ለርን ሚዲያ -Learn media

ለርን ሚዲያ -Learn media

Share

መማሪያ ሚዲያ

Photos from ለርን ሚዲያ -Learn media's post 28/02/2024



በየካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም. በኢትዮጵያና ኢጣሊያ መካከል የተካሄደ ውጊያ ሲሆን የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል ነው። በ ኢትዮጵያ አሸናፊነት የጣልያን የቀኝ ግዛት ማስፋፋት ተኮላሸ።
የአድዋ ጦርነት

የአንደኛው የኢትዮጵያና ጣሊያን ጦርነት ክፍል

ቀን
የካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ.ም.
ቦታ
አድዋ፤ ኢትዮጵያ
ውጤት
የኢትዮጵያ ድል

ወገኖች

ኢትዮጵያ
ጣሊያን
የደረሰው ጉዳት

ኢትዮጵያ
የሞቱ፦
ከ፬ እስከ ፭ ሺህ
የቆሰሉ፦
፰ ሺህ

ጣሊያን
የሞቱ፦
፯ ሺህ
የቆሰሉ፦
፩ ሺህ ፭፻
የተያዙ፦
፫ ሺህ
ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ ' ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤
***
ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤
***
የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤
የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቡሻኽር (Julian calendar) የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም፤ ወይም በአውሮጳውያን የዘመን አቆጣጠር (Gregorian Calendar) February (የካቲት) መጨረሻ እና March (መጋቢት) መጀመሪያ ላይ 1896. ለጦርነቱ መነሻ የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ ከአምባሰል ተራራ ሥር ወሎ ውስጥ ንጉሥ ይስማ እየተባለ በሚጠራ ሥፍራ ነው፡፡
ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳ ተራራ)፤ ማርያም ሸዊቶ፤ አዲ ተቡን፤ ረቢ አርእየኒ (እግዚሃር አሳየኝ)… በመሠኘት የሚታወቁት እነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡ በመቶ ሺህ የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት 23 ቀን) እንዳማርያም ላይ ተሰባስቦ በአንድ እግሩ ቆሞ ቀኙን (ድሉን) ለሰጠው አምላክ ምሥጋና አቅርቧል፡፡ አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን ድንበርና ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን እንድናሸንፍ (ድል እንድናደርግ) ስለረዳኸን እናመሰግንሃለን ...
ሃያ ዘጠኝ ሺህ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ማሸነፉን አረጋግጧል ይለናል የታሪክ ተመራማሪው ጆርጅ በርክሌይ የአድዋ ጦርነትና ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ በተሰኘና ዳኘው ኃይለሥላሴ ወደ አማርኛ በተረጐሙት መጽሐፉ ላይ፡፡ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ፈረሱ ላይ ሆኖ የጋሻውን እምብርት መሬት ላይ እያጠቀሰ ጐራዴውን አየር ውስጥ እየቀዘፈ ባበደ መንፈስ (በተቆጣና በቆረጠ መንፈሥ) በጀግንነት ተዋግቷል፡፡
ጦርነቱ በተጀመረ ከአምስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሃምሣ ስድስቱም የኢጣሊያ መድፎች ሙሉ ለሙሉ ተማርከዋል፤ የቅኝ ገዢውን ወራሪ ሠራዊት ከመሩት ጀኔራሎች ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ የሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ከጥቂት አጃቢዎቹና በሽንፈት ከተበታተኑ የኢጣሊያ ወታደሮች ጋር ሸሽቷል፡፡
በዚህ ድብልቅልቅ ያለ ውጊያ ከሃምሣ ስድስቱ የኢጣሊያ መድፎች በተጨማሪ ብዙ ሺህ ቀላልና ከባድ መትረየሶች እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ጠመንጃዎች በአሥር ሺሆችና በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር ተማርከዋል፡፡ በአጠቃላይ ምርኮው ወደ አዲስ አበባ የተጓጓዘው በአምስት መቶ አጋሰሶች ተጭኖ ነው፡፡
