መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Medhanialem General secondary school

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Medhanialem General secondary school

መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Medhanialem General secondary school Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Medhanialem General secondary school, School, Addis Ababa.

የመድኃኒዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በአዲስ አበባ /ፍንፊኔ / ከተማ ውስጥ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ ዘጠኝ ልዩ ስሙ መድኃኒአለም ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ የሚገኝ ሲሆን የመድኃኒአለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በጥቅምት 27፣ 1924ዓ.ም ተመሰረተ፡፡ይህ ት/ቤት ከ1924 ዓ.ም. እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ የክፍል ደረጃ እያስተመራ ይገኛል።ጉለሌ፣ መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህ

ጉለሌ፣ መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ ሐምሌ ዐ8 ቀን 2018 ዓ.ም""""""""""🇪🇹""""""""🇪🇹"""""""""""🇪🇹""""""""""ከሐምሌ 6 2018ዓ. ም ጀምሮ ...
15/07/2026

ጉለሌ፣ መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ ሐምሌ ዐ8 ቀን 2018 ዓ.ም
""""""""""🇪🇹""""""""🇪🇹"""""""""""🇪🇹""""""""""
ከሐምሌ 6 2018ዓ. ም ጀምሮ በመማር ማስተማር ላይ የሚገኘው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክላስተር ማዕከል ሶስተኛው ቀኑን ይዛዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ለተመረጡ ቶፕ 30 የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በክረምት መርሐ ግብር ማጠናከሪያ ትምህርት ከሐምሌ 6 ጀምሮ በተመረጡ የክላስተር ማዕከላት ትምህርቱን በመሰጠት ላይ ይገኛል::
ከነዚህ ማዕከላት መካከል አንድ በሆነውና በጉለሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክላስተር ማዕከል ትምህርቱ ከሀምሌ 6 ጀምሮ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በማዕከሉ 5 የግል እና 2 የመንግስት ትምህርት ቤቶች ማለትም
👉🇪🇹መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣
👉🇪🇹 ምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣
👉🇪🇹ኤልሻዳይ ሆሊሴቬር አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣
👉🇪🇹ቀ/አንዳርጌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣
👉🇪🇹እናት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
👉🇪🇹እትዮፓረንት አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና
👉🇪🇹 ሱሜያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት በመከታተል ላይ ይገኛሉ ፡፡
🇪🇹የትምህርት ቤቱ ዋና ር/መምህር የሆኑት አቶ ባይሳ ታዬ በሰልፍ ስነስርዓት ላይ በመገኘት እንደተናገሩት የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርቱ በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የጎላ ሚና እንዳለው በመግለፅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ X to E ን ጨምሮ በማላቅ እስትራቴጂ ትምህርቱ በሳምንት 5ቀን ለክረምት ወቅት ብቻ በተዘጋጀ ኮንደንስድ ካሪኩለም በመሰጠት ላይ ይገኛል ብለዋል ።
አቶ ባይሳ ታዬ የX ን የማረም ስትራቴጂን መሰረት በማድረግ የማስተማሪያ ስነዘዴው በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን ተማሪዎች ስህተቶቻቸውን እያረሙ በርካታ ጥያቄዎች የሚሰሩበት መልካም አጋጣሚ ነው ሲሉ ተደምጠዋል ::
ለበለጠ መረጃ የትምህርት ቤታችን ገፆችን ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://web.facebook.com/profile.php?id=61571824817562

https://t.me/medshschool

ክላስተር ትምህርት ቤቱ

15/07/2026
*ጉለሌ፣ መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ ሐምሌ ዐ6 ቀን 2018 ዓ.ም""""""""""🇪🇹""""""""🇪🇹"""""""""""🇪🇹""""""""""* በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሀገር...
14/07/2026

