22/08/2026
በደ/ም/ኢትዮጵያ በሎተሪ ሽፋን የተፈፀመ ሌብነት።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ምትኩ ታመነ ከኢህአዴግ ሥርዐት ጀምሮ እስካሁኑ ብልፅግና መንግስት ድረስ በተለያዩ የኃለፊነት ቦታዎች ላይ የህዝብ አደራ ተሠጥቷቸው በሥልጣን ካባ የህዝብን ሀብት እየዘረፉ እንደቆዩ ታወቀባቸው።
ግለሠቡ የህዝብን እና የመንግስትን አደራ በታማኝነት መወጣት ስገባው ፤ ይህንን ታላቅ የህዝብ አደራ ወደ ጎን በመተው ከተሾመበት ጊዜ አንስቶ ሌብነቱ እንዳይታወቅበትና እንዳይደረስበት ህዝብንና መንግስትን በተለያዩ ፌክ አካውንት እያደናገረ ሳይነቃበት የህዝብ ሀብት በተለያዬ መንገድ ዘርፎ ስያከማች ቆይቷል።
ይህ ግለሠብ ምንም ከሌለበት በሥልጣን ዘመኑ ዘርፎ ያገኘውን ሀብት ማስቀመጫ ቦታ ቢያጣ በ16 ሚ/ን የኢትዮጵያ ብር #ካሶን የሚባል የጭነት መኪና ገዝቷል።
ገንዘብ ከየት አምጥቶ ገዛ ተብሎ በህዝቡ ዘንድ ጥያቄ እንዳያስነሳበት ወይንም የገንዘቡ ምንጭ ምን እንደሆነ እንዳይነቃበት የፈለገው ይህ ግለሠብ የለመደውን የማደናገሪያ ድራማ በማዘጋጀት በonline የመኪና ሎቶሪ ቆርጬ የካሶን መኪና ዕጣ በሎተሪ ደረሰኞል ብሎ የስርቆቱ ምስጥር እንዳይታወቅበት ከፍተኛ ጥረት በማደረግ ይህንን የመሠለ ምርጥ የመደበቂያ ትወናም ተውኗል።
ዳሩ ግን ከህዝብ የሚደበቅ ነገር የለምና ሎተሪ የተባለው ነገር ድራማ እንደሆነ እና መኪናው የተገዛው በተዘረፈው በመንግስትና በህዝብ ሀብት መሆኑ ተደርሶበታል።
በተጨማሪም ይህ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ አመራር የሆነው ግለሠብ በክልሉ ጤና ቢሮ አማካኝነት ከሚገነቡ ሆስፒታሎች ፣ ጤና ጣቢዎች እና ሌሎች ግንባታዎች ለይ ግንባታውን ከሚያከናወኑ ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር ዘርፎ ባገኘው ሀብት #በአዳማ እና #በቢሾፍቱ አከባቢ የገዛቸውን ዘመናዊ ቤቶችን በተመለከተ በቀጣይ ክፍላችን በዝርዝር የምናቀርበው ይሆናል።
ስለዚህ የክልሉ መንግስት ይህንን መረጃ ወስዶ ጉዳዩን በጥልቀት እንዲመረምርና ውጤቱን ለሀብቱ ባለበት ለሆነው ህዝብ እንዲያሳውቅ አደራ እንላለን።
Via : Inbox
ትኩስ መረጃዎችን ለማገኘት ሁሌም ከእኛ ጋር ይሁኑ !
ሌብነትን በጋራ ታግለን እናስቆማለን!