Amen Electrical Technology

Amen Electrical Technology የአጭር ጊዜ የክህሎት ማሰልጠኛ ማዕከል/ Vocational and Technical Training Center
(1)

✅ ===↪️ዛሬም አንድ የቅጥር ደብዳቤ ለድርጅታችን ደርሶታል። ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ከዚህ በፊት ከተቋማችን          ከዚህ በታች ባለው  ሊንክ ሙሉ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና CV እን...
24/08/2026


===

↪️ዛሬም አንድ የቅጥር ደብዳቤ ለድርጅታችን ደርሶታል። ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ከዚህ በፊት ከተቋማችን
ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ሙሉ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና CV እንድትልኩልን እናሳስባለን ፡፡

↪️የተፈለገው ባለሙያ ብዛት

✅ 8 ባለሙያዎች❗️
✅ የስራ ቦታ አ.አ

❗️የሌሎችን እድል እያበላሻችሁ ነው❗️
👇👇👇👇
https://t.me/electricexpert

👉ድርጅታችን ለዚህ ማስታወቂያ ምንም አይነት ክፍያ አልተቀበለም❗️አይቀበልም❗️

👉ማሳሰቢያ መጀመሪያ አይተው ማስረጃ( ሲቪ) ለሚልኩልን 8 ባለሙያዎች ቅድሚያ የምንሰጥ ይሆናል❗️

ለሌሎችም #ሼር በማድረግ ውለታ ይዋሉላቸው❗️
👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
👉በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ❗️
ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️
Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL


fans

✅ በኤሌክትሪክ ጥገና ወቅት በብዛት ስለሚሰራ እና እጅግ አደገኛ ስለሆነ(ቤት እስከማቃጠል የሚደርስ) አንድ ስህተት እንመልከት❗️✂️===👉አንድ መደበኛ የቤት ሶኬት፣ የምጣድ ወይም የስቶቭ ሶ...
24/08/2026