በማግስቱ የካቲት 24 ቀን 1888 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ የኢጣሊያ ምርኮኞች በምኒሊክ ድንኳን ፊት ሲያልፉ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት እየፎከረ እየሸለለ አሳልፉዋቸዋል፡፡ ጄኔራል አልቤርቶኒ በምርኮኛነት ኢትዮጵያ ውስጥ ቆይቶ አገሩ ከተመለሰ በኋላ በፃፈው መጽሐፍ ላይ ከሚፎክሩት ጥቁር የነፃነት ተዋጊዎች መሃከል አንዱ እንደ እኛው ነጭ አውሮጳዊ ነው ብሎአል፡፡ ይህ ሰው ከፈረንሣይ አገር ወደ ኢትዮጵያ ለጦር መሣሪያ ጥገና የመጣ ካፒቴን ኦርዲናንስ ሲሆን፤ አሁን ጊዜው የጦርነት ስለሆነ ወደ አገርህ ተመለስ ቢባል ቢሠራ አሻፈረኝ ብሎ ከእኛ ጋር አድዋ ድረስ የዘመተ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ላይ ከተዋጋችባቸው የጦር መሣሪያዎች ሠማንያ ሺህ የሚሆኑት አሮጌ ጠመንጃዎች የተገዙት ከፈረንሳይ አገር በምሥጢር ነው፡፡ ጠመንጃዎቹን ገዝተው ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት በሥጋ በደምና በትውልድ አርመናዊ በነፍስና በመንፈስ በዜግነትና በልብ ፍቅር ኢትዮጵያዊ የሆኑት የኢትዮጵያ የልብ ወዳጅ ሰርኪስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡
አሁን በመዲናችን የሚገኘው የአርሾ ላቦራቶሪ ባለቤትና በዓለም ላይ ኢትዮጵያን የመሰለ ውብ አገር የለም ያሉኝ ዶክተር አርሻቪር ቴሪዝያን ኢትዮጵያ ውስጥ አርመናዊ ትውልድ ኖሮት ኢትዮጵያዊ ዜግነት የሌለው (ኢትዮጵያዊ ያልሆነ) አርመን ያለመኖሩን ያጫወቱኝ ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት ነው፡፡ የሠማንያ ሺህ ጠመንጃዎቹን አገዛዝ ሁናቴ የሚያውቁት ደግሞ ከአርሾ ቀደም የሚሉትና ከአሥራ ስድስት ዓመታት በፊት ለሪፖርተር ጋዜጣ ይሄንኑ በአንደበታቸው የገለፁት አቬዲስ ቴሪዝያን ናቸው፡፡ ሠርኪስ ቴሪዝያን ጠመንጃዎቹን ከገዙ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት በጅቡቲ በኩል ነፋስ ባህሩን ሲያነሳና እንደ ግድግዳ ሲያቆም በዚያ ተፈጥሮአዊ ክንውን በመጠቀም ደብቀውና ሸሽገው ነው፡፡
የአድዋ ድል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከበረው በሠባተኛ ዓመቱ በ1895 ዓ.ም (እ.ኤ.አ በ1903) ከአንድ መቶ ዘጠኝ ዓመታት በፊት አሁን ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ያለበት ሥፍራ ምኒሊክ አደባባይ ነው፡፡ በክብረ በዓሉ (በድል በዓሉ) ላይ ዲፕሎማቶችና የውጪ አገር መንግሥታት ተወካዮች አርበኞች የመንግስት ባለሥልጣኖች ብዙ ሺህ ፈረሰኞችና ሥፍር ቁጥር (ወፈ ሠማይ የሆኑ) ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ መገኘታቸውን፤ ከፈረሰኞቹ ብዛት የተነሳ ፀሐይ በአቧራ እስከመጋረድ መድረሷን ጳውሎስ ኞኞ የኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በተሰኘ መጽሐፉ ላይ ጽፎአል፡፡ እንዲሁም ተክለፃዲቅ መኩሪያን የመሳሰሉ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተመራማሪዎችና የውጪ አገር ዜግነት ያላቸው ፀሐፍትና ተመራማሪዎች በተለያዩ መፃሕፍቶቻቸው ይሄንን አሣምረው ጽፈውታል፡፡
ታላቁ የጥቁር ህዝቦች ድል (የአድዋ ድል) በመላው ዓለም ፖለቲካ ላይ ከፍተኛና ዋነኛ ለውጦች አምጥቶአል፡፡ የእንግሊዝ ጋዜጦች በአድዋ ድል ማግስት የዓለም ታሪክ ተገለበጠ ታላቅ የትውልድ ኃይል በአፍሪቃ ተቀሰቀሰ … ብለው ፃፉ፡፡ በኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ፡- ዘመናዊት ኢትዮጵያን የፈጠረ የተባሉት ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ በሌሉበት (እርሳቸው በአካል ባልተገኙበት የነፃነት ተጋድሎ መሪዎች ጉባኤ) የአፍሪቃና የመላው ዓለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ መሪ ተደርገው ተመረጡ፡፡
ጦርነቱ ከመደረጉ በፊት እ.ኤ.አ በ1880ዎቹ መጀመሪያ ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ላይ በተደረገው የአውሮጳ ቅኝ ገዢ (ኮሎኒያሊስት) መንግስታት ሥልጣናትና ልሂቃን የጦር ጄኔራሎችና ሊቃውንት ስብሰባ ላይ ጥቁር ትልቅ ትል ነው ቅንቡርስ ነው እንጂ ነፍስ ያለው ሰው አይደለም ብለው የነበሩ አፈሩ፤ እውነትና ፍትህ ኢትዮጵያና አፍሪቃ ከበሩ፡፡ ከሲግመንድ ፍሮይድ የሳይኮ አናላይሲስ ጥናትና ምርምር በፊት፡- ጥቁር ህዝብ ትልቅ ትል ላይሆን ነፍስ ያለው ሰው ከሰውም ሰው ጀግና መሆኑን በተጨባጭ ያስመሰከረ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ነው፡፡
