሸነፍ ባሻገር በተማሪዎች መካከል መልካም ግንኙነትና ትውውቅ ስለሚፈጥር የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
የስፖርት ውድድሩ ከማህበራዊ መስተጋብር በተጨማሪ ለጤናም ጭምር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ስላለው በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ለሌላውም የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ሞዴል በሚሆን መልኩ የጨዋታ መርሐግብሩን በጥሩ ዲሲፕሊን እንዲያሳኩም ዶ/ር ሽመልስ አደራ ብለዋል፡፡

በተካሄደው የመጀመሪያው የእግር ኳስ ውድድር የአይቲ እና ሒሳብ ትምህርት ክፍሎች የሳይኮሎጂ እና ስፔሻል ኒድ ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎችን 2 ለ 1 ያሸነፉ ሲሆን፣ ጨዋታው በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች መካከል ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆኔል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Photos from Kotebe University of Education's post 15/04/2026

መምህራን ተማሪዎቻቸው በመውጫ ፈተና እንዲያልፉ የማስቻል ተግባር ይጠበቅባቸዋል
- ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ

************* ************* *************

(ኮትዩ፣ ሚያዝያ 07 ቀን 2018 ዓ.ም) - በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ዝግጅት እና እስካሁን የተከናወኑ ሥራዎችን አፈጻጸም በተመለከተ የገለጻ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ መምህራን ከማስተማር፣ ተማሪን በእውቀት፣ በክሂሎትና በአመለካከት ከመገንባት ጎን ለጎን ተማሪዎቻቸው የተማሩትን በትክክል ስለማወቃቸው የሚመዘኑበትን የመውጫ ፈተና እንዲያልፉ የማስቻል ትልቅ ተግባር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አፅንኦት በመስጠት አስገንዝበዋል፡፡
የዘመኑ የመማር ማስተማር ሂደት ከተቋም ጀምሮ በየደረጃው ተጠያቂነት የተቀመጠለት በመሆኑ፣ እንደቀድሞው ጊዜ መምህራን ተማሪዎቻቸውን አስተምረው መተው ብቻ ሳይሆን፣ በቅተዋል ወይ ተብሎ የሚመዘኑበት አሠራር ስለተዘረጋና ይኸውም ስለመከናወኑ በተቀመጠው ቁልፍ የውጤት አመላካቾች (KPIs) መሠረት ተጠያቂነት እንዳለበት ተረድቶ፣ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት፣ ለዚህም ተጠባቂ ውጤት መምህራንም ሆኑ ተማሪዎች በልዩ ዲሲፕሊን እንዲሠሩ የትምህርት ክፍሎች ኃላፊዎች እና የኮሌጅ ዲኖች የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በጥብቅ አሳስበዋል፡፡ በቅርቡም በተቋሙ የአካዳሚክ ሪፎርም እንሚካሄድ ፕሬዘዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ከሚሶ በበኩላቸው፣ ከመማር ማስተማር ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ክፍተቶች በተማሪዎች የመውጫ ፈተና ላይ ተፅዕኖ ስላላቸው የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ትኩረት ሰጥቶ ማረም፣ በዘንድሮው ዓመት የመውጫ ፈተና የሚወስዱ 1050 የተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ማገዝና ይህንንም ለማሳካት የተነደፈውን የድርጊት ዕቅድ በቀሪው አጭር ጊዜ ውስጥ በጥንቃቄ መፈፀም እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እንዴት መደገፍ እንደሚቻል ስትራቴጂያዊ የድርጊት መርሐግብር ያቀረቡት የፈተናዎች፣ የትምህርት ምዘና እና እውቅና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ከበደ ትርፌሣ፣ ከዚህ በፊት የተሠሩ ሥራዎች ቢኖሩም መርሐግብሩን ለማስፈፀም የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ የትምህርት ክፍሎችና ዲኖች የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፣ በአፈፃፀሙም በጊዜ ሰሌዳው መሠረት የሚከናወኑ ተግባራት ማለትም መምህራን በተለያየ ደረጃ ለተማሪዎች የሚሰጡ የቁመና መለኪያ ፈተናዎችን እንዲያወጡና ተማሪዎችም ፈተናውን እንዲወስዱ ማገዝ፣ አካሄዱንም ሆነ ውጤቱን መገምገም፣ ተማሪዎች ዝቅተኛ ውጤት ባመጡባቸው ኮርሶች ላይ ልዩ ድጋፍ መስጠት፣ የውጤት ማሻሻያ እና ሞዴል ፈተና እንዲሁም ለፈተና መዘጋጃ የሚሆን የስነልቦና ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ፣ በመጨረሻም በራስ የመተማመን መንፈስ የመውጫ ፈተና እንዲፈተኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት እንዲሰጡ ማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በገለጻ መድረኩ መጨረሻ ላይ ንግግር ያሰሙት የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲው፣ ኮሌጆች እንዲሁም የትምህርት ክፍሎች የሚመዘኑበት በመሆኑ፣ የሥራ ባህልን ማጎልበት፣ ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡና ድጋፍ ለሚፈልጉትም ድጋፍ እንደሚሰጥ የገለፁ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ በተደረገው ውይይትም የድርጊት መርሐግበሩ ተፈፃሚነት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት በባለድርሻ አካላት መካከል ከመግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችንን ይከታተሉ:
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Photos from Kotebe University of Education's post 08/04/2026