✅ በኤሌክትሪክ ጥገና ወቅት በብዛት ስለሚሰራ እና እጅግ አደገኛ ስለሆነ(ቤት እስከማቃጠል የሚደርስ) አንድ ስህተት እንመልከት❗️✂️
===
👉አንድ መደበኛ የቤት ሶኬት፣ የምጣድ ወይም የስቶቭ ሶኬት ተበላሽቶ "ቀይርልኝ" ስትባል... ተረጋግተህ ብሎኑን በስርአት ከመፍታት ይልቅ፣ ጊዜ ለመቆጠብ በማሰብ ፕላየር(ፒንሳ) አውጥተህ ገመዱን ከስሩ የምትቆርጥ ባለሙያ አለህ። አስቡት አንድ ቤት በዓመታት ውስጥ ብዙ ጊዜ ሶኬት ሊቀየር ይችላል በዚህ ሁሉ ጊዜ ከተቆረጠ የኤሌክትሪክ ገመዱ በጣም ያጥራል። በዚህ ጊዜ የሚያስከትላቸው ችግሮች ከታች ተጠቅሰዋል።
👉 ...
✂️ እንዲህ አይነት ባለሙያ ቤትዎ መጥቶ ሶኬት ሲቀይር፣ አንድ ትልቅ መቀስ ይዛችሁ ከኋላው ቁሙ። ተረጋግቶ ብሎኑን ከመፍታት ይልቅ፣ ስራ ለማቅለል ብሎ የኤሌክትሪክ ገመዱን በፕላየር(በፒንሳ) ከቆረጠው... እናንተም አታንገራግሩ፣ በመቀስ እንትኑን ቁረጡለት❗️ 🤣✂️ (ለቀልድ ያህል ነው... ግን ድርጊቱ እጅግ ያናድዳል❗️)
👉አንብበው ሲጨርሱ ከወደዱት ለሌሎች #ሼር ያድርጉት❗️
👉ከቀልድ ባለፈ ግን፤ "ገመድ ቆርጦ ሶኬት መቀየር" በኤሌክትሪክ ሙያ ውስጥ ፈፅሞ የማይመከር እና ቤትን ለእሳት አደጋ የሚያጋልጥ ስህተት ነው። ይህ ድርጊት የሚያስከትለውን ችግር በጥልቀት እንየው፦
1⃣. የገመድ ማጠር (Wire Shortening)፦
👉በየጊዜው ሶኬት በተበላሸና በተቀየረ ቁጥር ገመዱ እየተቆረጠ ከሄደ፣ የገመዱ ርዝመት እያጠረ ይሄዳል።
👉በመጨረሻም ከአዲሱ ሶኬት ተርሚናል ላይ ለመድረስ ይቸገራል፤ ግድግዳው ውስጥ ያለውን ገመድ ደግሞ ጎትቶ ማውረድ አይቻልም።
2⃣. የጉልበት ውጥረት እና የላላ ንክኪ (Mechanical Tension & Loose Connection)፦
👉ገመዱ በተቆረጠ ቁጥር ስላጠረ፣ ባለሙያው ገመዱን በጉልበት ጎትቶ ከሶኬቱ ጋር ለማሰር መሞከሩ አይቀሬ ነው።
👉ይህ በገመዱ ላይ ከፍተኛ ውጥረት (Tension) ይፈጥራል።
👉ውጥረቱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ገመዱ ከሶኬቱ ብሎን ስር እንዲላቀቅ ወይም እንዲላላ ያደርገዋል።
👉የላላ ንክኪ ደግሞ በተለይ እንደ ምጣድ እና ስቶቭ ባሉ ከፍተኛ ሀይል በሚስቡ እቃዎች ላይ ሲፈጠር፣ አርክ (Arcing) ፈጥሮ ሶኬቱን እና ቤቱን ለእሳት ሊያጋልጥ ይችላል።
3⃣. አደገኛ የገመድ ቅጥያ (Dangerous Splicing in the Backbox)፦
👉ገመዱ ተቆርጦ በጣም ሲያጥር፣ ሌላ አዲስ ገመድ በማምጣት ግድግዳው ውስጥ ካለው አጭር ገመድ ጋር ቀጥሎ በቴፕ የመጠምጠም አዝማሚያ ይታያል። 👉ከሶኬት ጀርባ ባለው ጠባብ ሳጥን (Backbox) ውስጥ ገመድ መቀጠል፣ በተለይ ለስቶቭ እና ምጣድ፣ ፍፁም ክልክል ነው❗️ የተጠመጠመው በሙቀት ሲቀልጥ ቀጥታ ሾርት ሰርኪዩት (Short Circuit) ይፈጥራል።
⏺ ትክክለኛው የባለሙያ መፍትሄ ምንድን ነው❓
✅ በእርጋታ መፍታት፦
👉ሶኬቱ ቢበላሽም፣ የሶኬቱን ብሎኖች (Screws) ተገቢውን መፍቻ (Screwdriver) በመጠቀም በእርጋታ መፍታት እና ገመዱን ሳይቆርጡ ሙሉ በሙሉ በመፍታት ማውጣት ያስፈልጋል።
✅ ዝገትን ማስለቀቅ፦
👉ብሎኑ ዝጎ አልፈታ ካለ፣ ትንሽ ዝገት ማስለቀቂያ በመጠቀም ጥቂት ደቂቃ ጠብቆ መፍታት ይመከራል።
✅ የተበላሸውን ጫፍ ብቻ መቁረጥ፦
👉ገመድ መቆረጥ ያለበት፣ ከብሎኑ ስር የነበረው መዳብ (Copper) በሙቀት ምክንያት ከጠቆረ እና ካረረ ብቻ ነው። ያም ቢሆን ሙሉ ገመዱን ከነ ሽፋኑ መቁረጥ ሳይሆን፣ ያረረውን የመዳቡን ጫፍ (ከ 1 እስከ 2 ሳ.ሜ ብቻ) ቆርጦ አዲስ ንፁህ መዳብ ማውጣት በቂ ነው።
⏺ ​ታዲያ ገመዱ ከዚህ ቀደም ተቆርጦ ካጠረ (የመጨረሻ መፍትሄው) ምንድን ነው❓
👉አንድ ባለሙያ ስራ ቦታ ሲሄድ ገመዱ በሌሎች ስህተት አስቀድሞ አጥሮ ከጠበቀው፣ መፍትሄው በቴፕ ጠምጥሞ ማለፍ ሳይሆን የሚከተሉትን ማድረግ ነው፦
​1️⃣. ተርሚናል ብሎክ/ኮኔክተር (Terminal Block) መጠቀም፦
👉አጭሩን ገመድ ከሌላ ተመሳሳይ ውፍረት ካለው አዲስ ገመድ ጋር ለማገናኘት ስፕላይስ ከማድረግና በናስትሮ ማሰር ሳይሆን፣ የገመድ ማገናኛ (Connector) አጥብቆ ማሰር።
👉ለምጣድ እና ስቶቭ ከሆነ ደግሞ ሙቀትን የሚቋቋም ሴራሚክ ኮኔክተር (Ceramic Connector) መጠቀም ግድ ይላል።
2️⃣ አዲስ ገመድ መጎተት (Pulling New Wire)፦
👉አጭር ገመድ ላይ ሌላ መቀጠል አደጋ አለው ተብሎ ከታሰበ ወይም የገመዱ ኮንዱዩት ክፍትና ምቹ ከሆነ፣ አጭሩን ገመድ አውጥቶ ከቅርቡ ማከፋፈያ (Junction Box) አዲስ ገመድ መጎተት 100% አስተማማኙ መፍትሄ ነው። ነገር ግን መጀመሪያ ሲሰራ ኮንዲዩት በሚገባ ቤንድ ተድርጎ ካልነበር ይህንም ለማድረግ ቀላል አይደለ። ከዚህ ሁሉ ነገር በስነስርዓት ፈቶ መቀየር መልካም ነው❗️
👇 እስኪ የሙያ አጋሮች...
እንዲህ ገመድ አሳጥሮ ጥሎባችሁ ሄዶ የተቸገራችሁበት አጋጣሚ አለ❓ ያጠረን ገመድስ አደጋ በሌለው ሁኔታ እንዴት ትጠግኑታላችሁ❓ ሀሳባችሁን በኮመንት አጋሩን❗️