*ጉለሌ፣ መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ ሐምሌ ዐ6 ቀን 2018 ዓ.ም
""""""""""🇪🇹""""""""🇪🇹"""""""""""🇪🇹""""""""""*
በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል የክረምት ማላቃ እስትራቴጂ መተግበሪያ ትምህርት በመድሐኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ክላስተር መሰጠት ጀምራል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ከ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ለተመረጡ ቶፕ 30 የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በክረምት መርሐ ግብር ማጠናከሪያ ትምህርት በተመረጡ የክላስተር ማዕከል በመድሐኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መሰጠት ጀምሯል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ አሸናፊ ነገሽ መረሃ ግብሩ ተማሪዎች በዋናነት ለሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያደርግ መሆኑን ፤ በሀገር አቀፍ ፈተና የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲያስቻል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ተጀምሯል ብለው ትምህርቱ በሳምንት 5 ቀን ለክረምት ወቅት ብቻ በተዘጋጀ ኮንደንስድ ካሪኩለም ፕሮግራም ተዘጋጅቶ መማር ማስተማር የጀመረ እና ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረግ ተማሪዎች ስህተቶቻቸውን እያረሙ በርካታ ጥያቄዎች የሚሰሩበት እንዲሁም ትርፍ ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያውሉ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል::

ከዝህም በተጨማሪ ወላጆች ለልጆቻቸው የትምህርት ጉዞ በቅርበት በመከታተል እና በክረምት ማጠናከሪያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው እንዲማሩ በማበረታታት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ የትምህርት ቤቱ ወላጅ ተማሪ ተወካይ አቶ አይረድን አርጋነው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ የትምህርት ቤታችን ገፆችን ይመልከቱ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

❤️https://web.facebook.com/profile.php?id=61571824817562

❤️https://t.me/medshschool

ክላስተር ትምህርት ቤቱ

09/07/2026
ጉለሌ፣ መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም""""""""""🇪🇹""""""""🇪🇹"""""""""""🇪🇹""""""""""👉🇪🇹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደ...
07/07/2026

ጉለሌ፣ መድኃኔያለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
""""""""""🇪🇹""""""""🇪🇹"""""""""""🇪🇹""""""""""

👉🇪🇹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (AMN) ጋር በመተባበር አሸናፊ ትውልድ በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአድዋ ድል መታሰቢያ ተጀምሮ በቅርቡ በተመረቀው የቀበና ወንዝ ዳርቻ አካሂደዋል ።
👉🇪🇹በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች, መምህራን እና ር/መምህራን ተሳታፊ ስሆኑ የትምህርት ቤታችን ተማሪ የሆነው ተማሪ ጉሉማ ደጀኔ ከተሳተፉት ህብረተሰብ መካከል 3ኛ መዉጣት ችለዋል ::
👉🇪🇹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (AMN) ጋር በመተባበር ሁሉም ተሳታፊ የሜዳሊያ ተሸላሚ እንድሆነ አድርጓል ።
👉🇪🇹ተሳታፊዎች በሩጫው ወቅት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እያደነቁ የተጓዙ ሲሆን መርሃ ግብሩ ስፖርት የጤና መነሻ ብቻ ሳይሆን የህዝብ ትስስር፣ የአንድነት እና ለጋራ ልማት መነሳሻ መሆኑን በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኗል።
ለበለጠ መረጃ የትምህርት ቤታችን ገፆችን ይመልከቱ
👇👇👇??👇👇👇👇👇👇

https://web.facebook.com/profile.php?id=61571824817562

https://t.me/medshschool

ክላስተር ትምህርት ቤቱ

02/07/2026

ዉድ የትምህርት ቤታችን የመድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተነ ተፈታኝ ተማሪዎቻችን
🔐🔐🔐 ለበርካታ ዓመታት የለፋችሁበትን ውጤት የምታዩበት ወቅት በመሆኑ፣ ተረጋግታችሁና በራሳችሁ በመተማመን ፈተናውን እንዲትሰሩና ለቤተሰቦቻችሁም ሆነ ለሀገራችሁ ኩራት እንዲትሆኑ ምኞቴ ነው።
👉💚❤️💙ፈጣሪ ጥበቡን፣ማስተዋሉንና እዉቀቱን ይስጣችሁ።
🇪🇹❤️🇪🇹የዛሬ ተፈታኞች ፣የነገ ሀገር ተረካቢዎች መልካም መልካሙን ሁሉ ተመኘሁላችሁ!!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መድኃኔዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Medhanialem General secondary school posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category