28/09/2026
የXinye Special Steel ኩባንያ በኢትዮጵያ በዓመት 180 ሺህ ቶን አሉሚኒየም ለማምረት የሚያስችል ፕሮጀክት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2019 (ኢ.ኢ.ኮ) —
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ከሚፈልጉ የቻይና ኩባንያ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንም ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቻቸውን ከማስጀመር እስከ ማስፋፋት ድረስ ባለው የኢንቨስትመንት ጉዞ ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍና አገልግሎት ለማመቻቸት ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የXinye Special Steel ኩባንያ ሊቀመንበር ሚስተር ሹ ዌንፒንግ በውይይቱም ኩባንያው በገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በዓመት 180 ሺህ ቶን አሉሚኒየም ለማምረት የሚያስችል ፕሮጀክት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።
የሄናን ሁዋክሲ ፈርነስ ሪፍራክተሪ እና የሼንዘን ሰክሰስ ኤሌክትሮኒክስ ተወካዮችም በኢትዮጵያ የአይሲቲ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው በውይይቱ ላይ አንስተዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያም ልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የመደመር መንግስት የሀገር በቀል የኢኮኖሚክ ማሻሻያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
Xinye Special Steel Announces Readiness and Commencement of Operations for 180,000-Ton/Year Aluminum Project in Ethiopia
Addis Ababa, September 28, 2026 (EIC) —
The Commissioner of the Ethiopian Investment Commission, Dr. Zeleke Temesgen, held a discussion with leaders of Chinese companies seeking to engage in various investment sectors in Ethiopia.
During the meeting, Commissioner Dr. Zeleke Temesgen reaffirmed the Ethiopian Investment Commission's continued commitment to strengthening all necessary support and service facilitation for investors throughout their investment journey, from project initiation to full expansion.
Mr. Xu Wenping, Chairman of Xinye Special Steel, stated during the discussion that the company has completed all necessary preparations and commenced operations for a project capable of producing 180,000 tons of electrolytic aluminum per year in the Gada Special Economic Zone.
Representatives from Henan Huaxi Furnace Refractory Co., Ltd. and Shenzhen Success Electronics also expressed their interest during the meeting in investing in Ethiopia’s ICT sector.
In conclusion, the delegation expressed their readiness to invest in Ethiopia by leveraging the country's vast investment opportunities and the favorable environment created by the Medemer Government's Homegrown Economic Reform program.