ከፈረንጅ የአውሮጳ መንግሥታት ሩሲያና ፈረንሳይ የአድዋን ድል ከልብ ደገፉ፡፡ ጀኔራል ባራቴሪ በአገሩ በኢጣሊያ ጦር ፍርድ ቤት ቀርቦ ማዕረጉ ተገፈፈ፡፡ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲኞር ክሪስፒ በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቀቁ፡፡
የኢጣሊያዊው ንጉሥ አማኑኤል ኡምቤርቶ የልደት ቀን የሀዘን ቀን እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ሮማ (ሮም)ን ፍሎሬንስን ሚላኖ (ሚላን)ን ቬነስን…የመሳሰሉ የኢጣሊያ ከተሞች ምኒሊክ ለዘላለም ይኑር በሚሉ የተቆጡ አውሮጳውያን ትዕይንተ ህዝብ አድራጊዎች ተጥለቀለቁ፡፡ ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ወቅት በዋናው የጦር ግንባር ገጥማ በፍልሚያ ድል ማድረግ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በአራት መስክ ሠለጠነች በምትባለው አውሮጳዊት አገር ኢጣሊያ ላይ ድል ተቀዳጅታለች፡፡ ይኸውም፡- በጦርነት እና በወታደራዊ መረጃ (Military Security intellegence)፤ በዲፕሎማሲና በፖለቲካ ጥበብ ነው፡፡
በፖለቲካ ጥበብ በኢጣሊያ ቅኝ ገዢ ብልጣብልጥ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ድል የተቀዳጀችው ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ለጦርነቱ መጀመር መነሻ የሆነው የውጫሌ ውል በተደረገበት ሥፍራ ነው፡፡
የውጫሌ ውል አንቀጽ አሥራ ሰባት የጣሊያንኛው፡- ኢትዮጵያ ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት በኩል ማድረግ አለባት ሲል፤ አማርኛው ደግሞ ኢትዮጵያ ከአውሮጳ መንግሥታት ጋር ማድረግ የምትፈልገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግሥት በኩል ማድረግ ትችላለች ይላል፡፡
የአማርኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና ያከብራል፤ የጣሊያንኛው የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ልዕልና መድፈር ብቻ ሳይሆን ብሔራዊ ክብሯንና ጥቅሟን ይነካል፡፡ ይሄን የተገነዘቡት የኢትዮጵያ መሪዎች የውሉ አንቀጽ አሥራ ሰባት የጣሊያንኛ ትርጓሜ የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም በማይነካና ሉአላዊነቷን በሚያከብር መልኩ እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ወተወቱ፡፡ መወትወቱ ውጤት ሳያመጣ ቢቀር፤ ምኒሊክ፡- መዘግየት አደገኛ ነው ጣይቱ አሉ፤ ስለዚህ ጉዞ ወደ ወሳኙ ጦርነት (ማድረግ) የግድ ነበር፡፡
የኢትዮጵያን አገራዊ ክብርና ጥቅም ህልውናና ልዕልና ሲሆን ሲሆን በውድ ካልሆነ ደግሞ ሳይወድ በግድ ማስከበርና ማስጠበቅ የአንድ አገር መንግሥት ዋነኛ ግዴታና ኃላፊነት ነው፡፡
ስለዚህ አባቶቻችን (የጥንት ወላጆቻችን) ውትወታቸው አልሰማ ቢል ጦር እንግጠም አሉ፡፡
ይሄ የፖለቲካ ጥበብ ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡
በወታደራዊ መረጃ (Military Security intellegence) ብልጫ የኢንቲጮ ተወላጅ በሆኑት ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ኢትዮጵያ ሠለጠነ የተባለውን የአውሮጳ ኃይል አሸንፋ ጣሊያኖች ባልፈለጉት ቦታና ባልመረጡት ጊዜ ወደ ጦርነት እንዲገቡ አድርጋለች፡፡
በወታደራዊ ሣይንስ (Military Science) አገባብ ለጦርነት የተንቀሳቀሰ አንድ ሠራዊት ወዲያውኑ ወደ ጦር ግንባር መግባት አለበት፡- ይሄ አንድ ነጥብ ነው፡፡ ሌላው ነጥብ አንድ ለግዳጅ የተንቀሣቀሠ ሠራዊት ለመሰናዶም ሆነ ለመከላከል ውጊያ በአንድ የመከላከያ ወረዳ ከሠፈረ በዚያ መከላከያ ወረዳ ከስድስት ወራት በላይ መቆየት የለበትም፡፡ በአንድ ቦታ ላይ ከስድስት ወራት በላይ ከቆየ ሊደርስ የሚችል የወታደራዊ ሥነልቦና (Military Psychology) ጉዳት አለ፡፡ የመሸገበትን የመከላከያ ወረዳ እየተለመማመደ ሲሄድ ስለሚዘናጋና የውጊያ ስሜቱ እየቀነሰ (እየቀዘቀዘ) ስለሚመጣ ጉዳት አለው፡፡ ከሎጂስቲክ አኳያ የውጊያ ዝግጁነቱም አደጋ ላይ ስለሚወድቅ (በሌላ አነጋገር ስንቅ እየጨረሰ ስለሚሄድ) በነዚህ ምክንያቶች በአፋጣኝ ወደ ጦርነት መግባት ለሠራዊቱ ድል አድራጊነት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡
የኢትዮጵያ በሠላም ጊዜ ገበሬ በጦርነት ጊዜ ጀግና ተዋጊ እንጂ ዘመናዊ ወታደራዊ መሠረት ያለው Professional Army ባልነበራት በዚያ ዘመን ለአንድ መቶ ሃያ ሺህ ሠራዊት የሎጂስቲክ አገልግሎት እየሰጡ ለረጅም ጊዜ መቆየት አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ የጀግንነት ግለት ሳይበርድ የሎጂስቲክ (ስንቅ ትጥቅ መድሃኒት) አቅም ሳይዳከም በፍጥነት ጦር መግጠም እጅግ አስፈላጊ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሠራዊት ጦርነቱን ፈጥኖ ለመግጠም ጣሊያኖች ወደ አድዋ መምጣት አለባቸው፤ ወይም ደግሞ የእኛ ሠራዊት ጣሊያኖች ወደመሸጉበት የኤርትራ ከፍተኛ ቦታዎች መሄድ አለበት፡፡ ከነዚህ ሁለት ሁኔታዎች የአንደኛው መሆን የግድ ነበር፡፡ ወደ ጣሊያኖች መሄድ ከፖለቲካ ሁኔታዎች ባሻገር ከወታደራዊ ሳይንስ አንፃር የሚመረጥ አይደለም፡፡ በምሽግ ውስጥ ሆኖ የሚከላከል ሠራዊትና ከምሽግ ወጥቶ የሚያጠቃ ሠራዊት መስዋዕትነት የመክፈል ዕድሉ እኩል አይደለም፤ ለሚከላከል አንድ ወታደር ሶስት የሚያጠቃ ወታደር ነው የሚያስፈልገው፡፡
ስለዚህ ጣሊያኖች ወደ አድዋ እንዲመጡ ማድረግ የግድ ሆነና የአድዋ ድል ቁልፍ የምላቸው የአርባ ዓመቱ ጐልማሣ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት ተጠሩና ለአንድ ታላቅ አገራዊ ኃላፊነት እንዲሠናዱ ተደረገ፡፡ ይሄ ሁሉ በምሥጢር ነው የተከወነው፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት አውአሎም ለኢጣሊያ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎች ከሚሠልሉ የአገር ተወላጆች (ፌርማቶሪዎች) ጋር ወደ ባራቴሪ ተላኩ፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ስንቅ ማለቁና ተስቦ በሽታ በሠራዊቱ ውስጥ መግባቱ ፌርማቶሪዎች ባሉበት ተለፈፈ፡፡ አውአሎምና ፌርማቶሪዎቹ ወደ ኤርትራ ዘልቀው ለጄነራል ባራቴሪ ይሄንኑ ነገሩት፡፡
ባራቴሪ ጊዜው አሁን ነው አለና የካቲት 22 አመሻሽ ላይ በአውአሎም መሪነት ሠራዊቱን ይዞ ወደ አድዋ ተመመ፡፡ የካቲት 21 እንዳይነሣ ዝናብ ስለያዘው እንጂ ታላቁ ጦርነት የካቲት 22 ሊደረግ ይችል ነበር፡፡ ስለዚህ ጄነራል ባራቴሪ በዝናብ በመያዙ ምክንያት ዘመቻውን በማግሥቱ አደረገና የካቲት 22 ቀን 1888 ዓ.ም ሌሊቱን ሙሉ ሲጓዝ አድሮ ሊነጋ ሲል የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም አድዋ ጦር ግንባር ደረሠ፡፡ አውአሎም ከፊት ለፊታቸው የጀግናው የቱርክ ፓሻ የአፍሪቃ ጀኔራል አሉላ አባነጋ የገበሬ ሠራዊት ምሽግ እንደታያቸው መሮጥ ጀመሩ፡፡ ባራቴሪ፡- አውአሎም አውአሎም ብሎ ተጣራ፡፡ እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና ብለውት ዘለው አሉላ ምሽግ ውስጥ ገቡ፡፡ ዛሬ አንተን አያድርገኝ ማለታቸው ነው በአማርኛ፡- እስሀ ዝዋአልካዮ አያውለና፡፡
ከጥቂት ደቂቆች በኋላ ምድር ቁና የሆነችበት ድብልቅልቅ ያለው ጦርነት ተጀመረ፡፡ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ከጠዋቱ አራት ሠዓት ግድም ታላቁን የአድዋ ድል መቀዳጀቱን አረጋገጠ ፡፡ ብዙ ሺህ የኢጣሊያ ወታደሮች በጦር ሜዳ ተገደሉ፡፡ ብዙ ሺዎች ደግሞ ቁስለኛና ምርኮ ሆኑ፡፡ የተቀረውንና ድል ተመትቶ የተበታተነውን የኢጣሊያ ወታደር እያሣደደና እያባረረ አፍሪቃዊው ኃይል ፈጀው ብሎ ፅፎአል ጆርጅ በርክሌይ፡፡ ከሚሸሹት መሃከል አንዱ የአውሮጳዊው ወራሪ ሠራዊት ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ነው፡፡
ይሄ (በአውአሎም ብስለትና ሥልጡንነት መስዋዕትነትና ኢትዮጵያዊ ፍቅር የተገኘው) ሰለጠነ በሚባለው የአውሮጳ ኃይል ላይ አልሰለጠነም በሚባለው አፍሪቃዊ ኃይል የተጨበጠ ትልቅ የወታደራዊ መረጃ (Military Security intelligence) ብልጫ ወይም ድል ነው፡፡
በወታደራዊ ሣይንስ ደግሞ ወታደራዊ መረጃ ለወታደራዊ ግጃጅ አፈፃፀም ዋነኛና ወሣኝ ጠቀሜታ አለው፡፡ በዚህች ዓለም ላይ ከተደረጉ አብዛኞቹ ጦርነቶች ድል ያደረጉት የወታደራዊ መረጃ ብልጫ የነበራቸውና ፍትህና እውነትን ፖለቲካዊ መሠረት ያደረጉት ናቸው፡፡ እኛ ሁለቱንም ነበረን፤ ዓላማችን የአገራችንን ጥቅምና ክብር ህልውናና ልዕልና ማስከበር ነፃነታችንን ማስጠበቅ ሲሆን፡- ይህም የፍትህና የእውነት ነፍሥ ነው፡፡ በአገር ወዳዱ ባሻዬ አውአሎም ሀረጐት አማካይነት ደግሞ በአውሮጳ ላይ የወታደራዊ መረጃ ብልጫን ተቀዳጀን፡፡ ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን ታሪኳ ከውጪ ወራሪዎች ጋር ባደረገቻቸው ጦርነቶች ሁሉ፡- እውነትና ፍትህን መሠረት አድርጋለች፡፡
