ከእግዚአብሔር ጋር አቸንፈናል !!
*~★★~*
• ስለእኔ ሃዘን ለገባቸው ሁሉ ደስስ ይላቸው ዘንድ አድርጉልኝ።
| ~ ዛሬ በጀርመን እንዲህ ሆኖልኛል። እንዲህም ተደርጎልኛል።
•••
በዚሁ ኅብረት፣ አንድነት፣ ፍቅር፣ መተዛዘን፣ መተጋገዝ ኢትዮጵያዊነትና ኦርቶዶክሳዊነት ከፍ እንዲሉ በመሃላ ቃልኪዳናችንን አድሰን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንቀጥላለን።
•••
አንድነት ኃይል ነው። ድምጻችሁ አሸንፏል። አሁን እኔና ቤተሰቤ ለጊዜው በሃገረ ጀርመን እንደ ግማሽ ሰው ተቆጥረናል። እንደ ሙሉ ሰው ለመቆጠር ብዙ ይቀረናል። እኔ ሙሉ ሰው ነኝ። ነገር ግን በሰው ሃገር እንደ ሙሉ ሰው ለመቆጠርም አልፈልግም። ሙሉ ሰውነቴ ኢትዮጵያን የለቀቅኩ ቀን ቀርቷል። ቢያንስ ከውሾቻቸው፣ ለሶሪያና ለኤርትራውያን የሰጡትን ክብር ነበር የነፈጉኝ እሱን ከእግዚአብሔር ጋር በመጠኑ ከዓመታት በኋላ አግኝቻለሁ።
•••
አሁን እኔና ቤተሰቦቼ ካለመናገር ቀርቶብን የነበረው ደጃዝማችነታችን በመናገራችን ምክንያት ደጃዝማችነቱን አግኝተናል። የበላይ ዘለቀ፣ የአብዲሳ አጋ፣ የዘርዓይደረስ ልጅ መሆኔ ጠቀመኝ። የአሉላ አባ ነጋ፣ የእምዬ ምኒሊክ ልጅ መሆኔ በጀኝ። በስንት ዓመቴ ዘራፍ ብዬ በመፎከር ከጎዳና ሕይወት ጋር ፍቺ ፈጽመናል። ( ለሰሚ እኮ የማይታመን እኮ ነው። በጀርመን እንዲህ ይደረጋል ቢባል ማን ያምናል?) ከጀርመን የጎዳና ልጆችም ጋር በፍቅር ተለያይተናል። የልጆቼ ነገር ያስጨንቃቸው የነበሩት ጓደኞቼ ልጆቼ ከዚያ ጋርቤጅ በመውጣታቸው ከእኔ ይልቅ አበረውኝ የነበሩት ኅሙማን የጎዳና ጓደኞቼ ተደስተዋል። በፍቅርም ሸኝተውኛል። አሁንም የሚገባኝን ቦታ አግኝቻለሁ ብዬ ባልልም ቢያንስ ምግብ አብስለን የመብላት ዕድል አገኝተናል። ያለሰቀቀን ገላችንን ለመታጠብ፣ መጸዳጃ ቤት ለመጠቀም ታድለናል።
•••
“በዘመነ ሔኖክ አቆጣጠር” የእኔና የቤተሰቤ ፋሲካ ዛሬ ይጀምራል። የእናንተና የእህተ ሰይጣን እንኳን አልፏል። ደስብሎኛል ደስ ይበላችሁ። ሁላችሁንም አመሰግናለሁ። ለጀርመኗ መራሂተ መንግሥት አኔጌላ ሜርክል ሁላችሁም በኢሜይልና በፋክስ አቤት ስላላችሁልኝ አመሰግናችኋለሁ። ስለሚመሰገኑ ሰዎች በቀጣይ በዝርዝር የምመለስበት ሲሆን ለዛሬ ግን የማላልፋቸውን አመስግኜ ልለፍ።
ከቁጥር የማይገባው የመጀመሪያው ተመስጋኝ ፈጣሪዬና አምላኬ ልዑል እግዚአብሔር ነው። ተ መ ስ ገ ን ል ኝ ። የወልድ እናቱ አዛኝት አማላጂቱም ምስጋናዬ ይደርሳታል። ቅድስት ሆይ ለምኚልን።
• ከሰው ወገን ማመስገን እንጀምራለን። የእናንተ የጓደኞቼ እንዳለ ሆኖ ከዚህ በታች ያሉትን ግን በተለየ ሁናቴ አመሰግን ዘንድ ይፈቀድልኝ።
፩፥ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ
፪፥ ብፁዕ አቡነ ዲዮናሲዮስ በጅረምንና የምዕራብ አውሮጳ ሊቀጳጳስ
፫፥ ክቡር ልዑል አስፋወሰን አሥራተ ካሣ
፬፥ መቀመጫውን በሃገረ አሜሪካ ያደረገው የኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤት።
፬፥ የኢቫንጀሊካን ቄስና የበቦን ዩኒቨርሲቲው ጀርመናዊው ፕሮፌሰር ሄቨራልድና ባለቤታቸው ወሮ ሰላማዊትን አመስግኑልኝ።
