17/05/2024
ENPA-አምባ ትምህርት ለተቸገሩ በጎአድራጎት ማኅበር (EDUCATION FOR NEEDY PEOPLE ASSOCIATION-አምባ-ENPA) በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 2023 የኢትዮጵያ ነዋሪዎች የበጎአድራጎት ድርጅት በመሆን የተመዘገበና በተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ዕድል ያጡ ህፃናት ዘለቄታዊ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ወላጅ እና አሳዳጊዎቻቸው ከመንግስትና ተመሳሳይ አላማ ካላቸው አጋር ማህበራትና ድርጅቶች ጋር በማቀናጀት ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ድጋፍ ለመስጠት የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ የተቋሙ መሥራቾች በቀድሞ የኢትዮጵያ ህጻናት አምባ ውስጥ በህዝብ እና በመንግሥት ድጋፍና እንክብከቤ አድገው ዛሬ ሀገራቸውን በተለያየ መሥኮች እያገለገሉ ባሉ ጥቂት ወጣቶች ሲሆን መሠረታዊ አላማውም የህዝብና የሀገርን ውለታ መክፈል ነው፡፡
ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት በሺ ለሚቆጠሩ ሕፃናት ዘለቄታዊ ችግራቸው እንዲቀረፍ ሲደግፍ እና በጥሩ ስነምግባር ሲያስተምር እና ሲያንፅ, የነበረ በመሆኑ ከአዲስ አበባ መስተዳደር ሶስት ሺ ካሬ ቦታ ተሰጥቶት ስራዉን አጠናክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡
አሁንም ይህንኑ ሥራ አጠናክሮ በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡
ታድያ ሕፃናቱ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የተለያዩ ተሰጦአቸውን እንዲያሻሽሉ እና እንዲያዳብሩ ከፍተኛ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ በዚሁም መሰረት በየዓመቱ ትላልቅ ፕሮግራሞች ላይ እንዲያቀርቡ ይደረጋል፡፡ የሀይማኖታዊ፤ የባህላዊ እና አገራዊ በዓላትን ለምሳሌ የገና፤የፋሲካ በዓልን የአድዋ፤የአርበኞች ቀን ፤የአርበኞች ቀን የወላጆች ቀን
ለልጆቹ ተሰጦቸውን ማውጫ እንዲሆኑ መልካም አጋጣሚዎች ናቸው፡፡ዘንድሮም በ2016 የፋሲካ በዓልን የየሎወር ኬጂ ተማሪዎች ተሰጦአቸውን ሲያቀረቡት
ENPA _AMBA children are always dedicated to out cast their talent
08/04/2024
የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን
ችግኝ ለመትከል ከ ሶስት ዓመት በፊት የካ ሚካኤል ባለው ጫካ ወደ መድኃኒዓለም እና ኪዳነምህረት የሚወስደው ቦታ ላይ ይገኛሉ ፡፡ በእለቱ የነበረውን የችግኝ መትከል መረሃ ግብር ካጠናቀቁ በኃላ
እግረ መንገዳቸውን በ አከባቢው የነበረውን የ ENPA- አምባ በጎ አድራጎት ማህበርን እንዲጎበኙ
የጋበዛሉ ፡፡ ይህ በጋን ከክረምት ተዘግቶ የማያወቀው በጎ አድራጎት እየሰራ የበነበረውን አገልግሎት በተመስጦ አይተው ከተደሰቱ በኃላ ፡በወቅቱ የነበሩት ሀላፊዎች ከችግኝ ተከላው ባልተናነሰ እዚህ በጎ አድራጎት የሚሰራውን ሥራ በማየታችን ተደስተናል ብለው ይገልፃሉ ፡፡ወዲያውኑ ለድርጅቱ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ምን እንደሆነ እና ያለበትን እጥረት ካጣሩ በኋላ የሚያስፈልገውን ድጋፍ በዓይነት የምገባ ፕሮግርሙን የፅዳት እን የትምህርት ግብዓት ያሟላሉ ፡፡ ማህበራዊ ሀላፊነታችንን እንድንወጣ መልካም አጋጣሚ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ከበጎ አድራጎቱ ጋር በጋራ ለመስራት ቃል ገብተው ይሄዳሉ፡፡ ቃል በገቡት መሰረት ሳያቋርጡ ለሶስት ዓመት ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆን ፡፡አሁን ደግሞ መጋቢት ,20,2016 ዓ.ም የነበረውን የገቢ ማሰባሰብያው መረሃ ግብር ላይ ተገኝተው የመቶ ሺ ብር ለመለገስ ቃል ገብተዋል ፡፡
የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን ካለባቸው መደበኛ ሥራ በተጨማሪ እንዲህ ዓይነት ዓለማ ያላቸውን የሲቪክ ማህበራት እና ድርጅቶችን በመደጋፋቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ በማህበሩ አባለት እና ተገልጋዮች ስም እናመሰግናለን !!!!
በእለቱም የደግነት ተምሳሌት በሆነው ወንድማችን ክቡር ዶ/ር ቢንያም በለጠ ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
12/09/2022
ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በዕለተ እሑድ መስከረም 1 ከሌሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ከመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የዘመን መለወጫ በዓልን እናበሥራለን።
ኪዳን ዘነግህ፣ ቅዳሴ እና የአዲሱ ዓመት የበዓላትና አጽዋማት አዋጅ በቀጥታ ይተላለፋል።
የቀጥታ ስርጭቱን በቴሌቪዥን፣በዩቱዩብ እና በፌስቡክ አማራጮች መከታተል ይችላሉ።
30/08/2022
Enkuan le abuse Teklhaymanot Addersachu