የዲፕሎማሲያዊ ድሉን የተቀዳጀችው ኢትዮጵያ፡- አውሮጳ ውስጥ ባስቀመጠቻቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ወላጅ አባት ራስ መኮንንና ግራዝማች ዮሴፍ በተሰኙ ዲፕሎማቶቿ አማካይነት ነው፡፡ ጣሊያኖች ኢትዮጵያውያን ያልሰለጠኑ በመሆናቸው በምርኮኞች ላይ ሠብአዊነት የጐደለው ድርጊት ይፈፅማሉ ብለው ያስወራሉ፡፡ ግራዝማች ዮሴፍ በተለያዩ ቋንቋዎች እየፃፈ ለአውሮጳ ጋዜጦች ይሄን ያስተባብላሉ፡፡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ደግሞ ኢትዮጵያ ልክ ዲፕሎማቶቿ እንዳሉት ምርኮኞችን ግብር አብልታ አካላቸዉም ምቾታቸውም ሳይጓደል ወደ አገራቸው ሰደደች፡፡
በዚህም ዲፕሎማሲያዊ ሥልጣኔዋን ለመላው አውሮጳ እና ለመላው ዓለም በተጨባጭ አሳየች፡፡ ከመቶ ዓመታት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ብቸኛ አፍሪቃዊት አገር፡- ኢትዮጵያ ነች፡፡ የአብዛኞቹ የአፍሪቃ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ረጅም ዕድሜ ከስድሣ ዓመት አይዘልም፡፡ ኢትዮጵያ፡- ከኢጣሊያና ከፈረንሣይ ከአሜሪካ (USA) እና ከእንግሊዝ ከሩሢያና ከጀርመን (ከስድስት አገራት) ጋር ከመቶ ዓመታት ለሚበልጥ ጊዜ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን አዳብራ እና አፅንታ ቆይታለች፡፡
በአድዋ ድል፡-
ዋነኛው ድል በጦር ግንባር ፍልሚያ የተገኘው ድል ነው፤ ታላቁ የአድዋ ድል፡፡
የአድዋ ጦርነት(የጥቁሮች የነፃነት ተምሳሌት) የተደረገው በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው፡፡ ከዚያ በፊት በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት የተደረገው የመቅደላ ጦርነትም በሁዳዴ ፆም ውስጥ ነው የተካሄደው፡፡ በአድዋ ጦርነት ፆምና ውጊያ አብሮ ስለማይሄድ ግብፃዊውን ጳጳስ ሠራዊቱን ይፍቱትና እንደ ልቡ ይዋጋ ቢባሉም ባለመፍታታቸው ከኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት ጿሚ የሆነው እየፆመ ለመዋጋት ተገዶአል፡፡ በመቅደላ ውጊያ ዓፄ ቴዎድሮስ [ካሣ ኃይሉ ወልደጊዮርጊስ (አባ ታጠቅ ካሣ) (መዩሣው ካሣ) (ወሬሣው ካሣ)] ሊወጋቸው ለመጣው እንግሊዛዊው ጄኔራል ናፒዬርና ሠራዊቱ ፆምህን ፈትተህ ከእኔ ጋር ውጊያ ግጠም ብለው አንድ ሺህ በጐች ልከውለታል፡፡
ከአድዋ ጦርነት በፊት ባሉት ጥቂት ወራትና ሣምንታት መቀሌና አምባላጌ ላይ የተደረጉ ጦርነቶች አሉ፡፡ የመቀሌን ከተማ በኢጣሊያዊው ኮሎኔል ጋሊያኖ ከሚመራው አውሮጳዊ ሠራዊት ለማስለቀቅ መስዋዕትነቱ የበዛ በመሆኑ፡- መቀሌ የተለቀቀችው በፈረንጆች ሚሊኒየም BBC (British Broadcasting Corporation) የሚሊኒየሙ ምርጥ ሠብዕና ብሎ ከአህጉር አፍሪቃ ባጫቸው ከጐንደር ቤተሠብ በሚወለዱት እቴጌ ጣይቱ ብጡል ሥልጡን ወታደራዊ መላ ነው፡፡
ዝርዝሩን እዚህ አላወሣውም እንጂ መቀሌ በጣይቱ ልዩ ወታደራዊ ብቃት መያዝዋን መግለፅ ይጠቅማል፡፡ በኋላ ላይ ኮሎኔል ጋሊያኖ በአድዋ ጦርነት ተማርኮ፡- የምንሊክን ፊት ከማይ ግደሉኝ ብሎአል፡፡ በአምባላጌው ጦርነት ሊቀ መኳስ አባተ መድፍ ተኩሠው በጣሊያን መድፍ አፍ ውስጥ እስከ መክተት የዘለቀ አነጣጣሪነታቸውን አሣይተዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ሥልጣናት፡- ማዕከል ወሎ ውጫሌ በነበረበት ሁናቴ፤ ዳግማዊ ዓፄ ምኒሊክ (አባ ዳኘው) ለህዝባቸው የክተት ጥሪ ካደረጉ በኋላ ከዳር እስከ ዳር የተንቀሣቀሠው የተቆጣ ኢትዮጵያዊ ሠራዊት ሢተም፤ ሲገባኝ ከሠሜን ኢትዮጵያ ከጐንደር ከጐጃም ከወሎና ከትግራይ … የተንቀሳቀሰው አትንኩኝ ያለ ኢትዮጵያዊ ጀግና ከሚተምመው ሠራዊት የተገናኘው በትውልድ አቅራቢያው ሆኖ ነው፡፡
መጓጓዣ በሌለበት ዘመን የሠሜኑን የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት ወደ ሰሜን ለማዝመት ሲባል በመሀል አገር ማሰባሰብ የሚያስፈልግበት ሁኔታ አልነበረም፡፡[1]
(ይህ ታሪክ ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው።