አማራጭ የመምህርነት ስልጠናን በመውሰድ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ገለፃ ተሰጠ
************* ************* *************

(ኮትዩ፣ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም) - አማራጭ የመምህርነት ስልጠናን በመውሰድ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ለምልከታ ወደተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሲሄዱ ማድረግ ስለሚገባቸው ቅድመ ዝግጅቶች ገለፃ ተሰጥቷል፡፡

ገለፃውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የፕራክቲካም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዮሴፍ ሹሚ ሲሆኑ፣ በአማራጭ መምህርነት ሙያ ስልጠና ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለመጀመሪያው የፕራክቲካም ኮርስ ለምልከታ ወደተለያዩ ትምህርት ቤቶች ስለሚሄዱ ገለፃው ተማሪዎቹ ከመውጣታቸው በፊት ምን ምን ዝግጅት ማድረግ እና ምን ዓይነት ቅደም ተከተል መከተል እንዳለባቸው፣ የተዘጋጀላቸውን የምልከታ መመሪያ እንዴት መጠቀም እና ምን ዓይነት ባህሪ ማሳየት እንዳለባቸው የሚያመለክት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ሰልጣኞቹ ወደተመደቡበት ትምህርት ቤቶች ሲሄዱ እንደ መምህር ራሳቸውን ዝግጁ ማድረግ፣ ከፀጉር አቆራረጥ ጀምሮ የመምህርነት ስብዕና በመላበስ አርአያ ሆነው ከመገኘት በተጨማሪ የተዘጋጀላቸውን የምልከታ መመሪያ በጥንቃቄ መጠቀም እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡

ተማሪዎቹም በበኩላቸው የምልከታውን አተገባበር በተመለከተ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ የተሰጠባቸው ሲሆን፣ የአፈፃፀም ሂደቱ ለተማሪዎቹ ተግባራዊ እውቀትን በመስጠት በራስ የመተማመን መንፈሳቸውን እንደሚያዳብር ታምኖበታል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ:-
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Photos from Kotebe University of Education's post 08/04/2026

በዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች መካከል የሚካሄደው የ2018 ዓ.ም የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ
************* ************* *************

(ኮትዩ፣ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም) - በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች መካከል የሚደረገው የ2018 ዓ.ም የእግር ኳስ ውድድር ዛሬ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በውድድሩ የመክፈቻ ሥነስርዓትም ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ከሚሶ፣ የምርምርና የማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቴዎድሮስ ሙሉጌታ፣ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሽመልስ ዘውዴ እንዲሁም የየኮሌጆቹ ዲኖች እና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡

ዛሬ በዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች መካከል የተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ ዜሮ ለዜሮ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ጨዋታው በቀጣይ በተለያዩ ዙሮች የሚቀጥል ይሆናል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችቻችንን ይከታተሉ:-
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Photos from Kotebe University of Education's post 08/04/2026

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የዜግነት መብታቸውን ተጠቅመው በሀገራዊ ምርጫ ላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው
ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ
************** ************** **************

(ኮትዩ፣ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም) - ዘንድሮ የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ “የምርጫ ሕግ አጠቃላይ ዕይታ እና የመራጮች መብትና ግዴታ” በሚል ርዕስ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በተሰጠው ገለጻ ላይ የተገኙት የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተሾመ ነቃጥበብ፣ ተማሪዎች የዜግነት መብታቸውን ተጠቅመው በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ በመራጭነት በመመዝገብ እና ድምፅ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው አመልክተዋል፡፡
በታዳጊ ሀገራት ውስጥ የእኔ ተሳትፎ ትርጉም የለውም በሚል የተሳሳተ አመለካከት እና ግንዛቤ የተነሳ የተሳትፎ ውስንነት እንደሚስተዋል የገለጹት ዶ/ር ተሾመ፣ የአንድም ሰው ድምፅ ወሳኝ ሚና ያለው በመሆኑ፣ ተማሪዎች መብታቸውን ተጠቅመው በመመዝገብና በመምረጥ እንዲሁም ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

“የምርጫ ሕግ አጠቃላይ ዕይታ እና የመራጮች መብትና ግዴታ” በሚል ርዕስ የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት በዩኒቨርሲቲው የኢሞሽናል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር አልማው ክፍሌ በበኩላቸው፣ ምርጫ ዜጎች መሪዎቻቸውን ወይም አስፈላጊ የህዝብ ጉዳዮችን ድምፅ በመስጠት የሚመርጡበት ሂደት እና የዴሞክራሲ አስፈላጊ ክፍል በመሆኑ ተማሪዎች የተሻለ የሃሳብ ልዕልና ያለውን፣ ሀገርን እንደ ሀገር ማስቀጠል የሚችለውን ፓርቲ በመምረጥ የዜግነት መብታቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መክረዋል፡፡

የምርጫ ሕግ ምርጫዎች እንዴት እንደሚካሄዱ፣ ምርጫዎች ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ታማኝ እንዲሆኑ የሚያሳይና የሚያረጋግጥ ነው ያሉት ዶ/ር አልማው፣ ዋና ዓላማዎቹም ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ማረጋገጥ፣ የዜጎች የመምረጥ መብትን መጠበቅ፣ እኩል ተሳትፎን ማበረታታት፣ ተጠያቂነትን ማስፈን፣ በምርጫ ሂደት ውስጥ ሥርዓትና ህጋዊነትን መጠበቅ በመሆኑ በምርጫው ሂደት መሠረት ተማሪዎች የፈለጉትን እጩ ወይም ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ መምረጥ እንደሚችሉ አስረድተዋል፡፡

የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ዶ/ር ኃይሉ መገርሳ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፣ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በገለጻው የቀረቡትን የመምረጥ መብቶች በመጠቀም በተቻለ መጠን ከወዲሁ የዜግነት ድርሻቸውን በመወጣት ዲሞክራሲን እንዲለማመዱ አስገንዝበዋል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት



ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾቻችንን ይከታተሉ:-
Facebook፡ https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Photos from Kotebe University of Education's post 06/04/2026

ዩኒቨርሲቲው ፕራክቲካምን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና ሰጠ
***************** ***************** *****************