👉በተጨማሪ ደግሞ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልጠናዎች በጥልቀት ማወቅ ከፈለጉ በዚህ ሳምንት የሚጀምሩ ስለሆነ ዛሬውኑ ደውለው ይመዝገቡ❗️አንቱ የተባሉ ባለሙያ አድርገን በቀጥታ ሥራ እናስጀምርዎታለን❗️
1️⃣ አድቫንስድ የቤት ዕቃዎች ጥገና(ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ስማርት ቲቪ፣ እና የኤሌክትሪክ ምድጃ/ኦቨን ጥገና)
2️⃣ አድቫንስድ የደህንነት ሲስተም ዝርጋታ (CCTV ካሜራ፣ ፋየር አላርም፣ አክሰስ ኮንትሮል፣ የኤሌክትሪክ አጥር፣ ታይም አቴንዳንስ፣ ቪዲዮ ኢንተርኮም ወዘተ...)
3️⃣ አድቫንስድ የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች ጥገና (የጀነሬተር ጥገና፣ ሞተር ኮንትሮል ሲስተምና ኤሌክትሪካል ሞተር ሪዋይንዲንግ)
4️⃣ አድቫንስድ አውቶካድ ኤሌክትሪካል ዲዛይን
5️⃣ አድቫንስድ የሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ጥገና
👉 የምዝገባ ቦታ (ዋና ቢሮ)፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
📍 ስልጠናው የሚሰጥባቸው ቅርንጫፎች፦ ቦሌ ሚካኤል | መገናኛ | ሜክሲኮ
📞 ለበለጠ መረጃና ቦታ ለማስያዝ አሁኑኑ ይደውሉ፦
📱 0991 15 69 69
📱 0939 55 55 10
🔗 ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
🌐 Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
🌐 TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
🌐 Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
🌐 Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
"ወጣትነት በክህሎት ካልታጀበ፤ እርጅና በቁጭት ያልፋል❗️"
አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት — በእጅዎ የሚጨበጥ የነገ ብሩህ ተስፋ❗️
#ሶኬት Amen Electrical Technology fans

23/08/2026

ከሰኞ-አርብ ለ 1 ወር ከ3:00-6:30(መገናኛ) የሚሰጠው 63ኛው ዙር አድቫንስድ የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን መደበኛ ስልጠናው ነሐሴ 18/2018 ይጀምራል! ይመዝገቡ!