28/02/2024



የኢትዮጵያ ጸሐፊ እና ፖለቲከኛ (1910-2003)

ደራሲ ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (ሃዲስ ኣለማየሁ) ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በደብረ ማርቆስ አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በጥቅምት ፯ ቀን 1902 ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ፲፱፻፲፰ ዓ.ም. አዲስ አበባ በመሄድ በስዊድን ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ጊዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት ጣሊያን ወረራ ተከሰተ።

የኢጣልያ ወረራ ሲከሰት ከልዑል ራስ ዕምሩ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር በምዕራብ ኢትዮጵያ በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ ዕምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመታት በፖንዞ ደሴትና በሊፓሪ ደሴት ታስረው ቆይተዋል።

ከዚያም የተባባሪ ኃያላት ወታደሮች በ1935 ዓ.ም. ሲያስመልጧቸው በተመለሱበት ጊዜ በትምህርታቸው እንደገና በኦክስፎርድ ከገፉ በኋላ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት በተለይም በትምህርት ሚኒስቴር ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል።

•1936 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኛ
•1937-1938 - የኢትዮጵያ ቆንሱል በኢየሩሳሌም
•1938 - በ International Telecommunications Conference አትላንቲክ ከተማ፣ ኒው ጄርዚ ወኪል
•1938-1942 - በተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኒው ዮርክ ሠራተኛ
•1942-1948 - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳይረክተርና ምክትል
•1948-1952 - የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሰደር
•1952 - የትምህርት ሚኒስትር
•1952-1957 - የኢትዮጵያ አምባሰደር ወደ እንግሊዝና ሆላንድ
•1957-1958 - የልማት ሚኒስትር
•1960-1966 - ሴናቶር
ሀዲስ ዓለማየሁ በርካታ የስነጽሑፍ ሥራዋችን አበርክተዋል። ከነዚህም ውስጥ ታላቅ አድናቆትንና እውቅናን ያተረፈው ሥራቸው ፍቅር እስከ መቃብር (1958) በሁለት የተለያዩ መደቦች ውስጥ የሚገኙ የሁለት ሰዎች የፍቅር ታሪክ ላይ ሲያተኩር፤ በጊዜው የነበረውን ወግና ልማድ ይገልጻል። እንዲሁም በ1970 ወንጀለኛው ዳኛ በ 1980 ደግሞ ስለ ማህበራዊ ጉዳዮችና ስለ ጣሊያን ውርስ የሚዳስሰውን የልም እዣት የተሰኙትን ልብ ወለድ ታሪኮች ለንባብ አቅርባዋል።

ከዚህ ባሻገር:

የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ - ተውኔት
ተረት ተረት የመሰረት
ትዝታ
የተሰኙት ጽሁፎችና የሌሎች በርካታ ሥራዎች ባለቤት ናቸው።

ሀዲስ ዓለማየሁ በኢትዮጵያ የስነ ጽሑፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በማበርከታቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዶክቶርነት ማዕረግ ተሰጥቷቸዋል። ደራሲው በኅዳር 26 ቀን 1996 ዓ.ም. በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ሃዲስ በዝነኛው መጽሓፋቸው ያስተዋወቁትን የሞክሼ ፊደላት ቅነሳ ከተቃወሙት ኣንዱ ዶ/ር ኣበራ ሞላ ናቸው።

28/02/2024


(መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፴፫ እስከ ፳፻፩ ዓ.ም.) ዝነኛ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ጀግና ነበር ።

ጥላሁን ገሠሠ
መረጃ
የትውልድ ስም

ጥላሁን ገሠሠ ንጉሤ

የተወለዱት

መስከረም 19 ቀን 1933 ዓ.ም.

የሞቱት

ሚያዝያ 11 ቀን 2001 ዓ.ም.
የሥራ ዘመን
ከ1948 - 2001 ዓ.ም.