(ኮትዩ፣ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም) - ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ ለትምህርት አመራሮች እና ርዕሳነ መምህራን ያዘጋጀውን የፕራክቲካም አተገባበርን ውጤታማ የሚያደርግ ስልጠና በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ከሚሶ፣ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር ለረጅም ዓመታት በአጋርነት ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰው፣ የአማራጭ መምህርነት ሙያ ስልጠና እና ፕራክቲካምን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመተግበር አሁንም የቀድሞውን ትብብር በተጠናከረ ሁኔታ በማስቀጠል በጋራ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡

አማራጭ የመምህርነት ሙያ ስልጠናን የሚሰጡት ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውንና ከእነዚህም ዩኒቨርሲቲዎች ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛውን የሰልጣኝ ቁጥር በመቀበል ስልጠናውን በመስጠት ላይ በመሆኑ፣ መርሐግብሩም ሆነ የፕራክቲካም ኮርስ ስኬታማ እንዲሆን የትምህርት አመራሮች እና ርዕሳነ መምህራን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸው፣ ተሳታፊዎች የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ድርሻ በብቃት እንዲወጡ አደራ ብለዋል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ ከፕራክቲካም አተገባበር ጋር በተገናኘ በዘርፉ ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ ማስጨብጥ መሆኑን የጠቀሱት፣ የሥራ ላይ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ተሾመ ቁንዳሌ በበኩላቸው፣ በአማራጭ የመምህርነት ሙያ ስልጠና መርሐግብር ላይ እየተሳተፉ ያሉ ተማሪዎች የተማሩትን የንድፈሃሳብ ትምህርት በክፍል ውስጥ ለመተግበር ከሚያዚያ 5፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደየትምህርት ቤቶቹ እንደሚሄዱ ገልጸው፣ ይህ ገለጻ የተዘጋጀውም አስቀድሞ ተማሪዎቹን በየደረጃው የሚያግዙ አካላት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉላቸው ለማስቻል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ለመርሐግበሩ ተግባራዊነትም ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል በማድረግ እንደሚያስፈጽምም ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የፕራክቲካም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዮሴፍ ሹሚ፣ በአማራጭ መምህርነት ሙያ ስልጠና ላይ ለሚሳተፉ ተማሪዎች ሦስት የፕራክቲካም ኮርሶች መዘጋጀታቸውን፣ የመጀመሪያው የትምህርት ቤቱን አደረጃጀት እንዲያውቁ የሚደረግበት፣ ሁለተኛው ረዳት መምህር ሆነው የመምህርነትን ሙያ የሚያዳብሩበት፣ ሦስተኛው ደግሞ መምህሩን በመተካት ራሳቸውን ችለው የሚያስተምሩበት በመሆኑ፣ በዚህ ሂደት ውስጥ ባለድርሻ አካላት እገዛ እንዲያደርጉላቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እና ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለግማሽ ቀን በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ከአራት ክፍለ ከተማ የመጡ የትምህርት ዘርፍ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም ከ14 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

Education_committed_to_excellence_in_Education

ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችችንን ይከታተሉ:
Facebook: https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/

Photos from Kotebe University of Education's post 01/04/2026

“የሥራ ፈጠራ የመንግሥትም የዩኒቨርሲቲያችንም ትኩረት ነው”