22/08/2026

✅ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 15 /2018 ዓ.ም በታላቅ ቅናሽ የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ማሽን ጥገና (Generator, Motor Control & Rewinding) ይጀምራል❗️
=====
👉በዳሰሳ ጥናቱ ምክንያት ተድርጎ የነበረው 30%/20% ታላቅ ቅናሽም ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 15/2018 ይጠናቀቃል❗️
↪️ስልጠናው ቅዳሜ ከ8-11 እና እሁድ ከ3-6 ለ 2 ወራት ይሰጣል❗️
⏺ክፍያዎች፦
↪️ጀነሬተር ጥገና እና ዝርጋታ፦ 5,460/6240 ብር
↪️ሞተር ኮንትሮል ሲስተም፦ 4060/4640 ብር
↪️ሞተር ሪዋይንዲንግ፦ 6,860/7,840 ብር
↪️ጀነሬተር + ሞተር ኮንትሮል፦ 6,860/7840 ብር
↪️🔥 ሁሉንም በጥቅል (Package) ለሚወስድ፦11,060/12,640 ብር ብቻ❗️
👉 የምዝገባና የስልጠና ቦታ (ዋና ቢሮ)፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
📞 ለበለጠ መረጃና ቦታ ለማስያዝ አሁኑኑ ይደውሉ፦
📱 0991 15 69 69
📱 0939 55 55 10
🔗 ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
"ወጣትነት በክህሎት ካልታጀበ፤ እርጅና በቁጭት ያልፋል❗️
"አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት — በእጅዎ የሚጨበጥ የነገ ብሩህ ተስፋ❗️

fans Amen Electrical Technology

✅ ነገ ቅዳሜ  ነሐሴ 16 /2018 ዓ.ም በታላቅ ቅናሽ የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ማሽን ጥገና (Generator, Motor Control & Rewinding) ይጀምራል❗️=====👉በዳሰሳ ጥናቱ ...
21/08/2026

✅ ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 16 /2018 ዓ.ም በታላቅ ቅናሽ የኢንዱስትሪ ኤሌክትሪክ ማሽን ጥገና (Generator, Motor Control & Rewinding) ይጀምራል❗️
=====
👉በዳሰሳ ጥናቱ ምክንያት ተድርጎ የነበረው 30%/20% ታላቅ ቅናሽም ነገ ቅዳሜ ነሐሴ 15/2018 ይጠናቀቃል❗️
↪️ስልጠናው ቅዳሜ ከ8-11 እና እሁድ ከ3-6 ለ 2 ወራት ይሰጣል❗️
⏺ክፍያዎች፦
↪️ጀነሬተር ጥገና እና ዝርጋታ፦ 5,460/6240 ብር
↪️ሞተር ኮንትሮል ሲስተም፦ 4060/4640 ብር
↪️ሞተር ሪዋይንዲንግ፦ 6,860/7,840 ብር
↪️ጀነሬተር + ሞተር ኮንትሮል፦ 6,860/7840 ብር
↪️🔥 ሁሉንም በጥቅል (Package) ለሚወስድ፦11,060/12,640 ብር ብቻ❗️
👉 የምዝገባና የስልጠና ቦታ (ዋና ቢሮ)፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
📞 ለበለጠ መረጃና ቦታ ለማስያዝ አሁኑኑ ይደውሉ፦
📱 0991 15 69 69
📱 0939 55 55 10
🔗 ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
"ወጣትነት በክህሎት ካልታጀበ፤ እርጅና በቁጭት ያልፋል❗️
"አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት — በእጅዎ የሚጨበጥ የነገ ብሩህ ተስፋ❗️
Amen Electrical Technology fans

21/08/2026

ቅዳሜና እሁድ ለ 2 ወር የሚሰጠው የጀነሬተር፣ ሞተር ሪዋየንዲንግና ሞተር ኮንትሮል ሲስተም ስልጠና ቅዳሜ ነሐሴ 16/2018 ከቀኑ 8 ሰዓት ይጀምራል! ፈጥነው ይመዝገቡ!
0939555510/0991156969

✅የእንጀራ ምጣድ እና የኤሌክትሪክ ምድጃ ሴራሚክ ኮኔክተር (Ceramic Connector) እና ገመድ ለምን ይቀልጣል❓ ⚡️🔥=====👉በሀገራችን የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ጥገና ላይ እጅግ ተደጋጋሚ...
21/08/2026