ቀደምት የሕይወት ታሪክ

ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ጉሩሙ እና ከአባቱ ከአቶ ገሠሠ ንጉሤ በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ጠመንጃ ያዢ እየተባለ ከሚጠራው ሰፈር የመስቀል ዕለት ተወለደ። እድሜው - 14 ዓመት እንደሆነ ከአያቱ ጋር እንዲኖር ወደ ወሊሶ ተወሰደ በዚያም በራስ ጎበና በሚባለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት ጀመረ። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ከፍተኛ የሆነ የሙዚቃ ፍቅር እይሳየ ሄደ ። አያቱ ግን ትኩረቱን በሙሉ በትምህርቱ ላይ እንዲያደርግ ይመክሩት ነበር። የራስ ጎበና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተዳዳሪ የነበሩት ሱዳናዊው አቶ ሼዳድ የጥላሁንን የሙዚቃ ፍቅር በማየት ወደ ሱዳን እንዲሄድና በዚያም ሙዚቃ እንዲያጠና ይመክሩት ነበር። ጥላሁን ወደ ሱዳን ባይሄድም ምክራቸውን ግን ትልቅ ቦታ ስጥቶት ነበር። ከ[19[ሀገር ፍቅር ቲያትር]] ወ/ሮ ንጋትዋ ከልካይ እና አቶ ኢዮኤል ዮሃንስ ሌሎችም የሃገር ፍቅር ተዋንያን በትምህርት ቤታቸው ትርኢት ሊያሳዩ በመጡ ጊዜ ይህን እድል በመጠቀም ጥላሁን ለሙዚቃ ያለውን ፍቅር ከአቶ ኢዮኤል ጋር ባደረገው ውይይት በሙዚቃ መግፋት ከፈለገ ወደ አዲስ አበባ መሄድ እንዳለበት መከሩት። ጥላሁን ትምህርቱን አቋርጦ ጉዞውን ወደ አዲስ አበባ አቀና። ኩብለላውን በእግር የጀመረው ለአያቱ ሳይነግር ስለነበር ከቤት ሲጠፋ አያቱ ለአጎቱ ሁኔታውን በመንገር ጥላሁንን ይጠብቁ ጀመር። ጥላሁንም የአሥራ አምስት ኪ/ሜ መንገዱን ጨርሶ ቱሉ ቦሎ ደረሰ ከዚያም ከአክስቱ ከወ/ሮ ተመኔ ባንቱ ቤት አድሮ ወደመጣበት ወደ ወሊሶ አያቱ ዘንድ ተይዞ ተመለሰ ። በሙዚቃ ፍቅር በጣም የተቃጠለው ጥላሁን አያቱ ቤት አንድ ቀን ብቻ በማደር ጉዞውን እንደገና ወደ አዲስ አበባ አቀና በዚህ ጊዜ ግን በጭነት መኪና ላይ በመንጠልጠል ነበር። ጥላሁን አዲስ አበባ እንደገባ በሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ተቀጠረ። በዚያም ጥቂት አመታት ከሰራ በኋላ ወደ ክብር ዘበኛ ባንድ በመቀላቀል ታዋቂና ዝነኛ ለመሆን በቃ። ሆኖም በ ፲፱፻፶፫ ዓ/ም "የታሕሣስ ግርግር"ትልቅ ችግር ውስጥ ወድቆ ነበር ። ለጥቂት ጊዜም ታስሮ ተፈትቷል። ከዚያም ወደ ቀድሞው ሀገር ፍቅር በመመለስ ተወዳጅና ታዋቂ ለመሆን በቅቷል። ግርማዊ ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴ ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤትን በጎበኙበት ጊዜ ሦስት ጊዜ ወጥቶ ዘፍኗል ንጉሠ ነገሥቱም "ጥሩ ድምጽ አለህ፣ እንዳታበላሸው" የሚል አስተያየትም እንደሰጡት ይነገራል ። የጥላሁን ብዙዎቹ ስራዎቹ የአማርኛ ዘፈኖች ሲሆኑ የተወሰኑ ዘፈኖችን ደግሞ በኦሮምኛ እና በሱዳንኛ ዘፍኗል። ጥላሁን ለኢትዮጲያ ሙዚቃ ላደረገው አስተዋጽኦ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ለማግኘት በቅቷል ሌላም ህይወቱን በሙሉ ለሙዚቃ በማበርከቱ ከኢትዮጵያ ኪነጥበብና የብዙህን መገናኛ ሽልማት ድርጅት «የሙሉ ዘመን» ሽልማት ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። ክብር ለዶክተር ጥላሁን ገሰሰ

ህልፈት

ጥላሁን ባደረበት የስኳር በሽታ የትንሳዔ ዕለት ሚያዝያ ፲፩ ቀን፣ ፳፻፩ ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ሥርዓተ ቀብሩም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

ጥላሁን ገሠሠ በ ዋሽንግተን ዲሲ እግር ኳስ ውድድር ላይ

(2008 እ.ኤ.አ.)
"ትንፋሼ ተቀርጾ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይህ ነው የሞትኩኝ ለት የኔ ማስታወሻ
ውበቷን ሳሞግስ የለምለም ሃገሬን
ማንም አይዘነጋም በጩሀት መኖሬን
ዜማ እንጉርጉሬም የግሌ ቅላጼ
ተቀርጾ ይቀመጥ ታሪኬ ነው ድምጼ
ያስቀየምኩት ቢኖር የጠላኝ በቁሜ
ድምጼን ሰምቶ ያዝናል ለረገፈው አጽሜ
እኔን ለበደሉኝ ሰርዣለሁ ቂሜን
በኔም የከፋችሁ ይቅር በሉት አጽሜን"

28/02/2024

" " #ተባለ?