- ዶ/ር አለባቸው ከሚሶ

***************** ***************** *****************

(ኮትዩ፣ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም) በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሥራ ዝግጁነት እና የሥራ ፈጠራ ልማት ማዕከል፣ Pioneers of Change Africa ከተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር፣ “የሥራ ፈጠራ በትምህርት ውስጥ ያለው ጠቀሜታ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀው የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር አለባቸው ከሚሶ፣ የሥራ ፈጠራ የመንግሥትም የዩኒቨርሲቲያችንም ትኩረት በመሆኑ የሥራ ፈጠራን በዩኒቨርሲቲያችን የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ከማካተት ባሻገር፣ መምህራን ችግር ፈቺ ሃሳቦችን በማፍለቅ፣ ሙያና ልምዳቸውን በመጠቀም ለወጣቶች ብሎም ለራሳቸው የሥራ ፈጠራ ክሂሎትን ማዳበር፣ ለዚህም ከአጠገባችን ያለ ሰው የሥራ አጋራችን እንደሆነ ማሰብና በትበብር በመሥራት ተግባራዊ ለውጥ ማምጣት የሚያስፈልግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት አመራሮችን፣ መምህራንን፣ የስነልቡና እና የትምህርት ባለሙያዎችን እንደሚያፈራ የጠቆሙት ም/ፕሬዘዳንቱ፣ በመማር ማስተማሩ ሂደት ውስጥ እንደ ሀገር የሚስተዋሉ የትምህርት ጥራት ችግሮችን፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀሞችን እና ተግዳሮቶችን በጥልቀት በመመርመር መፍታት፣ በጉዳዩ ዙሪያም በተለያዩ ጊዜያት መመካከር፣ ልምድ ካላቸው ሰዎችም ተሞክሮ በመለዋወጥ ወደ ተግባር ማሸጋገር አስፈላጊ በመሆኑ ልምዳቸውን ለማካፈል የመጡትን ከፍተኛ ባለሙያዎች አመስግነው፤ ተሳታፊዎች በመድረኩ በንቃት እንዲሳተፉ አደራ ብለዋል፡፡

የPioneers of Change Africa ዋና ዳይሬክተር አቶ ብሩክ መሰለ ባደረጉት ንግግር፣ ድርጅታቸው በሥራ ፈጠራ መስክ ፈር ቀዳጅ የሆኑ ግለሰቦችን አሰባስቦ፣ ወጣቶች ልምድ እንዲቀስሙ፣ የሥራ ፈጠራ ሃሳብና ቁርጠኝነት እንዲኖራቸው የማድረግ ዓላማን ይዞ መመሥረቱን ገልጸው፤ በሀገራችንም ሆነ በመላው አፍሪካ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ሲወጡ እውቀትና ክሂሎታቸውን በመጠቀም ሥራ እንዲፈጥሩ ለማነቃቃት ክፍል ገብተው ከሚማሩት ትምህርት በተጨማሪ ሥራ በመፍጠር የተሳካላቸውንና በቂ የሕይወት ተሞክሮ ያላቸውን ሰዎች በመጋበዝ ልምድ እንዲቀስሙና ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል፣ ይህም ዓይነቱ የሥራ ፈጣሪ ስልት በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ የተለመደ እንዲሆን ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ብሩህተስፋ፣ የሥራ ፈጠራ በመማር ማስተማር መርሐግብር ውስጥ ሊካተት የሚችልበትን ዘዴ እና የሚያስገኘውን ጠቀሜታ በሚመለከት ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ የጠብታ አምቡላንስ መስራችና የኢትዮጵያ የሶሻል ኢንተርፕራይዝ ፕሬዘዳንት የሆኑት አቶ ክብረት አበበ ልምዳቸውን፣ ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እና ለስኬት እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ሽልማት የበቁበትን የሥራ ውጤት “ከጅማ እስክ ዳቮስ (From Jimma to Davos)” በሚል ርዕስ ብዙዎችን አቅርበዋል፡፡

በሥራ ፈጠራ የልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ተማሪዎች እንዲሁም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጋበዙ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

- የህዝብ እና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት

University_ofEducation_committed_to_excellence_in_Education

ለተጨማሪ መረጃ ይፋዊ ገጾችችንን ይከታተሉ:
Facebook: https://web.facebook.com/www.kue.edu.et
Website: https://www.kue.edu.et/
YouTube: https://youtube.com/
Facebook (https://web.facebook.com/www.kue.edu.et)
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Address


Kotebe, Sub City Yeka, Wo 10
Addis Ababa
31248

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00