✅የእንጀራ ምጣድ እና የኤሌክትሪክ ምድጃ ሴራሚክ ኮኔክተር (Ceramic Connector) እና ገመድ ለምን ይቀልጣል❓ ⚡️🔥
=====
👉በሀገራችን የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ጥገና ላይ እጅግ ተደጋጋሚ እና አስቸጋሪ ከሆኑት ውስጥ አንዱ የእንጀራ ምጣድ እና የኤሌክትሪክ ምድጃዎች መገናኛ (Ceramic Connector) እና አጠገቡ ያለው ገመድ ማቅለጥና መቃጠል ነው። ገመዱ እየተቆረጠ አዲስ ቢቀየርም ችግሩ ግን በድጋሚ ይከሰታል❗️
👉ይህ ችግር በዋነኝነት የሚፈጠረው የእቃዎቹን ትክክለኛ የኤሌክትሪክ ፍጆታ (Power Consumption) እና በኤሌክትሪክ ሳይንስ ወሳኝ የሆነውን የሴፍቲ ፋክተር (Safety Factor) ህግ ባለመከተል ነው።
👉አንብበው ሲጨርሱ ከወደዱት ሌሎች እንዲማሩበት #ሼር ያድርጉት! #ተጨማሪ እንድንቀርብላችሁ የምትፈልጉት ካለ ፃፉልን!
👉እስኪ የችግሮቹን መሰረታዊ መንስኤዎች ከነ አፋጣኝ የባለሙያ መፍትሄዎቻቸው ጋር በጥልቀት እንመልከት፦
1⃣. የኤሌክትሪክ ፍጆታ ስሌት እና የ "ሴፍቲ ፋክተር" መዘንጋት
❌ ችግሩ፦
👉በሀገራችን የሚመረቱ መደበኛ የእንጀራ ምጣዶች በአማካይ ከ 3,500W እስከ 4,00W (ዋት) የኤሌክትሪክ ሀይል ይስባሉ።የኤሌክትሪክ ህግን (Ohm's Law) ተጠቅመን ከረንቱን ስናሰላ፦I = P/V = {4000W/220V} = 18.18A (አምፔር) እናገኛለን።ነገር ግን የእንጀራ ምጣድ ለረጅም ሰዓት (Continuous Load) የሚሰራ እቃ ስለሆነ፣ በኤሌክትሪክ ስታንዳርድ (IEC) መሰረት 25% ሴፍቲ ፋክተር (Safety Margin) መጨመር ግዴታ ነው።ማለትም፦ 18.18A *1.25 = 22.7A. ስለዚህ የዲዛይን ከረንታችን 25 አምፔር ነው።
👉የኤሌክትሪክ ምድጃም የኤሌክትሪክ ፍጆታው ከ 3KW-3.5KW ነው❗️ከላይ ባየነው መሰረት ስንሰራው 20A ይመጣል።
✅ #መትሄ፦
👉ለምጣድ የብሬከሩ መጠን ቢያንስ 25A መሆን አለበት። ገመዱ ደግሞ ይህን መሸከም የሚችል ባለ 4mm² መሆን አለበት። ብዙ ጊዜ እዚህ ላይ ችግሮች አይስተዋልም እናቶችም ስለሚያውቁት በዚህ መሰረት ይዘረጋል፤ ምጣድ ላይ ግን በጣም አስቸጋሪው ነገር ነው በኋላ እናየዋለን❗️
👉በብዛት ችግሮች የሚሰተዋሉት የኤሌክትሪክ ምድጃ ላይ ነው የኤሌክትሪክ ምድጃ ከላይ እንደተገለፀው እስከ 3.5 KW የኤሌክትሪክ ፍጆታ ያለው ሲሆን የብሬከር መጠኑም ከ 20A/25A ማነስ የለበትም። ይህ ማለት ግን ከዚህ በታች ፍጆታ ያላቸው ኤሌክትሪክ ምድጃ የለም ማለት አይደለም❗️
👉በዚህ ዙሪያ የሚታዩ ትላልቅ ስህተቶች የሰርኪዩት ብሬከሩን ባለ 25A አድርጎ የኤሌክትሪክ የገመዱን መጠን 2.5mm² (ይህም ሆኖ ደረጃውን ያልጠበቀ ኬብል/ገመድ) ማድረግ❗️በዚህ ጊዜ ሰርኪዩት ብሬከሩ ሳይመልስ የኤሌክትሪክ ገመዱ ይቀልጣል ❗️
👉ሌላኛው ስህተት ገመዱን 2.5 mm² አድርጎ የሰርኪዩት ብሬከሩን መጠን ደግሞ 16A ማድረግ ነው። ይህ ለ 2..5mm² ገመድ የተመረጠው የብሬከር መጠን ትክክል ቢሆንም ኤሌክትሪክ ምድጃው ግን የሚፈልገው ከ 16A በላይ ስለሆነ በየመሃሉ የኤሌክትሪክ ምድጃው ብሬከር ይመልሳል❗️
👉ለዚህ ችግር ትክክለኛው መፍትሄ የሚሆነው ደረጃውን የጠበቀ ባለ 4mm² ገመድ እና ባለ 20A ወይም ባለ 25A ሰርኪዩት ብሬከር ተጠቅሞ መስራት ነው❗️
👉 እዚህ ላይ ትልቁ ስህተት ደግሞ ለባለ አንድ ኤሌክትሪክ ምድጃም ለባለ ሁለትም እኩል 2.5mm² እና 16A ሰርኪዩት ብሬከር መጠቀም ነው❗️ይህን ያደረገ ባለሙያ ምንም ሙያዊ ማብራሪያ ሊሰጥ አይችልም።
2⃣. የ 16A ሴራሚክ ኮኔክተር ማነቆነት (Connector Bottleneck)
❌ ችግሩ፦
