24/06/2022
በምዕራብ ወለጋ ከተፈፀመው ጭፍጨፋ ጋር የተያያዙ አዳዲስ መረጃዎች ይፋ ተደረጉ
ሰኔ 17/2014 ዓ.ም
ንሥር ብሮድካስት
የአማራ ማህበር በአሜሪካ ባለፈው ቅዳሜ በምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የደረሰውን ጥቃት አስመልክቶ አዳዲስ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረት አንዳንድ ተቋማት በጥቃቱ የተገደሉት በሺህ የሚቆጠሩ መሆናቸውን መግለፃቸው እንዳለ ሆኖ እስካሁን ድረስ 503 ሰዎች መገደላቸውን እንዳረጋገጠና ከእነዚህ ውስጥ የ282 ሟቾች ስም ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ይህ ጥቃት በእለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2 ሰአት አንስቶ እስከ ቀትር 11 ሰአት የቆየና 9 ሰአታትን የፈጀ እንደነበርም አስረድቷል፡፡
ሰዎችን ለመግደል ከባድ መሳሪያና ስለት ጭምር ጥቅም ላይ መዋሉን ከእማኞች ለመረዳት መቻሉን ያስታወቀው የማህበሩ መግለጫ ታጣቂዎቹ በመጀመሪያ በጦር መሳሪያ ጥቃቱን ከፈፀሙ በኋላ በመሳሪያው ህይወታቸው ያላለፈውን እየመረጡ በስለት ወግተው እንደገደሏቸውም አብራርቷል፡፡
‹‹እማኞች እንደተናገሩት በጥቃቱ ኢላማ የተደረጉት አማራዎች ሲሆኑ የሞቱት በሙሉም አማራዎች ናቸው›› ያለው መግለጫው በገና በተባለው ሰፈር ዘጠና ሁለት አስከሬኖች የተለቀሙ ቢሆንም በፀጥታ ስጋት አሁንም መሬት ላይ አስከሬኖች ወድቀው እንደሚገኙና የሟቾቹ ቁጥር እንደሚያሻቅብ መግለፃቸውን አስታውቋል፡፡
በቀበሌው አንድ መስኪድ ውስጥ 48 ሰዎች እንደተገደሉና በአካባቢው ደግሞ ሌሎች 15 አስከሬኖች በመገኘታቸው 63 ሰዎች በአንድ ላይ የተቀበሩበት ቦታ እንዳለም እማኞቹ መናገራቸውን አስረድቷል፡፡
በቀበሌው በሚገኙ ጫካዎች ውስጥ በተለያየ ቦታ በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች እንዳሉ የጠቀሰው መግለጫው እስካሁን በተረጋገጠው መሰረት ግድያው የተፈፀመባቸውን ሰፈሮች ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረት
በሲልሳው ሰፈር 143
በጨርቆሳ 104
በበገኔ 92
በሀያው 50
በጉቲን ሰፈር 39
በሴኒ 21
በካራቆሬ 35
በኦሮሞ ሸዋ 14
በቶሌ 5 እንዲሁም በአሶሳ ሰፈር የተገደሉት ቁጥር እስካሁን እንዳልተቆጠረ ገልጿል፡፡
በሲላው ሰፈር በሚገኘው ጃፋር መስኪድ ውስጥ ከተገደሉት 48 ሰዎች መካከል አብዛኛዎቹ ሴቶች መሆናቸውንና ታጣቂዎቹ ከገደሏቸው በኋላ አስከሬናቸውን የማቃጠል ሙከራ አድርገው እንደነበርም ጠቅሷል፡፡
ከተገደሉት ውስጥ እድሜያቸው የገፋ አዛውንቶችና በጣም ህፃናት እንደሚገኙበት የገለፀው የአማራ ማህበር በአሜሪካ ከእነዚህ መካከል በጨርቆሴ ሰፈር ነዋሪ የሆኑት የመቶ አመት አዛውንቱ አባ ሀጂ ሁሴንና የአንድ ወር ጨቅላ የሆነው አብዱ ጀማል እንደሚገኝበት አመልክቷል፡፡
በጨፌ ሰፈር ደግሞ 60 ሴቶችና ህፃናት ብቻ መደገላቸውን አስረድቷል፡፡ አንዳንዶቹ ግድያዎች መላ ቤተሰብ ላይ የተፈፀሙ መሆናቸውን ያስረዳው መግለጫው ከእነዚህ መካከል አህመድ ዩሱፍ የተባሉት የልጅ ልጆቻቸውን ጨምሮ 31 ዘመዶቻቸው እንደተገደሉ አስታውቋል፡፡
ሼክ መሀመድ አሊ በጥቃቱ ወቅት አንድ ጫካ ውስጥ ተደብቀው ህይወታቸውን ቢያተርፉም 8 ቤተሰቦቻቸው እንደተገደሉባቸውም አመልክቷል፡፡
ማህበሩ በጥቃቱ ከተገደሉ ሰዎች መካከል የተወሰኑ የፎቶ ግራፍ ማስረጃዎችን ያካተተ ሲሆን ማንነታቸው የታወቁትን 282 ሟቾች ስም ዝርዝርም በመግለጫው አስቀምጧል።
24/06/2022
ኢትዮጵያ በ2022 ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ከተመዘገበባቸው የአፍሪካ ቀዳሚ ሦስት አገራት መካከል ተካተተች
ሰኔ 17፣ 2014 ዓ.ም
ንሥር ብሮድካስት
የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጨምሩባት ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022 ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ከተመዘገበባቸው የአፍሪካ ቀዳሚ ሦስት አገራት መካከል ተካታለች፡፡
አፍሪካን ቢዝነስ ኢንሳይደር ይዞት የወጣው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ከተመዘገበባቸው የአፍሪካ አገራት መካከል በሦስተኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡
እንደ መረጃው በአህጉሩ ከፍተኛውን የዋጋ ግሽበት ያስመዘገበችው፤ ያለፉትን ዓመታት ፖለቲካዊ መረጋጋት የራቃት የኢትዮጵያ ጎረቤት ሱዳን ሆናለች፡፡ በሱዳን የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 245.1 በመቶ ሲሆን፣ በደቡባዊ ምሥራቅ የአፍሪካ ክፍል የምትገኘው ዚምባቡዌ 86.7 በመቶ የዋጋ ግሽበት ተመዝግቦባት ሁለተኛዋ አገር ሆናለች፡፡ በኢትዮጵያ የተመዘገበው የዋጋ ግሽበት 34.5 በመቶ ሆኗል፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኛ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ምክር ቤት በአገሪቱ በምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛው የዋጋ ግሽበት እየተመዘገበ መሆኑን ባለፈው ወር ገልጧል፡፡
ምክር ቤቱ የዘጠኝ ወራት የምጣኔ ሀብት አፈጻጸምን ገምግሞ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፤ የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብት ከፍተኛ ፈተና እየገጠመው ያለው ከዋጋ ግሽበት አንጻር መሆኑን ጠቁሞ ነበር፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ከሳምንታት በፊት ይፋ ባደረገው የጥናት ውጤት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አላቸው ከሚባሉ ዐሥር የዓለም አገራት ዘጠነኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አመልክቷል፡፡
ማኅበሩ በኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት፣ በዋጋ ግሽበት እና ችግሮች ዙሪያ ለስድስት ወራት ያደረገውን ጥናት በወቅቱ ይፋ ሲያደርግ የዋጋ ግሽበት የኢትዮጵያ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል ብሏል። የተፈጠረው የኑሮ ውድነት የኅብረተሰቡን ኅልውና እየተፈታተነ ይገኛል ሲልም አክሎ ነበር፡፡
በዓለም ገንዘብ ድርጅት መረጃ ከሱዳን፣ ዙምባቡዌ እና ኢትዮጵያ ውጪ ከአፍሪካ አንጎላ፣ ሴራሊዮን፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ እንዲሁም ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ እስከ አስረኛ ደረጃ ተቀምጠዋል።
12/12/2021
“ዘመን ባስ” ወደ ቀያቸው መመለስ ለሚፈልጉ ተፈናቃይ ወገኖች ለ10 ቀናት የሚቆይ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።
“ዘመን ባስ” ከሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ እና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ለ10 ቀናት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
በዛሬው እለትም ከሁለት አውቶብስ በላይ ተፈናቃዮች ተመዝግበው ነገ ጠዋት ጉዞ እንደሚጀምሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
ለአካል ጉዳተኞች፣ ለአቅመ ደካሞች፣ ለእናቶች እና ለህፃናት ቅድሚያ እንደሚሰጥ የገለፀው መረጃዉ መታወቂያ የያዘ ግለሰብ ከጠዋቱ 3 ሰአት ጀምሮ ላምበረት በሚገኘው መናህሪያ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል ታውቋል።
አገልግሎቱን ለማግኘት በ“ዘመን ባስ” የትኬት መቁረጫ ቢሮዎች ሜክሲኮ፣ መስቀል አደባባይ እና እዛው ላምበረት መናህሪያ በሚገኙ ቢሮዎች መመዝገብ እንደሚቻልም ተገልጿል።
25/11/2021
this is ethiopia
ኑ አላቸው ገፉት
ሊስም ቢያጎነብስ አምርረው ነከሱት!!
"አብይን በመሳም አሳልፈህ ትሰጠዋለህን??" ከበሻሻ እስከ መናገሻ ያለውን ጉዞ ካላወክ ልትጥለው ትታገላለህ! በመጨረሻ ግን እራስህ ትዘረራለህ! ሳይነካህ ፣ ሳይዝትብህ ትፈጠፈጣለህ!!
#ሰውየው
#ኢትዮጵያ
#ድል
#አሸናፊነት
Via ሰውየው ገፅ
16/08/2021
ኢትዮጵያዬ ትንሳኤሽን ቅርብ ያድርግልን!!!
06/08/2021
https://www.facebook.com/379128275967485/posts/951975688682738/?app=fbl
🔰በ5ሺ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘው ዩጋንዳዊው ቼፕቴጌ ሰለ ኢትዮጵያ ይናገራል . . . .
" እንደ አገር ፌዴሬሽናችሁ ለአትሌቶቹ ነፃነት እና ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል ። ፌዴሬሽኑ ያለው አትሌቶች ስላሉ ነው ። አትሌቶቹን በፈለጉት መንገድ ሊያግዛቸው ይገባል ። የሙክታር እድሪስ አለመኖር በጣም ገርሞኛል ። ሙክታር የ5 ሺ ሜትር ምርጥ አትሌት ነው ። ዶሀ ላይ ባለድል የነበረ አትሌት ነው ። እሱና ሰለሞን ባረጋ ቢኖሩ ምን አልባት ወርቁን ላጣው እችል ነበር ። ሁለቱንም በደምብ አውቃቸዋለሁ ብዙ ጊዜ አብረን ሮጠናል ። የሙክታር አለመወዳደር ከምላችሁ በላይ ጎድቷችኋል ። "via girmachew enyew
ማድረጋችሁን አትርሱ