14/08/2025
Vacancies
ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ኮሌጅ ድረስ ያሉ ተማሪወችን ልምድና ?
14/08/2025
Vacancies
14/08/2025
የትምህርት ቤት የስራ ማስታወቂያዎች
04/01/2022
Coming soon.
የአገልግሎት ዋጋን ጭማሪ የጀመረው ማነው?
Fair እንሁን ካልን የአገልግሎት ዋጋ ቀድሞ መጨመር የጀመሩት የመንግሥት ተቋማት ናቸው። መብራት ሀይል 3 እጥፍ (300%)፣ መንገድ ትራንስፖርት፣ አመታዊ የተሽከርካሪ እድሳት፣ የመንጃ ፈቃድ እድሳት ... እስከ 600% ጭማሪ አድርጓል፣ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር እጅግ የሚገርም ጭማሪ አድርጓል፣ ቀበሌ እንኳ በ5 ብር የሚታደስን መታወቂያ 150 ብር (30 እጥፍ) አድርጓል፣
ዝርዝሩ በየተቋሙ ብዙ ነው ...
የቤት አከራዮች ሁለት ሶስት ጊዜ ጭማሪ አድርገዋል። በሸቀጣ ሸቀጥ በምግብ፣ እና በፍጆታ እቃዎች ላይ ባለፉት ሶስት አመታት በሶስት እጥፍ ያልጨመረ ነገር ካለ ንገሩኝ።
የግል ትምህርት ቤቶች ሲጨምሩ አገር ምድሩ መንጫጫት የሚጀምረው ለምንድነው?
መምህራን የዋጋ ንረቱ አይመለከታቸውም? የቤት ኪራይ አልጨመረባቸውም? ደመወዛቸው ለነሱ ሲሆን በቂ ነው? መጨመር የለበትም?
ለመማር ማስተማር የሚሆኑ ግባቶች አልጨመሩም? ቤታቸው ወይንም ህንፃዎቻቸው ለግል ት/ቤት ያከራዩ ሰዎች የኪራይ ጭማሪ አላደረጉም?
ሁሉም ነገር በሁለት እና በሶስት እጥፍ(ከ200% በላይ) ሲጨምር ዝም ብለህ ከርመህ የግል ትምህርት ቤቶች 50% ጨመሩ ተብሎ እሪ ማለት ፌር አይደለም።
ከጮህን ሁሉም ላይ እንጩህ፣ አቅም በሌለው ላይ መዝመት ግን ተገቢ አይሆንም።
እናመሰግናለን!!!!
Hakim
ህፃን/ታዳጊ ልጆችን ስለ ስለኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዴት ማስረዳት ይቻላል?
ልጅዎ ስለወረርሽኙ ከሰማ/ች በኋላ ያያችሁት አሉታዊ ለውጥ አለ?
➦ህፃናትና ታዳጊዎች ለነገሮች ምላሽ የሚሰጡት በከፊልም ቢሆን በዙርያቸው ያሉ አዋቂዎች አይተው ነው።
➦ወላጆች በራስ መተማመንና በተረጋጋ ሁኔታ ስለኮሮና ቫይረስ በሽታ (COVID-19) ሲወያዩ ለልጆቻቸው የተሻለ እገዛ ማድረግ ይችላሉ።
➦ወላጆች በተሻለ ሁኔታ ከተዘጋጁ በዙርያቸው ላሉ በተለይም ለልጆቻቸው የበለጠ አፅናኝ/አበረታች ይሆናሉ።
➦ሁሉም ህፃናትና ታዳጊዎች በተመሳሳይ መንገድ ለጭንቀት ምላሽ አይሰጡም።
ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ምን አይነት ለውጦች መከታተል አለባቸው?
-------------------------------------------------------------------
1. በትናንሽ ልጆች ላይ ከልክ ያለፈ ለቅሶ መነጫነጭና ቁጣ
2. ህፃናት ልጆች ሆነው ወደተውት ባህሪያት መመለስ
ለምሳሌ በድንገት መፀዳዳት አልጋ ማርጠብ (መሽናት)
3. ከልክ ያለፈ ጭንቀትና ሃዘን
4. ጤናማ ያልሆነ የእንቅልፍ/የአመጋገብ ልማድ
5. የመነጫነጭ የቁጠኝነት እንዲሁም ለቁጥጥር የማስቸገር ባህሪያት
6. ትምህርት መማር አለመፈለግ/ደከም ያለ የትምህርት አቀባበል
7. ትኩረት ማጣት
8. ከዚህ ቀደም ሲተገብሩ የነበሩትን የሚወዱትን ተግባራት መተው
9. ይሄ ነው ብለው ለመግለጽ የሚያስቸግራቸው የሰውነት/የራስ ህመም
10. ሲጋራ አልኮልና ሌሎች እፆች መጠቀም (ታዳጊ ወጣቶች)
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ወቅት ወላጆች የልጆቻቸውን የአዕምሮ ጤና ለመጠበቅ ምን ያድርጉ?