👉ከላይ ባለው ስሌት መሰረት የ ምጣዱ ከረንት ከነ ሴፍቲ ፋክተሩ ~25A ደርሷል። ነገር ግን በገበያ ላይ የምናገኛቸው አብዛኛዎቹ የሴራሚክ ኮኔክተሮች የተሰሩት ቢበዛ ለ 16A (አምፔር) ብቻ ነው። 25A የሚፈልግን ምጣድ በ 16A ብቻ ማሳለፍ በሚችል ኮኔክተር ላይ ስናስረው፣ ኮኔክተሩ ማነቆ (Bottleneck) ይሆንና ከሚችለው በላይ ከረንት ሲያልፍበት ከፍተኛ የተቃውሞ ሙቀት ይፈጥራል። ሙቀቱ የኮኔክተሩን ብሎን አቅልጦት ስለሚጣበቅ ለመፍታት እንኳን አይቻልም። በዚህ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ ኮኔክተሩ ጋር የታሰረው ኤሌክትሪክ ገመድ መቅለጥና ኢንሱሌሽኑ መላላሽ ይጀምራል❗️
✅ መፍትሄ፦
👉ተራ የ 16A ኮኔክተሮችን ትቶ፣ ቢያንስ 25A እና ከዚያ በላይ መሸከም የሚችሉ (Heavy Duty)፣ ውስጣቸው ወፍራም የነሐስ (Brass) ብረት ያላቸውን የሴራሚክ ኮኔክተሮች ፈልጎ መግጠም።
3⃣. ደረጃቸውን ያልጠበቁ ገመዶች (Substandard / CCA Cables)
❌ ችግሩ፦
👉ሌላው ትልቁ የቃጠሎ ምክንያት ደረጃቸውን ያልጠበቁ ገመዶች ናቸው። እነዚህ ገመዶች በላያቸው ላይ "4mm² Pure Copper" ተብሎ ቢፃፍባቸውም፣ ውስጣቸው ግን የመዳብ ሽፋን ያለው አልሙኒየም (CCA - Copper Clad Aluminum) ወይም የውስጥ የመዳብ ውፍረታቸው ከ 2.5mm² በታች የሆነ ነው። አልሙኒየም ከመዳብ አንፃር ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተቃውሞ (Resistance) ስላለው፣ 25A ከረንት ሲያልፍበት ወዲያውኑ ወደ እሳትነት ተቀይሮ ገመዱን ያቀልጠዋል።
✅ መፍትሄ፦
👉ለከፍተኛ ፍጆታ እቃዎች 100% ከንፁህ መዳብ (Electrolytic Pure Copper) የተሰሩ ደረጃቸውን የጠበቁ ገመዶችን ብቻ መግዛት። ገመዱን ከመግዛት በፊት ቆርጦ በመመልከት የኬብሉን ትክክለኛ ውፍረት እና የመዳብ ጥራት ማረጋገጥ።
4⃣. የላላ ንክኪ (Loose Connection) እና ተርሚናል ላግ አለመጠቀም
❌ ችግሩ፦
👉ምጣዱ ሲበራ የሚፈጠረው ሙቀት ኮኔክተሩን ያሞቀዋል፤ ሲጠፋ ደግሞ ይቀዘቅዛል። በዚህ ተደጋጋሚ መለጠጥ እና ማጠር ምክንያት የኮኔክተሩ ብሎን በጊዜ ሂደት ይላላል። በተጨማሪም ጠጋኞች የተፈተለውን የመዳብ ገመድ (Stranded wire) ልጠው ዝም ብለው በብሎኑ ስር ሲያስሩት፣ መዳቡ ተበታትኖ ጥቂት ገመዶች ብቻ ይገናኛሉ። በነዚያ ጥቂት ገመዶች ላይ 25A ከረንት ሲያልፍ አርክ (Arcing) እና ከፍተኛ ሙቀት ተፈጥሮ ገመዱ ይቃጠላል።
✅ መፍትሄ፦
👉የተፈተለውን ገመድ ጫፍ በ Pin Lug ወይም Ferrule ውስጥ አስገብቶ በክሪምፐር (Crimping Tool) አጥብቆ መጭመቅ። ይህ 100% የኤሌክትሪክ ንክኪ እንዲኖር ያደርጋል። በተጨማሪም በየጊዜው የኮኔክተሩን ብሎኖች በዊንዶውስ ጠበቅ ማድረግ ያስፈልጋል።
5⃣. ተራ የ PVC ገመድ መጠቀም እና የመዳብ መዝገት (Oxidation)
❌ ችግሩ፦
👉ወደ ኮኔክተሩ የሚገባው ገመድ መደበኛ የፕላስቲክ (PVC) ሽፋን ያለው ከሆነ፣ ከምጣዱ ኤለመንት በሚመጣው ሙቀት ብቻ ሽፋኑ ቀልጦ ሾርት ሰርኪዩት ይፈጥራል። በተጨማሪም መዳቡ ከፍተኛ ሙቀት ሲያገኝ ኦክሳይድ (Oxidized) ሆኖ ይጠቁራል። ጥቁር መዳብ ኤሌክትሪክ አሳላፊነቱ ስለሚቀንስ ሙቀቱን በእጥፍ ይጨምረዋል።
✅ መፍትሄ፦
👉ወደ ኮኔክተሩ የሚገባው የገመድ ክፍል የፋይበር ግላስ ወይም የሲሊኮን ሽፋን ያለው Heat-Resistant Wire መሆን አለበት። ገመዱ አካባቢው ከተቃጠለ ደግሞ የጠቆረውን ገመድ ቆርጦ በመጣል ንፁህ እና የሚያበራ የመዳብ ቀለም እስኪያወጣ ድረስ ወደ ኋላ አዲስ ጫፍ ማውጣት ግዴታ ነው!