~ የማልደብቃችሁ ነገር ግን የቅዱስ ፓትርያርኩን በዚህ ዘመቻ ውስጥ መሳተፍ የሌለ ደስታና ሐሴት ፈጥሮብኛል። ( ይፍቱኝ አባቴ ) ነገ ስህተት አይቼ እሪሪሪ ማለቴ ባይቀርም ባለፈ በደሌ ሳይከፉብኝ የአባቶችን ጥያቄ ሰምተው ስለ እኔ በመጮሃቸው ተደምሜያለሁ። በእውነት ከአእምሮዬ በላይ ነው የሆኑብኝ። ዝርዝሩን እመለስበታለሁ።
•••
ሙስሊም ወንድሞቼ፣ ፕሮቴስታንት ወንድሞቼ፣ በብዙ ነገር የሚበሳጩብኝ። በሐረርጌው ጠባዬ የሚከፉብኝ ሁሉ “ አንተ እንኳን አፈር ብላ፣ አፈር ያስበላህ ነገር ግን ልጆችህ መሰቃየታቸውን አልፈልግም እያሉ እየተነጫነጩም ቢሆን ከጎኔ ቆመው ለጀርመን መንግሥት ደብዳቤ ጽፈው ኮፒ ልከዋል። ( አውቀው እኮ ነው ሲፎግሩ እንጂ ከልባቸው ነው የሚወዱኝ። ስጠፋ ቅር የሚላቸው እነዚህ ሰደብከን ገለመሌ የሚሉት እኮ ናቸው። ኤት’አባታቸውንስና ) ጀመረህ በሉኝ አሏችሁ ደግሞ።
•••
የመጨረሻው ተመስጋኝ ማኅበርተኛዬ ወንድም ኢሳይያስ ነው። የወለደች አራስ ባለቤቱን ከሆሲፒታል አስቀምጦ ከሌላ ከተማ መኪና ተከራይቶ ዕቃዬን ተሸክሞ ከእንግልት አድኖኛል። ለምስጋናዬ ቃላት የለኝም።
•••
ዳይ አሁን ወደ ሥራ። ወደ መንፈሳዊው ፍልሚያ። ልጆቼ መተኛት ይፈልጋሉ። ከሀሺሽ ከጋንጃ መታጠን ተገላግለዋል። ትንሽ እረፍትም ይፈልጋሉ። እኔ ግን ወደ ሥራዬ እመለሰላሁ። ከማዘዣ ጣቢያዬ መንፈሳዊ ፍልሚያዬን እመራለሁ። ጭቅጭቅ ንዝንዙም፣ ልቅሶ እንባና ሳቁም፣ ኃዘንና ደስታውም፣ ክርክር ሙጉቱም ይቀጥላል።
•••
“ የትናንቱን ለነገ” ማኅበራችንም በቅርብ ቀን እውን ይሆናል። የፌስ ቡክ እስራቴም ጥቂት ቀን ቀርቶታል። የትም ይሁን የት፣ መቼም ይሁን መች አሸናፊዎቹ እኛው ነን።
•••
" እኔ ግን እላለሁ ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።
"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን !
"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት።+49 1521 5070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።
¶ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ሚያዝያ 30/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
ሞገስ መኮንን ተሾመ - Mogess Mekonnen Teshome
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሞገስ መኮንን ተሾመ - Mogess Mekonnen Teshome, Addis Ababa.
08/05/2020
ተግሣጽ ለኵሉ - 4 መናፍቃን የቀለዱበት ስምንተኛው ሺ! - በመምህር ዶር ዘበነ ለማ ተግሣጽ ለኵሉ - 4 መናፍቃን የቀለዱበት ስምንተኛው ሺ! - በመምህር ዶር ዘበነ ለማ
19/11/2017
Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Culinary Team
Attire
Contact the school
Website
Address
Addis Ababa