==============================
➊ ጊዜ ሰጥታችሁ ከልጆቻችሁ ጋር ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) በሽታ ተወያዩ
➦ጥያቄዎቻቸውን መልሱ
➦በሚገባቸው መልኩ ስለ COVID-19 ትክክለኛ መረጃ አካፍሏቸው።
❷ ልጆቻችሁ (ህፃናት ወይም ታዳጊዎች) ደህና እንዲሆኑ እርግጠኛ እንዲሆኑ አበረቷቷቸው።
በዚህ ወቅት ጭንቀታችሁን እንዴት እንደተወጣችሁ አሳውቋቸው። ይሄም እንዴት ጭንቀታቸውን መቋቋም እንዲማሩ ይረዳቸዋል።
❸ ቤተሰባችሁን ስለሁኔታው ያላቸውን (ኮሮና ቫይረስ) ተጋላጭነት ገድቡ። ማህበራዊ ድህረገፅም ቢሆን።
➦ህፃናት የሚሰሙትን በተሳሳተ መንገድ ሊተረጉሙት ይችላሉ።
❹ እለት እለት የሚሰሩትን ሥራ ጠብቁ። አሁን ላይ ትምህርት ቤትም ስለተዘጋ ለመማር የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጁና የመማር ማስተማር ሂደቱን ቀጥሉ። እናም የሚያዝናናቸውን ድርጊቶች አታስቀሩባቸው። መከላከል ላይ የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች ሳይዘነጉ።
➎ እናንተ ለልጆቻችሁ ምሳሌ ሁኗቸው
➦እረፍት ውሰዱ
➦በቂ እንቅልፍ አግኙ
➦በበቂ ሁኔታ ይመገቡ
➦አካላዊ እንቅስቃሴ ያድርጉ
በበሽታና መቆጣጠር ማዕከል ከተዘጋጀው ለንባቢ እንዲስማማ የተተረጎመ
ቃልኪዳን ዮሐንስ
የስነ-አዕምሮ ህክምና ባለሙያ
"ትምህርት ቤት ለመሄድ ማስቸገርና የልጆች የትምህርት ቤት ፍራቻ" - በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ
እስከ አምስት በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ትምህርት ቤት መሄድን ይፈራሉ ወይም አይፈልጉም፤ ይህም የትምህርት ቤት ፍራቻ (school phobia) ይባላል፡፡ በነዚህም ልጆች ላይ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ የጭንቀትና አለመረጋጋት ምልክቶች ይስተዋላሉ፡፡
ትምህርት ባለባቸው ቀናት አመመኝ፣ ቆረጠኝ፣ ጨነቀኝ በማለት ተጨንቀው ሲታዩ ቅዳሜና እሁድ ግን ዘና ብለው ሲጫወቱ ይውላሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት ትምህርት ቤት መሄድ የሚፈሩትና የሚጨነቁት በሚከተሉት ምክንያቶች የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡
-ውድቀትን ፍራቻ
-ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት
ለምሳሌ፡- ወፍራም ወይም በጣም ቀጭን በመሆኑ ካሾፉበት
-ከአስተማሪዎች ከሚደርስባቸው ነቀፌታ
-ከጉልበተኛ ተማሪዎች ለሚደርስባቸው ድብደባ ፍራቻና የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ወላጆች ህፃናት ትምህርት ቤት በጥሩ መንፈስ እንዲሄዱና ከፍርሀታቸው እንዲላቀቁ በግልፅ የፍርሀቱ ምንጭ ምን እንደሆነና ትምህርት ቤት መሄድ ለምን እንደሚጨንቃቸው መወያየት አለባቸው።
በተጨማሪም
* የልጆችን ችግር ለመረዳት መሞከርና በአፋጣኝ ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ማስቻል፡፡ ልጆች ከትምህርት ቤት ብዙ ቀናት በቀሩ ቁጥር ለመመለስ ከባድ ስለሚሆን ይህንን ማስቀረት
* ከትምህርት ቤት ማህበረሰብ ጋር መወያየትና ችግሮችን ለማሻሻል መሞከር
* ትምህርት ቤት ለመቅረታቸው የጉልበተኛ ተማሪዎች ድብደባ ፍራቻና የአስተማሪ ነቀፌታ እንዲሁም የመሳሰሉት የሚስተካከሉ ነገሮች ከሆኑ ከትምህርት ቤት ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር ማስተካከል፡፡
*ሁል ጊዜ ጠዋት ላይ ልጃችን ወደ ትምህርት ላለመሄድ ሰበብ ሲያቀርብ በፍፁም ከትምህርት ቤት መቅረት እንደማይቻልና መሄድ እንዳለበት ማሳመን፡፡ ትምህርት ቤት መሄድ ግዴታ እንደሆነ ማሳወቅ፡፡
* ከትምህርት ቤት በየምክንያቱ አብዝተው የሚቀሩ ከሆነ በቤት ሲውሉ ከሌላው ጊዜ የተለየ እንክብካቤ አለማሳየት፡፡
* ልጆቻችን ከትምህርት ቤት መልስ ከሌሎች ህፃናት ጋር ከቤት ውጪ እንዲጫወቱና እንዲግባቡ ማድረግ ጭንቀታቸውን ይቀንሳል፡፡
በመጨረሻም እንደየአስፈላጊነቱ ችግሮች ከተባባሱ የህፃናት ሀኪምና የትምህርት ጉዳይ አማካሪዎችን እርዳታ በጊዜ መፈለግ ተገቢ ነው፡፡
የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በአግባቡ በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ምክረ ሀሳብ አቀረበ።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ ያተኮረ ሪፖርትና ምክረ ሀሳብ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።
ሚኒስትሯ ያቀረቡት ምክረ ሃሳብ ወረርሽኙን ለመከላከል እየተወሰዱ ያሉ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱ የሚል ነው፡፡
ትምህርት ለመጀመር ከመወሰኑ በፊት ግን ጠንካራ ግብረ ኃይል በየደረጃው ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ምክር ቤቱ በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያቀርብ መርቷል።