👇እስኪ ባለሙያዎችም ተጠቃሚዎችም ያጋጠማችሁ ችግር ካለ አካፍሉን❗️ለሌሎች #ሼር ማድረግም እንዳይረሱ❗️

👉በተጨማሪ ደግሞ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልጠናዎች በጥልቀት ማወቅ ከፈለጉ ዛሬውኑ ደውለው ይመዝገቡ❗️አንቱ የተባሉ ባለሙያ አድርገን በቀጥታ ሥራ እናስጀምርዎታለን❗️
1️⃣ አድቫንስድ የቤት ዕቃዎች ጥገና(ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ስማርት ቲቪ፣ እና የኤሌክትሪክ ምድጃ/ኦቨን ጥገና)
2️⃣ አድቫንስድ የደህንነት ሲስተም ዝርጋታ (CCTV ካሜራ፣ ፋየር አላርም፣ አክሰስ ኮንትሮል፣ የኤሌክትሪክ አጥር፣ ታይም አቴንዳንስ፣ ቪዲዮ ኢንተርኮም ወዘተ...)
3️⃣ አድቫንስድ የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች ጥገና (የጀነሬተር ጥገና፣ ሞተር ኮንትሮል ሲስተምና ኤሌክትሪካል ሞተር ሪዋይንዲንግ)
4️⃣ አድቫንስድ አውቶካድ ኤሌክትሪካል ዲዛይን
5️⃣ አድቫንስድ የሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ጥገና
👉 የምዝገባ ቦታ (ዋና ቢሮ)፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
📍 ስልጠናው የሚሰጥባቸው ቅርንጫፎች፦ ቦሌ ሚካኤል | መገናኛ | ሜክሲኮ
📞 ለበለጠ መረጃና ቦታ ለማስያዝ አሁኑኑ ይደውሉ፦
📱 0991 15 69 69
📱 0939 55 55 10
🔗 ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
🌐 Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
🌐 TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
🌐 Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
🌐 Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
"ወጣትነት በክህሎት ካልታጀበ፤ እርጅና በቁጭት ያልፋል❗️"
አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት — በእጅዎ የሚጨበጥ የነገ ብሩህ ተስፋ❗️
​ Amen Electrical Technology fans