ቴዲ አፍሮ የ፲፪ (12)ኛ ክፍል ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ሰፊ ጊዜ ሥለነበረው ከመቸውም በተለየ ሁኔታ በዚያን ጊዜ ነበር በእግር በፈረስ ሥለ ሙዚቃ መጋለብ እና መሮጥ የጀመረው። ፲፱፻፺፩ (1991) አመተ ምህረት አካባቢ ከ ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ ባለሙያዎች ላስታስ የተባለ የሙዚቃ ባንድ አቋቁመው ነበር:: በዚያን ጊዜ ቴዲ የራሱ የሆነ ባንድ እንዲኖረው ይፈልግ ሥለነበር ከሙያ ጉዋደኞቹ ጋር መመሆን በወቅቱ የነበሩትን ጥሩ ጥሩ የሙዚቃ መሳሪያዎች በመግዛት ላስታስ ከተባለው የሙዚቃ ባንድ ጋር አብሮ ለመሠራት ያላቸዉን ፍላጎት ለባንዱ አባላት ይገልፃሉ:: የባንዱ አባላትም በደስታ ይቀበሉዋቸዋል:: ብዙም ሳይቆዩ የባንዱ ስያሜ ከላስታስ ወደ አፍሮ ሳዉንድ ቀየሩት::

ባንዱንም በበላይነት በመቆጣጠር እና በመምራት ቴዲ ትልቅ ድርሻና ሃላፊነት ነበረው:: መሳሪያ ተጫዋቾቹ እንደሚሉት ከሆነ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣ ሽዋንዳኝ ሃይሉ እና ግሩም መዝሙር የአፍሮ ሳውንድ ባለቤቶች ተብለው የሚጠቀሱ ሲሆን "ቴዲ ግን እንደ ባንዱ ባለቤት ብቻ ሣይሆን እንደ ቅርብ ጏደኛችን ነበር የምናየው" ይሉታል። እንግዲህ በዚሕ ጊዜ ነበር ቴዎድሮስ ካሣሁን የሚለው ስሙ በቴዲ አፍሮ ተተክቶ ዋነኛ መጠሪያ ስሙ ለመሆን የበቃው።

28/02/2024

#ሳይንስ

ከተጨባጩ ዓለም በሥርዓት መረጃ የሚሰበስብ፤ ከተሰበሰበው መረጃ ተነስቶ ዕውቀት የሚገነባ እና በተመክሮ ቢፈተኑ ጸንተው ሊቆሙ የሚችሉ ትንቢቶችንና ማብራሪያዎችን የሚያስገኝ የዕውቀት ዓይነት ነው።

በፍልስፍና አስገዳጅ ዕውነት (የአምክንዮ ዕውነት) እና አጋጣሚ ዕውነት (ሓቅ) የተባሉ ሁለት ዓይነት ዕውነቶች አሉ። የሳይንስ ዕውቀቶች በአጋጣሚ ዕውነቶች (ሓቆች)ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ይህም ሲባል ለሓቆች እንዲህ ሆኖ መገኘትና፣ እንደዚያ ሆኖ አለመገኘት አስገዳጅ አመክንዮ የለም። ለምሳሌ መሬት በላይዋ ላይ ያለን ማንኛውንም ቁስ ትስባለች፣ ይህ ግን ያለንበት ዓለም ዕውነታ ነው እንጂ መሬት ማንንም ባትስብ ምንም የአመክንዮ መጣረስ አይኖርም። በሌላ አነጋገር፣ አንድ ሰው ከ ጥሩ መሪ ሃሳቦች ተነስቶ፣ በጥሩ አመክንዮ፣ «የመሬት ስበት የለም» እሚል ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል። ድምዳሜው ስህተት መሆኑን በምንም ዓይነት በአመክንዮ ብቻ ማዎቅ አይቻልም ምክንያቱም የአመክንዮ መጣረስ ስለማይፈጥር። በአጠቃላይ መልኩ፣ ሓቆች በአዕምሮ ፍልስፍና ብቻ ሊደረስባቸው አይቻልም።

ሳይንስ በአመክንዮ ብቻ ሳይሆን በተጨባጩ አለም ውስጥ በመሞከር፣ ከተሞክሮውም ዕውነትና ውሸቱ እየጠራና እየተመዘገበ በሂደት እየተሻሻለ የሚሄድ የዕውቀት አይነት ነው። የመሬትን ስበት ሓቅነት ለመገንዘብ እሚፈልግ በማሰብ ብቻ ሳይሆን ዘሎ መሬትን ለማምለጥ በመሞከር ሊያውቅ ይችላል። ለዚህና ለመሳሰሉት ስራዎች፣ ዘመናዊው ሳይንስ የሳይንሳዊ ዘዴን ይጠቀማል።

ዘመናዊው ሳይንስ ፣ ሰፊ ዕውቀትን በመሰብሰብ ብቻ ሳይሆን ይህን ዕውቀት በሥራ ላይ በማዋል ያለተወዳዳሪ የሰውን ልጅ ህይወት በማሻሻል ላይ ይገኛል። በሽተኞች መታከማቸው፣ የእርሻ ምርት መትረፍረፍ፣ የመገናኛ ብዙሃን መፈጠርና ማደግ፣ ወዘተ...እነዚህ ሁሉ የዚህን ዕውቅት ሥኬት የሚያሳዩ ናቸው።

28/02/2024



ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።

ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል።

03/06/2022

Esk

09/05/2020

la tewseta

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Telephone

Website

Address


Addis Abeba
Addis Ababa