21/08/2026

✅ ዛሬ አርብ ነሐሴ 15/2018 የ63ኛው ዙር አድቫንስድ የህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ስልጠና ኦረንቴሽን ተሰጥቷል❗️
===
👉ይህ የተግባር ስልጠና በታላቅ ቅናሽ ለተመዘገቡ ወጣቶች ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን ፈጥነው ለሚመዘገቡ አሁንም ውስን ቦታዎች አሉ❗️
↪️ የስልጠና ቦታ፦ መገናኞ
↪️ሙሉ ክፍያ፦ 6,960/7,840 ብር ብቻ
↪️የስልጠና ሰዓትና ቀን፦ ከሰኞ-አርብ ከዋቱ 3-6 ሰዓት ለ አንድ ወር
✅ #ማሳሰቢያ፦
1⃣. ስለጠናው የሚሰጠው #በክፍል፣ / #ኢንዱስትሪ/ በመሆኑ እጅግ ማራኪና የሚደሰቱበት ስልጠና ነው❗️
3⃣. ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ COC የሚመዘኑ ይሆናል❗️

✅ ፦
👉የምዝገባ ቦታ (ዋና ቢሮ)፦ ቦሌ ሚካኤል፣ የቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 2ኛ ፎቅ
👉ስልጠናው የሚሰጠው ቦሌ መገናኛ ነው❗️

📞 ለበለጠ መረጃና ምዝገባ አሁኑኑ ይደውሉልን፦
📱 0991 15 69 69
📱 0939 55 55 10
🔗 ማህበራዊ ሚዲያዎቻችንን ይከተሉ፦
Telegram: https://shorturl.at/zKTN2
TikTok: https://shorturl.at/VQN6I
Youtube: https://shorturl.at/I8eyb
Facebook: https://www.facebook.com/ameninstitutetechnology?mibextid=ZbWKwL
"ዛሬ የማትወስነው ውሳኔ፣ ነገ የምትኖርበትን የሕይወት ደረጃ ይወስነዋል!"
አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት — በ 1 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ሰልጥነው ወደ ሥራ ይግቡ❗️
አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት - ለላቀ የቴክኒክ እና ሙያ ክህሎት❗️
Amen Electrical Technology fans Amen Electrical Technology fans

⏺  👉ወንድማችን ወጣት ተሻገር አበባው አበበ  ከጎንደር ወደ አረርቲ ከተማ ለሥራ ብሎ ጥቅምት 2017 ዓ.ም እንደወጣ ወደ ቤቱ አልተመለሰም። እናም ውድ ኢትዮጵያውያን ይህንን ከታች በፎቶ የ...
21/08/2026



👉ወንድማችን ወጣት ተሻገር አበባው አበበ ከጎንደር ወደ አረርቲ ከተማ ለሥራ ብሎ ጥቅምት 2017 ዓ.ም እንደወጣ ወደ ቤቱ አልተመለሰም። እናም ውድ ኢትዮጵያውያን ይህንን ከታች በፎቶ የሚታየውን ወንድማችን ያያችሁ ጥቆማ ትሰጡን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንማጸናችኋለን። ይህን ልጥፍም #ሼር እያደረጋችሁ ብዙዎች ጋር ታደርሱልን ዘንድ እንማጸናለን።
ፋላጊ እህቱ ባንችአምላክ አበባው እና ቤተሰቦቹ
0922633991

Address

Bole Michael
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 18:00
Tuesday 09:00 - 18:00
Wednesday 09:00 - 18:00
Thursday 09:00 - 18:00
Friday 09:00 - 18:00
Saturday 09:00 - 18:00
Sunday 09:00 - 00:00

Telephone

+251911585854

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amen Electrical Technology posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The School

Send a message to Amen Electrical Technology:

Shortcuts

Share